"ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ © አለም አቀፍ የድንች ምርምር ማዕከል፣ አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጲያ ፣ እ.ኤ.አ 2020 ዓ.ም ISBN: 978-92-9060-548-5 DOI: 10.4160/9789290605485.v7 የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የህትመት ውጤቶች የተለያዩ የምርምርና የልማት መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች በስፋት ያደርሳሉ፡፡ ተጠቃሚዎች እነዚህን መረጃዎች ለራሳቸው በሚመች ሁኔታ እንዲጠቀሙ ወይም እንዲያራቡ ማዕከሉ ያበረታታል፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ሕትመቶቹ ባለቤት የማዕከሉ መረጃዎች ጥቅም ላይ በዋሉባቸው ሌሎች ሕትመቶች ላይ የማዕከሉ ስም በምስጋና እንዲገለጽና የሕትመቶቹ ግልባጭ እንዲደርሰው ይፈልጋል፡፡ የሕትመቶቹን ግልባጮች ለማዕከሉ ሕዝብ ግንኙነትና ማስታወቂያ መምሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ እንዲላኩልን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ International Potato Center P.O. Box 1558, Lima 12, Peru cip@cgiar.org • www.cipotato.org ጥራዝ 7 የስልጠና መምሪያ በሌሎች ሕትመቶች ላይ ለመጠቀም ትክክለኛው አገላለጽ የሚከተለው ነው፡፡ Stathers, T., Low, J., Munyua, H., Mbabu, A., Ojwang, F. (2013). Everything You EverWanted to Know about Sweetpotato: Reaching Agents of Change ToT Manual. 7: Using the ‘everything you ever wanted to know about sweetpotato’ TOT course; Reflections. International Potato Center, Nairobi, Kenya. vol.7. የስልጠና መምሪያው የአማርኛ ዝግጅት አስተባባሪዎች የአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል ዋና ሳይንቲስት ዶ/ር ሮላንድ ብሮወር - "የተሻለ አመጋገብ ለተሻለ ጤና" ፕሮጀክት አስተባባሪ አቢዮት አራጋው - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የምርምር ኦፊሰር የመምሪያው የአማርኛ ትርጉም ኤዲተሮች አቢዮት አራጋው - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የምርምር ኦፊሰር አሸብር ክፍሌ - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የምርምር ኦፊሰር ዶ/ር ብርሃኑ ቢያዝን - በአለም አቀፍ ሰብል ምርምር ተቋም በደረቃማ አካባቢ (ኢክሪሳት) ከፍተኛ የምርምር መኮንን ምሕረቱ ቸርነት - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የምርምር ሥራ አመራር አስተባባሪ የመምሪያው የአማርኛ ንድፍና ሽፋን ዝግጅት ፍሬዘር አስፋው - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል ዳታቤዝ ማኔጅሜንት ስፔሻሊስት የመጀመሪያ ህትመት ሰኔ 2012 ዓ.ም. CIP thanks European Union for funding the production of this manual. CIP thanks all donors and organizations that globally supports its work through their contributions to the CGIAR Trust Fund: www.cgiar.org/funders Copyright 2020 © International Potato Center. All rights reserved. This publication is copyrighted by the International Potato Center (CIP). It is licensed for use under the Creative Commons Attribution 4.0 International License መግቢያ ባለፉት አስር አመታት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ዘንድ የስኳር ድንች ሰብል ፍላጎት እየጨመረ፣ ሰብሉ ላይ የሚሰሩ ፐሮጀክቶች ቁጥር እያደገ እንዲሁም ስለሰብሉ የተሻሻለ አመራረት፣ አያያዝና አጠቃቀም ላይ የሚጠየቁ የስልጠና ድጋፎች እየጨመሩ መጥተዋል፡፡ ይህንን እያደገ የመጣ ፍላጎትን ለመመለስ የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከልና በየአገራቱ ያሉ የብሄራዊ ምርምር ተቋማት ተመራማሪዎች ተበታትነው ያሉ የስልጠና ጹሑፎችን በማሰባሰብ ከ1-3 ቀናት የሚፈጁ የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ የሚነሱ ፍላጎቶችን ለመመለስ የዚህ አይነት አቀራረብ ዉስንነት እንደተጠበቀ ሆኖ ምሉዕ የሆኑ የስልጠና መምሪያዎች እስከአሁን ድረስ አልተዘጋጁም፡፡ "የለውጥ ሐዋርያትን መድረስ" የተሰኘው ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም መጀመር ሁኔታዎች በመሰረታዊነት እንዲቀየሩ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ በአለም አቀፍ የድንች ምርምር ማዕከልና በሄለን ኬለር ፋውንዴሽን ትብብር የተተገበረ ሲሆን ስለብርቱካናማ ስኳር ድንች አስፈላጊውን ግንዛቤ ለመፍጠርና ያሉ ሃብቶችን በሰብሉ ላይ በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ለማንቀሳቀስ እንዲቻል አስፈላጊውን አቅም ለመገንባት ያለመ ነበር፡፡ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በቫይታሚን ኤ የበለጸገውን የብርቱካናማ ስኳር ድንች ስርጭትና አጠቃቀም ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ መተግበር እንዲችሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ሰራተኞች አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል፡፡ አጠቃላይ ግቡ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ፣ ደቡብ አፍሪካና ምዕራብ አፍሪካ ክፍለ-አህጉራት በስኳር ድንች አመራረትና አጠቃቀም አዳዲስ ግኝቶች ዙሪያ ለከፍተኛ የስርጸት ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት የሚያስችል አቅም ዘላቂ በሆነ መንገድ መፍጠር ነው፡፡ ስለሆነም "ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" ስልጠናን እንዲሰጡ የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል በሞዛምቢክ፣ ታንዛኒያና ናይጄሪያ አገር በቀል ተቋማትን ለይቷል፡፡ በመጀመሪያው ስልጠና ወቅት የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል ከአገር በቀል ተቋማቱ ጋር በቅርበት ሰርቷል፡፡ በሁለተኛው ዙር ስልጠና አገር በቀል ተቋማቱ ከማዕከሉ ተመራማሪዎች በተሰጣቸው ድጋፍ የስልጠናውን ተግባራት መምራት የቻሉ ሲሆን በሶስተኛ ዙር ስልጠና ወቅት ደግሞ ከማዕከሉ በተደረገላቸው የገንዘብ ድጋፍ አገር በቀል ተቋማቱ ስልጠናውን ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ማከናወን ችለዋል፡፡ በቀጣይ አመታትም ይህ ስልጠና ሳይቋረጥ በአገር በቀል ተቋማቱ እንደሚቀጥልና በወጪም ረገድ ራሱን እንደሚችል ይታመናል፡፡ የዚህን ስልጠና ይዘት በማዘጋጀት ረገድ የግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሃብት ኢንስቲትዩት ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ስታተርስ ያሉትን የስልጠና መምሪያዎች በመከለስ፣ ከተለያዩ የስኳር ድንች ተመራማሪዎች የተገኙ አዳዲስ ዕውቀቶችን በማካተትና ጠንካራ የ"በመስራት- መማር" ተግባራትን በመንደፍ ከፍተኛ ትበብር አድርገዋል፡፡ እኚህ ሳይንቲስት ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ በ2005 ዓ.ም ከኡጋንዳ ብሔራዊ የግብርና ምርምር ድርጅት ተመራማሪዎችና ኬንያ ከሚገኘው የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት የአይ.ፒ.ኤም ማስተባበሪያ ጋር በመሆን ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት የሚሆን ሁሉን አቀፍ የአርሶ አደሮች የመስክ ትምህርት ቤት መምሪያ አዘጋጅተዋል፡፡ በተጨማሪም ይህንን ስልጠና በማዘጋጀት ሂደት ዶ/ር ስታተርስ የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ተመራማሪዎች የሆኑትን ሮበርት ሙዋንጋ፣ ቴድ ካሬይ፣ ጃን ሎው፣ ማሪያ አንድራዴ፣ ማርጋሬት ማክኢዋን፣ ጁዴ ጆኩ፣ ሳም ንማንዳ፣ ሳሚ አጊሊ፣ ጆናታን ኩምቢራ፣ ጆይስ ማሊንጋና ጎድፍሬይ ሙሉንጎን የኤች.ኬ.አይ የስርዓተ ጾታ ስፔሻሊስት የሆኑትን ሶኒ ዴቪድና አብረዋት የሚሰሩትን የኤን.አር.አይ ባልደረቦች ሪቻርድ ጊብሰን፣ ኦሬሊ ቤኮፍና ኬት ቶምሊንስን አማክረዋል፡፡ በዚሁ ሂደትም እኒሁ ሳይንቲስት የስልጠና ዶክመንቶችን ከዶናታ፣ የመጨረሻ ተጠቃሚዎችን መድረስና ሌሎች ፕሮጀክቶች ለዚህ ስልጠና በሚስማማ መልኩ በመውሰድ አዘጋጅተዋል፡፡ ስልጠናው እ.ኤ.አ በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ከተካሄደና የስልጠና መምሪያውም ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ የሰልጣኞችንና አመቻቾችን ፍላጎት ባማከለ ሁኔታ የተከለሰ ሲሆን ለስልጠናው አጋዥ የሆኑ የፓወር ፖይንት ገለጻወችም እንዲታከሉበት ተደርጓል፡፡ ይህ ደረጃውን የጠበቀ የስልጠና መምሪያና አጋዥ ዶክመንቶች እንዲዘጋጁ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ስላደረጉ ዶ/ር ስታተርስን በዚህ አጋጣሚ እናመሰግናለን፡፡ የዚህ ስልጠና ደረጃ የሚመጥነው ሌሎችን በተመሳሳይ ሁኔታ ሊያሰለጥኑ የሚችሉ ከፍተኛ የስርጸት ባለሙያዎችንና የእርሻ ሥራ አስኪያጆችን ነው፡፡ ስልጠናውን በየጊዜው የሚመጡ አዳዲስ ዕውቀቶችና የተሳታፊዎች ግብረ-መልሶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በየአመቱ ለመከለስ ታሳቢ ተደርጓል፡፡ በዚህ ሂደት በመጪው ጊዜያት ንቁና በስኳር ድንች ዕውቀት የበለጸገ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ዕቅድ ተይዟል፡፡ ይህ "ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" ስልጠና ኮርስ ስኳር ድንች ለገቢ ማስገኛና ጤና ማሻሻያ እንቅስቃሴን ዓላማዎች ለማሳካት አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ መተግበር የተጀመረው እ.ኤ.አ በ2009 ዓ.ም ሲሆን ዋና ግቡም እ.ኤ.አ በ2020 ዓ.ም ከሰሃራ በታች በሚገኙ 16 አገራት የሚገኙ 10 ሚሊዮን ቤተሰቦች ኑሮን በዘርፈ-ብዙ የስኳር ድንች ዝርያዎች ጥቅም ማሻሻል ነው፡፡ የአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው፣ በአለም አቀፍ የድንች ምርምር ማዕከል የስኳር ድንች ለገቢ ማስገኛና ጤና ማሻሻያ እንቅስቃሴ መሪ እ.ኤ.አ 2014 ዓ.ም ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 1 ምስጋና ይህ የስልጠና መምሪያና ሌሎች አጋዥ ዶክመንቶች የተዘጋጁት በአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው የቅርብ ዕገዛ በዶ/ር ታንያ ሰታተርስ ነው፡፡ ዶ/ር ታንያ የኮርሱ የተለያዩ ርዕሶችን ከዚህ በታች ከተገለጹት ተመራማሪዎች ጋር በመሆን አዘጋጅተዋል፡፡ ርዕስ ሁለትን ከአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው ጋር፣ ርዕስ ሶስትን ከቴድ ካሬይ፣ የአለም ሎሬት ሮበርት ሙዋንጋ፣ ጁዴ ጆኩ፣ ሲልቨር ቱም ዎጋሚሬ፣ ጆይስ ማሪንጋና የአለም ሎሬት ማሪያ አንድራዴ ጋር፣ ርዕስ አራትን ከማርጋሬት ቤንጃሚን፣ ሂዘር ካቸር፣ ጀሲካ ብላከንሺፕና የአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ርዕስ አምስትን ከማርጋሬት ማክኢዋን፣ ሪቻርድ ጊብሰን፣ የአለም ሎሬት ሮበርት ሙዋንጋ፣ ቴድ ካሬይ፣ ሳም ንማንዳ፣ ኢርና አቢዲን፣ የአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ጆይስ ማሊንጋ፣ ሳሚይ አጂሊ፣ የአለም ሎሬት ማሪያ አንድራዴና ጆናታን ኩምቢራ፣ ርዕስ ስድስትን ከቴድ ካሬይ፣ የአለም ሎሬት ሮበርት ሙዋንጋ፣ ጁዴ ጆኩ፣ ጆይስ ማሪንጋና አንቶኒ ጆኩ ጋር፣ ርዕስ ሰባትን ከሪቻርድ ጊብሰንና ሳም ንማንዳ ጋር፣ ርዕስ ስምንትን ከኦሬሊ ቤኮፍና ኪሪሚ ሲንዲ ጋር፣ ርዕስ ዘጠኝን ከኦሬሊ ቤኮፍና ኪሪሚ ሲንዲ ጋር፣ ርዕስ አስርን ከየአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ኪሪሚ ሲንዲና ዳንኤል ዲታቡላ ጋር፣ ርዕስ አስራ አንድን ከሶኒ ዴቪድ ጋር፣ ርዕስ አስራ ሁለትን ከአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ጎድፍሬይ ሙሎንጎና አዲየል ምባቡ፣ ርዕስ አስራ ሶስትን ከአለም ሎሬት ጃን ሎው ጋር፡፡ በተጨማሪም ሂልዳ ሙልዩአ፣ አዲየል ምባቡና ፍራንክ ኦጅዋንግ በሂደቱ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ነበራቸው፡፡ የዝግጅት ቡድኑ አባላት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት በስኳር ድንች አመራረት፣ አጠቃቀምና የአርሶ አደሮች የመማማር ሂደት ዙሪያ ያላቸውን የካበተ ተሞክሮ በመጠቀም ይህንን የስልጠና መምሪያ አዘጋጅተው አቅርበዋል፡፡ በርግጥ እነዚህ ተሞክሮዎች በክፍለ አህጉሩ ካሉ በርካታ የስኳር ድንች አርሶ አደሮችና እንደ የስርጸት ባለሙያዎች፣ ብሔራዊ ተመራማሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ አጓጓዦች፣ መንግስታዊ ካለሆኑ ድርጅቶች፣ የስነ-ምግብ ባለሙያዎች፣ ሚዲያዎችና የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ከመሳሰሉ ባለድርሻ አካላት ትብብር ውጪ የተገኙ ባለመሆናቸው በዚህ አጋጣሚ እያመሰገንን ይህ የስልጠና መምሪያ በስኳር ድንች ላይ ለሚሰሩት ስራ ጥሩ ግብዓት እንደሚሆናቸው እንተማመናለን፡፡ በዚህ መምሪያ ውስጥ የተካተቱት ፎቶግራፎች ከተለያዩ ቦታዎች የተገኙ ሲሆን ማርጋሬት ማክኢዋን፣ የአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ሪቻርድ ጊብሰን፣ ኢርና አቢዲን፣ ኦሬሊ ቤኮፍ፣ ኬት ቶምሊንስ፣ ሳም ንማንዳ፣ ጄ.ኦ ሱሊቫን፣ ጋብሬላ ቡርጎስ፣ ታንያ ስታተርስ፣ ኦላሳንሚ ቡንሚ፣ ቤንሰን ኢጂኦማ፣ ግራንት ሊ ኑርንበርግ፣ ሳሚይ አጂሊ፣ በሞት የተለየው ኮንስታነስ ኦዎሪ፣ ቴድ ካሬይ፣ የአለም ሎሬት ሮበርት ሙዋንጋ፣ አና ፓንታ፣ ኪሪሚ ሲንዲ፣ ፍራንክ ኦጅዋንግ፣ የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል ዲጅታል ክምችት፣ ጂ. ሆልምስ፣ ቢ. ኤድሙንድስና ኒኮል ስሚት ፎቶግራፎቹን ስላካፈሉን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በመምሪያው ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉት አብዛኞቹ ካርቱኖች የተሳሉት ደግሞ በሙቪን ዌር ነው፡፡ የዚህ መምሪያ የእንግሊዝኛ ጥራዞች የተዘጋጁት በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የሚደገፈው የለውጥ ሐዋርያትን መድረስ ፕሮጀክት አካል ሆነው ሲሆን የአማርኛ ጥራዞቹ ደግሞ በአውሮፓ ኮሚሽን የሚደገፈው የተሻለ አመጋገብ ለተሻለ ጤና ፕሮጀክት አካል ሆነው ነው፡፡ ይህንን መምሪያ በሌሎች ሕትመቶች ላይ ለመጠቀም ትክክለኛው አገላለጽ የሚከተለው ነው፡፡ Stathers, T., Low, J., Mwanga, R., Carey, T., David, S., Gibson, R., Namanda, S., McEwan, M., Bechoff, A., Malinga, J., Benjamin, M., Katcher, H., Blakenship, J., Andrade, M., Agili, S., Njoku, J., Sindi, K., Mulongo, G., Tumwegamire, S., Njoku, A., Abidin, E., Mbabu, A. (2013). Everything You Ever Wanted to Know about Sweetpotato: Reaching Agents of Change ToT Manual. International Potato Center, Nairobi, Kenya. 7 vols. x , 390 p. ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 2 ይህንን የስልጠና መምሪያ እንዴት መጠቀም ይቻላል? ይህ መምሪያ ስለ ስኳር ድንች ማውቅ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ይዟል፡፡ ስለሆነም በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ የስርጸት ባለሙያዎችንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞችን በማሰልጠን ተግባር ለተሰማሩ አካላት ጉልህ ጥቅም እንዳለው ይታመናል፡፡ በእነዚህ አካላት ስልጠና የወሰዱ ባለሙያዎች በበኩላቸው አርሶ አደሮችን ተግባር ተኮር በሆኑ መንገዶች በማሰልጠን ችግሮችን የመፍታትና ውሳኔ የመስጠት ክህሎታቸውን አሳድገው በኑሯቸው የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶችንና መልካም አጋጣሚዎችን በአግባቡ ማስተናገድ እንዲችሉ የመማር፣ የመጠየቅና የመሞከር ልምዳቸውን እንዲቀጥሉ ያበቋቸዋል፡፡ የስልጠናው መምሪያ 14 ርዕሶችን የያዘ ሲሆን ከመጀመሪያዎቹ የጎልማሶች ስልጠናና የሰብሉ መገኛና ጠቀሜታ ርዕሶች በመቀጠል ያሉ ርዕሶች የተዋቀሩት የሰብሉን የዕድገት ዑደት ተከትሎ ነው፡፡ እያንዳንዱ ርዕስ ስለ ርዕሱ ሊታወቁ የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን ከተነተነ በኋላ ለተግባራዊ የመማማር ተግባራት ግብዓት እንዲሆኑ የደረጃ በደረጃ መመሪያዎችን በመዘርዘር በአስሩ ቀን የአሰልጣኞች ስልጠና መርሃ-ግብር ውስጥ እንዴት ሊካተቱ እንሚችሉ ጥቆማን ይሰጣል፡፡ የመጨረሻዎቹ ሁለት ርዕሶች በዋነኝነት የሚያተኩሩት በአሰልጣኞች ስልጠናው መርሃ-ግብር አወቃቀርና ሊደረጉ በሚገቡ ዝግጅቶች ላይ ነው፡፡ በመምሪያው የተካተቱት አስራ አራቱ ርዕሶች ከዚህ በታች በአጭሩ ተገልጸዋል፡፡ ርዕስ 1 ጎልማሶችን እንዲማሩ መርዳት፡ ይህ ርዕስ የጥሩ የስልጠና አመቻች ባሕሪያትን በመተንተን እንዴት የማመቻቸት ክህሎትን ማሻሻል እንደሚቻል ይገልጻል፡፡ የፍላጎት ዳሰሳ በማከናወን፣ የመማማር ውጤቶችን በመቅረጽ፣ ግንዛቤን በመፍጠር፣ ተሳታፊዎችን በመመረጥ፣ የስልጠና መርሃ-ግብርን በማዘጋጀት፣ ግኝት-ተኮር የመማማር ዘዴዎችን በመቅረጽ፣ የረዥም ጊዜ ክትትል ስልቶችን በመቀየስና የማስፋትና ማስፋፋት ተግባራትን በመጠቀም እንዴት ስልጠናን ማቀድ እንደሚቻል ይጠቁማል፡፡ የ"በመስራት-መማር" ተግባራት ሰልጣኞች የተለያዩ ርዕሶችን በሚያመቻቹበት ወቅት ክህሎታቸውን ለማዳበር የሚያስችሉ ልምምዶችን እንዲያደርጉና ሰልጠናውን የመገምገም ጠቀሜታን እንዲረዱ ዕድል ይፈጥሩላቸዋል፡፡ ርዕስ 2 የስኳር ደንች መገኛና ጠቀሜታ፡ ይህ ርዕስ የስኳር ድንችን ታሪካዊ መገኛና ስርጭቱን እንዲሁም ወቅታዊ ጥቅሞቹንና በዓለም ደረጃ ያለውን የምርት መጠን ያብራራል፡፡ ርዕስ 3 የስኳር ድንች ዝርያ መረጣና ባሕሪያት፡ የስኳር ድንች የስር ቆዳና ስጋ ቀለም ከሃምራዊ እስከ ብርቱካንማ፣ ከቢጫ እስከ ነጭ፣ ከክሬም እስከ ወይንጠጅ ባለው