Climate Smart Feed and Forage Innovations Training Workshop የተሻሻሉ የመኖ ሰብሎችን በኢትዮጵያ ደጋማና ወይና ደጋ አካባቢዎች አመራረትና አጠቃቀም Melkamu Bezabih |Aberra Adie |Getnet Assefa |Kindu Mekonnen |Million Gebreyes | 16-18 May 2022| Bahir Dar| Ethiopia መግቢያ በሀገራችን የእንስሳት መኖ በበቂና በጥራት አለመኖሩ የእንስሳት ምርታማነት በጣም ዝቅተኛ አድርጎታል ያሉት የእንስሳት መኖዎች ጥራታቸው ዝቅተኛ አቀርቦቱም ውስን ነው • የተፈጥሮ ግጦሽ ቦታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበቡ ከመምጣታቸው ባሻገር የተራቆቱ ናቸው • የግብርና ሰብል ተረፈ ምርቶች የንጥረ ምግብ ይዘታቸው በጣም ዝቅተኛ ነው • የድጎማ መኖዎች ዋጋቸውውድ ነው፣ እንዲሁም የትም ቦታ በቀላሉ አይገኙም አሁን ባለው የድጎማመኖ አቅርቦት ሁኔታ እንስሳት አርቢዎችምርታማነታቸውን ትረጉም ባለውሁኔታ ለማሳደግ የተሻሻሉ የመኖ ስብሎችን አምርተውመጠቀም ተስፋ ሰጪ አማራጭ ነው የስልጠናው ዓላማዎች • የተሻሻሉ የመኖ ሰብሎች እንስሳትንና ሰብልን በጥምር በሚያመርቱ ገበሬዎች የእንስሳት እርባታን ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ያላቸውን ጠቀሜታ ለመረዳት • የተሻሻሉ የመኖ ሰብሎች ጠቀሜታና ዋና ዋና ባህርያትና የአጠቃቀም ዘዴዎች ግንዛቤ ለመስጠት • በደጋማና ወይና ደጋ አካባቢዎች የተሻሻሉ የመኖ ሰብሎች የአመራረት የግብርና ዘዴ ምን እንደሚመስል ግንዛቤ መፍጠር • ለእንስሳት አርቢዎችና መኖ አምራቾች የተለያዩ የመኖ ዝርያዎችን እንዴት በአግባቡ እንደሚያመርቱና እንድሚጠቀሙ ምክር መስጠት የመኖ ሰብሎችን ለምን ማልማት ያስፈልጋል ? 1. ገበሬዎች በአካባቢያቸው በቀላል ዋጋ ጥራት ያለው መኖ ማምረት ስለሚያስችል • ለአብዛኛወ አነስተኛ ገበሬ የመኖ ሰብሎችን በአካባቢያቸው ጥራት ያለው መኖ ማምረት ጠቃሚ ነው ምክንያቱም የተመጣጠነ የድጎማ መኖ ለመግዛት ዋጋውውድ ከመሆኑም በላይ በቅርብ ማግኘት ስለሚያስቸግር፡፡ • የመኖ ሰብሎችን በአካባቢያችን በተለያየ አማራጭ መንገዶች ማልማት ይቻላል የመኖ ሰብሎችን ለምን ማልማት ያስፈልጋል ? 2. የተሻሻሉመኖዎችምርታማነታቸው ክፍተኛ ነው ተ.ቁ የመኖ ሰብሉ ዓይነት የድርቆሽ ምርት ቶን በሄከታር 1 የሳር መኖ ዝርያዎች (Grasses) 8 - 15 2 የቅጠላቅጠል መኖ ሰብሎች (Legumes) 6 - 10 3 የቅንጠባ መኖ ዛፎች (Browse trees) 6 - 13 4 የተፈጥሮ ግጦሽ (Natural Pasture) 1 - 2 • የመኖ ምረታማነቱና ጥራቱ እንደዝርያው ዓይነት ይለያያል • የመኖ ሰብሎች ዓመታዊ ወይም ሰንባች ሊሆኑ ይችላሉ • የመኖ ሰብሎቸን በዝናብ ወይም በመስኖ ማልማት ይቻላል የመኖ ሰብሎችን ለምን ማልማት ያስፈልጋል ? 3. የመኖ ሰብሎች ጥምር ጠቀሜታ አላቸው፤ ለእንስሳት መኖነት፣ ለሰው ምግብነት እንዲሁም ለማገዶ ይጠቅማሉ • የተወሰኑ የመኖ ሰብሎቸ ከፍተኛ ጥራት ያለው የእንስሳት መኖ ይሰጣሉ • የከብት አተርን የመሳሰሉመኖዎች ፍሪያቸው ለሰው ምግብነት ቅጠላቸው ደግሞ ለእንስሳት መኖነት ይውላል • የቅንጠባ መኖ ዘፎች ግንድና ቅርንጫፎች ለማገዶነት ይጠቅማሉ ለምሳሌ - የእርግብ አተር፣ የከብት አተር የመኖ ሰብሎችን ለምን ማልማት ያስፈልጋል ? 4. የአካባቢ ጥበቃ አገልግሎት • የመኖ ሰብሎች በተዳፋት ቦተዎች ለይ በሚዘራበት ወይም በሚተከሉበት ጊዜ የአፈር መሸርሸርና ይከላከላሉ እንዲሁም የዝናብ ውሃ ወደ መሬት ውስጥ ሰረጎ እንዲገባ ያደርጋሉ • የቅጠላቅጠል የመኖ ሰብሎች የመሬት ለምነትን ይጨምራሉ • የመኖ ሰብሎች በአየር ውስጥ ያለውን ካርቦንዳይአክሳይድ በመምጠጥ የአካበቢሙቀት መጨመርን ይከላከላሉ • ጥራቱ ከፍተኛ የሆኑ መኖዎችን ለእንስሳት መመገብ እንስሳት የሚያመነጩትን አየር በካይ ጋዝ መጠን ይቀንሳል የመኖ ሰብሎችን ለምን ማልማት ያስፈልጋል ? 5. ከመኖ ሰብሎች ልማት ጋር የተቀናጀ የእፅዋት በሽታና ተባይ ቁጥጥር • የበቆሎ አገዳ ትል (maize stem borers) የዝሆኔ ሳረና ዲስሞዲየምንና በቆሎን በቅንጀት በመዝራት መከላከል ይቻላል. ከዚህም በተጨማሪ ጠራት ያለውመኖ ማመረት ያስችላል • የመኖ ሰብሎችን ከምግብ ሰበሎች ጋር በፈረቃመዝራት የተለያዩ የሰብል በሽታዎች፣ ተባዬችንና አረሞችን መቆጣጠር ያስችላል የመኖ ሰብሎችን ለምን ማልማት ያስፈልጋል ? 6. የመኖ ሰብሎች የገቢ ምንጭ ናቸው • የመኖ ሰበሎችን ለገበያ ማምረት አወጭ የስራ መስክ ነው • የመኖ ሰብሎች በአረን ዴነታቸውታጭደው ለገበያ ይቀርባሉ ለምሰሌም • ሰናር መኖ በስላሌ አካባቢ • በቆሎና ማሽላ በአፋር • የሱዳን ሳር በጅግጅጋና በጎዴ • አሸት በቆሎ የተቆረጠለት አገዳ በአረንገዴነቱ ለእነስሳት መኖ በሐዋሳ አካባቢ ይሸጣል የመኖ ስበሎች አመራረት ዘዴዎች የተሻሻሉ የመኖ ሰብሎቸን በሁለት ዋና ዋና መንገዶች ማምረት ይቻላል 1. የመኖ ሰበሎችን ልክ እንደ ሌሎች የምግብ ሰብሎች በመደበኛ የአመረረት ዘዴ ማልማት 2. የመኖ ሰብሎችን ከሌሎች ሰብሎች ጋር በቅንጅት አንዲሁም ከሌሎች የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎችና ሌሎች የግብርና ዘዴዎች ጋር ማልማት ናቸው የመኖ ልማት መሰረታዊ የሆኑ የመስክ ስራዎች 1. ተስማሚ አካባቢና ፣ ማሳ መረጣ 2. የማሳ ዝግጅት 3. የዘር ዝግጅት 4. ዘር መዝራት ፣ መትከል አና ማዳበሪያ መጨመር 5. አረም፣ በሽታና ተባይ ቁጥጥር 6. አጨዳ ወይም በእንስሳት ማስጋጥ 7. የ ሚ የመኖ ሰብሎች ቀጣይ አያያዝ ሀ) የመኖ ዝርያ መረጣ በአንደ በተወሰነ አካበቢ መኖ ለማልማት በሚፈለገበት ጊዜ ተሰማሚ የሆነ የመኖ ዝርያ ለመምረጥ የአካባቢውን የአየር ሁኔታ፣ የአፈር ዓይነት አንዲሁም የግብርና ዘዴ በቂ መረጃመኖር አለበት • የሚመረተውመኖ ለምን ጥቅም እንደታቀደማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ የወተት ላሞችን ከሆን የሚዘራውመኖ ለወተት ከብቶች ተስማሚመሆን አለበት • በአካባቢው ያለውን የመኖ ልማት ስራዎች ማወቅና ውጤታማልምዶችን መቅሰም ይመከራል • ከላይ የተዘረዘሩት ሁኔታዎችመሰረት ተደርጎ የመኖ ዝርያዎችን መምረጥ ያሰፈልጋለ.የመኖዎች ዝርያም • ዓመታዊና ሰንባች (ዘላቂ) • የሳር፣ ቅጠላቅጠል አና የቅንጠባ መኖ ዛፎች ሊሆኑ ይችላሉ ለ) ማሳ ዝግጅት • የመኖ ሰብሎችን ለመዝራት የሚደረግ የማሳ ዝግጅት እንደ ሰብሎች ዓይነት ይለያያል • ደቃቅ ዘር ላላቸው የመኖ ሰብሎች የማሳ ዝግጅቱ በደመብ የለሰለሰ ፣ እንዲሁም ከአረም የነፃ መሆን አለበት • አብዛኞቹ ዓመታዊ የመኖ ሰብሎች የማሳ ዘግጅታቸው ቀላል ነው • ማሳን በጊዜ ማዘጋጀት አንዲሁም በማሳውውሰጥ አስፈላጊውን ተፋሰስ መስራት ቡቃያወ በጥሩ ሁኔታ እንዲያድግ ይርዳል ሐ) ዘር ዝግጅት እንደ ዝርያው ዓይነት የሰብሉ የመባዣመንገድ በዘር፣ በግንደ ቁረጥራጭ እንዲሁም ከስር ግንጣይ ሊሆን ይችላል • ዘሩ ከመዘራቱ በፊት የጥራት ደረጃው መፈተሽ አለበት - ከተለያየየ ብአድ ነገሮች ነፃ መሆኑ መረጋገጥ አለበት - የብቅለት ደረጃው ምን ያህል እንደሆን መታወቅ አለበት • የሚያስፈለገው ዘር በብቅለት ደረጃው ተሰተካክሎ መገመት • ዘሩ ከመዘራቱ በፊት ሌሎች ቅድመ ዝግጅት ካሉ ማረጋገጥ • ለምሳሌ ዘሩ ራይዞቢየም የሚባል የባክቴሪያ ሰትሬን ኢኖኩላንት የሚያስፈለገው መሆኑን ማረጋገጥ መ) የዘር መጠን • የመኖ ሰብሎች አንደ ዘር መጠናቸውና ያአስተዳደግ ባህሪያቸው የዘር መጠናቸው በሄክታር ይለያያል • ደቃቅ ዘር ያለቸው ዝርያዎች በአብዛኛወ ከ 2-10 ኪ.