ውስጥ ይለያያል፡፡ በተጨማሪም ሰብሉ የተለያየ የቅጠል ቅርጽ፣ የስር መጠንና ቅርጽ፣ ጥፍጥና፣ ልስላሴና የመድረሻ ጊዜ አለው፡፡ እነዚህ ባህሪያት አርሶ አደሮች የትኛውን ዝርያ ማምረት እንዳለባቸው ለመምረጥ ይረዷቸዋል፡፡ የዝርያዎችን የተለያዩ ባህርያት በአርሶ አደር ማሳ ላይ የማወዳደሪያ ዘዴዎች በዚህ ርዕስ ስር ተገልጸዋል፡፡ ርዕስ 4 ብርቱካናማ ስኳር ድንችና ስርዓተ-ምግብ፡ በዚህ ርዕስ ስር የምግብ ክፍሎችና ጥሩ አመጋገብን በተመለከተ ገለጻ የተሰጠ ሲሆን የቫይታሚን ኤ እጥረትን ጨምሮ ደረጃውን ያልጠበቀ አመጋገብ የሚያስከትለውን ጉዳትና ተለምዷዊ የድቀላ ዘዴን በመጠቀም ሰብሎችን በስነ-ሕይወታዊ መንገድ እንዴት ማበልጸግ እንደሚቻል ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ቫይታሚን ኤን የመሳሰሉ በቀላሉ ለመለየት የሚያስቸግሩ የንጥረ-ነገር ፍላጎቶችን ለማርካት ፍላጎትን የመፍጠር ሂደትን ውስብስብነት ጨምሮ ብርቱካናማ ስኳር ድንችን አዘውትሮ የመመገብ ጥቅም በስፋት ተብራርቷል፡፡ ርዕስ 5፡ የስኳር ድንች ዘር ስርዓት፡ በዚህ ርዕስ የተለያዩ የዘር ብዜት ደረጃዎችና የዘር ስርዓት ባለድርሻ አካላት በስርዓቱ ውስጥ ያላቸውን ሚና ጨምሮ የስኳር ድንች የዘር ስርዓቶች በሰፊው ተብራርተዋል፡፡ ብርቱካናማ ስኳር ድንችን ለማስፋፋት ይቻል ዘንድ የአንድ ጊዜ ዘር ስርጭትን ወይም ቀጣይነት ያለው ስርጭት አቀራረብን ለመጠቀም ውሳኔ ላይ መድረስ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፉ ጉዳዮችን በተመለከተ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የዘር ብዜትና ስርጭት ዘዴዎችን ለማቀድ የሚረዱ ምሳሌዎች የተሰጡ ሲሆን ንጹህ ዘር ለመምረጥ፣ ለማቆየትና ለማባዛት የሚጠቅሙ ዘዴዎችም ቀርበዋል፡፡ ርዕስ 6 የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ፡ ይህ ርዕስ በቂ ዘር በተከላ ወቅት ማግኘት እንዲቻል ቀድሞ የማቀድን ጥቅም ጨምሮ ለጥሩ የስርና ሃረግ ምርት የመሬት ዝግጅት፣ የተከላ ዘዴዎች፣ የሰብል ስብጥር፣ የንጥረ-ነገር ፍላጎት፣ የሰብሉ ዋና ዋና የዕድገት ደረጃዎችና በተጓዳኝ የሚያስፈልጉ የአያያዝ ተግባራትን በስፋት ይዳስሳል፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ተባይና በሽታ ቁጥጥር፡ ይህ ርዕስ የስኳር ድንች ቀንደኛ አጥፊ ተባይ የሆነውን ነቀዝና ዋና በሽታ የሆነውን ቫይረስ የህይወት ዑደት በአግባቡ መገንዘብ ተባዩና በሽታው የሚያደርሱትን ጉዳት አርሶ አደሮች ስኬታማ በሆነ መንገድ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 3 እንዲቆጣጠሩ እንዴት እንደሚያስችላቸው ያብራራል፡፡ በተጨማሪም እንደ ፍልፈል የመሳሰሉ እንስሳቶችን የጉዳት ምልክቶችና የመቆጣጠሪያ መንገዶች ይተነትናል፡፡ ርዕስ 8 ምርት መሰብሰብና ድሕረ-ምርት አያያዝ፡ በምርት መሰብሰብና ማጓጓዝ ወቅት የሚደርሱ ጉዳቶች የስሩን የቆይታ ጊዜና ዋጋን ይቀንሳሉ፡፡ ለድርቆሽ የሚዘጋጅ የስኳር ድንች ስርን ከመጠን በላይ በጸሐይ ማድረቅና ለረዥም ጊዜ ማከማቸት የቤታ ካሮቲን ይዘቱ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ ይህንን ችግር መቅረፍ እንዲቻል ይህ ርዕስ ለድርቆሽ ጥሩ የሆኑ የድሕረ-ምርት አያያዝና አከመቻቸት ተግባራትን የሚተነትን ሲሆን የስር አቅርቦትን፣ ጥራትንና ዋጋን ለመጨመር የሚያስችሉ የማጥገግና የክምችት ዘዴዎችንም ያቀርባል፡፡ ርዕስ 9 ምርት ማቀነባበርና አጠቃቀም፡ ጣፋጭና በንጥረ-ነገር የበለጸጉ በርካታ ምግቦችና ሌሎች አዋጪ የምግብ ምርቶችን ከብርቱካናማ ስኳር ድንች ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ ይህ ርዕስ አነዚህ ምግቦችን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል የሚገልጽ ሲሆን ስኳር ድንች ለእንስሳት መኖነት ያለውንም ጥቅም ይዳስሳል፡፡ ርዕስ 10 ግብይትና ስራ ፈጠራ፡ በዚህ ርዕስ አምስቱ የግብይት ምሶሶዎች (ማለትም ምርት፣ ዋጋ፣ ቦታ፣ ማስተዋወቅና ሰው) ከስኳር ድንች ስርና ሌሎች ምርቶች አኳያ ተተንትነዋል፡፡ ርዕስ 11 የስርዓተ-ጾታና ብዝሃነት ጉዳዮች፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ በግብርና በአጠቃላይና በስኳር ድንች እሴት ሰንሰለት ውስጥ በተለይ የስርዓተ-ጾታና ብዝሐነት ጉዳዮችን ጠቀሜታ መገንዘብ ምን ያክል አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ስኳር ድንች በሴቶች ብቻ የሚመረትበት፣ በወንዶች ብቻ የሚመረትበት ወይም በሁለቱም የሚመረትባቸው ሁኔታዎች የቀረቡ ሲሆን ወንድና ሴት አርሶ አደሮች የሚገጥሟቸው ተግዳሮቶችና ቅድሚያ የሚሰጧቸው ፍላጎቶቻቸውም ተብራርተዋል፡፡ የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች እንዴት በስኳር ድንች ፕሮግራሞች ውስጥ ሊካተቱ እንደሚችሉ የሚያሳዩ ጥሩ ተሞክሮዎችም ቀርበዋል፡፡ ርዕስ 12 የብርቱካናማ ስኳር ድንች ስርጭትና አቀባበልን መከታተል፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ የክትትል አስፈላጊነትና በክትትልና ግምገማ መካከል ያለው ልዩነት ተገልጧል፡፡ አስከትሎም የስኳር ድንች ዘርን ስርጭት፣ የምርት አቅምና ጥቅም ለመከታተል የሚያስችሉ የተለያዩ ዘዴዎች ተብራርተዋል፡፡ የስኳር ድንች ስልጠናዎችን የረዥም ጊዜ ተጽዕኖና ተደራሽነት ለመረዳት ማን እንደሰለጠነ ሙሉ መረጃ መመዝገብ አስፈላጊ መሆኑና ይህም መረጃ ለክትትል ተግባራት ወሳኝ መሆኑ ተገልጧል፡፡ ርዕስ 13 ስለ "ስኳር ደንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ የ10 እና 5 ቀናቱ የ"በመስራት-መማር" የአሰልጣኞች ስልጠና መርሃ-ግብር ዝርዝር ቀርቧል፡፡ መርሃ-ግብሩ በየቀኑ የሚሸፈኑ ርዕሶችን፣ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶችን፣ የሚከወኑ ተግባራትን ቅደም-ተከተልና ጊዜ እንዲሁም የሚያስፈልጉ ግብዓቶችንና ቅድመ-ዝግጅቶችን በዝርዝር ይገልጻል፡፡ የስልጠና አመቻቾች በአካባቢያቸው ያሉ ተሳታፊዎችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በዚህ ርዕስ ስር የተጠቀሰውን መርሃ-ግብር ሊያሻሽሉት ይችላሉ፡፡ ርዕስ 14 ግብረ-መልሶች፡ የስልጠናው መምሪያ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ የበለጠ እንዲሻሻል ተሳታፊዎች ግብረ-መልስ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ ግብረ-መልሶቹን ለመስጠት የሚያስችሉ ቅጾች ተዘርዝረዋል፡፡የዚህ የስልጠና መምሪያ ተጠቃሚዎች የሚኖራቸውን ማንኛውንም አስተያየት በዚህ ርዕስ ውስጥ በተጠቀሱት ቅጾች ላይ በበሙላት ለዝግጅት አስተባባሪዋ ለአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው በኢሜይል አድራሻቸው j.low@cgiar.org መላክ የሚችሉ ሲሆን አስተያየቶቹም ጠቃሚ ሆነው ከተገኙ በመምሪያው ቀጣይ ህትመቶች ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋል፡፡ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 4 ማውጫ ርዕስ 13፡ “ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም .....................................................6 13.1 ስለ አስሩ ቀን የ“ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና አጠቃላይ መግለጫ........................................ 6 13.2 የአምስቱ ቀን “ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና መግለጫ..................................................... 20 13.3 የ “ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና ደጋፊ ገለጻዎች ............................................................ 28 13.4 “ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠናን ለመደገፍ የተዘጋጁ የመማሪያ ካርዶች ................................ 29 ርዕስ 14: ግብረ-መልስ ............................................................................................................................................30 አባሪዎች ............................................................................................................................................................34 አባሪ 1. ማነቃቂያዎች፣የቡድን መልመጃዎች እና የስልጠና ድርጊት መርኃ-ግብር ........................................................................ 34 አባሪ 1.1ሀ. ማነቃቂያዎች........................................................................................................................................... 34 አባሪ 1.1ለ. የቡድን መልመጃዎች................................................................................................................................. 34 አባሪ 1.2. መሰረታው የስኳር ድንች ዕውቀት ዳሰሳ ፈተና................................................................................................... 36 አባሪ 1.3. የስልጠና የድርጊት መርኃ-ግብር .................................................................................................................... 37 አባሪ 2. የስኳር ድንች ዕውቀት ድረ-ገጽ ላይ ያሉ ጹሑፎችን እንዴት መጠቀም ይቻላል? ............................................................. 38 አባሪ 3. የስኳር ድንች ዝርያዎች ባሕሪያት መተንተኛ ቻርት፣ የቤታ ካሮቲን ቀለም ቻርትና በአርሶ አደር ማሳ ላይ የሚደረጉ ሙከራዎች መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ .................................................................................................................................................... 38 አባሪ 3.1 የስኳር ድንች ዝርያዎች ባሕሪያት መተንተኛ ...................................................................................................... 38 አባሪ 3.2. የስኳር ድንች የቤታ ካሮቲን መጠን ማሳያ የቀለም ቻርት ..................................................................................... 41 አባሪ 3.3. የስኳር ድንች ዝርያዎችን ለመለየት የምንጠቀምባቸውን ቁልፍ የተክል ገጽታ መረጃዎች መሰብሰቢያ ቅጽ ........................ 42 አባሪ 3.4. በአርሶአደር ማሳ ላይ ለሚከናወኑ ሙከራዎች ከአርሶአደሩ ጋር የሚደረግ የውል ስምምነት ናሙና .................................. 43 አባሪ 5. ከቲሹ-ከልቸር ላቦራቶሪ ለሚወጡ ተክሎች እንክብካቤ ማድረግና የመረብ ድንኳን መገንባት ............................................. 52 አባሪ 5.1 ከቲሹ-ከልቸር ላቦራቶሪ የወጡ ተክሎችን ማጓጓዝ፣ መቀበል፣ ማጠንከር፣ ማዛመት እና እንክብካቤ ማድረግ .......................... 52 አባሪ 5.2. መስራች ዘሮችን በመረብ ድንኳን ሳይበከሉ የማቆየት ዘዴ .................................................................................... 54 አባሪ 6. የአፈር አይነትን ማወቅ .................................................................................................................................. 56 አባሪ 11. የሥርዓተ-ጾታ የሁኔታዎች ትንተና ቢጋር............................................................................................................. 57 አባሪ 11ሀ. ለቡድን ቃለ-መጠይቆች የሥርዓተ-ጾታ የሁኔታዎች ትንተና ቢጋር .......................................................................... 57 አባሪ 11ለ. ለወንድና ሴት የመሬት ባለቤቶች ቡድን የተዘጋጀ ቢጋር (ወንዶችና ሴቶች የተለያየ የስኳር ድንች ማሳ ያላቸው እንደሆነ) ...... 59 አባሪ 12. የስኳር ድንች መሰረታዊ መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ................................................................................................. 63 ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 5 ርዕስ 13፡ “ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም 13.1 ስለ አስሩ ቀን የ“ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና አጠቃላይ መግለጫ እነዚህ የ“እየሰሩ-መማር” ላይ ተመስርተው የሚከናወኑ ተግባራት የተቀረጹት በዚህ ስልጠና ላይ የሚሳተፉት ሰልጣኞች ግኝትን መሰረት ያደረገ የተግባር ስልጠና ዕድሎችን እንዲያገኙ ለመርዳት ነው፡፡ ስለስኳር ድንች በዚህ አይነት መንገድ መሰልጠን ሰልጣኞችን በተመሳሳይ መንገድ ሌሎችን እንዲያሰለጥኑ ዕድል እንደሚሰጣቸው ይታመናል፡፡ ሙሉው የአስር ቀኑ የአሰልጣኞች ስልጠና መርኃ-ግብር በዚህ ንዑስ-ርዕስ ስር የተገለጸ ሲሆን (ሰንጠረዥ 13.1ን ይመልከቱ) በቀጣይ የሚከናወነው የአምስት ቀናት ስልጠና መርኃ-ግብር ደግሞ በዚሁ ርዕስ በንዑስ-ርዕስ 13.2 ላይ ተዘርዝሯል፡፡ ይህ የስልጠና መርኃ- ግብር አመቻቾች ስልጠናውን ለማቀድ እንዲችሉ ዕገዛ የሚያደርግላቸው ቢሆንም ሙሉ በሙሉ እንዲተገብሩት የሚገደዱት አይደለም፡፡ ስለሆነም ሰልጣኞችን ባማከለ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ አመቻቾች የራሳቸውን ፈጠራ መጨመር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከ“ስለስኳርድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና የሚጠበቁ አጠቃላይ ውጤቶች በአስሩ የስልጠና ቀናት የተሰጡትን ጽንሰ-ሐሳቦች፣ የተግባር ልምምዶችና ስትራቴጂዎች በመተግበር ተሳታፊዎች:  ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ያሉትን የስኳር ድንች አመራረት፣ አጠቃቀምና እና ግብይት ጉዳዮች ይረዳሉ፤  እንደ ንጹህ የስኳር ድንች ዘር መረጣና ማቆየት፣ የስኳር ድንች ሰብል ተባይና በሽታ ቁጥጥር እና ከብርቱካንማ ስኳር ድንች የተለያዩ ምግቦች አዘገጃጀት የመሳሰሉ ቁልፍ ክህሎቶችን ለሌሎች ያካፍላሉ፣  በሰው ልጅ የምግብ ስርዓት ውስጥ የቫይታሚን ኤ ጠቀሜታን እና ብርቱካናማ ስኳር ድንችና ሌሎች ምግቦች እንዴት የቫይታሚን ኤ እጥረትን ለመቅረፍ እንደሚያስችሉ ይረዳሉ፤  ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት የስርዓተ-ጾታ ሚናዎች እንዴት የስኳር ድንች አመራረት፣ አጠቃቀምና እና ግብይት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳርፉ ይረዳሉ፤  ለመስክ የመንግስት የልማት ስርጸት ሰራተኞችና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች የሚሰጡ ግኝት ተኮር የሆኑ "እየሰሩ-የመማር" ስልጠናዎችን በልበ-ሙሉነት ለማከናወን ይችላሉ፡፡ ዒላማ የተደረጉ የስልጠናው ተሳታፊዎች፡ በወረዳ ደረጃ የሚገኙ የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች፣ የግብርና ተመራማሪዎች እና የጤና ስርጸት ሰራተኞች ስልጠናውን ይወስዱታል ተብሎ ይታሰባል፡፡ አነኚህ ሰልጣኞች በቀጣይ አርሶአደሮችን ለማሰልጠን እንዲችሉ ለግልና ለመንግስት የመስክ የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ስልጠናውን እንዲሰጡ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ከዚህ በታች የተመለከተው የስልጠና መርኃ-ግብር የስልጠናውን ርዕስ፣ ከስልጠናው ሊገኙ የሚችሉ ውጤቶች ብሎም በሚቀጥሉት 10 ቀናት የአሰልጣኞች ስልጠና ቆይታ ወቅት የሚከወኑ ተግባራትን አካቷል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ርዕሶች ስር የ"እየሰሩ-መማር" ተግባራቱ ደረጃ በደረጃ ተጠቅሰዋል፤ ለምሳሌ ተግባር 1.3.1 በንዑስ-ርዕስ 1.3 ላይ ተጠቅሷል፡፡ የ"እየሰሩ-መማር" ተግባራት ዝርዝሮች ተጠባቂ ውጤቶችን፣ የሚፈጁትን ጊዜ፣ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶችንና ግብዓቶችን እንዲሁም አመቻቹ ተግባራቱን ለመምራት የሚያስችለውን የደረጃ በደረጃ ምክሮችን ያጠቃልላሉ፡፡ ይህንን ስልጠና ለመስጠት የሚያስፈለጉ ቅድመ-ዝግጅቶች በሰንጠረዡ የመጨረሻው ረድፍ በዝርዝር የተገለጹ ሲሆን ይህም የመማማሪያ ማሳዎችንና ገበያዎችን፤ በተለይ ማሳዎች መተከል የሚገባቸው ከሆነ አስቀድሞ ለማዘጋጀት እንዲያስችል ለማድረግ ነው፡፡ የስልጠናው የመስክ ተግባራት የአጠቃላይ የአስር እና አምስት ቀናት ስልጠናው ዋና አካላት ሲሆኑ የመማማሪያ ማሳዎቹ ለስልጠናው ቦታ ቅርብ የሆኑ፣ የተለያዩ የስኳር ድንች ዝርያዎች የተተከሉባቸው፣ የደረሱ ሀረጎችና ስሮች ያሏቸው፣ ጥቂት በቫይረስና በነቀዝ የተጠቁ ተክሎች ያሉባቸውና ለመማማሩ ሂደት የሚያስፈልጉ ናሙናዎች እንዲወሰዱ ፈቃደኛ በሆኑ አርሶአደሮች የተያዙ መሆን ይገባቸዋል፡፡ በጽንሰ-ሃሳብ ደረጃ ሰልጣኞቹ የስኳር ድንች ፈጣን የማባዣ ዘዴን የሚተገብሩበት መደብና ለስር ማከማቻ የሚሆኑ ጉድጓዶችን የሚያዘጋጁበት መሬት ለስልጠናው ቦታ በጣም ቅርብ በሆኑ አርሶአደሮች ዘንድ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቅድመ-ዝግጅቶች የጊዜ ሰሌዳ በሰንጠረዥ 13.2 ላይ ተመልክቷል፡፡ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 6 ሰንጠረዥ 13.1. የአስሩ ቀናት “ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና መርኃ-ግብር ዝርዝር የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ 1 መግቢያ፣ተሳታፊዎች የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - መግቢያ፡ የቡድን ተግባራት [30 ደቂቃ] - ፍሊፕ ቻርቶች፣ አድምቆ ለመፃፍ የሚያስችሉ ባለህብረ ቀለም ከስልጠናው የሚጠብቁት - የስልጠናውን መርሃ ግብር - የሰልጣኞች ግምት፡ ሰልጣኞች በተናጠል በወረቀት ማርከሮች፣ ወረቀት ግድግዳ ላይ ማያያዣ መርፌዎች፤ ነገር፣ በመማማር መረዳትና እንዴት ሌሎችን ያስቀመጧቸውን ተጠባቂ የመማማር ውጤት ግምቶች ለሌሎች - ሰልጣኞች ስለ ስኳር ድንች ያላቸውን እውቀት ለመለካት ውጤቶች ላይ ስምምነት በስኳር ድንች ዙሪያ ማካፈልና ወረቀቶቹን በቡድን መከፋፈል፤ በሰልጣኞቹ የሚረዱ ፈተና ወረቀቶች (አባሪ 1.2) ፤ ላይ መድረስ፣ስለስኳር እንዲያሰለጥኑ ለመርዳት ያቀደ የተሰጡትን ግምቶች ከአመቻቾቹ ግምት ጋር በማጣጣም - የስልጠና መርኃ-ግብሩ አጭር መግለጫ (ቀናት እና ለየቀናቱ ድንች ጠቀሜታ አጠቃላይ መሆኑን ይገነዘባሉ፤ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶቹን መከለስ የተዘረዘሩ ርዕሶችን) ፤ መግለጫ፣ ስርዓተ-ጾታና - በስኳር ድንች አመራረትና [45 ደቂቃ] ፤ ብዝኃነት በስኳር ድንች - በንዑስ-ርዕስ 9.4.1 እና 9.4.2 ላይ ለተገለጹት ከስኳር ድንች አጠቃቀም ዙሪያ ስላሉ - የመግቢያ ፈተና፡ ስልጠናውን ከመጀመራችን በፊት ሰልጣኞች ዕሴት ሰንሰለት ውስጥ ለሚዘጋጁ የምግብ አይነቶች ግብዓት የሆኑ ቁሶች፣ ማነቆዎች ያውቃሉ፤ ስለ ስኳር ድንች ያላቸውን አጠቃላይ እውቀት መለካት ያለው ጠቀሜታ፣ ማብሰያዎችና ማገዶ፤ - የሥርዓተ-ጾታ ጉዳዮች በስኳር ያስፈልጋል [30 ደቂቃ] (አባሪ1.2) የብርቱካንማ ስኳር ድንች አጥሚት: ለ4 ሰዎች የሚሆን ድንች የዕሴት ሰንሰለት ውስጥ - የስልጠናው መርሃ ግብር ቅኝት [10 ደቂቃ] ያላቸውን ጠቀሜታ ይረዳሉ ለማዘጋጀት(የግብዓቶቹን መጠን እንደተጠቃሚው - ስለ ስኳር ድንች ታሪካዊ አመጣጥና በሰልጣኞች ዘንድ ያለው - ሁለት የስኳር ድንች ምግቦችን ብዛት ማስተካከል ይቻላል) የሚሆኑ ቅመማ ቅመሞች፣ እውቀት፡ ጥቂት አባላት ባሉት የሰልጣኞች ቡድን በኩል ያዘጋጃሉ፤ 1 ሙሉ የገበታ ማንኪያ ስፍር የስኳር ድንች ዱቄት፣ 4 ስለስኳር ድንች ያላቸውን እውቀት፣ ታሪካዊ አመጣጡን፣ ባህላዊ ጠቀሜታውን፣ የአመራረት ሂደቱንና አጠቃቀሙን፣ እንዲሁም ሙሉ የገበታ ማንኪያ ስፍር የማሽላ፣ ካሳቫ ወይም በአርሶ አደሩ ዘንድ የሚታዩ መሰረታዊ ማነቆዎችን መወያየት በቆሎ ዱቄት፤ 1 ሙሉ የገበታ ማንኪያ ስፍር የአኩሪ (30 ደቂቃ ለቡድን ውይይት እና 5 ደቂቃ ለእያንዳንዱ ቡድን አተር ዱቄት፣ 1 አነስተኛ ሎሚ፣፣ 2 የሻይ ማንኪያ ለማቅረብ) ስኳር፣ 6 ኩባያ ውሃ፣ ስኒዎች፣ ባለ እጀታ ብረት ድስት፣ - የብርቱካንማ ስኳር ድንች ምግብ ዝግጅት፡ ቡድኖች እንደ ማብሰያ፣ ክብሪት፣, ከእንጨት የተሰራ ማማሰያ፣ የገበታ አጥሚትና ቦምቦሊኖ የመሳሰሉ ምግቦችን ያዘጋጃሉ፡፡ ማንኪያ፣ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ዝርዝር በንዑስ-ርዕስ 9.4 ላይ የብርቱካንማ ስኳር ድንች ቦምቦሊኖ: የዚህን አይነት ተገልጧል [1.5 ሰዓት] ምግብ ለ10 ሰዎች በሚበቃ መልኩ ለማዘጋጀት ግማሽ - ገለጻ 2፡ የስኳር ድንች አመጣጥ እና ጠቀሜታው (ርዕስ 2) ኩባያ የስኳር ድንች ልንቅጥ ወይም ዱቄት (30 በመቶ) እንዲቀርብ ተደርጎ የቡድን ውይይት እንዲካሄድ ማድረግ፣ [45 ፣ ሁለት ኩባያ የስንዴ ዱቄት (70 በመቶ) ፣ 2 የገበታ ደቂቃ] ማንኪያ ሙሉ ስፍር ስኳር፣ ትንሽ ጨው፣ 2 ኩባያ የምግብ ዘይት፣ 1 የገበታ ማንኪያ ሙሉ ስፍር እርሾ፣ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 7 የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ - ገለጻ 11፡. የስርዓተ-ፆታ እና ብዝሃነት ጉዳዮችና ለስኳር ድንች ሙቅ ውሃ፣ ጎድጓዳ ሰሃን፣ ማጥለያ፣ ሊጥ ማድቦልቦያ፣ ተግባራት የሚኖራቸው ጠቀሜታ፣ ይህንንም በቡድን ውይይት መጥበሻ፣ ሳህን፤ መደገፍ [45 ደቂቃ] - ገለጻ 2፡ የስኳር ድንች አመጣጥ እና ጠቀሜታው - ገለጻ 11፣. የስርዓተ-ፆታ እና ብዝሃነት ጉዳዮችና ለስኳር ድንች ተግባራት የሚኖራቸው ጠቀሜታ፣ 2 የተለያዩ የስኳር ድንች የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 3.5.1: ልዩነትን መንቀስ፤ የመስክ ተግባር: በቅርብ ቦታ - ተግባር 3.5.1. ሰልጣኞች ጥቂት ናሙናዎችን ሊሰበስቡባቸው ዝርያዎችና ባህሪያቸው - ስለስኳር ድንች መሰረታዊ ከሚገኘው መስክ ላይ የተለያዩ የስኳር ድንች ባህሪያትን መለየት፤ የሚችሉበት ብዙ ዝርያዎች የተተከሉበት በአካባቢ የሚገኝ የዝርያ ልዩነቶች ይገነዘባሉ፤ ከአርሶአደሩ/ሯ ጋር ለምን እያንዳንዱን ዝርያ እንደሚያመርቱ ማሳ፣ ፍሊፕ ቻርት ፣ ማርከር፣ ነጭ ወረቀት፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ - ለአካባቢያቸው ተስማሚ መወያየት እና ከእነኝህ የተለያዩ ዝርያዎች ስሮችን በማውጣት ለተሳታፊዎች ማስታወሻ ደብተር፣ የስኳር ድንች ዝርያዎችን ስለሆኑ ቢያንስ ስለ 3 ለጣዕም ሙከራ መጠቀም (3.5.1 ይመልከቱ) [2 ሰዓት 45 ባህሪያት መተንተኛ (አባሪ 3.1) እና የቤታ ካሮቲን ይዘትን ዝርያዎች ባህሪ ያውቃሉ፤ ደቂቃ] ፤ መለኪያ የእጅ መፅሀፍ (አባሪ 3.2) በበቂ መጠን፤ አሳታፊ - በስኳር ድንች ዝርያዎች ላይ - ተግባር 3.5.2: የስኳር ድንች ዝርያዎችን መምረጥ፡ የትኛው የስኳር ድንች ስር ጣዕም መገምገሚያ ቅጽ (ቅጽ 5ለ እና 5 ቢ የሚታዩትን ዋና ዋና ባህሪያት ባህሪ ለየትኛው ጉዳይ እንደሚጠቅም በዋና ዋና የስኳር ድንች ለ2፣ አባሪ 3.5ለ) በበቂ መጠን፤ ምድጃ፣ ነዳጅ፣የማብሰያ ለይተው አርሶአደሮች መለያዎች/ባህሪያት ላይ የቡድን ውይይት ማድረግ፡፡ ከዚያም እቃ፣ ውሃ፣ ክብሪት እና ቢላዋ፡፡ እንዲለዩ መርዳት ይችላሉ፤ ተሳታፊዎች የማስተዋወቂያ ፖስተሮችን ያዘጋጃሉ/ - ተግባር 3.5.2. ፍሊፕ ቻርት (ቢቻል 1 ገፅ ለአንድ ተሳታፊ) ፣ - የዝርያ ምርጫ እንደየሰዉ ለአካባቢያቸው እንደሚመች በዋና ዋና የስኳር ድንች ዝርያዎች ባለቀለም ብዕር ቢቻል ብዛት ያለው ሰማያዊ፣ ቡናማ፣ እንደሚለያይ ይረዳሉ፤ ላይ የስልጠና ቁሳቁሶችን ያዘጋጃሉ (3.5.2ን ይመልከቱ) [70 ብርቱካንማ እና ቢጫ፣ በአለም አቀፍ የድንች ምርምር ማዕከል - በምርት መሰብሰቢያ ወቅት ለምን ጥንቃቄ መደረግ ደቂቃ] የተዘጋጀው የብርቱካንማ ስኳር ድንች ዝርያዎች ማውጫ፤ ፤ - ገለጻ 3፡ የስኳር ድንች ሰብል ተለያይነት፤ የዝርያ ባህርያትና እንዳለበት ያውቃሉ፤ - ገለጻ 3. ተፈጥሯዊ የስኳር ድንች ተለያይነትን መዳሰስ፡ የተለያዩ የተለያዩ የስኳር ድንች ዝርያዎችን በአርሶ አደር ማሳ ላይ - ዝርያዎችን በቅደም ተከተል የስኳር ድንች ዝርያዎችን ባህሪያትና በአርሶ አደር ማሳ ላይ የመገምገሚያ ዘዴዎች፣ የማስቀመጡን ሙከራ እንዴት የተለያዩ ዝርያዎችን የመሞከር ስልትን መግለጽና ውይይት (45 - ቅድመ ዝግጅቶች፣ ለተግባር 3.5.1. - የተለያዩ ዝርያዎችን ማድረግ እንዳለባቸው ደቂቃ) ፡፡ የያዘና ለስልጠናው ቦታ ቅርብ የሆነ የአርሶአደር ማሳ መለየት፣ ያውቃሉ (ቀይ፣ ቢጫና አርሶአደሩን በማግኘት ማሳው በሰልጣኞች እንደሚጎበኝ፣ አረንጓዴ ካርዶች መጠቀም) ፤ በሰልጣኞቹ ቃለ-መጠይቅ እንደሚደረግ፣ ከየዝርያው ከ1-2 - የጣዕም ሙከራ ለማከናወን ተክሎች ለመማማሪያ ስራቸውና ሃረጋቸው እንደሚነቀል ልምድ ያገኛሉ (ቀይ፣ ቢጫና በመንገር ስምምነቱን መጠየቅ፡፡ ለተነቀሉት ተክሎች ማካካሻ አረንጓዴ ካርዶች መጠቀም) ፤ ለአርሶ አደሩ መስጠት እንደሚገባ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 8 የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ 3 ብርቱካንማ ስኳር ድንችና የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ሃሳብ ማንሸራሸር፡ የተመጣጠነ ምግብ ማለት ምን ማለት ነው? - ፍሊፕ ቻርት፣ ባለቀለም ማርከር፣ ፕላስተር፣ ግድግዳ ላይ ስርዓተ-ምግብ - የተመጣጠነ አመጋገብ ምን - ገለጻ 4ሀ እና ተግባር 4.8.1፡ ምግቦቻችን ምን ያክል ማጣበቂያ መርፌ፣ እንደሆነና ለምን የተመጣጠኑ ናቸው? ጥሩ የሆነ ስርዓተ-ምግብ ምንድነው? - ተግባር 4.8.1: ገለጻ 4ሀ፣ ፍሊፕ ቻርት፣ ብዕር፣ ፕላስተር፣ እንደሚጠቅም ይረዳሉ፤ (ንዑስ ርዕስ 4.8.1ን ይመልከቱ) [10 እና 40 ደቂቃ - ተግባር 4.8.2፡ ገለጻ 4ለ፣ ነጭ ወረቀት፣ ብዕር፣ እንደ ዱባ፣ - ብርቱካንማ ስኳር ድንች በተከታታይ] ፤ ፓፓያ፣ ብርቱካንማ ስኳር ድንች፣ የሚገኙ ከሆነ አገር በቀል እንዴት የቫይታሚን ኤ እና ከውጪ የገቡ አትክልቶች ያሉ በቫይታሚን ኤ የበለጸጉ - ገለጻ 4ለ እና ተግባር 4.8.2፡ በቫይታሚን ኤ ከዳበሩ ምግቦች እጥረትን ለመቀነስ እንደሚረዳ ተክሎች፤ ያውቃሉ፤ መመገብ፡ ቫይታሚን ኤ፣ ብርቱካንማ ስኳር ድንች ለምን - ተግባር 4.8.3. በፎቶግራፍ የተደገፉ ተመሳስሏዊ አጥሚት - ለህጻናት ተስማሚ የሆኑና የቫይታሚን ኤ እጥረትን ይታደጋል? የቫይታሚን ኤ እጥረት ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ካርዶች እና በንጥረ-ነገር የበለጸገ በንጥረ-ነገር የበለጸጉ ተጠቂዎች እነማናቸው? (ንዑስ ርዕስ 4.8.2ን ይመልከቱ) [10 የህጻናት ምግብ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ግብዓቶች ዝርዝር የብርቱካናማ ስኳር ድንች እና 20 ደቂቃ በተከታታይ] (በእጅ የሚያዝ መማሪያ መፅሃፍ 4.8.3ሀ) ፤ ምግቦችን በአካባቢ ከሚገኙ - ተግባር 4.8.3: ተመሳስሏዊ የአጥሚት አሰራር (ንዑስ ርዕስ - ተግባር 4.8.4: የርዕስ 4 የስልጠና መምሪያ፤ ግብዓቶች እንዴት ማዘጋጀት 4.8.3ን ይመልከቱ) {ማስታወሻ: ዕውነተኛው የአጥሚት አሰራር እንደሚችሉ ያውቃሉ፤ የሚከናወነው በስልጠናው የመጀመሪያ ቀን ሲሆን ሌሎች - የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ምግቦች ደግሞ በስልጠናው ዘጠነኛ ቀን ላይ ይከናወናሉ. [1 በቤተሰብ ስርዓተ-ምግብ ሰዓት] ውስጥ ያላቸውን ጠቀሜታ - ተግባር 4.8.4: ግንዛቤን ማሳደግና የብርቱካንማ ስኳር ድንች ይረዳሉ፤ ፍላጎትን መፍጠር (ንዑስ ርዕስ 4.8.4ን ይመልከቱ) [55 ደቂቃ] - የቡድን ውይይት፡ የአካሄዶቻችንን ጥንካሬና ድክመት ብሎም የተጠቀምናቸውን መሳሪያዎች መገምገም፡፡ ስርዓተ-ፆታን በስራዎቻችን ውስጥ ማካተታችንን ማየት? [30 ደቂቃ] 4 የስኳር ድንች የተከላ ሃረግ የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 5.10.1: ንጹህና የተባዙ ለተከላ የሚሆኑ ሀረጎች: ንጹህ - ተግባር 5.10.1: በቫይረስ የተጠቁ ጥቂት ተክሎች ያሉበት ቁርጥራጮችን መምረጥ፣ - ጥራት ያላቸውን የስኳር ድንች የተከላ ሃረግ ቁርጥራጮችን ለማግኘት የመስክ ተግባር፣ የተከላ በቅርብ የሚገኝ ማሳ፣ በግማሽ የተጠናቀቀ የፈጣን ሃረግ ማቆየትና ማባዛት የተከላ ሃረጎችን መለየት፣ ሀረጎችን መውሰድ፣ ወደ ተከላ ቁርጥራጮች መቆራረጥ፣ በፈጣን ማባዣ መደብ፣ አምስት ቢላዋዎች፣ሁለት የውሃ ባልዲ፣ የእጅ መምረጥ፣ ማቆየት ይችላሉ፤ የማባዣ መደብ ላይ እንዴት ማባዛት እንደሚቻል መማር፣ መኮትኮቻዎች፡፡ የተለያየ የመባዛት አቅም ያላቸው ሁለት - ሥለ አሉታዊ /ነጋቲቭዊ/ እና እንዴት መንከባከብ እንደሚቻል እንዲሁም መቼና እንዴት ዝርያዎች ከስልጠናው ጊዜ ስምንት ሳምንታት ቀድሞ ብሎ አዎንታዊ /ፖዘቲቭ/ የስኳር ይተከላሉ ብሎ መወያየትና፣ የሀረግ የመባዛት አቅምን ማስላት የተተከሉበት ፈጣን የሃረግ ማባዣ መደብ፣ ፍሊፕ ቻርት፣ [2.5 ሠዓት] ፤ እስክሪብቶ፤ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 9 የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ድንች የተከላ ሃረግ የመምረጥ - ገለጻ 5ሀ. የስኳር ድንች የተከላ ሃረግ ቁርጥራጮች ፣ ባህላዊ - ገለጻ 5ሀ. ለተከላ የሚሆኑ የስኳር ድንች ሃረጎች እና የማቆየት መርህ ያውቃሉ፤ የሀረግ ማቆያ ተግባራት፣ የዘር ሃረግ ብዜት ውሃ ቁጥጥር - ተግባር 5.10.2: በመጠን የተለያዩና በከፊል የተጎዱ 200 - የሀረጎች የመባዛት አቅምና (የጠብታ መስኖ) ፣ የሶስት ኤስ /አማማ/ ስርዓት እና የመረብ የሚሆኑ የስኳር ድንች ሰሮች፣ 6 የፕላስቲክ ሳፋዎች፣ ጋዜጣ፣ በምን ያህል ደረጃ ዝርያዎች ዋሻ [20 ደቂቃ] ፤ 5 ባልዲዎች፣ 5 መጥረጊያዎች፣ ሰልጣኞቹ ያጎነቆሉ ስሮችን እንደሚለያዩ እንዴት ማስላት - ውይይት፡ ነባር የስኳር ድንች የዘር ስርዓቶች [20 ደቂቃ] ፤ እንደሚቻል ይገነዘባሉ፤ ማየት እንዲችሉ ከ3 ወር በፊት የተዘጋጀ የሶስት ኤስ ሰርቶ - ተግባር 5.10.2: የሶስቱ ኤስ ስርዓቶች (አሸዋ፣ ማስቀመጥ፣ ማሳያ፡፡ ማስጎንቆል/አማማ) ፡ ከስር መረጣ ጀምሮ ቀዝቃዛና በደረቅ ቦታ ቅድመ -ዝግጅቶች ላይ እስከማስቀመጥ ያለውን ተግባር መለማመድ [1.5 ሠዓት] ፤  ለተግባር 5.10.1 ከባለቤቱ ጋር ማሳው መጎብኘት - ተጨማሪ ተግባራት: ጊዜ ካለ የመረብ ዋሻ መገንባት (አባሪ 5.2) በሚችለበት፣ የተከላ ሃረግ መምረጥና መውሰድ በሚቻልበት ወይም ከቲሹ ከልቸር የተገኙ ችግኞችን የማጠንከሪያ ተግባራት አግባብ ዙሪያ ለመወያየት ቀጠሮ መያዝ፤ ሰልጣኞቹ አሉታዊ መለማመድ (አባሪ 5.1) ፤ የዘር መረጣን እንዲለማመዱ ለማስቻል የአርሶ አደሩ ማሳ በከፊል በቫይረስና በነቀዝ የተጠቃ መሆን ይኖርበታል (ይህ የመረጣ ዘዴ በበሽታና ተባይ የተጠቁ ተክሎችን ነቅሎ ከማሳ ውስጥ የማስወገድ ዘዴ ነው) ፤  በጣም የተለያየ የመባዛት አቅም ያላቸው ዝርያዎችን (ለምሳሌ ዝርያ 1 በአንድ ካሬ ሜትር 50 ቁርጥራጭ እና ዝርያ 2 በአንድ ካሬ ሜትር 10 ቁርጥራጭ) የያዙና ስልጠናው ከመጀመሩ ስምንት ሳምንታት በፊት የተተከሉ የፈጣን ሃረግ ማባዣ መደቦችን ማዘጋጀት፤  ሰልጣኞች ተከላውን እንዲያጠናቅቁትና የመረጡትን ሃረግ እንዲተክሉ፣ በአፈር እንዲሸፍኑና ውሃ እንዲያጠጡ ቀደም ብሎ በግማሽ የተተከለ የፈጣን ሃረግ ማባዣ መደብ ማዘጋጀት፣  ለተግባር 5.10.2. ስሮቹን ገልጠው ጉንቁሉን እንዲያዩና ተከላውን እንዲለማመዱ ለማድረግ የባለሶሰት ኤስ የዘር ማቆያ ስርዓትን ከስልጠናው ጊዜ ጥቂት ወራቶች ቀደም ብሎ ማዘጋጀት፤ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 10 የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣  በመረብ ዋሻ አሰራር ላይ እና ከላቦራቶሪ የወጡ ተክሎችን ለማጠንከር የተግባር ልምምድ ካቀድን በአባሪ 5.1 እና 5.2 ላይ የተገለጹትን ተግባራት ማከናወን ይጠበቅብናል፤ 5 የስኳር ድንች ተባዮች፣ የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 7.9.1: የስኳር ድንች ተባዮችንና በሽታዎችን በመስክ - ተግባር 7.9.1: ፡ በማደግ ላይ ያለ በቫይረስ የተጠቃ፣ ቀደም በሽታዎች እና - የስኳር ድንች ቁልፍ ተባዮችና ላይ ማደንና እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል መማር፤ የተጠቁ ብሎ በስኳር ድንች የተተከለ እና ሰልጣኞች በሽታና ተባይ የመቆጣጠሪያ መንገዶች፤ በሽታዎችን ናሙና መስክ ላይ ስሮችን እንዲሁም የተጎዱና የታመሙ ቅጠሎችን መሰብሰብ፣ ሊያገኙበት የሚችሉት የደረሰ ወይም ያረጀ በቅርብ የሚገኝ ያገኛሉ፤ የሚያስከትሏቸውን በመስክ ላይ የተባዮችን የተወሰነ እንቅስቃሴ በትኩረት ማሳ መለየት፤ 20 መቆፈሪያ በትር፣ የተጎዱ ስሮችን ለማጓጓዝ ጉዳቶች ይገልጻሉ፣ያሳያሉ፤ መመልከት፣ እነኝህ ተባዮችና በሽታዎች ከየት እንደመጡና 8 ባልዲ፣ 8 ከረጢቶች፣ ጥቃቅን ቀዳዳና ክዳን ያላቸው - የእነኝህን ቁልፍ ተባዮችንና እንዴት እንደሚሰራጩ በቡድን መወያየትና ሀሳብ ማጋራት መያዣዎች፣ 20 ማጉሊያ መነፅሮች፣ ተሳታፊዎች የመማሪያ በሽታዎችን የመቆጣጠሪያ (ከተቻለ ነጫጭ ዝንቦችን ጨምሮ) ፡፡ በውይይቱ ወቅት የአፈር ደብተሮቻቸውን መያዝ ይኖርባቸዋል፣ ፍሊፕ ቻርት፣ እርሳስ፣ የተለያዩ ዘዴዎችን ያውቃሉ፤ ማሳቀፍና የስኳር ድንች ቫይረስ በሽታዎችን የመንቀስ ተግባራትን ማርከር፣ ማጣበቂያ ፕላስተር፤ ማካተት (7.9.1ን ተመልከቱ) [85 ደቂቃ] ፤ - ገለጻ 7ሀ፡ የዋና ዋና የስኳር ድንች ተባዮችና በሽታዎች - ገለጻ 7ሀ. ቁልፍ የስኳር ድንች ነፍሳት ተባዮችና በሽታዎች የህይወት ዑደት፤ የህይወት ዑደት [30 ደቂቃ] ፤ - ተግባር 7.9.2: እስከ 50 የሚሆኑ በነቀዝ የተጠቁ የስኳር - ተግባር 7.9.2: ድብቅ ጉዳት፤ የተጠቃውን የስኳር ድንች ስር ድንች ስሮች፣ 20 የእንጨት መክተፊያዎች፣ 20 ስል ለሁለት ከፍሎ የተለያዩ የስኳር ድንች ነቀዝ የዕድገት ደረጃዎችን ቢላዋዎች፣ 20 ማጉሊያ መነፅር፣ 40 ሳህኖች፣ ወይም የላስቲክ ለማየትና ለመለየት መሞከር፣ ምን ያህሉ እንደተጎዳ መቀመር ከረጢቶች፣ 1 የተበላሹ እና ያልተበለሹ የስኳር ድንች ስሮችን [ማስታወሻ: ከስልጠናው አስቀድሞ አመቻቹ የተወሰኑ የተጠቁ ለመመዘን የሚረዳ ሚዛን፣ ለተሳታፊ ሰልጣኞች ደብተርና ስሮችን ማዘጋጀት አለበት] (7.9.2ን ይመልከቱ) [1 ሠዓት] ፤ እርሳስ፣ - ገለጻ 7ለ. የስኳር ድንች ተባዮችንና በሽታዎችን የመቆጣጠሪያ - ገለጻ 7ለ ፡ የስኳር ድንች ተባይና በሽታ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች፤ ተግባራት (ፍልፈልን ጨምሮ) እና ውይይት [45 ደቂቃ] ፤ - ተግባር 7.9.3: በዚያን ዕለት ጧት በተባይ አደን ወቅት - ተግባር 7.9.3: በስኳር ድንች ቁልፍ ተባዮችና በሽታዎች ላይ የሰበሰቡት የስኳር ድንች ስሮች፣ ተባዮች፣ ተገላላጭ ቻርት/ፍሊፕ ለሌሎች ስልጠና መስጠት፤ በዋና ዋና የስኳር ድንች ተባዮችና ቻርት፣ 40 ማርከር እስክሪብቶዎች፣ ማጣበቂያ ፕላስተሮች፣ ማጉያ በሽታዎች ላይ በቂ ገለጻና ተግባራትን ማዘጋጀት (7.9.3ን መነጽሮች፣ የተሳታፊዎች ማስታወሻ ደብተሮችና እስክሪብቶዎች፤ ይመልከቱ) [1 ሠዓት ከ 45 ደቂቃ] ፤ ቅድመ-ዝግጅት ለተግባር 7.9.1: የስኳር ድንች ቫይረስ በሽታ ያለበት አዲስ ማሳ፣ ከዚህ ቀደም ብሎ ስኳር ድንች ተመርቶ የነበረበት ማሳ እና ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 11 የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ተሳታፊዎች ዞረው ሊያዩ የሚችሉበት በስኳር ድንች ተባይና በሽታ የተጠቃ የደረሰ ወይም ያረጀ ማሳ ማግኘት፤ ለተግባር 7.9.2: ከስልጠናው ሁለት ሳምንታት በፊት በስኳር ድንች ነቀዝ የተጠቁ ስሮችን መሰብሰብ፣ ተሳታፊዎች ምናልባት በአደን ወቅት የተወሰኑትን ሊያገኙ ይችላሉ፣ ምናልባት ካላገኙ በመሰንጠቅ የዕንቁላሎችን፣ ትሎችንና ዕጮችን/ፑፓዎችን እንዲያውም የመመገቢያ ቀዳዳዎችን እንዲያዩ አመቻቾች የተወሰኑ እንዳሏቸው ማረጋገጥ፣ በስልጠናው ወቅት ከማሳ የሚሰበሰቡ ናሙናዎች/ተምሳሌቶች ላይ በቀላሉ የማይገኙ ከሆነ በሰው ሰራሽ መንገድ ተባዮቹን በስኳር ድንች ስሮች ውስጥ በላቦራቶሪ እንዲገቡ ማድረግን ሊጠይቅ ይችላል፤ 6 የስኳር ድንች አመራረትና የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 6.9.1: የተለያዩ የስኳር ድንች ዝርያዎችንና የሰብል - ተግባር 6.9.1. ተገላላጭ ቻርት፣ እስክሪብቶዎች፣ ገመድ፣ ሰብል አያያዝ - አርሶአደሮች የተለያዩ አያያዝ ተግባራትን ማነጻጸር፡ የስኳር ድንች የመስክ ሙከራ ሜትር፣ አካፋ፣ መለያ፣ እንጨት፣ በቅርብ ቦታ የሚገኝ ሙከራው ዝርያዎችን ወይም የተለያዩ ማቋቋም (ለዝርዝሩ 6.9.1ን ተመልከቱ) [3 ሠዓት] የሚቀመጥበት ማሳ፣ የዚህ መምሪያ ርዕስ 3፣ 6 እና 7፣ “ስኳር የሰብል አያያዝ ዘዴዎችን - ተግባር 6.9.2: ቅድመ ዕቅድ፡ ድንቼን ምን እያጠፋብኝ ነው?” በሚለው መጽሃፍ ውስጥ ከገጽ ለማነጻጸር የመስክ ሙከራ - የስኳር ድንች የእርሻ ተግባር ቀን መቁጠሪያ ማዘጋጀት፤ 20-22 ላይ የተጠቀሰው፤ እንዲያከናውኑ ይረዳሉ፤ - ተያያዥ የሆኑ የሰብል አያያዝ ተግባራትንና ቅድመ እቅዶችን - ተግባር 6.9.2. ተገላላጭ ቻርት፣ ሉኮች፣ የማርከር እስክሪብቶ፣ - የተለያዩ የስኳር ድንች መለየት እርሳሶች፣ ፕላስቲክ ማጣበቂያ፤ የዕድገት ደረጃዎችንና - ከተግባራቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ የሥርዓተ-ጾታ ሚናዎችንና