ግ. ዘር በሄክታር በቂ ነው • ለመኖ ሰብሎች የዘር መጠኑን ክፍ አድረጎ መዝራት በዙ ጊዜ ምንም ጉዳት የለውም፤ ነገር ግን ዘሩን በኢኮኖሚመጠቀም ይገባል • በአጠቃላይ የአያአንዳንዱ የመኖ ዝርያ አንደየአካባቢው፣ የማሳ ሁኔታ የተሰጠውን ምክረ-ሀሳብ (recommendation) የዘር መጠን መዝራት ጥሩ ነው • በመስመር በሚዘራበት ጊዜ በመሰመር እና በተክሎችመካከል የሚኖረውን ስፋት በሚሰጠውምክረ-ሀሳብ (recommendation) መሰረትመጠቀምውጤታማ ያደርጋል ሰ) ማዳበሪያ • ከተቻለ የማሳዎቹ የአፈር ለምነት ምርመራ ማደረግ የሚያስፈልገውን የማዳበሪያ ዓይነትና መጠን ለመወሰን ይጠቅማል • መሬቱ ምን ተዘርቶበት እንደነበርና አጠቃላይ መረጃውችን ማወቅም ይረዳል • አፈሩ ምን ዓይነት ንጥረ ምግብ እጥረት እንዳለበት ማወቅ ለምሳሌ (ናይትሮጅን፣ ፎስፈረስ፣ፖታሲየም) - ምን ዓይነት ማዳበሪያ እንደሚገኝና የትኛውን መጠቀም እንደሚሻል ማወቅ፣ - ኮምፖስት ወይም ፍግ - ዩሪያ ፣ ዳፕ እና የመሳሰሉት - ሰብሉ እንደ መሬቱ ሁኔታ ምን ያህል ማዳበሪያ እንደሚያስፈለገው ማወቅ - በምከረ ሀሳብ የተሰጠውን የአጨማመር ዘዴ መጠቀም ለምሳሌ ሁለት ጊዜ ከፍሎ መጨመር - የተለያዩ የማዳበሪያ ዓይነቶች ሲጨመሩመጠኑን በጥንቃቄ ማስላት ያስፈልጋል ሰ) ማዳበሪያ ገበሬው በብዛት የሚጠቀማቸው የማዳበሪያ ዓይነቶች • ዩሪያ – (ናይትሮጅን ፡ ፎስፈረስ፡ ፖታሲየም - 46:0:0) • ዳፕ (Dai-ammonium Phosphate) – (NH4)2HPO4 (ናይትሮጅን ፡ ፎስፈረስ፡ ፖታሲየም - 18:46:0) • ቲኤስፒ – (Triple Super Phosphate) – (ናይትሮጅን ፡ ፎስፈረስ፡ ፖታሲየም - 0:46:0) • ሌሎችም ረ) መዝራት / መትከል • የመኖ ሰብሎች በተለያዩ መንገዶች ሊዘሩ ይችላሉ - በማሽነሪ የታገዘ አዘራር፣ በእንስሳት የታገዘ ወይም በሰው ጉለበት - በብተናመዝራት ወይም በመስመርመዝራት • ትልልቅ የዘር ፈሬ ያላቸው ዝርያዎች አዘራራቸው እንደ ምግብ ሰብሎች ተማሳሳይ ነው • ነገር ግን ብዛት ያለቸው የመኖ ዝርያዎች ዘራቸው ደቃቅና ቀላል በመሆነቸው ሲዘሩ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል • ይህም ዘሮቹ በጣም እንዳይቀበሩ ማድረግ • አዘራሩም እኩል እንዲዳረስ ተደረጎ መዘራት አለበት ምክንያቱም ቀላል ዘሮች በንፋስ ይወሰዳሉ • ዘሩን ልምድ ያለቸው ባለሙያዎች ቢዘሩት ይመረጣል ሠ) ዘር የማልበስ ዘዴ • ዘር ከተዘራ በ ላ በትክክለኛ መጠን አፈር መልበስ አለበት • በጣም ደቃቅ ዘሮች ከተዘሩ በ ላ የዛፍ ቅርንጫፍ በመጎተት ማልበስ አንድ አማራጭ ሊሆን ይችላል • በማሳው ላይ ከበት መንዳትና መዝራት (የበህላዊ የጤፍ አዘራር ዘዴ መጠቀም) • ዘሩን ዘረቶ አፈር ሳያለብሱ እንዲሁ መተው • ዘሩን በትክክል ለማዳረስ ዘሩ ላይ አፈር፣ አሸዋ ወይም ማዳበሪያ በመቀላቀል መዘራት • በግንድ፣ አገዳ፣ ወይም በሰር ግንጣይ የሚተከሉ ዝርያዎች በቀላሉ ሰለሚለመዱ የተሻለ መንገድ ነው • ለምሳሌም እንደ ዝሆኔ ሳርና ደሾ ሳር ሸ) አረምን መቆጣጠር • ዘር ከተዘራ በ ላ ማሳውንና ቡቃያውን መከታተል ያስፈልጋል ምክንያቱም • ዘሩ በወፍና፣ በተበይ ሊበላ ይችላል • ቡቃያው በተበይ፣ በሽታና ለጠቃና