ምን ደረጃዎቹ በስብል አያያዝ ላይ - ገለጻ 6፡ የስኳር ድንች የዕድገት ደረጃዎችና ተጓዳኝ የሰብል አያያዝ ያላቸውን እንድምታ ይረዳሉ፤ ለውጦች እየታዩ እንደሆነ መወያየት (6.9.2ን ይመልከቱ) [75 ተግባራት፡፡ ደቂቃ] ፤ - ቅድመ-ዝግጅት: ገለጻ 6. የስኳር ድንች የዕድገት ደረጃዎች (የድህረ-ምርት ደረጃዎችን ጨምሮ) ለተግባር 6.9.1. ተሳታፊዎች የሙከራውን ንድፍ ፡ ገለጻውን ተከትሎ ተሳታፊዎች የሚያስቀምጡበትንና ሙከራውን የሚያካሂዱበትን በአቅራቢያ በማስታዎሻ ደብተሮቻቸው ላይ የሰብሉን ሙሉ የዕድገት ደረጃዎችን ይስላሉ፡፡ በገለጻው ላይ ውይይት ከተካሄደ በኋላ የሚገኝ 30 በ 30 ሜትር የሆነ ባዶ ማሳ ማግኘት፤ ተሳታፊዎች በየዕድገት ደረጃው ለየትኛው ተግባር ትኩረት መሰጠት እንደሚያስፈልግ በዝርዝር ያስቀምጣሉ [45 ደቂቃ] ፤ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 12 የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ 7 የተከላ ሃረግ የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ገለጻ 5ለ. የስኳር ድንች የተከላ ሃረግ ቁርጥራጮችን የማምረትና - ገላጻ 5 ለ፡ በመሰረታዊ መርሆች ዙሪያ፤ ቁርጥራጮችን የማሰራጫ - በስፋት በማባዛት ወይም የማሰራጨት ቁልፍ መርሆዎች [30 ደቂቃ] ፤ ተግባር 5.10.3፡ ተገላላጭ ቻርት እና ማርከር፤ 35 ኮፒ የስኳር ፕሮግራም ዕቅድ መስራት፤ ባልተማከለ የሃረግ ብዜት - ተግባር 5.10.3: የማባዣና ማሰራጫ ስልት ማቀድ - የተግባር ድንች እርሻ ተግባር ቀን ማመልከቻ/መቁጠሪያ መመሪያ (ጽሁፍ ዕቅድና ስርጭት ሂደት ያሉ ልምምድ [3 ሠዓት] ፤ 5.10.3ሀ) ፣ 35 ኮፒ የስኳር ድንች ማባዣ ስልት የሚሰላበት ቁልፍ የደረጃ በደረጃ - የቡድን ውይይት: ስልቶችን ከተለያዩ ዕቅዶች አኳያ ማስተያየት፤ የቀመር ወረቀት (ጽሁፍ 5.10.3ለ) ፣ 35 ኮፒ የስኳር ድንች ተግባራት እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ይገነዘባሉ፤ - ተግባር 5.10.4: ካልተማከለ የተከላ ሃረግ ቁርጥራጭ/ሀረግ ስርጭት ዕቅድ ቅጽ (ጽሁፍ 5.10.3ሐ) ፤ - በአካባቢያቸው ለሚገኙ አባዦች ጋር መስራት - ተግባራዊ ልምምድ [2.5 ሠዓት] ፤ ተግባር 5.10.4፡ በአቅራቢያው የሚገኝ ሁለት ዝርያዎች ተለይተው 5000 ቤተሰቦች ለማዳረስ - ገለጻ 5ሐ. የማሰራጨት ተግባር ወጪን መገመት [10 ደቂቃ] ፤ የተተከሉበትና መለያም የተደረገባቸው ማሳዎች እንዲሁም ከበሽታ የሚውል የማሰራጫ ንድፍ - ገለጻ 12. ክትትልና ግምገማን መግለጽ [20 ደቂቃ] ፤ የጸዱ የማሳያ ማሳዎችና ሁለት የተለያዩ ዝርያዎች ተቀላቅለው የማውጣቱን ተግባር - ተግባር 12.3.1: የት ነው የሄደው? የተከላ ሃረግ ቁርጥራጮች የተተከሉበት ንጹህና በቫይረስ በሽታ የተጠቁ ተክሎችን የያዙ ይለማመዳሉ፤ ስርጭት ክትትል ማድረግ ላይ መለማመድ [30 ደቂቃ] ፤ ማሳዎች ለስልጠናው ያስፈልጋሉ፤ ተገላላጭ ቻርት፣ ማርከር - ተግባራትን የመከታተልና - የቤት ስራ: የማሰራጫ ስልት ወጪዎችን ማስላት፤ እስክሪብቶ፣ ማጣበቂያ፣ የጽሁፍ 5.10.4ሀ እና 5.10.3ለ ኮፒዎች፤ የመገምገም አስፈላጊነትን ይረዳሉ፤ - ገለጻ 5 ሐ፡ የዘር ብዜትና ስርጭት ወጪዎችን ማስላት፤ - የተከላ ሃረግ ቁርጥራጮች - ገለጻ 12፡ የክትትልና ግምገማ ዘዴን ማስተዋወቅ፤ ስርጭትን መከታተል ተግባር 12.7.1፡ 200 በሰንጠረዥ12.5.2 የተጠየቁ መረጃዎችን ይለማመዳሉ፤ በመያዝ ተሞልተው የተጠናቀቁ የስኳር ድንች ደረሰኞች፣ የቅጽ 12.5.2 40 ቅጅዎች እና እስክሪቢቶ፤ ቅድመ-ዝግጅት፡ ለተግባር 5.10.4.፡ ሁለት የተለያዩ ዝርያዎችን እያንዳንዳቸውን በሁለት በተለያዩ ቁራጭ መሬቶች ላይ ለይቶ መትከል፤ በአንደኛው መሬት ላይ በሽታ የታየባቸውን ተክሎች ነቅሶ ማስወገድ፤ በሌላኛው መሬት ላይ ያሉትንና የቫይረስ ጥቃትና ምልክት የሚታይባቸውን ተክሎች እንዳለ መተው፤ ለተግባር 12.7.1.፡ 200 የተጠናቀቁ የዘር ደረሰኞችን መሰብሰብ ወይም መሙላት፤ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 13 የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ 8 ምርት አሰባሰብ፣ ድህረ- የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 8.9.1: የስኳር ድንች ስሮችን በማስቀመጥ ገቢን - ተግባር 8.9.1፡ እያንዳንዱ ቡድን 10 ተክሎችን ለመቆፍርና ምርት አያያዝና ማቀነባበር - ስለ ስኳር ደንች ምርት ማሳደግ፡፡ ስሮችን የመሰብሰብ፣ የተበላሹትን የመለየትና ምርቱን ለመቀመር የሚያመች በአቅራቢያው የሚገኝ የስኳር ድንች አሰባሰብ፣ ድህረ-ምርት የተጠበቀ ማስቀመጫ ጉድጓድ የመስራት የመስክ ልምምድ ማሳ፣ ሚዛን፣ ከረጢት/ጆንያ፣ የሂሳብ መስሪያ/ካሉኩሌተር፣ አያያዝና አቀነባበር ቁልፍ (ማስታወሻ፤ ጉድጓድ፣ ለመሸፈኛ የሚሆን ሳር፣ ቀርከሃ እና እስክሪብቶና ወረቀት፣ አካፋ፣ መቆፈሪያ፣ የሳር ጉዝጓዝና ማሰሪያ ጉዳዮችን ያውቃሉ፤ እንጨት በቅድሚያ መዘጋጀት አለባቸው) (ተግባር 8.9.1ን ገመድ፤ - ምርት ማቀነባበርና ለብዙ ጊዜ ተመልከቱ) [2 ሰዓት] - ተግባር 8.9.2.፡ 50 የብርቱካንማ ስኳር ድንች ስሮች፣ መቆራረጫ ማስቀመጥ የብርቱካንማ ስኳር - ተግባር 8.9.2: በጸሐይ ማድረቅና ለብዙ ጊዜ ማስቀመጥ ማሽን፣ ከፍ ያለ ማድረቂያ፣ ቢያንስ ሶስት የናሙና ከረጢቶች፣ ድንች የቤታ ካሮቲን ይዘት ላይ በብርቱካንማ ስኳር ድንች ቤታ ካሮቲን መጠን ላይ መለያዎች/ስም መጻፊያዎች፣ ፓርከር እስክሪብቶዎች፣ ቤታ ካሮቲን እንዴት ተጽዕኖ የሚያደርሰው ጉዳት፡፡ ተሳታፊዎቸ ለ7፣ ለ5 እና ለ2 ቀናት እንደሚያሳድር ይረዳሉ፤ ምን ያህል እየቀነሰ እንደሚሄድ የሚያሳዩ መረጃዎች (ጽሑፍ በጸሐይ የደረቁ የብርቱካንማ ስኳር ድንች ስር ቁርጥራጮችን - በክህሎት መገንቢያና 8.9.2ሀን ይመልከቱ) ፡፡ ልዩነት ይመለከታሉ፡፡ የቤታ ካሮቲን መጠን ለብዙ ጊዜ ስኳር በማቀነባበሩ ስልጠና ወቅት ድንችን ስናስቀምጥ ምን ያህል እንደሚቀንስ መገንዘብ እንዲችሉ - ገለጻ 8፡ የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች በስኳር ድንች ምርት ስብሰባ፣ የተለያዩ ቡድኖችን የማሳተፉን የቤታ ካሮቲን መጠን መገመቻ ይሰጣቸዋል፡፡ (ተግባር 8.9.2ን ማድረቅ፣ ማጥገግና ድህረ-ምርት ላይ፤ አስፈላጊነት ይረዳሉ፤ ተመልከቱ) [30 ደቂቃ] ተግባር 9.8.1: ድስት፣ በከሰል ወይም በጋዝ የሚሰራ ምድጃ፣ - ገለጻ 8. ማጥገግ፣ ትንሽ በትንሹ ምርት መሰብሰብና የስር መጥበሻ፣ መክተፊያ፣ መዳመጫ፣ የፍራፍሬ መጭመቂያ፣ ቁርጥራጭ ማድረቅ የስርዓተ-ጾታን ጉዳዮች ጨምሮ ለተሻሻለ ሳህን/ትሪ፣ ማቡኪያ፣ ቢለዋዎች፣ ፍሊፕ ቻርት፣ ማርከር ብዕሮች፣ የድኅረ-ምርት ቆይታ፡፡ አዲስ የተቆፈሩ ስሮችና የደረቁ የስር ማጣበቂያ ፕላስተር፣ 2 ከ.ግ የስንዴ ዱቄት፣ ግማሽ ከ.ግ ቁርጥራጮች ድህረ- ምርት አያያዝ፤ የማስቀመጫ ቁሳቁሶች፣ የብርቱካናማ ስኳር ድንች ስር፣ ግማሽ ከ.ግ የተቀቀለ ብርቱካናማ ስኳር ድንች፣ ግማሽ ከ.ግ የብርቱካናማ ስኳር ድንች ዱቄት፣ አንድ ከተባይ መከላከልና በየጊዜው መጎብኘት፡፡ በቤት ውስጥ ስኳር ኩባያ የአትክልት ዘይት፣ ጥቂት ጨው፤ ድንችን ለማስቀመጥ ማን ተጠሪ እንደሆነና መረጃዎች እንዴት እንደሚደርሷቸው ስለማረጋገጥ መወያየት? [45 ደቂቃ] - ተግባር 9.8.2: 4 ኩባያ ስኳር፣ ተቀቅለው የተላጡ 8 መካከለኛ - ተግባር 9.8.1: ቂጣ ለመጋገር የስንዴን ዱቄት በስኳር ድንች መጠን ያላቸው የስኳር ድንች ስሮች፣ 3 የሻይ ማንኪያ ሲትሪክ ዱቄት መተካት፣ ተግባር 9.8.2 የስኳር ድንች ጭማቂ ማዘጋጀት አሲድ/የሎሚ ጭማቂ/5 ሎሚ፣ ተፈልቶ የቀዘቀዘ 5 ሊትር ውሃ፣ እና 9.8.3 የስኳር ድንች ጥቢኛ ማዘጋጀት፡፡ ማጣፈጫ አስፈላጊ ከሆነ/አንድ ጠብታ ታማሪንድ ተሳታፊዎችን ቅመም/ብርቱካን/ሆጲ/አናናስ፣ ወንፊት፣ መጥበሻ፣ የፍራፍሬ ለሁለት ወይም ለትናንሽ ቡድኖች መክፈልና ተግባር 9.8.1ን መጭመቂያ፣ የእንጨት ማንኪያ፣ 5 ባለ 1 ሊትር ጠርሙሶች፣ ወይም (9.8.2ን እና 9.8.3ን) እንዲከተሉ መስጠት [2 ሠዓት ማቀዝቀዣ፤ ከ30 ደቂቃ] - ተግባር 9.8.3: 300ግ (ከ2-2 ከግማሽ ኩባያ) የስንዴ ዱቄት፣ 50ግ የአትክልት ቅቤ፣ 200ግ (ከ1-1 ከግማሽ ኩባያ) ልንቅጥ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 14 የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ - ገለጻ 9. ማቀነባበርና ለማቀነባበር ስልጠና ማንን ዒላማ ማድረግ ስኳር ድንች፣ 65ግ (ሩብ ኩባያ) ስኳር፣2 እንቁላል፣ዘይት እንደሚገባ መወያየት፣ ለምሳሌ በአነስተኛ ደረጃ በምግብ ለመጥበሻ፣2 የሻይ ማንኪያ መጋገሪያ እርሾ/ዱቄት፤ ማቀናበር ስራ ላይ የተሰማሩና ብርቱካንማ ስኳር ድንችን ገለጻ 9፡ ምርት ማቀነባበር፣ ማንን በምርት ማቀነባበር ስልጠና ላይ ለማካተት ፈቃደኛ የሆኑት ላይ ትኩረት ማድረግ፣ ወንዶች ማሳተፍ እንዳለብን መወሰንና የስርዓተ-ፆታ ጉዳዮች፤ በምግብ ዝግጅቱ ዋና ተዋናይ ባይሆኑም ምን ሰብል መተከል እንዳለበት ወይም መገዛት እንዳለበት ውሳኔ የሚሰጡ ስለሆነ ቅድመ-ዝግጅት እነሱን በማሳተፉ ረገድ ውይይት ማድረግ [45 ደቂቃ] - ለተግባር 8.9.1. ሰልጣኞቹ ቆፍረው ምርቱን መቀመር የሚችሉበትን የስኳር ድንች ማሳ ከአካባቢው መለየት ወይም አስቀድሞ መትከል፤ - ለተግባር 8.9.2. በአስሩ ቀን የአሰልጣኞች ስልጠና የመጀመሪያው ቀን ላይ በጸሐይ ላይ የሚሰጣ ትንሽ የብርቱካንማ ስኳር ድንች ስር ቁርጥራጭ ድርቆሽ ማዘጋጀትና ከፍ ባለ ማንጠልጠያ ማድረቅ (ይህ በኋላ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በጸሐይ የሚደርቅ ናሙና ይሆናል)፣ በሶስተኛው ቀን የተወሰኑ ተጨማሪ ስሮችን መቆራረጥና በተመሳሳይ መልኩ ከፍ ባለ ማስቀመጫ ማድረቅና ለብቻ ማስቀመጥ፡፡ ናሙናዎቹ በሚገባ መለያ የተደረገባቸው መሆኑና የተጠበቁ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ፤ በስድስተኛው ቀን የተወሰኑ ተጨማሪ ስሮችን መቆራረጥና በተመሳሳይ መልኩ ከፍ ባለ ማስቀመጫ ማድረቅና ከመጀመሪያዎቹ ናሙናዎች ጋር ያለመቀላቀሉንና በሚገባ መለያ የተደረገበት መሆኑን ማረጋገጥ፡፡ በ9ኛው የስልጠና ቀን ሶስቱንም ናሙናዎች በጥንቃቄ ሰብስቦ ወደ ስልጠና ክፍሉ መውሰድና በአንድ ወገን ባለው ጠረጴዛ ላይ ማስቀመጥ (ተለይተው መያዝ አለባቸው)፡፡ - ለተግባር 9.8.1. ለእያንዳንዱ ቡድን ግማሽ ኪ.ግ እንዲደርስ በቂ የስኳር ድንች ስር ማዘጋጀት፣ የጊዜ እጥረት ካለ ተሳታፊዎች ወዲያው ወስደው እንዲጠቀሙ ለማድረግ አስቀድሞ መቀቀልና መለንቀጥ፤ - ለተግባር 9.8.2 እና 9.8.3. ለስራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ማደራጀት፣ በቂ የስኳር ድንች ስሮች ማግኘት፣ የጊዜ እጥረት ካለ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 15 የስልጠና ቀን ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ስኳር ድንቹን አስቀድሞ መቀቀልና ተሳታፊዎች ለንቅጠው ከሚፈለገው የምግብ አይነት ውስጥ መጨመር እንዲችሉ ማድረግ፤ 9 ግብይትና ሥራ-ፈጠራ የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 10.10.1: የገበያ ጉዞ. ፡ ጥናታዊ ጉዞ ወደ ገበያ - ግማሹ - ተግባር 10.10.1.፡ በአቅራቢያ ያለ ገበያ፣ ትራንስፖርት፣ 5 - ስለ ግብይትና ገበያ-ተኮርነት ቡድን በጥሬ ስር ግብይት የትርፍ ልዩነት እና ችግሮች ዙርያ የመለኪያ ኩባያዎች፣ 5 ፕላስቲክ መያዣዎች (እስከ 2ኪ.ግ. ስር ያውቃሉ፤ ሲያደርግ የተቀረው ግማሹ ቡድን ደግሞ በተቀነባበሩ ምርቶች የሚይዙ) ፣ ማስታዎሻ ደብተሮች እና እስክሪብቶ፣ ፊሊፕ ቻርቶችና - አምስቱን የግብይት ምሶሶዎች ዙርያ ያደርጋል፤ የየችግሮችን (የሥርዓተ-ፆታንም ጭምር) ማርከሮች፤ ይረዳሉ፤ ባህርያትንና ውስንነታቸውን ለማወቅ መሞክር፡፡ ቡድኖቹ ወደ - በስኳር ድንች ስር እና ስልጠናው ማዕከል በመመለስ ያገኙትን የጥናት ውጤት ጠቅለል - ገለጻ 10 ሀ፡ በግብይት እና ስራ ፈጠራ እንዲሁም ተጓዳኝ የተቀነባበረ ምርት ግብይት አድርገው ማቅረብ እና መወያየት (ክፍል 10.10.1 ይመልከቱ). በሆኑ የስርዓተ-ፆታ ጉዳዮች ላይ፤ ውስጥ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችንና [4.5 ሰዓት] - ተግባር 10.10.2. ለእያንዳንዱ ሰው በአስቴር ላይ የተደረገው ተግዳሮቶችን ይረዳሉ፤ - ገለጻ 10ሀ፡- ግብይትና ሥራ-ፈጠራ እና ተያያዥ የሥርዓተ-ፆታ የኩነት-ጥናት (በሳጥን 10.3 ያለው) እንዲኖረው በቂ ፎቶ ኮፒዎች፤ - በእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ ያሉ ጉዳዮች፡፡ የቡድን ግብይት [20 ደቂቃ] የሥርዓተ- ተግባር 10.10.3. 20 የብርቱካናማ ስኳር ድንች ስሮች፣ ስቲከሮች፣ ፆታ - ተግባር 10.10.2: የትርፍ ልዩነትን ማስላት፡፡ የአንድ አርሶ አደር ማርከሮች፣ ፍሊፕ ቻርቶች፣ ፕላስተር ፤ ጉዳዮችን/ችግሮችን ያስሳሉ፤ የኩነት-ጥናትን (case study) በመውሰድ በእያንዳንዱ የእሴት - የነጋዴዎችን ሥልጠና - ገለጻ 10ለ፡ በአምስቱ የግብይት ምሶሶዎች እና ለገበያ የሚሆኑ ሰንሰለት ደረጃ የትርፍ ልዩነትን ተሳታፊዎች ያሰላሉ (ክፍል የማግኘት ጥቅም ይረዳሉ፤ ምርቶችን እንዴት እንደምንመርጥ፤ 10.10.2ን ከታች ይመልከቱ). [45 ደቂቃ] - ተገቢው የተቀነባበረ ምርት እንዴት ይመረጣል የሚለውን - ተግባር 10.10.3: 5ቱ የግብይት ምሶሶዎች፡፡ የግብይትን ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ያውቃሉ፤ ችግሮች ተሳታፊዎች ማሰስ እንዲችሉ በትወና መልክ ማቅረብ - የጥሬ ስር ንግድ የትርፍ ልዩነት (ክፍል10.10.3 ይመልከቱ). [55 ደቂቃ] - ተግባር 10.10.1. ትራንስፖርትን ማቀናጀት፣ አመቻቹ ወደ ገበያው ቀደም ብሎ ሄዶ የስኳር ድንች ነጋዴዎች የት እንደሆኑና (marketing margins) - ገለጻ 10ለ፡- 5ቱ የግብይት ምሶሶዎች እና ለገበያ የሚሆኑ ማንኛውም ዓይነት የተቀነባበረ የስኳር ድንች ምርት ይነግዱ እንዴት እንደሚሰላ ያውቃሉ፤ ምርቶችን እንዴት መምረጥ አለብን፡፡ [20 ደቂቃ] እንደሆነ ማየት (ይህ ከሆነ ተሳታፊዎች የትኛው የተቀነባበረ ምርት - የተቀነባበረ ምርትን (ዱቄት ላይ ማጥናት እንዳለባቸው ለመወሰን ይረዳል) ፤ ወይም ልንቅጥ) ንግድ የትርፍ ልዩነት (marketing margins) እንዴት እንደሚሰላ ያውቃሉ፤ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 16 ተ.ቁ ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ 10 የ"ስለስኳርድንች ማወቅ የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 1.4.1 የ“በመስራት-መማር” ስልጠና አመቻች ለመሆን - ተግባር 1.4.1. የአምስቱ ቀን ስልጠና ዋና ዋና ርዕሶች በላያቸው የምትፈልገው ሁሉ" - ለሚሰጡት የስኳር ድንች ስልጠና መለማመድ፤ ገንቢ የሆነ ግብረ-መልስ በመስጠትና በመቀበል ላይ የተጻፉባቸው ካርዶች (ዘር ማቆየትና ማባዛት፣ ንጹህ ዘርን ስልጠናን ለሌሎች የሚያስፈልጉትን የመማማር መርሆዎች ላይ የቡድን ውይይት ማድረግና በቁልፍ የስኳር ድንች መምረጥ፣ የስኳር ድንች ነቀዝን መቆጣጠር፣ የስኳር ድንች ለመስጠት ማቀድ ውጤቶችና የስልጠናውን አቀራረብ፣ ርዕስ ላይ የአመቻችነት ሚናን መለማመድ (ተግባር 1.4.1ን ቫይረስን መቆጣጠር፣ ስኳር ድንችን ማቀነባበር፣ ገበያ፣ ቫይታሚን አስፈላጊ የስልጠና ቁሳቁሶችና ሌሎች ተመልከቱ) (2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ)፤ ኤ አመጋገብ ወዘተ)፣ የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ግብዓቶችን (ጊዜ፣ቦታ፣ማሳዎች፣ - ገለጻ 1፡ ጎልማሶችን እንዲማሩ መርዳትና ከ5 ቀናቱ የአሰልጣኞች ሁሉ" ስልጠና መምሪያ፣ ማስታወሻ ደብተርና ብዕር፣ ተጣባቂ ተሳታፊዎች ወዘተ) ተረድተው ስልጠና መርሃ-ግብር ጋር እንዲተዋወቁ ማድረግ፤ ስለ መርሃ ግብሩ ወረቀት፣ ፍሊፕ ቻርት፣ ፕላስተር፣ ማርከር፣ ከፊሉ የብርቱካናማ ያዘጋጃሉ፤ መወያየትና ስልጠናውን ለመስጠት አስፈላጊ ስለሆኑ አቅርቦቶች ስኳር ድንች የሆነ 100 ስሮችን ጨምሮ ማንናቸውም በስልጠናው - "ስለስኳር ድንች ማወቅ ንድፍ ዕቅድ ማዘጋጀት (አባሪ 1.3ን ተመልከቱ) (1 ሰኣት) ወቅት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶች፡፡ የምትፈልገው ሁሉ" ስልጠናን - ተግባር 1.4.2 ለተጨማሪ የስኳር ድንች የ“በመስራት-መማር” - ገለጻ 1. ጎልማሶችን እንዲማሩ መርዳትና ከ5 ቀናቱ የአሰልጣኞች ለአምስት ቀናት መስጠት ይችላሉ፤ ተግባራት የሚሆኑ ሃሳቦች (ተግባር 1.4.2ን ተመልከቱ) (1 ሰኣት ስልጠና መርሃ ግብር ጋር እንዲተዋወቁ ማድረግ (ርዕስ 13ን ከ 20 ደቂቃ) ተመልከቱ) ፤ - ተግባር 1.4.3 ስልጠናውን መገምገም (ተግባር 1.4.3ን - ተግባር 1.4.2. “ስለ ስኳርድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” ተመልከቱ) ( የስልጠና መምሪያ፣ ማስታወሻ ደብተር፣ እስክሪቢቶ፣ ተለጣፊ እንደ መውጫ የስኳር ድንች ዕውቀት ዳሰሳ ፈተናን ማስታወሻ መጻፊያ፣ ፊሊፕ ቻርት፣ ማጣበቂያ፣ ባለቀለም መጻፊያ፣ በድጋሚ መስጠት (አባሪ 1.2) (1 ሰኣት) ሌሎች ከፊሉ ብርቱካንማ የሆነ 100 የስኳር ድንች ስሮችን ጨምሮ - የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ለተሳታፊዎች መስጠት (1 ሰኣት) በአሰልጣኞች ስልጠና ወቅት ጥቅም ላይ ውለው የነበሩ ቁሳቁሶች፤ - ተግባር 1.4.3. በክፍል 12.5.5ሐ የተገለጸውን የስልጠና መገምገሚያ ቅጽ ለእያንዳንዱ ተሳታፊ እንዲደርስ በበቂ መጠን አባዝቶ ማዘጋጀት፣ እስክርቢቶ - ሰርቲፍኬት አጠናቆ ማዘጋጀት፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 17 ሠንጠረዥ 13.2 ለአስሩ ቀናት የአሰልጣኞች ስልጠና የሚያስፈልጉ ቅድመ-ዝግጅቶች የአሰልጣኞች ስልጠናው ከመሰጠቱ በፊት ለሚደረገው ቅድመ- ዝግጅት መሰጠት ያለበት የጊዜ ገደብ ቅድመ ዝግጅት አመቻቾችን መምረጥና መገናኘት፣ የአሰልጣኞች ስልጠናውን ማስተዋወቅ አስፈላጊ የሆኑ የመስክ ዝግጅቶችን ማቀድ (ከታች የተመለከተውን ዝርዝር ይመልከቱ) ተግባር 3.5.1: ልዩነትን መንቀስ፤ የመስክ ተግባር: በቅርብ ቦታ ከሚገኘው መስክ ላይ የተለያዩ የስኳር ድንች ባህሪያትን መለየት፤ ከአርሶአደሩ/ሯ ጋር ለምን እያንዳንዱን ዝርያ እንደሚያመርቱ መወያየት እና ከእነኝህ የተለያዩ ዝርያዎች ስሮችን በማውጣት ለጣዕም ሙከራ መጠቀም፡፡ ለመወያየትና ለማቀድ ከአርሶ አደሩ ጋር መገናኘት፡፡ ተግባር 5.10.1: ንጹህና የተባዙ ለተከላ የሚሆኑ ሀረጎች: ንጹህ የተከላ ሃረግ ቁርጥራጮችን ለማግኘት የመስክ ተግባር፣ የተከላ ሀረጎችን መውሰድ ፣ ወደ ተከላ ቁርጥራጮችን መቆራረጥ፣ በፈጣን የማባዣ መደብ ላይ እንዴት ማባዛት እንደሚቻል መማር፣ እንዴት መንከባከብ እንደሚቻል እንዲሁም መቼና እንዴት ይተከላሉ ብሎ መወያየትና የሀረግ የመባዛት አቅምን ማስላት፡፡ ተግባር 5.10.1: በጣም የተለያየ የመባዛት አቅም ያላቸው ዝርያዎችን (ለምሳሌ ዝርያ 1 በአንድ ካሬ ሜትር 50 ቁርጥራጭ እና ዝርያ 2 በአንድ ካሬ ሜትር 10 ቁርጥራጭ) የያዙና ስልጠናው ከመጀመሩ ስምንት ሳምንታት በፊት የተተከሉ የፈጣን ሃረግ ማባዣ መደቦችን ማዘጋጀት፡፡ ሰልጣኞቹ ሃረጎቹን ይሰበስባሉ፡፡ ተግባር 5.10.1: ሰልጣኞች ተከላውን እንዲያጠናቅቁትና የመረጡትን ሃረግ እንዲተክሉ፣ አፈር እንዲሸፍኑና ውሃ እንዲያጠጡ ቀደም ብሎ በግማሽ የተተከለ የፈጣን ሃረግ ማባዣ መደብ ማዘጋጀት፡፡ ተግባር 5.10.2: ስሮቹን ገልጠው