በጎርፍ ሊጠረግ ይችላል • ዘርና ቡቃያ በተባይ እንዳይጠቃ ዘሩን በኬሚካለ ማሸት ወይም ቡቃየውን መርጨት ይቻላል • የማሳ ዘግጅት በሚደረግበት ወቅትና የመዝሪያውን ቀን/ወቅት በማስተካከል የተባይ፣ በሽታና አረምን መቀነስናመከላከል ይቻላል • አረም በተለይ በሰነባች የመኖ ሰብሎች ለይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ዘላቂ ወይም ሰንባች ዝርያ ቡቃያዎች እድገታቸው ዘገምተኛ በመሆኑ የአረሙን ፈጣን እድገት መ ም አይችሉም ፡፡ ስለዚህ • ተገቢው የማሳ ዝግጅት በወቅቱ ማድረግ • በሰው ጉለበት በእጅ ማረም • የተመረጡ የአረም ማጥፊያ መድሃኒቶችን መጠቀም • አረሙንና የመኖ ሰብሉን በለጋነታቸውማጨድ ወይም በከብት ማስጋጥ ዋና ዋና የአረም መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ናቸው ቀ) አጨዳ ወይም ግጦሽ የመኖ ሰብሎችን ለማጨድ በምንዘጋጅበት ጊዜ መታወቅ ያለባቸው ዋና ዋና ነገሮች • የሰብሉ የማጨጃ ጊዜ መቸ እንደሆንና የሰብሉ የአደገት ደረጃ • ሲታጨድ ሊሰጠው የሚችለው የመኖ ምርት • ሲታጨድ የሚነረው የመኖ የንጥረ ምግብ ይዘት • የማጨጃው መሳረያ በአጭር ጊዜ አጭዶ መጨረስ የሚያስችል መሆኑን ማረጋገጥ • ተከማችቶ የሚቆይበትን መንገድ (ደረቆሽ / ገፈራ) መወሰን • በእንስሳት የመበላት መጠኑና ሌሎችንም ማወቅ የመኖ ሰብሉ ሲታጨድ እንደ መመሪያ መወሰድ ያለበት የመኖ ምርታማነትና ጥራት ከፈተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ነው ቀ) አጨዳ ወይም ግጦሽ • የመኖ ሰብሎች በአብዛኛው ጥራቱና ምርታማነቱ የተመጣጠነ የሚሆኑበት የእድገት ደረጃ ሰብሉ ማበብ ከጀመረበት እሰክ 50% አበባ እስከሚያወጣበት ጊዜ ነው፡፡ • የመኖ ሰብሎች አጨዳ በአጭር ጊዜ ውስጥመጠናቀቅ አለበት ምክንያቱም የአጨዳ ጊዜ በተራዘመ ቁጥር የጥራት ደረጃው እየቀነሰ ስለሚሄድ ነው፡፡ በ) የመኖ ሰብሎች ቀጣይ አያያዝ • የመኖ ሰብል የሚታጨድበት ወቅት ከፈተኛ ምርት በሚሰጠበት ጊዜ መሆን አለበት፣ ለምሳሌ የዝናብ መጨረሻ ወቅት • ለዘላቂ የመኖ ሰብሎች የማጨጃ ወቅት ቀጣዩን የእድገት ወቅት ያገናዘበ መሆን አለበት ለምሳሌ የዝናብ መጀመሪያ ወቀት ማጨድ በቀጣይ ጥሩ ምርት ለማግኘት ያስችላል • ውርጭ ባለበት አካባቢ ወርጭ የሚያጠቃቸውን የመኖ ሰብሎችውርጭ ከመድረሱ በፊት መታጭደ አለበት • በዘላቂ መኖ ሰብሎች ላይ በዓመት አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ አረም ማረም፣ ወይም የአረም መድሃኒት መርጨት እንዲሁም ፍግ ወይም ማዳበሪያ መጨመር ያስፈልጋል. • ማዳበሪያና ፍግ የሚጨመረው አንደመሬቱ ለምነት ሁኔታ እየታየ መሆን አለበት • በበጋ ወራት መስኖ መጠቀም ከተቻል ከፈተኛ ምርት ሊያስገኝ ይችላል በደጋና በወይና ደጋው አካባቢ የተላመዱና በምርታማነታቸውና በጥራተቸውውጤታማ የሆኑ የተመረጡ የመኖ ሰብል ዝርያዎች 1. ስናር / ሸማሜ / ሻሎ (Oats ) • ሰናር ዓመታዊ ቁመቱ እስከ 2 ሜትር የሚደረስ የሳር ዝርያ ነው • ተስማሚ የአየር ሁኔታ - ቀዝቃዛና ደጋማ የአየር ሁኔታና የአፈር ለምነቱ ደካማ የሆኑ መሬቶች ላይ በብዛት ይመረታል • ስናር የተለያዩ ዝርያዎች አሉት - እነዚሀም በቁመት ለአጨዳ በመደረሱበት የጊዜ ርዝመት በዘር ፍሬቸው መጠን አና በመሳሰሉት ይለያያሉ • ስናር የሚባዛው በዘር ሲሆን 100 ከ.ግ. ዘር በሄክታር ይበቃል ፣ በመስመር ሲዘር መስመሮቹ 15-20 ሳ.ሜ. መራራቅ አለባቸው • ስናር ከመኖ ያ ጋር ተደባለቆ (25/75 ያ/ ስናር ኪ.ግ. በሄከታር) ሲዘራ ጥራት ያለው ብዙ ምረት ይስጣሉ • ማዳበሪያ - ሰብሉ ሲዘራ 100 ከ.ግ ዳፕ በሄከተር ወይም ፍግ በበቂ መጨመር፤ አንደ ዝናቡ ሁኔታ ማደባሪያውን ከሁለት ከፍሎ መጠቀም ምርታማነቱን ይጨምራል 1. ስናር / ሸማሜ / ሻሎ (Oats ) • አረም ቁጥጥር – በሰው ጉልበት በእጅ ማረም ወይም ፀረ አረም መድሃኒት መርጨት • አጨዳ – በማጭድ፣ በፋልች (scythe) ወይም በማሽን ስናሩ 50% ሲያዘረዝር መታጨድ አለበት • የስናር መኖን በድረቆሽ ወይም በገፈራ መልክ ተዘጋጅቶ አከማችቶ ማቆየት ይቻላል • አጠቃቀም – የስናር ደረቆሽ ጥሩ የመኖ ምንጭ ነው በተለይ በአረን ዴነቱ መጠቀምዉጤታማ ነው ፤ ነገር ግን ተጨማሪ የድጎማመኖ ያስፈልገዋል • ምርታማነት – ከ 8 - 15 ቶን ድርቆሽ በሄክታር ማግኘት ይቻላል. ዝናብ ባለበት አካባቢ ስናር ከታጨደ በ ላ አንደገና ያድጋል መኖም ሊሰጥ ይችላል • ዘር – ስናር ጥሩ ዘር የሚሰጥ ሲሆን እንደዝርያው ዓይነት ከ5 እስከ 35 ኩንታል ዘር በሄክታር ይሰጣል • የስናር ዘር - ለሰው ምግብነት እንዲሁም ለእንስሳት መኖነት ሊውል ይችላል • ዘር በሚመረትበት ወቅት ገለባው ለእንስሳት መኖነት ይውላል ስናር / ሸማሜ / ሻሎ (Oats ) – የተለያዩ ዝርያዎች 2. የመኖ ጓያ (Vetches) • የመኖ ጓያ ዓመታዊ ቅጠላቅጠልመኖ ሲሆን አስተዳደጉም የሀረግነት ባህሪ ያለው ነው • የመኖ ጓያ ቀዝቃዛ በሆኑ ደጋና ወይና ደጋ አካባቢዎች የተንጣፈፈ መሬት ይስማማዋል • የተለያዩ ዝርያዎች ፤ ፈጥነውና ዘግይተው የሚደረሱ አና ሌሎችም ባህሪዎች አላቸው • የመኖ ጓያ የሚባዛው በዘር ሲሆን 25 ከ.ግ ዘር በሄክታር ይዘራል፡፡ በመስመር ሲዘራ ከ20-30 ሴ.ሜ. ተራርቀውመዘራት አለባቸው • የመኖ ጓያ ከስናር ጋር ተደባለቆ (25/75 ጓያ/ ስናር ኪ.ግ. በሄከታር) ሲዘራ ጥራት ያለው ብዙ ምረት ይስጣሉ • የመኖ ጓያ ዝርያዎች በደጋ በቆሎውስጥ በቅንጅት በመዝራት ተጨማሪ መኖ ማግኘት ያስችላል • ማዳበሪያ የሚጨመረው የማሳው አፈር ከተመረመረ በጓላ ቢሆን ይመከራል ፣ በአጠቃላይ 100 ኪ.ግ. ዳፕ በሄክታር በዘር ወቅት መጨመር ይመከራል 2. የመኖ ጓያ (Vetches) • የአረም ቁጥጥር – በሰው ጉልበት በእጅ ማረም • አጨዳ – በማጭድ በፋልች (scythe) የመኖ ጓያው 50% ሲያብብ መታጨድ አለበት • የመኖ ጓያ በድርቆሽ ወይም ከሌሎች መኖዎች ጋር በገፈራ መልክ ተዘጋጅቶ ማከማቸት ይቻላል • አጠቃቀም – የመኖ ጓያ ከፍተኛ ፕሮቲን ስላለው ጥሩ የድጎማ መኖ መሆን ይችላል ፣ ስለዚህ ከሳር ድረቆሽ ወይም ከገለባ ጋር ተቀላቅሎ ቢሰጥ መልካም ነው • ምርታማነት – ከ 6 -13 ቶን ድርቆሽ በሄክታር ይስጠል • ዘር – የመኖ ጓያ ጥሩ ዘር ይሰጣል ምርታማነቱም ከ2 እሰከ 6 ኩንታል በሄክታር ይሰጣሉ ነገር ግን ውርጭ ባለበት አካባቢ የመኖ ጓያ በውርጭ ይጠቃል ለዚህም የዘር ምርት ለማግኘት ያስቸግራል 3. ላብላብ (Dolichos lablab) • ዓመታዊ / የአጭር ጊዜ ሰንባች ቅጠላቅጠል ዝርያ – እንደ ሐረግ በፍጥናትና በግዝፈት የሚያድግ • በወይና ደጋና በቆላማ አካባቢ የተላመደና በዝናብና በመስኖ የሚለማ • ለተለያዩ ስነ-ምህዳሮች ተስማሚ የሆኑ ዝርያወች አሉት • ላብላብ የሚባዛው በዘር ሲሆን የዘር መጠኑም ከ 15 - 25 ኪ.ግ በሄክታር ሲሆን በመስመር ሲዘራ ከ80 -100 ሴ.ሜ በመስመር መካከል እንዲሁም 30-50 ሴሜ በተክል መካከል መራራቅ አለባቸው • እንድ ፓኒከም ካሉ የሳር ዝርያዎች ጋር በድብለቅ በመዝራት ጥራት ያለው መኖ ማምረት ይቻላል • በበቆሎና ማሽላ ስር በመዝራት ከእህል ምርት በተጨማሪ ጥራት ያለው መኖ ማምረት ይቻላል • እንደ መሬቱ ለምነት ዳፕ ማዳበሪያ 100 ኪ.