ጉንቁሉን እንዲያዩና ተከላውን እንዲለማመዱ ለማድረግ የባለሶሰት ኤስ የዘር ማቆያ ስርዓትን ከስልጠናው ጊዜ ጥቂት ወራቶች ቀደም ብሎ ማዘጋጀት፤ ተግባር 5.10.4: ሁለት የተለያዩ ዝርያዎችን እያንዳንዳቸውን በሁለት በተለያዩ ቁራጭ መሬቶች ላይ ለይቶ መትከል፤ በአንደኛው መሬት ላይ ያለውን በሽታ ያለበትን ተክል ነቅሶ ማስወገድ፤ በሌላኛው መሬት ያለውን የቫይረስ ጥቃትና ምልክት ይታያል በሚል ዕሳቤ እንዳለ መተው፤ ተጨማሪ ተግባራት፣ በመረብ ዋሻ አሰራር እና ከላቦራቶሪ የወጡ ተክሎችን ለማጠንከር የተግባር ልምምድ ካቀድን በአባሪ 5.1 እና 5.2 ላይ የተገለጹትን ተግባራት ቀደም ብሎ ማከናወን ይጠበቅብናል፤ ተግባር 6.9.1: የስኳር ድንች ዝርያዎችንና አያያዝ ተግባራትን ማነጻጸር፡ ተሳታፊዎች የሙከራውን ንድፍ የሚያስቀምጡበትንና ሙከራውን የሚያካሂዱበትን በአቅራቢያ የሚገኝ 30 በ 30 ሜትር የሆነ ባዶ ማሳ ማግኘት፤ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 18 ከ 6 ወራት በፊት መትከል ወይም መትከል ወይም ከ 5 ወራት ማቀድ ማቀድ በፊት ከ 4 ወራት በፊት ከአንደኛው ማሳ ቦታ መለየት መለየት መከታተል ከ 3 ወራት ላይ የታመሙትን በፊት ነቅሶ ማስወገድ ማዘጋጀት መትከል ከ 2 ወራት በፊት መለየት ዕቅድና መከታተል መከታተል መከታተል መከታተል መከታተል ከ 1 ወራት መመስረት በፊት መከታተል መከታተል መከታተል መከታተል መትከል መከታተል መከታተል መከታተል ከ 1 ሳምንት በፊት የአሰልጣኞች ስልጠናው ከመሰጠቱ በፊት ለሚደረገው ቅድመ- ዝግጅት መሰጠት ያለበት የጊዜ ገደብ ቅድመ ዝግጅት ተግባር 7.9.1: የስኳር ድንች ተባይና በሽታ የመሰክ አደን እና እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል፤ በአቅራቢያ ያሉ 3 የስኳር ድንች ማሳዎችን መለየት - አንደኛው ቫይረስ በሽታ ያለበት አዲስ ማሳ፣ ሁለተኛው ከዚህ ቀደም ብሎ ስኳር ድንች ተመርቶ የነበረበት ማሳ እና ሶስተኛው ቀደም ብሎ የተተከለ ወይም የደረሰ ማሳ፡፡ ተሳታፊዎች እነዚህን ማሳዎች በማሰስ ከተባይና በሽታ አንጻር እንዲያወዳድሯቸው ማድረግ፡፡ ተግባር 7.9.2: ስውር ጉዳት፡ ሰልጣኞች በስልጠናው ጊዜ ቆርጠው እንዲመለከቷቸው እስከ 30 የሚሆኑ በነቀዝ የተጠቁ ስሮችን መሰብሰብና በጥንቃቄ ማስቀመጥ፡፡ ተግባር 8.9.1: የስኳር ድንችን ስሮች በማስቀመጥ ገቢን ማሳደግ፡ ሰልጣኞቹ ቆፍረው ምርቱን መቀመር የሚችሉበትን የስኳር ድንች ማሳ ከአካባቢው መለየት ወይም አስቀድሞ መትከል፤ ተግባር 8.9.2: በጸሐይ ማድረቅና ለብዙ ጊዜ ማስቀመጥ በብርቱካንማ ስኳር ድንች ቤታ ካሮቲን መጠን ላይ የሚያደርሰው ጉዳት፡ በተግባር 8.9.2 ላይ እንደተገለጸው የብርቱካንማ ስኳር ድንች ስሮችንና ክትፍታፊዎችን ለተለያዩ የቆይታ ጊዜያቶች በጸሃይ ለማድረቅ ማዘጋጀት፡፡ ተግባር 10.10.1: ጉዞ ወደ ገበያ፡ የትኛው ገበያ በጥሬ ስርና በተቀነባበሩ የስኳር ድንች ውጤቶች ግብይት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፉ ጉዳዮችን በበለጠ ለማሳየት እንደሚረዳ ለመወሰን ከስልጠናው ቀን ቀደም ብሎ ቼክ ሊስት ይዞ በአቅራቢያ ወደሚገኙ ገበያዎች በመሄድ ዳሰሳ ማድረግ፡፡ በስልጠናው ወቅት ለሚደረግ የገበያ ጉዞ ማጓጓዣ ማዘጋጀት፡፡ በስልጠናው ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን ለገለጹ ተሳታፊዎች ቶሎ ግብረ-መልስ መስጠትና አጠር ያለ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፡፡ ስለስልጠናው መምሪያ፣ አቀራረብ፣ ተግባራት፣ ስለሚቀርቡ ገለጻዎች፣ መርኃ- ግብር እና ቀን ለአመቻቾች ማስተዋወቅ (ይህ ከቅድመ-ስልጠና ዝግጅት መርኃ- ግብር ጋር ሊቀናጅ ይችላል) ፡፡ ስለስልጠናው መርኃ-ግብርና ስልጠናውን ስለሚሰጡበት ቀን ለሁሉም አመቻቾች ማስታወሻ መላክ፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎችን መለየትና ስለስልጠናው መርኃ-ግብር፣ የስልጠናው ቦታና አቅጣጫ ዝርዝር መረጃ መላክ፡፡ የሰልጣኞችን ዝርዝር፣ የኋላ ታሪካቸውንና ፍላጎታቸውን የሚያሳይ ማጠቃለያ ለአመቻቾች መላክ፡፡ ለ"እየሰሩ-መማር" ስልጠናው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችንና ግብዓቶችን ሁሉ ማዘጋጀት (ለዝርዝሩ የሰንጠረዥ 13.1ን የመጨረሻው ረድፍ ይመልከቱ)፡፡ የስልጠና አመቻቾችን አስቀድሞ በማግኘት ስለ ስልጠናው እና በስልጠናው ላይ ስለሚገኙባቸው ቀናቶች የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡ ለስልጠናው የሚያስፈልጉ እንደ ማስታወሻ ደብተር፣ እስክሪቢቶ፣ ፎቶ ኮፒ፣ የስም መለያ ባጅ፣ አልጋ፣ ምግብ እና ምስክር ወረቀት የመሳሰሉትን ግብዓቶች አስቀድሞ ማዘጋጀት፡፡ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 19 ከ 6 ወራት በፊት መትከል ወይም መትከል ወይም ማቀድ ከ 5 ወራት ማቀድ በፊት ከ 4 ወራት በፊት መከታተል መከታተል ከ 3 ወራት በፊት ከ 2 ወራት በፊት የቅድመ ጉብኝትና የጉዞ መከታተል ስሮችን መከታተል ከ 1 ወራት ዕቅድ መሰብሰብ በፊት የብርቱካንማ መከታተል መከታተል መከታተል ከ 1 ሳምንት ስኳር ድንች በፊት ክትፍታፊዎችን ማዘጋጀት 13.2 የአምስቱ ቀን “ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና መግለጫ የአስር ቀኑን የአስልጣኞች ስልጠና የወሰዱት የወረዳ የልማት ሰራተኞችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች በመስክ ላሉ የስራ ባልደረቦቻቸው ለአምስት ቀናት ስልጠና እንደሚሰጡና የመስክ ሰራተኞቹ በተራቸው ደግሞ ለአርሶአደሮች ስልጠናውን እንደሚያወርዱ ይታመናል፡፡ በመሆኑም በርካታ በተግባር የመማማር ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያስችል የአምስት ቀን የስልጠና መርኃ-ግብር ተዘጋጅቶ ከታች ቀርቧል፡፡ እንደተክሉ የዕድገት ደረጃ አመቻቾች የአምስቱን ቀን ስልጠና በተከታታይ ወይም በተለያዩ ቀናት ማካሄድ ይችላሉ፡፡ አመቻቾች ከአምስት ቀን በላይ ጊዜ ማግኘት የሚችሉ ከሆነ የገበያ ጉዞን ማካተትና (ተግባር 10.10.1) ተሳታፊዎቹ በራሳቸው መንገድ ስልጠናውን እንዲለማመዱ ጊዜ ወስዶ መደገፍ በእጅጉ ይመከራል፡፡ እነዚህ መግለጫዎች አመቻቾችን ሊረዱ እንደሚችሉ የሚታመን ሲሆን ግብረ-መልሶችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ አስተያየትዎን ለመግለፅ እንዲያመችዎ እባክዎትን ርዕስ 14ን ይመልከቱ፡፡ ሠንጠረዥ 13.3. የአምስቱ ቀን “ስለስኳር ድንች ማወቅ የምትፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና መርኃ-ግብር የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት 1 መግቢያ፣ተሳታፊዎች የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - መግቢያ፡ የቡድን ተግባር [15 ደቂቃ] - ፍሊፕ ቻርቶች፣ አድምቆ ለመፃፍ የሚያስችሉ ባለህብረ ከስልጠናው የሚጠብቁት - የስልጠናውን መርሃ ግብር ይረዳሉ፣ እንዴት - የሰልጣኞች ግምት፡ ሰልጣኞች በተናጠል በወረቀት ቀለም ማርከሮች፣ ወረቀት ግድግዳ ላይ ማያያዣ ነገር፣ በመማማር ውጤቶች ሌሎችን በስኳር ድንች ዙሪያ ያስቀመጧቸውን ተጠባቂ የመማማር ውጤት ግምቶች መርፌዎች፤ ላይ ስምምነት ላይ እንደሚያሰለጥኑ ለመርዳት ያቀደ መሆኑን ለሌሎች ማካፈልና ወረቀቶቹን በቡድን መከፋፈል፤ - ሰልጣኞች ስለ ስኳር ድንች ያላቸውን እውቀት ለመለካት መድረስ፣ስለስኳር ድንች ይገነዘባሉ፤ በሰልጣኞቹ የተሰጡትን ግምቶች ከአመቻቾቹ ግምት ጋር የሚረዱ ፈተና ወረቀቶች (አባሪ 1.2) ፤ ጠቀሜታ አጠቃላይ - በስኳር ድንች አመራረትና አጠቃቀም ዙሪያ በማጣጣም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተጠባቂ የመማማር መግለጫ፤ - የስልጠና መርኃ-ግብሩ አጭር መግለጫ (ቀናት እና ስላሉ ማነቆዎች ያውቃሉ፤ ውጤቶቹን መከለስ [30 ደቂቃ] ፤ ለየቀናቱ የተዘረዘሩ ርዕሶችን) ፤ - ከስኳር ድንች የሚሰሩ ምግቦችን ማዘጋጀት - የመግቢያ ፈተና፡ ስልጠናውን ከመጀመራችን በፊት - ተግባር 9.8.1፡ ድስት፣ በከሰል ወይም በጋዝ የሚሰራ ይችላሉ፤ ሰልጣኞች ስለ ስኳር ድንች ያላቸውን አጠቃላይ እውቀት ምድጃ፣ መጥበሻ፣ መክተፊያ፣ መዳመጫ፣ የፍራፍሬ - በዋና ዋና ምግቦች ዝግጅት ብርቱካንማ መለካት ያስፈልጋል [30 ደቂቃ] (አባሪ1.2) መጭመቂያ፣ ሳህን/ትሪ፣ ማቡኪያ፣ ቢለዋዎች፣ ፍሊፕ ስኳር ድንች ሌሎች ግብዓቶችን እንዴት - የስልጠናው መርሃ ግብር ቅኝት [10 ደቂቃ] ቻርት፣ ማርከር ብዕሮች፣ ማጣበቂያ ፕላስተር፣ 2 ከ.ግ ሊተካ እንደሚችል ያውቃሉ፤ - ስለ ስኳር ድንች ታሪካዊ አመጣጥና በሰልጣኞች ዘንድ የስንዴ ዱቄት፣ ግማሽ ከ.ግ የብርቱካናማ ስኳር ድንች ስር፣ - የሥርዓተ-ጾታ ጉዳዮች በስኳር ድንች ያለው እውቀት፡ ጥቂት አባላት ባሉት የሰልጣኞች ቡድን ግማሽ ከ.ግ የተቀቀለ ብርቱካናማ ስኳር ድንች፣ ግማሽ ከ.ግ የዕሴት ሰንሰለት ውስጥ ያላቸውን ጠቀሜታ በኩል ስለስኳር ድንች ያላቸውን እውቀት፣ ታሪካዊ የብርቱካናማ ስኳር ድንች ዱቄት፣ አንድ ኩባያ የአትክልት ይረዳሉ፤ አመጣጡን፣ ባህላዊ ጠቀሜታውን፣ የአመራረት ሂደቱንና ዘይት፣ ጥቂት ጨው፤ አጠቃቀሙን፣ እንዲሁም አርሶ አደሩ ዘንድ የሚታዩ - ተግባር 9.8.2: 4 ኩባያ ስኳር፣ ተቀቅለው የተላጡ 8 መሰረታዊ ማነቆዎችን መወያየት (30 ደቂቃ ለቡድን መካከለኛ መጠን ያላቸው የስኳር ድንች ስሮች፣ 3 የሻይ ውይይት እና 5 ደቂቃ ለእያንዳንዱ ቡድን ለማቅረብ) ማንኪያ ሲትሪክ አሲድ/የሎሚ ጭማቂ/5 ሎሚ፣ ተፈልቶ የቀዘቀዘ 5 ሊትር ውሃ፣ ማጣፈጫ አስፈላጊ ከሆነ/አንድ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 20 የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት - የብርቱካንማ ስኳር ድንች ምግብ ዝግጅት፡ የስንዴን ዱቄት ጠብታ ታማሪንድ ቅመም/ብርቱካን/ሆጲ/አናናስ፣ ወንፊት፣ በስኳር ድንች በመተካት እንደ ቂጣ (ተግባር 9.8.1) እና መጥበሻ፣ የፍራፍሬ መጭመቂያ፣ የእንጨት ማንኪያ፣ 5 አጥሚት (ተግባር 9.4.1) የመሳሰሉ ምግቦችን ያዘጋጃሉ፡፡ ባለ 1 ሊትር ጠርሙሶች፣ ማቀዝቀዣ፤ - የብርቱካንማ ስኳር ድንች አጥሚት ለማዘጋጀት የሚውሉ እንዲሁም የስኳር ድንች ጭማቂ (ተግባር 9.8.2) ያዘጋጃሉ፡፡ በተቻለ መጠን ብዙ አይነት ምግቦችን ግብዓቶች፣ቁሶች፣ ማብሰያዎችና ማገዶ (ተግባር 9.4.1ን እንዲያዘጋጁ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ (2 ሰዓት ከአምስት ተመልከቱ) ደቂቃ) - ገለጻ 2፡ የስኳር ድንች አመጣጥ እና ጠቀሜታው (ርዕስ 2) - ገለጻ 2፡ የስኳር ድንች አመጣጥ እና ጠቀሜታው እንዲቀርብ ተደርጎ የቡድን ውይይት እንዲካሄድ ማድረግ፣ - ገለጻ 11፣. የስርዓተ-ፆታ እና ብዝሃነት ጉዳዮችና [45 ደቂቃ] ፤ ለስኳር ድንች ተግባራት የሚኖራቸው ጠቀሜታ፣ - ገለጻ 11፣. የስርዓተ-ፆታ እና ብዝሃነት ጉዳዮችና ለስኳር የሚያስፈልግ ቅድመ-ዝግጅት ድንች ተግባራት የሚኖራቸው ጠቀሜታ፣ ይህንንም እያንዳንዱ ቡድን ግማሽ ኪሎ የብርቱካንማ ስኳር ድንች በቡድን ውይይት መደገፍ [45 ደቂቃ] ፤ ስር ማግኘት እንዲችል በቂ ስር ማዘጋጀት፡፡ ሰልጣኞቹ ስሩን ለመቀቀልና ለመለንቀጥ ጊዜ የማይኖራቸው ከሆነ ቀድሞ በማዘጋጀት ልምምዱን ሲጀምሩ በቀጥታ ወደማደባለቁ እንዲሄዱ ማድረግ፡፡ የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት 2 ብርቱካንማ ስኳር ድንችና የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ሃሳብ ማንሸራሸር፡ የተመጣጠነ ምግብ ማለት ምን ማለት - ፍሊፕ ቻርት፣ ባለቀለም ማርከር፣ ፕላስተር፣ ግድግዳ ስርዓተ-ምግብ - የተመጣጠነ አመጋገብ ምን እንደሆነና ለምን ነው? ላይ ማጣበቂያ መርፌ፣ እንደሚጠቅም ይረዳሉ፤ - ገለጻ 4ሀ እና ተግባር 4.8.1.፡ ምግቦቻችን ምን ያክል - ተግባር 4.8.1: ገለጻ 4ሀ፣ ፍሊፕ ቻርት፣ ብዕር፣ - ብርቱካንማ ስኳር ድንች እንዴት የተመጣጠኑ ናቸው? ጥሩ የሆነ ስርዓተ-ምግብ ምንድነው? ፕላስተር፣ የቫይታሚን ኤ እጥረትን ለመቀነስ (ንዑስ ርዕስ 4.8.1ን ይመልከቱ) [10 እና 40 ደቂቃ - ተግባር 4.8.2፡ ገለጻ 4ለ፣ ነጭ ወረቀት፣ ብዕር፣ እንደ እንደሚረዳ ያውቃሉ፤ ዱባ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካንማ ስኳር ድንች፣ የሚገኙ ከሆነ በተከታታይ] ፤ - ለህጻናት ተስማሚ የሆኑና በንጥረ-ነገር እንደ አገር በቀል እና ከውጪ የገቡ አትክልቶች ያሉ - ገለጻ 4ለ እና ተግባር 4.8.2.፡ በቫይታሚን ኤ ከዳበሩ የበለጸጉ የብርቱካንማ ስኳር ድንች በቫይታሚን ኤ የበለጸጉ ተክሎች፤ ምግቦች መመገብ፡ ቫይታሚን ኤ፣ ብርቱካንማ ስኳር ድንች ምግቦችን በአካባቢ ከሚገኙ ግብዓቶች - ተግባር 4.8.3. በፎቶግራፍ የተደገፉ ተመሳስሏዊ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚችሉ ያውቃሉ፤ ለምን የቫይታሚን ኤ እጥረትን ይታደጋል? የቫይታሚን ኤ አጥሚት ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ካርዶች እና ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 21 የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት - የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች በቤተሰብ ስርዓተ- እጥረት ተጠቂዎች እነማናቸው? (ንዑስ ርዕስ 4.8.2ን በንጥረ- ነገር የበለጸገ የህጻናት ምግብ ለማዘጋጀት ምግብ ውስጥ ያላቸውን ጠቀሜታ ይረዳሉ፤ ይመልከቱ) [10 እና 20 ደቂቃ በተከታታይ] የሚያስችሉ ግብዓቶች ዝርዝር (በእጅ የሚያዝ መማሪያ - ተግባር 4.8.3: ተመሳስሏዊ የአጥሚት አሰራር (ንዑስ ርዕስ መፅሃፍ 4.8.3ሀ) ፤ 4.8.3ን ይመልከቱ) [1 ሰዓት] - ተግባር 4.8.4: የርዕስ 4 የስልጠና መምሪያ፤ - የቡድን ውይይት: ግንዛቤን ማሳደግና የብርቱካንማ ስኳር ድንች ፍላጎትን መፍጠር (ንዑስ ርዕስ 4.8.4ን ይመልከቱ) [55 ደቂቃ] - የቡድን ውይይት፡ የአካሄዶቻችንን ጥንካሬና ድክመት ብሎም የተጠቀምናቸውን መሳሪያዎች መገምገም፡፡ ስርዓተ-ፆታን በስራዎቻችን ውስጥ ማካተታችንን ማየት? [30 ደቂቃ] የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት 3 - የተለያዩ የስኳር ድንች የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 5.10.1: ንጹህና የተባዙ ለተከላ የሚሆኑ ሀረጎች: - ተግባር 5.10.1: በቫይረስ የተጠቁ ጥቂት ተክሎች ዝርያዎችና ባህሪያቸው፤ - ጥራት ያላቸውን የስኳር ድንች የተከላ ሃረግ ንጹህ የተከላ ሃረግ ቁርጥራጮችን ለማግኘት የመስክ ያሉበት በቅርብ የሚገኝ ማሳ፣ በግማሽ የተጠናቀቀ - የስኳር ድንች የተከላ ሃረግ ቁርጥራጮችን መለየት፣ መምረጥና ማቆየት ተግባር፣ የተከላ ሀረጎችን መውሰድ ፣ ወደ ተከላ የፈጣን ሃረግ ማባዣ መደብ፣ አምስት ቁርጥራጮችን መምረጥ፣ ይችላሉ፤ ቁርጥራጮች መቆራረጥ፣ በፈጣን የማባዣ መደብ ላይ ቢላዋዎች፣ሁለት የውሃ ባልዲ፣ የእጅ መኮትኮቻዎች፡፡ ማቆየትና ማባዛት፤ - ሥለ አሉታዊ /ነጋቲቭ/ እና አዎንታዊ እንዴት ማባዛት እንደሚቻል መማር፣ እንዴት መንከባከብ የተለያየ የመባዛት አቅም ያላቸው ሁለት ዝርያዎች /ፖዘቲቭ/ የስኳር ድንች የተከላ ሃረግ እንደሚቻል እንዲሁም መቼና እንዴት ይተከላሉ ብሎ የተተከሉበት ከስልጠናው ጊዜ ስምንት ሳምንታት የመምረጥ እና የማቆየት መርህ ያውቃሉ፤ መወያየትና፣ የሀረግ የመባዛት አቅምን ማስላት (ተግባር ቀድሞ ብሎ የተተከለ ፈጣን የሃረግ ማባዣ መደብ፣ - ስለስኳር ድንች መሰረታዊ የዝርያ ልዩነቶች 5.10.1ን ይመልከቱ) [1.5 ሠዓት] ፤ ፍሊፕ ቻርት፣ እስክሪብቶ፤ ይገነዘባሉ፤ - ተግባር 3.5.1: ልዩነትን መንቀስ፤ የመስክ ተግባር: በቅርብ - ተግባር 3.5.1. ሰልጣኞች ጥቂት ናሙናዎችን - ለአካባቢያቸው ተስማሚ ስለሆኑ ቢያንስ ቦታ ከሚገኘው መስክ ላይ የተለያዩ የስኳር ድንች ሊሰበስቡባቸው የሚችሉበት ብዙ ዝርያዎች የተተከሉበት በአካባቢ የሚገኝ ማሳ፣ ፍሊፕ ቻርት ፣ ስለ 3 ዝርያዎች ባህሪ ያውቃሉ፤ ባህሪያትን መለየት፤ ከአርሶአደሩ/ሯ ጋር ለምን እያንዳንዱን ማርከር፣ ነጭ ወረቀት፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ ለተሳታፊዎች - በስኳር ድንች ዝርያዎች ላይ የሚታዩትን ዋና ዝርያ እንደሚያመርቱ መወያየት እና ከእነኝህ የተለያዩ ማስታወሻ ደብተር፣ የስኳር ድንች ዝርያዎችን ባህሪያት ዋና ባህሪያት ለይተው አርሶአደሮች እንዲለዩ ዝርያዎች ስሮችን በመውሰድ ለጣዕም ሙከራ መጠቀም መተንተኛ መግለጫ (አባሪ 3.1) እና የቤታ ካሮቲን መርዳት ይችላሉ፤ (3.5.1ን ይመልከቱ) [2 ሰዓት 45 ደቂቃ] ፤ ይዘትን መለኪያ የእጅ መፅሀፍ (አባሪ 3.2) በበቂ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 22 የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት - የተለያዩ ሰዎች የዝርያ ምርጫ እንደሚለያይ - ተግባር 3.5.2: የስኳር ድንች ዝርያዎችን መምረጥ፡፡ መጠን፤ አሳታፊ የስኳር ድንች ስር ጣዕም መገምገሚያ ይረዳሉ፤ የትኛው ባህሪ ለየትኛው ጉዳይ እንደሚጠቅም በዋና ዋና ቅጽ (ቅጽ 5ለ እና 5 ቢ ለ2፣ አባሪ 3.5ለ) በበቂ - በምርት መሰብሰቢያ ወቅት ለምን ጥንቃቄ የስኳር ድንች መለያዎች/ባህሪያት ላይ የቡድን ውይይት መጠን፤ ምድጃ፣ ነዳጅ፣የማብሰያ እቃ፣ ውሃ፣ ክብሪት መደረግ እንዳለበት ያውቃሉ፤ ማድረግ፡፡ ከዚያም ተሳታፊዎች ለአካባቢያቸው እና ቢላዋ፡፡ - የጣዕም ሙከራ ለማከናወን ልምድ ያገኛሉ እንደሚመች በዋና ዋና የስኳር ድንች ዝርያዎች ላይ - ተግባር 3.5.2. ፍሊፕ ቻርት ቢያንስ 1 ገፅ በተሳታፊ (ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ ካርዶች መጠቀም) ፤ የስልጠና ቁሳቁሶችን ያዘጋጃሉ (3.5.2ን ይመልከቱ) [70 ቁጥር፣ ባለቀለም ብዕር ቢቻል ብዛት ያለው ሰማያዊ፣ ደቂቃ] ፤ ቡናማ፣ ብርቱካንማ እና ቢጫ፣ በአለም አቀፍ የድንች - ገለጻ 3. ተፈጥሯዊ የስኳር ድንች ተለያይነትን መዳሰስ፡ ምርምር ማዕከል የተዘጋጀው የብርቱካንማ ስኳር ድንች ዝርያዎች ማውጫ፤ የተለያዩ የስኳር ድንች ዝርያዎችን ባህሪያት መግለጽ (20 ደቂቃ) - ገለጻ 5ሀ እና 5ለ፡ የተከላ ሃረጎችን መምረጥ፣ ማቆየትና ማባዛት (20 ደቂቃ) ፤ - ተግባር 5.10.2: የሶስቱ ኤስ ዘር ማቆያ ስርዓት (አሸዋ፣ ማስቀመጥ፣ ማስጎንቆል/አማማ) - ከስር መረጣ ጀምሮ ቀዝቃዛና በደረቅ ቦታ ላይ እስከማስቀመጥ ያለውን ተግባር መለማመድ [1.5 ሠዓት] ፤ ቁሳቁሶችና እና የሚያስፈልጉ ቅድመ-ዝግጅቶች፡ - ገለጻ 3፡ የስኳር ድንች ሰብል ተለያይነት እና የዝርያ ባህርያት፤ - ገለጻ 5ሀ እና 5ለ፡ የተከላ ሃረጎችን መምረጥ፣ ማቆየትና ማባዛት - ተግባር 5.10.2: በመጠን የተለያዩና በከፊል የተጎዱ 200 የሚሆኑ የስኳር ድንች ሰሮች፣ 6 የፕላስቲክ ሳፋዎች፣ ጋዜጣ፣ 5 ባልዲዎች፣ 5 መጥረጊያዎች፣ ሰልጣኞቹ ያጎነቆሉ ስሮችን ማየት እንዲችሉ ከ3 ወር በፊት የተዘጋጀ የሶስት ኤስ ሰርቶ ማሳያ፡፡ ቅድመ -ዝግጅቶች፡- - ለተግባር 3.5.1. - የተለያዩ ዝርያዎችን የያዘና ለስልጠናው ቦታ ቅርብ የሆነ የአርሶአደር ማሳ መለየት፣ አርሶአደሩን በማግኘት ማሳው በሰልጣኞች እንደሚጎበኝ፣ በሰልጣኞቹ ቃለ-መጠይቅ እንደሚደረግ፣ ከየዝርያው ከ1-2 ተክሎች ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 23 የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት ለመማማሪያ ስራቸውና ሃረጋቸው እንደሚነቀል በመንገር ስምምነቱን መጠየቅ፡፡ ለተነቀሉት ተክሎች ማካካሻ ለአርሶ አደሩ መስጠት እንደሚገባ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ - ለተግባር 5.10.1 ከባለቤቱ ጋር ማሳው መጎብኘት በሚችለበት፣ የተከላ ሃረግ መምረጥና መውሰድ በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ ለመወያየት ቀጠሮ መያዝ፤ ሰልጣኞቹ አሉታዊ የዘር መረጣን እንዲለማመዱ ለማስቻል የአርሶ አደሩ ማሳ በከፊል በቫይረስና በነቀዝ የተጠቃ መሆን ይኖርበታል (ይህ የመረጣ ዘዴ በበሽታና ተባይ የተጠቁ ተክሎችን ነቅሎ ከማሳ ውስጥ የማስወገድ ዘዴ ነው)፣ በጣም የተለያየ የመባዛት አቅም ያላቸውን ዝርያዎች (ለምሳሌ ዝርያ 1 በአንድ ካሬ ሜትር 50 ቁርጥራጭ እና ዝርያ 2 በአንድ ካሬ ሜትር 10 ቁርጥራጭ) የያዙና ስልጠናው ከመጀመሩ ስምንት ሳምንታት በፊት የተተከሉ የፈጣን ሃረግ ማባዣ መደቦችን ማዘጋጀት፣ ሰልጣኞች ተከላውን እንዲያጠናቅቁትና የመረጡትን ሃረግ እንዲተክሉ፣ በአፈር እንዲሸፍኑና ውሃ እንዲያጠጡ ቀደም ብሎ በግማሽ የተተከለ የፈጣን ሃረግ ማባዣ መደብ ማዘጋጀት፣ - ለተግባር 5.10.2. ስሮቹን ገልጠው ጉንቁሉን እንዲያዩና ተከላውን እንዲለማመዱ ለማድረግ የባለሶሰት ኤስ የዘር ማቆያ ስርዓትን ከስልጠናው ጊዜ ጥቂት ወራቶች ቀደም ብሎ ማዘጋጀት፤ የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት 4 - የስኳር ድንች አመራረትና የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 7.9.1: የስኳር ድንች ተባዮችንና በሽታዎችን - ተግባር 7.9.1: ፡ በማደግ ላይ ያለ በቫይረስ የተጠቃ፣ ሰብል አያያዝ፤ - የተለያዩ የስኳር ድንች የዕድገት ደረጃዎችንና በመስክ ላይ ማደንና እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል ቀደም ብሎ በስኳር ድንች የተተከለ እና ሰልጣኞች በሽታና - የስኳር ድንች ተባዮች፣ ደረጃዎቹ በስብል አያያዝ ላይ ያላቸውን መማር፤ የተጠቁ ስሮችንና የተጎዱና የታመሙ ቅጠሎችን ተባይ ሊያገኙበት የሚችሉት የደረሰ ወይም ያረጀ በቅርብ በሽታዎች እና የመቆጣጠሪያ እንድምታ ይረዳሉ፤ መሰብሰብ፣ በመስክ ላይ የተባዮችን የተወሰነ እንቅስቃሴ የሚገኝ ማሳ መለየት፤ 20 መቆፈሪያ በትር፣ የተጎዱ ስሮችን መንገዶች፤ - የስኳር ድንች ቁልፍ ተባዮችና በሽታዎችን በትኩረት መመልከት፣ እነኝህ ተባዮችና በሽታዎች ከየት ለማጓጓዝ 8 ባልዲ፣ 8 ከረጢቶች፣ ጥቃቅን ቀዳዳና ክዳን ናሙና መስክ ላይ ያገኛሉ፤ እንደመጡና እንዴት እንደሚሰራጩ በቡድን መወያየትና ያላቸው መያዣዎች፣ 20 ማጉሊያ መነፅሮች፣ ተሳታፊዎች የሚያስከትሏቸውን ጉዳቶች ሀሳብ ማጋራት (ከተቻለ ነጫጭ ዝንቦችን ጨምሮ) ፡፡ የመማሪያ ደብተሮቻቸውን መያዝ ይኖርባቸዋል፣ ፍሊፕ ይገልጻሉ፣ያሳያሉ፤ በውይይቱ ወቅት የአፈር ማሳቀፍና የስኳር ድንች ቫይረስ ቻርት፣ እርሳስ፣ ማርከር፣ ማጣበቂ ፕላስተር፤ - የእነኝህን ቁልፍ ተባዮችንና በሽታዎችን በሽታዎችን የመንቀስ ተግባራትን ማካተት (7.9.1ን ተግባራዊ የመቆጣጠሪያ የተለያዩ ዘዴዎችን ተመልከቱ) [75 ደቂቃ] ፤ - ተግባር 6.9.1. ተገላላጭ ቻርት፣ እስክሪብቶዎች፣ ያውቃሉ፤ - ተግባር 6.9.1: የተለያዩ የስኳር ድንች ዝርያዎችንና የሰብል ገመድ፣ ሜትር፣ አካፋ፣ መለያ፣ እንጨት፣ በቅርብ ቦታ - አርሶአደሮቹ የተለያዩ ዝርያዎችን ወይም አያያዝ ተግባራትን ማነጻጸር፡ የስኳር ድንች የመስክ ሙከራ የሚገኝ ሙከራው የሚተከልበት ማሳ፣ የዚህ መምሪያ ርዕስ የተለያዩ የሰብል አያያዝ ዘዴዎችን ለማነጻጸር ማቋቋም (ለዝርዝሩ 6.9.1ን ተመልከቱ) [3 ሠዓት] 3፣ 6 እና 7፣ “ስኳር ድንቼን ምን እያጠፋብኝ ነው?” የመስክ ሙከራ እንዲያከናውኑ ይረዳሉ፤ በሚለው መጽሃፍ ውስጥ ከገጽ 20-22 ላይ የተጠቀሰው፤ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 24 የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት - ገለጻ 6. የስኳር ድንች የዕድገት ደረጃዎች (የድህረ-ምርት - ገለጻ 6፡ የስኳር ድንች የዕድገት ደረጃዎችና ተጓዳኝ የሰብል ደረጃዎችን ጨምሮ) ፡ ገለጻውን ተከትሎ ተሳታፊዎች አያያዝ ተግባራት፤ በማስታዎሻ ደብተሮቻቸው ላይ የሰብሉን ሙሉ የዕድገት - ገለጻ 7ሀ እና 7ለ. ፡ ቁልፍ የስኳር ድንች ነፍሳት ተባዮችና ደረጃዎችን ይስላሉ፡፡ በገለጻው ላይ ውይይት ከተካሄደ በሽታዎች የህይወት ዑደት እና የመቆጣጠሪያ ተግባራት፤ በኋላ ተሳታፊዎች በየዕድገት ደረጃው ለየትኛው ተግባር ትኩረት መሰጠት እንደሚያስፈልግ በዝርዝር ያስቀምጣሉ [30 ደቂቃ] ፤ - ገለጻ 7ሀ እና 7ለ.፡ ቁልፍ የስኳር ድንች ነፍሳት ተባዮችና በሽታዎች የህይወት ዑደት እና የመቆጣጠሪያ ተግባራት (ፍልፈልን ጨምሮ) (45 ደቂቃ)፤ የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት 5 - የብርቱካንማ ስኳር ድንች የስልጠናው ተሳታፊዎች፡- - ተግባር 8.9.1: የስኳር ድንችን ስሮች በማስቀመጥ ገቢን - ተግባር 8.9.1፡ እያንዳንዱ ቡድን 10 ተክሎችን በመቆፈር ምርት - ስለ ስኳር ደንች ምርት አሰባሰብ፣ ድህረ- ማሳደግ፡፡ ስሮችን የመሰብሰብ፣ የተበላሹትን የመለየትና ምርቱን ለመቀመር የሚያመች በአቅራቢያው የሚገኝ የስኳር መሰብሰብ፣ማቀነባበርና ምርት አያያዝና አቀነባበር ቁልፍ ጉዳዮችን የተጠበቀ ማስቀመጫ ጉድጓድ የመስራት የመስክ ልምምድ ድንች ማሳ፣ ሚዛን፣ ከረጢት/ጆንያ፣ የሂሳብ ግብይት፤ ያውቃሉ፤ (ማስታወሻ፤ ጉድጓድ፣ ለመሸፈኛ የሚሆን ሳር፣ ቀርከሃ እና መስሪያ/ካሉኩሌተር፣ እስክሪብቶና ወረቀት፣ አካፋ፣ - የ"ስለስኳርድንች ማወቅ - ማቀነባበርና ለብዙ ጊዜ ማስቀመጥ እንጨት በቅድሚያ መዘጋጀት አለባቸው) (ተግባር መቆፈሪያ፣ የሳር ጉዝጓዝና ማሰሪያ ገመድ፤ የምትፈልገው ሁሉ" የብርቱካንማ ስኳር ድንች የቤታ ካሮቲን 8.9.1ን ተመልከቱ) [2 ሰዓት] - ተግባር 8.9.2.፡ 50 የብርቱካንማ ስኳር ድንች ስሮች፣ ስልጠናን ለሌሎች ይዘት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር - ተግባር 8.9.2: በጸሐይ ማድረቅና ለብዙ ጊዜ ማስቀመጥ መቆራረጫ ማሽን፣ ከፍ ያለ ማድረቂያ፣ ቢያንስ ሶስት ለመስጠት ማቀድ፤ ይረዳሉ፤ በብርቱካንማ ስኳር ድንች ቤታ ካሮቲን መጠን ላይ የናሙና ከረጢቶች፣ መለያዎች/ስም መጻፊያዎች፣ ፓርከር - ስለ ግብይትና ገበያ-ተኮርነት ያውቃሉ፤ የሚያደርሰው ጉዳት፡- ተሳታፊዎቸ ለ7፣ ለ5 እና ለ2 ቀናት እስክሪብቶዎች፣ ቤታ ካሮቲን ምን ያህል እየቀነሰ - በስኳር ድንች ስር እና የተቀነባበረ ምርት በጸሐይ የደረቁ የብርቱካንማ ስኳር ድንች ስር እንደሚሄድ የሚያሳዩ መረጃዎች (ጽሑፍ 8.9.2ሀን ግብይት ውስጥ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችንና ቁርጥራጮችን ልዩነት ይመለከታሉ፡፡ የቤታ ካሮቲን መጠን ይመልከቱ) ፤ ተግዳሮቶችን ይረዳሉ፤ ለብዙ ጊዜ ስኳር ድንችን ስናስቀምጥ ምን ያህል - ገለጻ 8፡ የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች በስኳር ድንች ምርት - በ “ስለስኳር ድንች ማወቅ የምትፈልገው እንደሚቀንስ መገንዘብ እንዲችሉ የቤታ ካሮቲን መጠን ስብሰባ፣ ማድረቅ፣ ማጥገግና ድህረ-ምርት ላይ፤ ሁሉ” ዙሪያ ለአምስት ቀናት ስለሚሰጡት መገመቻ ይሰጣቸዋል፡፡ (ተግባር 8.9.2ን ተመልከቱ) [30 - ገለጻ 10ሀ እና 10ለ፡ በግብይት ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ፤ ስልጠና ማቀድና መለማመድ ይጀምራሉ፤ ደቂቃ] ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 25 የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት - ገለጻ 8. ማጥገግ፣ ትንሽ በትንሹ ምርት መሰብሰብና የስር - ተግባር 1.4.1. የአምስቱ ቀን ስልጠና ዋና ዋና ርዕሶች ቁርጥራጭ ማድረቅ የስርዓተ-ጾታን ጉዳዮች ጨምሮ በላያቸው ላይ የተጻፉባቸው ካርዶች (ዘር ማቆየት፣ ለተሻሻለ የድኅረ-ምርት ቆይታ፡፡ አዲስ የተቆፈሩ ስሮችና ማባዛትና ንጹህ ዘርን መምረጥ፣ የስኳር ድንች ነቀዝን የደረቁ የስር ቁርጥራጮች ድህረ- ምርት አያያዝ፤ መቆጣጠር፣ የስኳር ድንች ቫይረስን መቆጣጠር፣ ስኳር የማስቀመጫ ቁሳቁሶች፣ ከተባይ መከላከልና በየጊዜው ድንችን ማቀነባበር፣ ገበያ፣ ቫይታሚን ኤ አመጋገብ ወዘተ)፣ መጎብኘት፡፡ በቤት ውስጥ ስኳር ድንችን ለማስቀመጥ ማን የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" ስልጠና ተጠሪ እንደሆነና መረጃዎች እንዴት እንደሚደርሷቸው መምሪያ፣ ማስታወሻ ደብተርና ብዕር፣ ተጣባቂ ወረቀት፣ ስለማረጋገጥ መወያየት? [45 ደቂቃ] ፍሊፕ ቻርት፣ ፕላስተር፣ ማርከር፣ ከፊሉ የብርቱካንማ - ለማቀነባበር ስልጠና ማንን ዒላማ ማድረግ እንደሚገባ ስኳር ድንች የሆነ 100 ስሮችን ጨምሮ ማናቸውም መወያየት፣ ለምሳሌ በአነስተኛ ደረጃ በምግብ ማቀናበር በስልጠናው ወቅት ጥቅም ላይ የዋሉ ቁሳቁሶች፡፡ ስራ ላይ የተሰማሩና ብርቱካንማ ስኳር ድንችን ለማካተት ፈቃደኛ የሆኑት ላይ ትኩረት ማድረግ፣ ወንዶች በምግብ - ተግባር 1.4.3. በክፍል 12.5.5ሐ የተገለጸውን ዝግጅቱ ዋና ተዋናይ ባይሆኑም ምን ሰብል መተከል የስልጠና መገምገሚያ ቅጽ ለእያንዳንዱ ተሳታፊ እንዳለበት ወይም መገዛት እንዳለበት ውሳኔ የሚሰጡ እንዲደርስ በበቂ መጠን አባዝቶ ማዘጋጀት፣ የስኳር ስለሆነ እነሱን በማሳተፉ ረገድ ውይይት ማድረግ [45 ድንች አጠቃላይ ዕውቀት መገምገሚያ ፈተና በቂ ደቂቃ] [10 ደቂቃ] ቅጂዎች (አባሪ 1.2) ፣እስክርቢቶ፤ - ሃሳብ ማንሸራሸር፡ በአዲስ የስኳር ድንች ስር ግብይት ዙሪያ - የተጠናቀቁ ሰርቲፊኬቶች፤ ለስላሳ መጠጦች፣ ባሉ ዕድሎችና ተግዳሮቶች ላይ፣ [10 ደቂቃ] - ገለጻ 10ሀ እና ለ. የግብይት ፅንሰ ሀሳብ፣ የነጋዴዎች ቅድመ-ዝግጅት ስልጠና እና የስርዓተ-ፆታ ጉዳይን በማካተት ረገድ፣ [20 - ለተግባር 8.9.2. ከአሰልጣኞች ስልጠናው 3 ቀን ቀደም ደቂቃ] ብሎ የብርቱካንማ ስኳር ድንች ስር ቁርጥራጭ ድርቆሽ - ተግባር 1.4.1 የ“በመስራት-መማር” አመቻች ለመሆን ማዘጋጀትና በጸሃይ እንዲደርቅ ከፍ ባለ ማንጠልጠያ መለማመድ፤ ገንቢ የሆነ ግብረ መልስ በመስጠትና በመቀበል ማስቀመጥ (ይህ በኋላ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በጸሐይ መርሆዎች ላይ የቡድን ውይይት ማድረግና በቁልፍ የስኳር የሚደርቅ ናሙና ይሆናል)፣ የተሰወነ ስር ከስልጠናው አንድ ድንች ርዕስ ላይ የአመቻችነት ሚናን መለማመድ (ተግባር ቀን ቀደም ብሎ ቆራርጦ ከመጀመሪያው ጋር እንዳይቀላቀል 1.4.1ን ተመልከቱ) (2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ)፤ ጥንቃቄ በማድረግ በተመሳሳይ መልኩ ከፍ ባለ ማስቀመጫ ማድረቅ፡፡ ናሙናዎቹ በሚገባ መለያ የተደረገባቸው መሆኑና የተጠበቁ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ ፡፡ በአምስቱ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 26 የስልጠና ርዕስ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶች ተግባራት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና ቅድመ-ዝግጅቶች፣ ቀናት - ተግባር 1.4.3 ስልጠናውን መገምገም (ተግባር 1.4.3ን ቀን ስልጠና ሶስተኛው ቀን ላይ ተጨማሪ ስሮችን ቆራርጦ ተመልከቱ) (እንደ ማጠናቀቂያ የስኳር ድንች ዕውቀት ዳሰሳ በተመሳሳይ መልኩ ከፍ ባለ ማስቀመጫ ማድረቅ፡፡ ፈተናን በድጋሚ መስጠት (አባሪ 1.2) (1 ሰኣት) ናሙናዎቹን በስልጠናው አምስተኛ ቀን ላይ ለማስተማሪያነት መጠቀም፡፡ - የተሳትፎ ምስክር ወረቀት መስጠት፤ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 27 13.3 የ “ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና ደጋፊ ገለጻዎች የስልጠናው ደጋፊ የሆኑ የፓወር ፖይንት ገለጻዎች ከዚህ የስልጠና መምሪያ ጋር ተዘጋጅተዋል፡፡ እነዚህ ደጋፊ ገለጻዎች በንዑስ-ርዕስ 13.1 እና 13.2 በተገለጹት መርኃ-ግብራት መሰረት ለአስር እና አምስት ቀናቱ ስልጠናዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና የተቀረጸው በዋናነት ሂደቱ ተግባር ተኮር እንዲሆን ተደርጎ በመሆኑ አመቻቹ አብዛኛውን የስልጠና ጊዜ ማዋል ያለበት ለተግባር ተኮር ትምህርቶች ሲሆን የፓወር ፖይንት ገለጻዎቹን መጠቀም ያለበት ለእነዚህ ተግባራት ድጋፍ ለማድረግ፣ የየርዕሱን ማጠቃለያ ለመስጠት፣ በመስክ ተግባራት ላይ የማይገኙ ከሆነ የሰብሉን የዕድገት ደረጃዎች እና በሽታና ተባዮች በፎቶግራፍ ለማሳየት እና የቡድን ውይይቶችን ለማቀላጠፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ በስልጠናው መምሪያ ላይ ለሚገኙት ለእያንዳንዳቸው ርዕሶች የፓወር ፖይንት ገለጻ የተዘጋጀላቸው ሲሆን እንደ የዘር ስርዓት ላሉ በጣም ሰፊ ርዕሶች ገለጻው በንዑስ ርዕስ እንዲከፋፈል ተደርጓል፡፡ አመቻቾች እነዚህን ገለጻዎች ለአካባቢያቸው በሚመች መልኩ ማስተካከል ይችላሉ፡፡ ስዕል 13.1. “ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና ርዕስ 3 የተዘጋጁ የፓወር ፖይንት ገለጻዎች ምሳሌዎች Recently released orange-fleshed sweetpotato Everything You Ever Wanted to varieties Know about Sweetpotato Country Recently released OFSP varieties Presentation 3. Mozambique Tio Joe, Namanga, Bela, Lourdes, Ininda, Irene, Cecilia, Erica, Delvia, Melinda, Amelia, Sumaia, Esther, Sweetpotato Jane, Gloria varieties and Tanzania Mataya and Kiegea Uganda NASPOT 8, Vita and Kabode their Rwanda RW11—266 and RW11-2910 characteristics Malawi Zondeni Ghana Bokye and Apomuden Nigeria King J and Mother’s delight Reaching Agents of Change (RAC) June 2013 How do breeders produce new Gender and diversity aspects of sweetpotato varieties? sweetpotato varietal selection • Females and males are often interested in different characteristics of sweetpotato – For example: women tend to be interested in cooking qualities of the roots such as low oil Clipped flower to prevent absorption during frying and the tendency of cooked roots to crumble. Where men are Crossing block Screenhouse pollination (in circle) responsible for root sales, they are more likely than women to be interested in market-related characteristics. • A sweetpotato needs assessment will help to understand the different roles sweetpotato plays in the livelihoods of the different groups in the community (e.g. men and women, children, different wealth, age, and religious groups). Botanical or ‘true seeds’ of • On-farm trials can then be developed involving a diverse and representative the sweetpotato plant group of the community Field trials – The gender representation should be proportional to those growing sweetpotato in the community. This also applies to wealth groups. – Where women are the major producers of sweetpotato, work directly with women. However, their husbands should be invited to the planning meeting to get buy-in and alleviate any suspicions • Meetings and field activities should be arranged at locations and times that are Laboratory care of seeds convenient and safe for those involved, including women. Hand pollination ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 28 13.4 “ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠናን ለመደገፍ የተዘጋጁ የመማሪያ ካርዶች ይህንን ስልጠና ለማካሄድ ከተዘጋጁት የስልጠና መምሪያዎችና ገለጻዎች በተጨማሪ ለማስተማሪያ የሚውሉ ካርዶች ተዘጋጅተዋል፡፡ እነዚህ ካርዶች የስልጠናውን ርዕሶች በቅደም ተከተል የሚሸፍኑ ሲሆን እያንዳንዱ ካርድ በፊት ገጹ ፎቶግራፎችን ወይም ስዕላዊ መግለጫዎችን በጀርባ ገጹ ደግሞ ከሚሰጠው ርዕስ ጋር ተያያዥ የሆኑ ቁልፍ ነጥቦችን ይይዛሉ፡፡ አመቻቾች እነዚህን ካርዶች በስልጠና ተግባራቶቻቸው ወቅት እንደ ፈጣን የገለጻ ግብዓቶች እንደሚጠቀሙባቸው ይታመናል፡፡ በካርዶቹ የፊትለፊት ገጽ ላይ ያሉትን ምስሎች ስለሚያስተምሩት ርዕስ ለሰልጣኞች/ለአርሶአደሮች ለማሳየት መጠቀም የሚችሉ ሲሆን እግረመንገዳቸውንም አመቻቾቹ የስልጠናው ዋና ዋና ነጥቦች በካርዱ የጀርባ ገጽ ላይ መካተታቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ካርዶች የተዘጋጁት ለስልጠናው ዕገዛ ለማድረግ በመሆኑ ተግባራዊ የ"እየሰሩ-መማር" ተግባራትንና ከአርሶአደሮች ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን የሚተኩ ተደርገው በፍጹም መወሰድ የለባቸውም፡፡ ስዕል 13.2 የማስተማሪያ ካርድ ቁጥር 5.3. የፊት ለፊት እና የጀርባ ገፅታዎች ምሳሌ Dry season preservation of root planting materials (Triple S system) • The Triple S system is a way of preserving sweetpotato planting materials during the dry season • Select small/ medium sized undamaged roots from the roots you have harvested from healthy plants • Place the roots carefully in a basin and make alternating layers of cool sand and roots, ending with sand on top • Place the container somewhere dry, cool and safe away from chickens and children • 6-8 weeks before the on-set of the rains, uncover the now sprouting roots and plant them in a nursery bed at a spacing of 50*50cm and a depth of 5cm under the soil • Water them every 3-4 days and within a few weeks 40 roots can