ግ. ዳፕ በሄክታር ሲዘራ ቢጨመር ጥሩ ነው (100 kg DAP (18 kg N + 46 kg P2O5 / ha) ) 3. Lablab (Dolichos lablab) • አረም – በሰው ጉለበት በእጅ ማረም • አጨዳ – ሰብሉ 50% ሲያብብ በማጭድ ወይም በፋልች (scythe) ማጨድ • የታጭደውመኖ በድረቆሽ ወይም ከሌላ መኖ ጋረ ተቀላቅሎ በገፈራ (silage) መልክ ተዘጋጅቶ ሊቀመጥ ይችላል • አጠቃቀም - ጥራት ያለውመኖ ስለሆን ከገለባ ወይም ከሳር ድረቀሽ ጋር ቀላቅሎ መመገብ ጥሩ ነው • ምርታማነት – ከ 6 - 9 ቶን በሄክታር ድርቆሽ ይሰጣል፤ በመስኖ በሚዘራበት ወቅት ምርታማነቱ ከዚህ እጅግ የላቀ ነው • ዘር – ላብላብ ብዙና ጥራት ያለው ዘር ይስጣል፣ ከ 9 - 25 ኩንታል በሄክታር 4. የላም አተር (Cowpea) • ዓመታዊ የመኖ ቅጠላቅጠል (legume) – የሐረግነት ፀባይ ያለው ዝርያ ነው • ተስማሚ የአየር ሁኔታ - በወይናደጋና ቆላማ አካባቢወች በዝናብና በመስኖ በጥሩ ሁኔታ ያድጋል • የላም አተር የተለያዩ ዝርያዎች አሉት • የሚባዛው በዘር ሲሆን የዘር መጠኑም ከ 15 - 25 ኪ.ግ. በሄክታር ሲሆን በመስመር ሲዘራ 80-120 ሴሜ በመስመር መካከል እንዲሁም 30-50 ሴሜ በተክል መካከል ማራራቅ ያስፈልጋል • እንደ ፓኒከም ካሉ የሳር ዝርያዎች ጋር በስብጥር ሲዘራ ውጤታማ ነው • የላም አተር እንደ በቆሎና ማሽላ ካሉ ሰበሎች ጋር በስረቸው ቢዘሩ (undersown) ጥራት ያለው መኖ ይስጣሉ • እንደ ማሳወ ዓይነትና ሁኔታ ሲዘራ ማዳበሪያ መጨመር ጥሩ ነው 100 ኪ.ግ. ዳፕ በሄክታር (100 kg DAP/ha (18 kg N + 46 kg P2O5 / ha) 4. የላም አተር (Cowpea) • አረም – በሰው ጉለበት በእጅ ማረም • አጨዳ – ሰብሉ 50% ሲያብብ በማጭድ ወይም በፋልች (scythe) ማጨድ • የታጭደውመኖ በድርቆሽ ወይም ከሌላ መኖ ጋረ ተቀላቅሎ በገፈራ (silage) መልክ ተዘጋጅቶ ሊቀመጥ ይችላል • አጠቃቀም - ጥራት ያለውመኖ ስለሆን ከገለባ ወይም ከሳር ድርቀሽ ጋር ቀላቅሎመመገብ ጥሩ ነው • ምርታማነት – ከ 6 - 9 ቶን በሄክታር ድርቆሽ ይሰጣል፤ በመስኖ በሚዘራበት ወቅት ምረታማነቱ ከዚህ እጅግ የላቀ ነው • ዘር – የላም አተር ብዙና ጥራት ያለው ዘር ይስጣል፣ ከ 9 - 25 ኩንታል በሄክታር 5. የከበት ድንች (Fodder beet) • ዓመታዊ የመኖ ስራስር ተክል • ተስማሚ የአየር ሁኔታ - የከበት ድንች ቀዝቃዛ በሆኑ ደጋማ አካባቢዎች ለምና ውሃ የማይ ጥርና አሸዋማ አፈር ይስማማዋል • የሚባዛው በችግኝ ሲሆን አልፎ አልፎ በቀጥታ ዘሩንም መዝራት ይቻላል • በማሰመር ሲዘራ 50 ሴሜ በመስመር መካከል እንዲሁም 30-60 ሴሜ በተክል መካከል አራርቆ መትከል ያስፈልጋል • ማዳበሪያ - ለም በሆነ መሬት ወይም በ ሮ አካበቢ መትከል አንዲሁም በሌሎች ቦታዎች ላይ 100 ኪግ. ዳፕ በሄክታር መጨመር 5. የከበት ድንች (Fodder beet) • አረም – በሰው ጉለበት በእጅ ማረም አና በተደጋጋሚ መኮትኮት አና አፈር ማስታቀፍ • የከበት ድንች ለመኖነት ከደረሰ በ ላ መሬት ውስጥ እንዳል ለረጅም ጊዜ መቆየት ይችላል • አጠቃቀም – ቀረጣጥፎ ከሌሎች መኖዎች ጋር ቀላቅሎ ለእንስሳት መመገብ • ምርታማነት – ከ 5 – 10 ቶን ደረቅ መኖ በሄከታር ይሰጣል፤ • ዘር – የከብት ድንች የሚያብበውና ዘር የሚሰጠው በጣም ቀዝቃዛ በሆኑ ቦታዎች ነው ለምሳሌመራሮ (አርሲ) 6. ዝሆኔ ሳር (Elephant grass) • ለዓመታት የሚቆይ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ የሳር ዝርያ ነው • ተስማሚ የአየር ሁኔታ - በቆላማ አካባቢወች በዝናብና በመሰኖ በጥሩ ሁኔታ ያድጋል ከዚህም በተጨማሪ በደጋ አካበቢ ተስማሚ ዝርያዎች አሉ ነግር ግን ውርጭ ያጠቃዋል • ዝሆኔ ሳርን ከአገዳው ወይም ከሰር ግንጣይ በመትከል በቀላሉ ማልማት ይቻላል • በመስመር ሲዘራ 1 ሜ በመስመር መካከል እንዲሁም 30-50 ሴሜ በተክል መካከል አራርቆ መትከል ያስፈልጋል • ማዳበሪያ - ሲተከል 100 ከ.