produce 1,500 cuttings in time forS wtheeetp sottaatrot s oeefd t shysete rmasin- s.5.3 የማስተማሪያ ካርድ ቁጥር 5.3 የፊት ለፊት ገፅታ የማስተማሪያ ካርድ ቁጥር 5.3 የጀርባ ገፅታ ርዕስ 13 - የ"ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም - 29 ርዕስ 14: ግብረ-መልስ ግብረ-መልስ በማንኛውም የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ወሳኝ ክፍል ነው፡፡ ይህንን ስልጠና እና የስልጠና መምሪያ በመስክ ለመተግበር ከተደረገ ከእያንዳንዱ ሙከራ በኋላ ተሳታፊዎች ካላቸው ልምድ በመነሳት ስልጠናው እና መምሪያው በይበልጥ ስለሚሻሻልበት ሁኔታ የራሳቸውን ግብረ-መልስ እና አስተያየት ይሰጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ለተሞክሮ ቦታ ሰጥቶ መነሳት ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለማጣጣም ይረዳል፡፡: በመሆኑም እያንዳንዱ የስልጠና ርዕስ ከተጠናቀቀ በኋላ ግብረ-መልስ እንዲሰጥበት ማድረግ ስልጠናው በተሻለ ሁኔታ ትርጉም እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ሰልጣኞች የራሳቸውን ግብረ-መልስ እንዲሰጡ ሁለት ቅጾች ቀርበዋል፡፡ ማጠቃለያ ገጽ (ሰንጠረዥ 14.1) ከእያንዳንዱ ቀን የስልጠና ውሎ በኋላ ከዚህ ቀደም ባላቸው ልምድ ወይም በስልጠና መምሪያው የተካተቱ ምልከታዎች መሻሻል ስለሚችሉበት ሁኔታ ሁሉም ሰልጣኞች ግብረ-መልሳቸውን የሚሞሉበት ነው፡፡ ምናልባት ሰልጣኞች በእያንዳንዱ የስልጠና ርዕስ ላይ ያላቸውን ግብረ-መልስ ለመስጠት አንድ ገጽ ሙሉ መጠቀም የሚፈልጉ ከሆነ ሰንጠረዥ 14.2 በተሻለ ሁኔታ ሊያገለግል ስለሚችል በፎቶ ኮፒ በማባዛት እንደ መነሻ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ከእያንዳንዱ ገጽ አናት ላይ የስልጠናው ርዕስ ቁጥር እና የስልጠናው ርዕስ መጻፍ ይኖርበታል፡፡ እነዚህ ቅጾች በስኳር ድንች የእውቀት መረጃ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ http://sweetpotatoknowledge.org/projects- initiatives/reaching-agents-of-change-rac/rac-tot-course- forms/Table%2014.1%20and%2014.2_Reflections%20on%20RAC%20ToT%20course.docx/view ፡፡ በስልጠና መምሪያው ላይ በርዕስ 12 እንዲሁም በስኳር ድንች የእውቀት መረጃ ድረ-ገጽ መደበኛ የሆነ የስልጠና መገምገሚያ ቅጽ ይገኛል (ቅጽ 12.5.5ሐ) ፡፡ ምናልባት አንዳንድ የስልጠና ቡድኖች በእያንዳንዱ ሰልጣኝ አማካኝነት በተናጠል ከሚሞላው ቅጽ በተለየ ሁኔታ አነስተኛ የግብረ- መልስ ኮሚቴ በመፍጠር በስልጠና ሂደት መካከል የተሳታፊዎችን ምልከታ በመልቀም በሰንጠረዥ 14.1 ወይም 14.2 ላይ ያሰፍራሉ፡፡ ሌሎች ቡድኖች ደግሞ የሚመርጡት በየዕለቱ ስልጠና ከመጀመሩ በፊት ባለፈው ቀን በተማሩት ዙርያ የተረዱትን እና ግርታ የፈጠረባቸውን ለይተው የሚያቀርቡ ሰዎችን ማዘጋጀት ነው፡፡ በሌላ መልኩ የስልጠና አመቻቹ በእያንዳንዱ የስልጠና ቀን ማጠቃለያ ላይ ተሰታፊዎች በየዕለቱ ከተማሩት ውስጥ ስለ ሶስት በሚገባ ስለተረዷቸው ርዕሶች እና ምንም ሊረዱ ስላልቻሏቸው ርዕሶች እንዲያስቡ በማድረግ ክፍሉ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ እያንዳንዳቸው ስለ አንዱ እንዲናገሩ ያደርጋል፡፡ የዚህ አይነት መንገድ የተሻለ ሊጠቅም የሚችለው በሰልጣኞች እና በአመቻቹ መካከል ግልጽ የመቀባበል ሁኔታ ያለ ከሆነ እና አመቻቹ የሚሰጡ ጥቆማዎችን ተቀብሎ ለመሻሻል ዝግጁ መሆኑን ተሳታፊዎች ካመኑበት ነው፡፡ ስልጠናውን እና የስልጠና መምሪያውን ለማሻሻል በአለምአቀፍ የድንች ምርምር ማዕከል መሪ ተመራማሪ ለሆነችው ለጃን ሎው በኢ- ሜል (አድራሻዋ ከስር ይገኛል) ስለምትልኳቸው ማናቸውም አስተያየቶች በቅድሚያ እያመሰገንን አስተያየቶችን እንዳስፈላጊነቱ የይዘቱ አካል አድርገን ልናካትት እንችላለን፡፡ ለ: J.LOW@CGIAR.ORG ጉዳዩ: “ስለ ስኳርድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአልጣኞች ስልጠና ይዘት እና የስልጠና መምሪያ ላይ የተሰበሰበ ግብረ- መልስ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች- - 30 ሠንጠረዥ 14.1 በስልጠናው እና በስልጠና መምሪያ ላይ የተሰበሰቡ ግብረ-መልሶች ማጠቃለያ ገጽ በ“ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና እና የሰልጠና መምሪያ ላይ የተሰጠ ግብረ-መልስ ስም:- ፆታ: መገኛ ሀገር እና ዓመት: ከዚህ ርዕስ በጣም ደስ ከስልጠናው መሻሻል ያለበት የቱ በስልጠናው ሳይካተት በስልጠና መምሪያው መሻሻል በስልጠና መምሪያው ተጨማሪ አስተያየት ያሰኘህ/ሽ የትኛው ነው? ነው፣ በምን መልኩ መሻሻል የቀረው የቱ ነው? ያለበት የቱ ነው፣ በምን መልኩ ሳይካተት የቀረው የቱ ነው? ካለዎት? ይኖርበታል? መሻሻል ይኖርበታል? ርዕስ 1: ጎልማሶች እንዲማሩ መርዳት ርዕስ 2: የስኳር ድንች መገኛ እና ጠቀሜታው ርዕስ 3: የስኳር ድንች ዝርያዎች እና ባህሪያት ርዕስ 4: ብርቱካንማ ስኳር ድንች እና ስርዓተ-ምግብ ርዕስ 5: የስኳር ድንች ዘር ስርዓት ርዕስ 6: የስኳር ድንች አመራረት እና አያያዝ ርዕስ 7: የስኳር ደንች ተባዮች፣ በሽታዎችና የመቆጣጠሪያ መንገዶች ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 31 ርዕስ 8: ምርት አሰባሰብና ድህረ-ምርት አያያዝ ርዕስ 9: ምርት ማቀነባበርና እና አጠቃቀም ርዕስ 10: ግብይት እና ስራ-ፈጠራ ርዕስ 11: ስርዓተ-ፆታ እና ብዝሃነት ርዕስ 12: የብርቱካንማ ስኳር ድንች ስርጭትን እና አቀባበልን መከታተል ርዕስ 13: የ“ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 32 ሠንጠረዥ 14.2 በ “ስለስኳርድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” ስልጠና እና የስልጠና መምሪያ በእያንዳንዱ ርዕሰ ላይ የተሰጡ ግብረ-መልሶች መሰብሰቢያ ቅጽ “ስለስኳርድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” ስልጠና እና የስልጠና መምሪያ በእያንዳንዱ ርዕሰ ላይ የተሰጡ ግብረ-መልሶች ስም: ፆታ: ቦታ እና ዓመት: የርዕሱ መጠሪያ እና ቁጥር: ከዚህ ርዕስ በጣም ደስ ያሰኘህ/ሽ የትኛው ነው? ከዚህ ርዕስ መሻሻል ያለበት የቱ ነው፣ በምን መልኩ መሻሻል ይኖርበታል? በዚህ ርዕስ ሳይካተት የቀረው ምንድነው? ስለዚህ ርዕስ በስልጠና መምሪያው መሻሻል ያለበት የቱ ነው፣ በምን መልኩ መሻሻል ይኖርበታል? ስለዚህ ርዕስ በስልጠና መምሪያው ሳይካተት የቀረው ምንድነው? ተጨማሪ አስተያየት ካለዎት? ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 33 አባሪዎች አባሪ 1. ማነቃቂያዎች፣የቡድን መልመጃዎች እና የስልጠና ድርጊት መርኃ-ግብር አባሪ 1.1ሀ. ማነቃቂያዎች ማነቃቂያዎች በተለይ የተዳከሙ ተሳታፊዎችን ለማነቃቃት የሚጠቅሙ አጭር የሰውነት እንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡ ተሳታፊዎቹ ጥሩ የሆኑ ማነቃቂያዎችን ሊያውቁ ስለሚችሉ ለቡድናቸው እንዲያካፍሉ ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡ መስታወት መሆን ተሳታፊዎች በጥንድ በጥንድ እንዲሆኑ በማድረግ አንዱ እንደመስታወት እንዲሆን ማድረግ፡፡ እንደመስታወት የሆነው ተሳታፊ የተጣማጁን እንቅስቃሴ አቃቂር እንዲያወጣ ማድረግ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ሚናቸውን እንዲቀያየሩ ማድረግ፡፡ ምን ተቀየረ? ተሳታፊዎች በጥንድ በጥንድ እንዲሆኑ በማድረግ በሚገባ ፊት ለፊት ተያይተው አንዱ የአንዱን ገጽታ እንዲያስታውስ ማድረግ፡፡ በመቀጠል አንደኛው ተጣማጁን ፊቱን እንዲያዞር ነግሮ ገጽታው ላይ የተወሰኑ ለውጦችን ለምሳሌ፡- የእጅ ሰዓቱን ከግራ ወደ ቀኝ እጅ ማዞር፣ የአይን መነጽሩን ማውለቅ፣ የሸሚዙን እጅጌ መጠቅለል የመሳሰሉትን ካደረገ በኋላ ተጣማጁ የተቀየሩትን ነገሮች እንዲዘረዝር ማድረግ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ሚናቸውን እንዲቀያየሩ ማድረግ፡፡ አባሪ 1.1ለ. የቡድን መልመጃዎች የቡድን የስራ ግንኙነትን ለማጠናከርና ወዲያውም ጠቃሚ ጉዳዮችን እያዋዙ ለመካፈል የቡድን ጨዋታዎች ወይም እንቅስቃሴዎች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ዓይነ-ስውሩን መምራት: አላማዎች: - ዓይነ-ስውር መሆን ወይም ምን እየተፈጠረ እንዳለ አለማወቅ የሚፈጥረውን ስሜት ለመካፈል፤ - ድጋፍ የሚሹ ሰዎች ምን እንደሚሰማቸው ግንዛቤን ለመፍጠር፤ - ጥሩ አመቻች ለመሆን የሚያስፈልጉ ነገሮችን ግንዛቤ ለመጨመር፤ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች: ብርሃን የማያሳልፍና አይንን ለመሸፈን የሚያስፈልግ ጥቁር ቀለም ያለው ጨርቅ፤ የሚስፈልግ ጊዜ: 15 ደቂቃ፤ የድርጊት ቅደም ተከተል: ሀ) ተሳታፊዎች በጥንድ በጥንድ እንዲሆኑ በማድረግ የአንዱን አጣማጅ አይን መሸፈን፤ ለ) አይኑ ያልተሸፈነው ተጣማጅ አይኑ የተሸፈነውን በክፍሉ ውስጥ ለ5 ደቂቃ ያክል መሰናክል ባለበት አቅጣጫ እየቀያየረ እንዲወስደው ማድረግ፤ ውይይት: አይነ-ሥውራን ሰዎች ማየት ባለመቻላቸው ምን ይሰማቸዋል? በክፍሉ ውስጥ ሲመሯችሁ ስለነበሩት ሰዎች ምን ተሰማችሁ? አምናችኋቸው ነበር? ለምን? ሲመሯችሁ የነበሩት ሰዎች ይጠነቀቁልን ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ወይስ ሲያታልሏችሁ ነበር? ለምን? መሪዎቹስ አይነ-ስውርን መምራት ምን ስሜት አሳደረባቸው? ጓደኞቻቸውን ለመምራት ምን የተለየ ጥረት አድርገው ነበር? ጓደኞቻቸውን እንዲለማመዱ በቀናው ወይስ በአስቸጋሪው መንገድ ሲወስዷቸው ነበር? ለሚመሯቸው ጓደኞቻቸው ሙሉ ትኩረት ይሰጡ ነበር? ለተመሪ ጓደኞቻቸው እንደፈለጉ እንዲሆኑ ይፈቅዱላቸው ነበር ወይስ በጥብቅ ይቆጣጠሯቸው ነበር? እነዚህን ኩነቶች ቀደም ብሎ መግለጽ ይቻል ነበር? በውይይቱ ጊዜ የተሰጡትን መልሶች መሰረት በማድረግ ስለአመራርና አመቻችነት ጥቂት ማጠቃለያዎችን መስጠት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፡- ጥሩ አመቻቾች:  ሌሎች ሰዎች የእነርሱን ዕቅድ ብቻ እንዲከተሉ አያስገድዱም፤  ተዓማኒና ወቅቱን የጠበቀ ገለጻ ይሰጣሉ፡፡ ሌሎችን አያስፈራሩም ይሁን እንጂ ያሉ ችግሮችን ከመናገር አይቆጠቡም፤  በተሳታፊዎቹ ችሎታና ስሜት ወሰን ብቻ ያመቻቻሉ፤  ተሳታፊዎች በአቅማቸው ሊያከናወኑ የሚችሉትን ተግባራትና ኃላፊነቶች እንዲወጡ ውክልናን ይሰጣሉ፤ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 34 ራስን ማወቅ: ዓላማ: በየጊዜው የሚያጋጥሙንን ነገሮች እንዴት በሚገባ እንደማናጤናቸው ማሳየት፤ የሚፈጀው ጊዜ: 10 ደቂቃ የትግበራ ደረጃዎች: ሀ) ተሳታፊዎችን በጥንድ በጥንድ እንዲሆኑ መጠየቅ፤ ለ) የጥንዶቹን አንዳንድ አባላት ዓይናቸውን እንዲጨፍኑ መጠየቅ፡፡ አይናቸውን የጨፈኑት ተሳታፊዎች ለጓደኞቻቸው ምን እንደለበሱ በዝርዝር እንዲገልጹላቸው ማድረግ (ቀለም፣ በቲሸርቶቻቸው ላይ ያሉ ምስሎችና ጹሑፎች ወዘተ. ቀዳዳዎች፣ ሰዓት፣ ጌጣጌጦች ወዘተ):: አይናቸውን ያልጨፈኑት ተሳታፊዎች የጨፈኑ ጓደኞቻቸውን በሚገባ ማውጣጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ሲጨርሱ ታዛቢዎች ከ1- 10 ነጥብ እንዲሰጡ ማድረግና ምን ጎደለ፣ ለምን መዘርዘር አስቸጋሪ ሆነ ወዘተ በሚሉት ጉዳዮች ዙሪያ መልመጃውን መገምገም፡፡ ሐ) በመቀጠል ተጣማጆቹ ሚናቸውን እንዲቀያየሩ በማድረግ በተራቸው በእጃቸው ሳይዳስሱ በእጅ ቦርሳቸው ውስጥ ምን እንዳለ በዝርዝር እንዲገልጹ ማድረግ፡፡ ጠያቂዎቹ በሚገባ ማውጣጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ሲጨርሱ በትክክል እንደመለሱ ለማረጋገጥ የእጅ ቦርሳቸውን ከፍተው እንዲያሳዩ ማድረግ፡፡ ታዛቢዎች ከ1-10 ነጥብ እንዲሰጡ ማድረግና በጋራ መልመጃውን መገምገም፡፡ ውይይት: እንደቡድን ተሳታፊዎቹ ከመልመጃው ምን ተማሩ? እስከምን ድረስ ስለለበስነው ልብስ ወይም በቦርሳችን ስለያዝናቸው ነገሮች ዝርዝር ማብራሪያ እንሰጣለን? ለምንድነው በጥልቅ ተመልካቾች ያልሆነው? እንዴት በጥልቅ ተመልካችነታችንን ማሻሻል እንችላለን? የቡድን መልመጃዎችንና ማነቃቂያዎችን የያዙ በርካታ ድረ-ገጾችን በኢንተርኔት ላይ በቀጥታ ማግኘት የምንችል ሲሆን http://www.community4me.com/Resources.html ድረ-ገጽ ከእነዚህ መሃል አንደኛው ነው፡፡ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 35 አባሪ 1.2. መሰረታው የስኳር ድንች ዕውቀት ዳሰሳ ፈተና ሙሉ ስም: ጾታ: የስልጠና ቦታ: ቀን: 1. የስኳር ድንች ስር ስጋ ቀለም ዓይነቶች ምን ምን ናቸው? 2. የተመጣጠነ ምግብ ማለት ምን ማለት ነው? 3. ለተከላ የሚውለው የስኳር ድንች ሐረግ ክፍል የትኛው ነው? 4. በቫይረስ የተጠቃ የስኳር ድንች ተክል የሚያሳያቸው ምልክቶች ምን ምን ናቸው? 5. የስኳር ድንች ተክሎች በቫይረስ ተጠቅተው ብታገኙ ምን እርምጃ ትወስዳላችሁ? 6. ይህንን ተባይ ከዚህ ቀደም አይታችሁት ታውቃላችሁ? ከስኳር ድንች ጋር የሚያገናኘው ነገር ምንድነው? 7. በስኳር ድንች ማሳ ውስጥ በብዛት የሚገኙና ለአርሶ አደሩ ጠቃሚ የሆኑ ነፍሳት አሉ? ካሉ እነማናቸው? 8. በስዕሉ ላይ የምታዩትን ጉዳት በስኳር ድንች ስር ላይ እንዲፈጠር ያደረገው ምንድነው? 9. የቫይታሚን ኤ እጥረት ያለበት ሰው ምን ምን ችግሮች ይኖሩበታል? 10.ከስኳር ድንች ስር ማጓጓዝ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ዋና ዋና ችግሮች ምንድናቸው? 11.አምስቱ የግብይት ምሶሶዎች እነማንናቸው? 12.የስኳር ድንች እሴት ሰንሰለት አራት ዋና ዋና ተዋናዮችን/ባለድርሻ አካላትን ስም ጥቀስ? 13.ከስኳር ድንች ምን ምን ምግቦችን ማዘጋጀት ይቻላል? 14.ለእንስሳት ምግብነት ሊውል የሚችለው የስኳር ድንች ተክል አካል የትኛው ነው? 15.ወንዶችንና ሴቶችን በአንድነት በስኳር ድንች ዙሪያ በሚዘጋጁ ስልጠናዎች ላይ ማሳተፍ ለምን ያስፈልጋል? ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 36 አባሪ 1.3. የስልጠና የድርጊት መርኃ-ግብር “የለውጥ ሐዋርያትን መድረስ” የአሰልጣኞች ስልጠና “ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” ስልጠና የድርጊት መርሐ ግብር የዚህ የድርጊት መርኃ-ግብር አላማ የአስሩ ቀን ስልጠና ተሳታፊዎች ያገኙትን አዲስ ዕውቀትና ክህሎት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለማስቻል ነው፡፡ ከስልጠናው አመቻቾችና ከተሳታፊዎች አስተያየትና ግብዓት ለማግኘት እንዲቻል መርኃ-ግብሩ የሚዘጋጀው በስልጠናው ሁለተኛው ግማሽ ሳምንት ውስጥ ይሆናል፡፡ የተጠናቀቀው የድርጊት መርኃ-ግብር ቅጂ ለአመቻቹ በስልጠናው የመጨረሻ ቀን የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ስም፡………… የሚሰራበት ተቋም፡ ቀን ይህንን ስልጠና ለመሳተፍ ምክንያትህ/ሽ ምን ነበር? …………………………………………………………………………………………………………………… …………………………………………………………………………………………………………………… … ይህ ስልጠና ከተጠናቀቀ በኋላ ስለ “ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” ለሌሎች ለማሰልጠን ያለህ/ሽ ዕቅድ ምንድነው? ………………………………………………………………………………………… …………………………………………………………………………………………………………………… …………………………………………………………………………………………………………………… …… ከ“ስለስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ” ስልጠና ውስጥ የትኛውን ርዕስ ለማሰልጠን አቅደሃል/ሻል? …………………………………………………………………………………………………… …………………………………………………………………………………………………………………… ስልጠናውን መቼ ትሰጣለህ/ሽ? የስልጠናው መጀመሪያ ቀን፡) …የስልጠናው ማብቂያ ቀን፡)…... የስልጠናው ተሳታፊዎች እነማን ናቸው? …………………………………………………………………………………………………………………… ………………………………………………………………………………………………….……… በስልጠናው ልትፈታው/ቺው ወይም ልትቀንሰው/ሽው ያቀድከው/ሽው ማነቆዎች ምንድናቸው? …………………………………………………………………………………………………………………… …………………………………………………………………………………………………………………… የስልጠናው ተጠባቂ ውጤቶች ምንድናቸው? …………………………………………………………………………………………………………………… …………………………………………………………………………………………………………………… ምንያክል ተሳታፊዎችን ለማሰልጠን አቅደሃል/ሻል? …………………………………………………………………………………………………………………… … ስልጠናውን የሚሰጠው ቡድን ማን ማንን ያካተተ ነው? …………………………………………………………………………………………………………………… …………………………………………………………………………………………………………………… …… የሚያስፈልገው በጀት ዕቅድ፡……… የበጀት ምንጭ፡ … የአመቻቹ ፊርማ፡ የሰልጣኙ ፊርማ፡ የሰልጣኙ ኢሜይል፡ የሰልጣኙ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር፡ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 37 …… …………………… . አባሪ 2. የስኳር ድንች ዕውቀት ድረ-ገጽ ላይ ያሉ ጹሑፎችን እንዴት መጠቀም ይቻላል? የስኳር ድንች ዕውቀት ድረ-ገጽ በትብብር የተመሰረተ የኢንተርኔት የቀጥታ ግንኙነት መድረክ ሲሆን የስኳር ድንች ባለድርሻ አካላት መረጃና ዕውቀት የሚለዋወጡበት ነው፡፡ የመድረኩ ዓላማ የአፍሪካን ህዝብ የምግብና የንጥረ-ነገር ዋስትና ለማረጋገጥ የቴክኒክ፣ ሳይንሳዊ፣ አገር በቀልና የልማት ዕውቀቶችን ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡ ይህ መድረክ ከቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በስኳር ድንች ለምግብና ጤና ዋስትና በአፍሪካ ፕሮጀክት በኩል በሚገኝ በጀት በአለም አቀፉ የድንች ምርምር ማዕከል በኩል ይደገፋል፡፡ መድረኩ ለሁሉም የስኳር ድንች ባለድርሻ አካላት ክፍት ሲሆን ስለስኳር ድንች ያላቸውን ማንኛውንም ዕውቀትና መረጃ በድረ-ገጹ ላይ መጫን ይችላሉ፡፡ ሲጀመር መድረኩ የስኳር ድንች ሳይንቲስቶችን ለመርዳት ብቻ የተዘጋጀ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ክፍት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ባለድርሻ አካላት ስራዎቻቸውን በድረ-ገጹ ላይ ቢያወጡ የስራቸውን ዋጋ ከፍ ስለሚያደርገው እንዲያደርጉት ይበረታታሉ፡፡ የመድረኩ ፖሊሲ የጹሑፉ ባለቤቶችን የሚያበረታታ ቢሆንም መረጃና ዕውቀት የህዝብ ሃብት እንዲሆኑም ጥረት ያደርጋል፡፡ የስልጠና አመቻቾች አባል ሆነው ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በትብብር እንዲሰሩ ይበረታታሉ፡፡ በ http://www.sweetpotatoknowledge.org/register አድራሻ ገብቶ አባል መሆን ይቻላል፡፡ የተመዘገቡ አባላት የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ይፈቀድላቸዋል:  ከስኳር ድንች ጋር የተያያዙ ነገሮችን መጫን፣ ማረም፣ ማተም፤  አባላቱና የወከሏቸው ሰዎች ብቻ ሊያዩት የሚችሉት የፕሮጀክት የግል መያዣ መፍጠር (እንደ ቀን መቁጠሪያ፣ በጀት፣ ሪፖርት የመሳሰሉትን ለማስቀመጥ) ፤  ከሌሎች አባላት፣ ተባባሪዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር መገናኘት፤  የውይይት መድረኮችን መሳተፍ፤  በድረ-ገጹ ላይ የሚወጡ ጹሑፎችን ማግኘት፤ ተመዝግበው አባል ያልሆኑ የሚፈቀድላቸው በድረ-ገጹ ላይ የታተሙ መረጃዎችን መፈለግ እና ለጸሃፊዎቹ ወይም ለውይይት መድረኩ አስተያየት መስጠት ብቻ ነው፡፡ የድረ-ገጹን ይዘቶች ለማግኘት በመግቢያ ገጹ ላይ ያለውን ነጭ ቀስት ማስፈንጠር ይቻላል፡፡ አባሪ 3. የስኳር ድንች ዝርያዎች ባሕሪያት መተንተኛ ቻርት፣ የቤታ ካሮቲን ቀለም ቻርትና በአርሶ አደር ማሳ ላይ የሚደረጉ ሙከራዎች መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ አባሪ 3.1 የስኳር ድንች ዝርያዎች ባሕሪያት መተንተኛ ምንጭ: CIP, AVDRC, IBPGR, 1991 የተክል አይነት: 1. ቀጥ ያለ = ርዝመቱ ከ75 ሳ.