ግ ዳፕ በሄከተር ወይም ፍግ በበቂ መጨመር፤ ሁለተኛው ዓመት በ ላም በየዓመቱ ፍግና ማዳበሪያ እንደየሁኔታው መጨመር • የመኖ ያና ዲስሞዲየም ከ ዝሆኔ ሳር ጋር በስብጥር ቀላቅሎ መዝራት ምርታማነቱንና የመኖ ጥራቱን ይጨምራል 6. ዝሆኔ ሳር (Elephant grass) • አረም – በየተወሰነ ጊዜ በተለይ ከአጨዳ በ ላ ቢታረምና ቢኮተኮት በጣም ጥሩ ነው • ቁመቱ ከ 1 -1.5 ሜሲሆን ማጨድ ምርቱንም የመኖ ጥራቱንም ከፍተኛ ያደረገዋል • አጠቃቀም – አረን ዴውን አጭዶ ለእንስሳት መመገብ ተመራጭ ነው፤ ገፈራ (silage) ሰረቶ ማቆየትም ሌላ አማራጭ ነው • በእንስሳቶች ተወዳጅና የፕሮቲን መጠኑም 9% በላይ ነው • ምርታማነት – 10 - 30 ቶን በሄክታር ድርቆሽ በዝናብ ይሰጣል በመሰኖ ደግም በጣም ከፍ ያለ ምርት ይስጣል • ዘር – ዝሆኔ ሳር በአብዛኛወ ዘር አይሰጥም ነግር ግን በቀላሉ ከአገዳው ወይም ከስር ግንጣይ በቀላሉ ይባዛል፣ 7. ብራኬሪያ ሳር (Brachiaria grass) • የብራካሪያ ሳር በዝናባማና ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የተላመደ ሰንባች (ዘላቂ) የሳር ዝርያ ሲሆን በኢትዮጵያ ሙላቶ 2 (Mullato II) የሚባለው ዝርያ በብዙ ቦታወች የተላመደ ነው • የሚባዛወ በዘር ሲሆን ከ 5 – 10 ኪ.ግ. ዘር በሄክታር ይበቃል፣ • ከዚህ በተጨማሪ የስር ግንጣይ በመጠቀም ማልማት ይቻላል፡፡ • በመስመር በሚዘራበት ጊዜ በመስመሮችመካከል 50 ሴ.ሜ. እንዲሁም በተክሎችመካከል 50 ሴ.ሜ መራራቅ አለባቸው • ማዳበሪያ ወይም ፍግ እንደ አፈሩ ሁኔታ መጨመር ውጤታማ ያደርጋል፡፡ በአጠቃለይ ግን ሲዘራ ወይም ሲተከል 100 ኪ.ግ. ዳፕ በሄከታር እንዲሁም በቀጣዮቹ ዓመታት 50 - 75 ኪ.ግ ዩሪያ በሄክታር በየዓመቱ መጨመር ይጠቅማል 7. ብራኬሪያ ሳር (Brachiaria grass) • የብራኬሪያ ሳርን ድርቆሽ ወይም ገፈራ በመሰራት መቆየት ይቻለል • በብዙ አገሮች ብራኬሪያ ሳር የሚጠቀሙት ለግጦሽ ነው እንዲሁም በአረን ዴነቱ እያጨዱ ለእንስሳት መመገብ ይቻላል • ምርታማነቱም እሰከ 13 ቶን ድረቆሽ በሄክታር ሲሆን በመስኖ ሲዘራ ግን በጣም ከፍተኛ ምርት ይሰጣል • ዘር – ብራኬሪያ ሳር ጥሩ ዘር ይሰጣል ነገር ግን በሀገራችን በአብዛኛው የሚባዛው በስር ግንጣይ ነው 8. ደሾ ሳር (Desho grass) • ደሾ ሳር ሀገር በቀል የሆን ሰንባች የመኖ ሳር ነው • ሰፋ ባል ስነምህዳር በተለይም ዝናባማ በሆኑ ወይና ደጋ እስክ ቆላማ ቦታዎች የተላመደ ነው • የሚባዛው በስር ግንጣይ ሲሆን በማስመር በሚዘራበት ጊዜ በመሰመሮች መካከል 10 ሴ.ሜ. እንዲሁም በተክሎች መካከል 10 ሴ.ሜመራራቅ አለባቸው • ፍግና ማዳበሪያ መጨመር ምርታማነቱን ይጨምራል . • ምርታመነቱ ከ 10 እስከ 20 ቶን ድርቆሽ በሄክታር ይሠጣል፣ በዓመትም በዝናብ ከ 2 – 4 ጊዜ ማጨድ ይቻላል • ቁመቱ 80 ሴ.ሜሲሆን እያጨዱ ለእንስሳት መመገብ የተሻለ የአጠቃቀም ዘዴ ነው፡፡ • ዘር ብዙ ጊዜ አይሰጥም 9. ሮደስ ሳር (Rhodes grass) • ከ 1 – 2 ሜትር ቁመት የሚያድግ ሰንባች (ዘላቂ) የመኖ የሳር ዝርያ ነው • ሮደስ ሳር ከደጋ አስከ በርሃ የአየር ሁኔታ ባለቸው አካበቢዎች መብቀል ይችላል • የሚባዛው በዘር ሲሆን እንደየ ሁኔታው ከ 2-10 ኪ.ግ. ዘር በሄክታር ይዘራል ፡፡ ሲዘራም በብተና ወይም በመሰመር 20 ሴሜ አራርቆ መዝራት ይቻላል • ከአልፋአለፋ አና ከእስታይሎ ከሚባሉ የቅጠላቅጠል ዝርያዎችና እንዲሁም ከሌሎችም ጋር በድበልቅ መዝራት ጥራት ያለው መኖ ይሰጣል • ማዳበሪያ - አንደ መሬቱ ለምነት ይወሰናል በጥቅሉ ግን ሲዘራ100 ኪ.ግ ዳፕ ማዳበሪያ በሄክታር እንዲሁም ከሁለተኛወ ዓመት ጀመሮ አንደየሁኔታው ፍግ ወይም ዩሪያ ማዳበሪያ መጨመር ያስፈልጋል 9. ሮደስ ሳር (Rhodes grass) • አረም ቁጥጥር – በሰው ጉልበት በእጅ ማረም ወይም ፀረ አረም መድሃኒት መርጨት • አጨዳ – በማጭድ፣ በፋልች (scythe) ወይም በማሽን 50% ሲያዘረዝር መታጨድ አለበት • ምርታማነት – ከ 8 - 25 ቶን ድርቆሽ በሄክታር ይሰጣል፣ በደጋ አካባቢ ዝቅተኛ ሲሆን ሞቃታማ አካቢቢ ከፍተኛ ነው፣ በመስኖ ሲሆን በጣም ከፍተኛ ምርት ይሰጣል • ደርቆሽ ቀላሉ አከማችቶ የማቆያ ዘዴ ሲሆን በአረን ዴነቱ እንስሳትን መመገብ ጠቃሚ ነው • አጠቃቀም – የሮደስ ሳር እንደመሰረታዊ መኖ (basal diet) ይጠቅማል ስለዚህ ለምረታማ እንስሳት የድጎማ መኖ ያስፈልጋቸዋል፤ የሮደስ ሳር ማሳ በቀላል ግጦሽ ማስጋጥ ይቻላል • ዘር – ከ 200 - 500 ኪ. ግ. ዘር በሄክታር ይሠጣል 10. ትሪሉሰርን የቅንጠባመኖ ዛፍ • ትሪሉሰርን ቀሚ የሆን የቅንጠባ መኖ ዛፍ ነው • ደጋና ቀዝቃዘ አካበቢ የተንጣፈፈ አፈር ይስማማዋል • የሚባዛው በችግኝ ሲሆን በተወሰኑ አካባቢዎች በቀጥታ ዘሩን መዘራት ይቻላል. በማሰመር ሲተከል 1 ሜ በመሰምረ መካከል እንዲሁም 50 ሴ.ሜ. በተክል መካከል ማራራቅ ያስፈልጋል፤ ዘሩ በደምብ እንዲበቀል በፈላ ውሃ ከ7 እሰከ 9 ደቂቃ መቀቀል አለበት • ማዳበሪያ – ሲተከል ዳፕ በመጠኑ ቢጨመር ለእድገት ይረዳዋል • ምርታማነት – ከ 4 -10 ቶን በሄከታር የሚበላ ድረቀሽ ይሰጣል • የትሪሉሰርን አበባ ለንቦች ጥሩ መኖ ነው • አጠቃቀም - በአረን ዴነቱ እየቆረጡ አጠውልጎ ለእንስሳት መመገብ ጥሩ ዘዴ ነው • ዘር – ጥራትና ብዛት ያለው ዘር ይሰጣል አልፋአልፋ (Alfalfa) • አልፋአልፋ ከፈተኛ የነጥረ ምግብ ይዘት ያለው ሰንባች (ዘላቂ) የቅጠላቅጠል መኖ ዝርያ ነው • በተለያዩ የአየርና አፈር ሁኔታዎችና አከባቢዎች የተላመደ ሲሆን ከደጋ እስከ በርሃ ደረስ መብቀል ይችላለ- አሲዳማ አፈር አይስማማውም • አልፋአልፋ በቀላሉ ከዘር መባዛት ይችላል፣ ሲዘራም በብተና ወይም በመስመር (20 ሴሜ አራረቆ) እንደየሁኔታው ከ 2-10 ኪ.ግ. ዘር መጠን በሄክታር በመጠቀም መዝራት ይቻላል • ከፓኒከም፣ ከሮደስ አንዲሁም ከሌሎች ሳሮች ጋር በድብልቅ መዝራት ብዛት ያለውመኖ ይሰጣል • ማዳበሪያ ወይም ፍግ እንደ መሬቱ ለምነት መጨመር ይቻላል፡፡ ሲዘራ 100 ኪ.ግ. ዳፕ በሄክታር መጨመር ለእድገት ይርዳዋል መልመጃ • የመጣችሁበትን አካባቢ (ወረዳ/ቀበሌ) ውሰዱና ዋና ዋና መረጃዎችን አጠናቅሩ፣ መረጃዎቹም የአካባቢውን አማካኝ ያአየር ሁኔታ (የዝናብ መጠን፣ የአየር ሙቀት፣ ወዘተ)፣ የእንስሳት ዓይነትና ብዛት፣ የአርባት ዘዴ በመዘርዘር ተወያዩበት • ከላይ ያለውን መረጃ መሰረት በማድረግ የትኞቹ የመኖ ሰብሎች ባአካባቢው ሊለሙ ይችላሉ፣ የእንስሳት አረቢዎችስ የተኞቹን ይመርጣሉ ብላችሁ ታስባለችሁ? ለምን? • የተመረጡ የመኖ ሰብሎችን ዘርዝሩና በምን ዓይነት መልኩ መልማት አንደሚቻልና በአጭሩ መሰረታዊ ለማልማት የሚያስፈለጉ ሁኔታዎችን ግለፁ