ሜ ያነሰ 2. በከፊል ቀጥ ያለ = ርዝመቱ 75-150 ሳ.ሜ 3. ዘርዘር ያለ = ርዝመቱ 151- 250 ሳ.ሜ 4. እጅግ በጣም ዘርዘር ያለ = ርዝመቱ ከ 250 ሳ.ሜ የበለጠ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 38 የሃረጉ ዋና ቀለም: 1. አረንጓዴ 3. ጥቂት የወይን ጠጅ ነጠብጣብ ያለበት አረንጓዴ 4. ብዙ የወይን ጠጅ ነጠብጣብ ያለበት አረንጓዴ 5. ብዙ ጥቁር የወይን ጠጅ ነጠብጣብ ያለበት አረንጓዴ 6. በአብዛኛው የወይን ጠጅ 7. በአብዛኛው ጥቁር የወይን ጠጅ 8. ሙሉ በሙሉ የወይን ጠጅ 9. ሙሉ በሙሉ ጥቁር የወይን ጠጅ የሃረጉ ሁለተኛ ቀለም፡ 0. የለም 1. መነሻው ላይ አረንጓዴ 2. ጫፉ አረንጓዴ 3. እንቡጦቹ አረንጓዴ 4. መነሻው የወይን ጠጅ 5. ጫፉ የወይን ጠጅ 6. እንቡጦቹ የወይን ጠጅ 1. ክብ 2. የኩላሊት ቅርጽ 0. ያልተከፋፈለ 1. በጣም በትንሹ የተከፋፈለ 3. የልብ ቅርጽ 4. ሶስት ማዕዘን 3. በትንሹ የተከፋፈለ 5 በመጠኑ የተከፋፈለ 5. ጦር መሳይ 6. የተከፋፈለ 7. ጣት መሳይ 7. በጥልቅ የተከፋፈለ 9. በጣም በጥልቅ የተከፋፈለ የቅጠል አጠቃላይ ገጽታ የቅጠል ክፍልፋይ አይነት የቅጠል ክፍልፋይ ቁጥር የመካከለኛው የቅጠል ክፋይ ቅርጽ የቅጠል ደም ስር ቀለም: 1. ቢጫ 2. አረንጓዴ 3. በመካከለኛው የቅጠል ደም ስር መነሻ ላይ የወይን ጠጅ ነጠብጣብ 4. በብዙ የቅጠሉ ደም ስሮች ላይ የወይን ጠጅ ነጠብጣብ 5. ዋናው የቅጠሉ ደም ስር በከፊል የወይን ጠጅ 6. ዋናው የቅጠሉ ደም ስር በአብዛኛው ወይም በሙሉ የወይን ጠጅ 7. ሁሉም የቅጠሉ ደም ስሮች በሙሉ የወይን ጠጅ 8. ሁሉም የቅጠሉ ደም ስሮች በአብዛኛው ወይም በሙሉ የወይን ጠጅ 9. የቅጠሉ የታችኛው ገጽታና ደም ስሮች ሙሉ በሙሉ የወይን ጠጅ የደረሱ ቅጠሎች ቀለም: 1. ቢጫ - አረንጓዴ 2. አረንጓዴ 3. አረንጓዴ ሆኖ ጫፎቹ የወይን ጠጅ 4. አመድማ አረንጓዴ 5. አረንጓዴ ሆኖ በላይኛው የቅጠሉ ገጽታ ላይ ያሉ የደም ስሮች የወይን ጠጅ 6. በትንሹ የወይን ጠጅ 7. በአብዛኛው የወይን ጠጅ 8. የላይኛው ገጽታ አረንጓዴ የታችኛው ደግሞ የወይን ጠጅ 9. የሁለቱም ገጽታዎች የወይን ጠጅ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 39 ያልደረሱ ቅጠሎች ቀለም: 1. ቢጫ - አረንጓዴ 2. አረንጓዴ 3. አረንጓዴ ሆኖ ጫፎቹ የወይን ጠጅ 4. አመድማ አረንጓዴ 5. አረንጓዴ ሆኖ በላይኛው የቅጠሉ ገጽታ ላይ ያሉ የደም ስሮች የወይን ጠጅ 6. በትንሹ የወይን ጠጅ 7. በአብዛኛው የወይን ጠጅ 8. የላይኛው ገጽታ አረንጓዴ የታችኛው ደግሞ የወይን ጠጅ 9. የሁለቱም ገጽታዎች የወይን ጠጅ የስር ቆዳ ቀለም: 1. ነጭ 2. ክሬም 3. ቢጫ 4. ብርቱካንማ 5. ቡኒ ብርቱካንማ 6. ሐምራዊ 7. ቀይ 8. ቀይ የወይን ጠጅ 9. ጥቁር የወይን ጠጅ የስር ቆዳ ቀለም ጥልቀት: 1. ደብዛዛ 2. መካከለኛ 3. ጥልቅ የስር ስጋ ቀለም: 1. ነጭ 2. ክሬም 3. ጥልቅ ክሬም 4. ደብዛዛ ቢጫ 5. ጥልቅ ቢጫ 6. ደብዛዛ ብርቱካንማ 7. መካከለኛ ብርቱካንማ 8. ጥልቅ ብርቱካንማ 9. በአንቶሲያኒን በጥልቅ የቀለመ የስር ቅርጽ የስር አፈጣጠር ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 40 አባሪ 3.2. የስኳር ድንች የቤታ ካሮቲን መጠን ማሳያ የቀለም ቻርት አዲስ የተሰበሰቡ የስኳር ድንች ስሮች ክትፍታፊዎችን የቤታ ካሮቲን ይዘት ለመለካት፡- መመሪያ: 1. አዲስ የተሰበሰቡትን የስኳር ድንች ስሮች በቁመታቸው መቁረጥ 2. የተቆረጠውን ስር ከቀለም ቻርቱ ጎን በማድረግ ለየትኛው ቀለም በይበልጥ እንደሚቀርብ ማየት 3. ተቀራራቢ የቤታ ካሮቲንና የቫይታሚን ኤ ይዘታቸውን ከቻርቱ ላይ ማንበብ፡፡ ማስታወሻ፡ ይህ መንገድ የሚያገለግለው ለብርቱካንማ ስኳር ድንች ዝርያዎች ሲሆን የቢጫ ስኳር ድንች ዝርያዎች ቤታ ካሮቲን መጠን ከፍተኛ ተለያይነት ስለሚታይበት ሌላ መንገድ መጠቀም ይመከራል፡፡ A B C D ቤታ ካሮቲን: 0.03 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ፣ ቤታ ካሮቲን: 0.00 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ፣ ቤታ ካሮቲን: 0.15 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ፣ ቤታ ካሮቲን: 1.32 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ፣ ቫይ. ኤ: 2.5 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ክ ቫይ. ኤ: 0.0 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ክ ቫይ. ኤ: 12.5 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ቫይ. ኤ: 110.0 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ክ ክ E F G H ቤታ ካሮቲን: 1.65 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ፣ ቤታ ካሮቲን: 3.96 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ፣ ቤታ ካሮቲን: 4.92 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ ቤታ ካሮቲን: 6.12 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ፣ ቫይ. ኤ: 137.5 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ቫይ. ኤ: 330.0 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ቫይ. ኤ: 410.0 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ቫይ. ኤ: 510.0 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ክ ክ ክ ክ I J K L ቤታ ካሮቲን: 7.76 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ፣ ቤታ ካሮቲን: 10.5 ሚ. ግ/100ግ ት.ክ፣ ቤታ ካሮቲን: 12.39 ሚ. ግ/100ግ፣ ቤታ ካሮቲን: 14.37 ሚ. ግ/100ግ ቫይ. ኤ: 646.7 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ቫይ. ኤ: 875.0 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ት.ክ ት.ክ፣ ክ ክ ቫይ. ኤ: 1032.5 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ቫይ. ኤ: 1197.5 ማ. ግ ተ.ሬ.ተ/100ግ ት. ክ ት.ክ መፍቻ: ት.ክ = ትኩስ ክብደት ቫይ.ኤ = ቫይታሚን ኤ ተ.ሬ.ተ = ተመጣጣኝ የሬተኖል ተግባር ሚ.ግ =ሚሊ ግራም ማ.ግ = ማይክሮ ግራም ምንጭ: Adapted from Burgos et al., (2001) “A colour chart to screen for high beta-carotene content in OFSP breeding” ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 41 አባሪ 3.3. የስኳር ድንች ዝርያዎችን ለመለየት የምንጠቀምባቸውን ቁልፍ የተክል ገጽታ መረጃዎች መሰብሰቢያ ቅጽ (ለተጨማሪ ማብራሪያ አባሪ 3.1 እና 3.2ን ተመልከቱ) የዝርያ ስም የተክል ዋና የሃረግ ቀለም ሁለተኛ የሃረግ የቅጠል የቅጠል የቅጠል የመሃለኛው የቅጠል ደም ስር የደረሰ ቅጠል ያልደረሰ ቅጠል የስር ቆዳ ቀለምና የስር ስጋ ቀለም የቤታ ካሮቲን የስር ቅርጽ የስር አፈጣጠር ዓይነት ቀለም አጠቃላይ ክፍልፋይ ክፍልፋይ ቅጠል ቀለም ቀለም ቀለም ጥልቀት ይዘት ግምት ገጽታ አይነት ቁጥር ክፍልፋይ ቅርጽ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 42 አባሪ 3.4. በአርሶአደር ማሳ ላይ ለሚከናወኑ ሙከራዎች ከአርሶአደሩ ጋር የሚደረግ የውል ስምምነት ናሙና ------------------------------------- የተባለው የባለድርሻ አካል ተቋም ተወካይ ባለበት በተመራማሪው ስም------------------------- ------------------------ እና በአርሶአደሩ ስም-------------------------------------------- መካከል የተከናወነ የውል ስምምነት እኛ ከታች ፊርማችንን ያስቀመጥነው፡ 1. የሙከራው ማሳ የመካከል 3 መስመሮች ተመራማሪውና የአካባቢው ባለድርሻ አካል ተቋም ተወካይ ባሉበት የሚሰበሰቡና ከመድረሻቸው ጊዜ በፊት በፍጹም መነካት እንደሌለባቸው፣ አንዱ መስመር ስሮችን በአፈር ውስጥ በማስቀመጥ ለሚደረግ ጥናት የሚተው መሆኑንና የተቀረውን አንድ መስመር ግን አርሶአደሩ በፈለገው ጊዜ የሚጠቀምባቸው መሆኑን ተስማምተናል፡፡ 2. አርሶአደሩ የሚከተሉትን የሰብል እንክብካቤ ተግባራት ለማከናወን ተስማምቷል፡- ሀ. የሙከራ ማሳዎቹን በሚገባ ለመንከባከብ፣ ለማረምና እንዲሁም ተመራማሪው በሚሰጠው ምክር መሰረት ስምምነት ላይ የደረሱበትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡ - የቦዩ ከፍታ 40 ሳ.ሜ በሆነ መደብ ላይ በ30 ሳ.ሜ ርቀት ስኳር ድንቹን ይተክላል፡፡ - የመጀመሪያ አረም በተተከለ ከ3 ሳምንታት በኋላ ያከናውናል፡፡ - ሁለተኛ አረምና አፈር ማስታቀፍ እንደአስፈላጊነቱ ተመራማሪው በሚያሳየው መሰረት ያከናውናል፡፡ ለ. ማሳውን በጥንቃቄ በመምረጥ ወይም አጥር በመስራት (ከቁጥቋጦ ወይም ከሌላ ቁሳቁስ) የሙከራ ማሳውን ከእንስሳት ጥቃት ይከላከላል፡፡ ሐ. በስኳር ድንች ሰብል አያያዝ ላይ በሚዘጋጁ ስልጠናዎች ላይ ይሳተፋል፡፡ 3. ሌሎች አርሶ አደሮችና የማኅበረሰቡ አካላት በማሳው ላይ በሚዘጋጁ የመስክ ቀኖችም ሆነ በሌላ ጊዜ በሚደረጉ ጉብኝቶች እንደሚጋበዙ ያውቃል፡፡ 4. በተክሉ የዕደገት ወቅት መረጃ ለመሰብሰብ ተመራማሪዎች ተደጋጋሚ የመስክ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይረዳል፡፡ 5. ለማብሰልና ለማስቀመጥ ሙከራ ከሚፈለጉት ስሮች (ቢበዛ 20 ስሮች) በስተቀር ሌላው ምርት ሁሉ የራሱ መሆኑን ያውቃል፡፡T 6. ሌሎች ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ጉዳዮች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ፊርማና ቀን: አርሶአደር(ሮች) ቀን ተመራማሪ(ዎች) ቀን የአካባቢ ባለድርሻ ተቋም ቀን ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 43 አባሪ 3.5.ሀ. በተመራማሪዎች፣ በስርጸትና መያድ ሰራተኞች ጥቅም ላይ የሚውል በመስክ ላይ የሚደረግን የስኳር ድንች ዝርያዎች ሙከራ የቅድመ-ምርት ስብሰባና የምርት ስብሰባ መረጃ መመዝገቢያ ቅጽ ቅጽ 4ለ. የቅድመ-ምርት ስብሰባ ቅጽ ሀገር ቦታ የሙከራው አይነት አመት ወቅት ገጽ የዕድገት 3-4 ሳምንት ከተከላ በኋላ የቫይረስ ምልክት አልተርናሪያ ጥንካሬ ከ6-8 ከምርት ከ6-8 ከምርት ሳምንት ስብሰባ ሳምንት ስብሰባ ከምርት ከተከላ 1 ወር ከተከላ 1 ወር ስብሰባ 1 1- በኋላ በፊት በኋላ በፊት ወር በፊት መለያ አደራረግ ማወዳደሪያ 1-ምንም ምልክት 1-ምንም ምልክት የማሳ ዝርያ 2- የተተከሉ የጸደቁ የለም 9- ከባድ የለም 9- ከባድ 1-ምንም ቁጥር ድግግሞሽ ዝርያ (ስም ወይም ቁጥር) መለያ አዲስ ዝርያ ሃረጎች ቁጥር ሃረጎች ቁጥር ምልክት አለ ምልክት አለ 9-ጠንካራ የቫይረስ ምልክቶች የአልተርናሪያ ምልክቶች 1- ምንም ምልክት የለም 1- ምንም ምልክት የለም 2-ግልጽ ያልሆነ ምልክት 2-ግልጽ ያልሆነ ምልክት 3-ግልጽ የሆነ ምልክት በማሳው ከ5 በመቶ ባነሱ ተክሎች ላይ 3- በማሳው 1 ተክል ላይ ግልጽ ምልክት 4- ግልጽ የሆነ ምልክት በማሳው ከ6-15 በመቶ 4- ግልጽ የሆነ ምልክት በማሳው ከ6-15 በመቶ ተክሎች ላይ ተክሎች ላይ 5- ግልጽ የሆነ ምልክት በማሳው ከ16-33 በመቶ 5- ግልጽ የሆነ ምልክት በማሳው ከ16-33 በመቶ ተክሎች ላይ ተክሎች ላይ 6- ግልጽ የሆነ ምልክት በማሳው ከ33-66 በመቶ 6- ግልጽ የሆነ ምልክት በማሳው ከ33-66 በመቶ ተክሎች ላይ ተክሎች ላይ 7- ግልጽ የሆነ ምልክት በማሳው ከ67-99 በመቶ 7- ግልጽ የሆነ ምልክት በማሳው ከ67-99 በመቶ ተክሎች ላይ ተክሎች ላይ 8- በሁሉም ተክሎች ላይ መቀንጨር የሌለበት ግልጽ የሆነ 8- በማሳው አብዛኛው ተክሎች ላይ ግልጽ የሆነ ምልክት ምልክት 9- በማሳው ሁሉም ተክሎች ላይ ከባድና ግልጽ 9- መቀንጨር ያለበት ከባድ ምልክት በሁሉም ተክሎች ላይ የሆነ ምልክት የሃረግ ዕድገት ጥንካሬ 1- ምንም የሃረግ ዕድገት የለም 2. ልፍስፍስ ሃረግ፣ ቀጭን ግንድ፣ በጣም የተራራቁ አንጓዎች 3- ከልፍስፍስ እስከ መካከለኛ ጠንካራ ሃረግ፣ መካከለኛ ውፍረት ያለው ግንድ፣ የተራራቁ አንጓዎች 4- በመካከለኛ ደረጃ ጠንካራ ሃረግ፣ በመካከለኛ ደረጃ ወፍራም ግንድ፣ መካከለኛ የአንጓ ርቀት 5- በመካከለኛ ደረጃ ጠንካራ ሃረግ፣ ወፍራም ግንድ፣ የተራራቁ አንጓዎች 6- በመካከለኛ ደረጃ ጠንካራ ሃረግ፣ ወፍራም ግንድ፣ መካከለኛ የአንጓ ርቀት 7- ጠንካራ ሃረግ፣ ወፍራም ግንድ፣ አጭር የአንጓ ርቀት፣ መካከለኛ የሃረግ ርዝመት 8- ጠንካራ ሃረግ፣ ወፍራም ግንድ፣ አጭር የአንጓ ርቀት፣ ረዥም ሃረግ 9- በጣም ጠንካራ ሃረግ፣ ወፍራም ግንድ፣ አጭር የአንጓ ርቀት፣ በጣም ረዥም ሃረግ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 44 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 45 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 46 ቅጽ 5ሀ1. የጥንድ ማወዳደሪያን በመጠቀም የዝርያዎችን አጠቃላይ የመስክ አቋም በቡድን ደረጃ ማውጣት ዝርያ ዝርያ A B C D E F A X B X C X D X E X F X አጠቃላይ ድግግሞሽ በዝርያ ደረጃ ከፍተኛ ደረጃ ላገኙ ዝርያዎች ምክንያት: _____________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ዝቅተኛ ደረጃ ላገኙ ዝርያዎች ምክንያት: ______________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 47 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 48 ቅጽ 5ለ2. የጥንድ ማወዳደሪያ ዘዴን በመጠቀም የስኳር ድንች ዝርያዎችን ስር ጣዕም አጠቃላይ ተቀባይነት በቡድን ደረጃ ማውጣት ዝርያ ዝርያ A B C D E F A X B X C X D X E X F X አጠቃላይ ድግግሞሽ በዝርያ ደረጃ ከፍተኛ ደረጃ ላገኙ ዝርያዎች ምክንያት: _____________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ዝቅተኛ ደረጃ ላገኙ ዝርያዎች ምክንያት: ______________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 49 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 50 ቅጽ 5ሐ1. የጥንድ ማወዳደሪያን በመጠቀም የስኳር ድንች ዝርያዎችን አጠቃላይ የቅጠል የምግብነት ጥራት በቡድን ደረጃ ማውጣት ዝርያ ዝርያ A B C D E F A X B X C X D X E X F X አጠቃላይ ድግግሞሽ በዝርያ ደረጃ ከፍተኛ ደረጃ ላገኙ ዝርያዎች ምክንያት: _____________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ዝቅተኛ ደረጃ ላገኙ ዝርያዎች ምክንያት: ______________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ______________________________________ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 51 አባሪ 5. ከቲሹ-ከልቸር ላቦራቶሪ ለሚወጡ ተክሎች እንክብካቤ ማድረግና የመረብ ድንኳን መገንባት አባሪ 5.1 ከቲሹ-ከልቸር ላቦራቶሪ የወጡ ተክሎችን ማጓጓዝ፣ መቀበል፣ ማጠንከር፣ ማዛመት እና እንክብካቤ ማድረግ መሸከፍና ማጓጓዝ: ከቲሹ-ከልቸር ላቦራቶሪ የወጡ ተክሎች ከመጓጓዛቸውቸ9 በፊት መያዣ ብልቃጦቹ ለሁለት ቀናት በመጠኑ ቀዝቃዛና የተወሰነ ብርሃን ባለው ቤት ውስጥ መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ በመቀጠልም በትልቅ ጠንካራ ካርቶን ውስጥ ታሽገው “ተሰባሪ”፣ ወደላይ አመልካች ቀስትና ካርቶኑ እንዴት ማጓጓዣው ላይ መቀመጥ እንዳለበት የሚገልጽ ጽሑፍ ይደረግባቸዋል፡፡ ተክሎቹ ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር የሚጓጓዙ ከሆነ አስፈላጊ የሆኑ የጉሙሩክ መረጃዎችን (ለምሳሌ የዕጽዋት ዘር ማስገቢያ ፈቃድ፣ ከበሽታና ተባይ ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣በአገራት መካከል የሚደረግ የዕጽዋት ዘር ዝውውር ውል ወዘተ.) ከጉዞ በፊት ቀደም ብሎ መጨረስ ተክሎቹ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች በሙሉ የማጓጓዣ መኪናውን የምዝገባ ቁጥር፣ የካርቶኖቹን ብዛት፣ ተክሎቹን የያዙ ማሸጊያዎችን ብዛትና በየማሸጊያዎቹ ያለ የተክል ብዛት እንዲሁም የተጫኑበትን ቀን በግልጽ ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ መረጃዎቹም በበቂ ቅጂ ተባዝተው ጉሙሩክ ላይ በሚጠየቅ ጊዜ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማጓጓዣው መኪና ምንም አይነት ችግር የሌለበት መሆን የሚገባው ሲሆን አቧራና ሌሎች አየር-ወለድ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ወደተክሎቹ እንዳይገቡ በጉዞው ወቅት ሁሉም መስኮቶቹ ዝግ ሆነው መቆየት አለባቸው፡፡ የተሸከርካሪው የጉዞ ፍጥነት ከ60 – 80 ኪ.ሜ በሰዓት መብለጥ የሌለበት ሲሆን ብልሽት ቢገጥመው ለማስጠገኛ የሚሆን በቂ ገንዘብ መያዝ ያስፈልጋል፡፡ ጉዞውን በቀን ማድረግም የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ቀላል ይሆናል፡፡ ከተቻለ ሜካኒክ አብሮ እንዲጓዝ ማድረግ ተመራጭ ሲሆን የተቀባዩን ዝርዝር አድራሻም መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ መቀበል: ተቀባዩ ማንኛውንም ብክለት ለመቀነስ ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ተክሎች ሲደርሱ የሚቆዩበትን ቦታ (የመረብ ቤት) በጸረ-ተባይና በሽታ መድኀኒቶች መርጨት ይኖርበታል፡፡ መቀበያው ቦታ ብልቃጦቹን በሚገባ ለማስቀመጥ መደርደሪያ ሊኖረው የሚገባ ሲሆን የሙቀት መጠኑም ከ24 – 29 ዲ.ሴ መሆን ይገባዋል፡፡ በተጨማሪም ተክሎቹ በዕኩል ደረጃ እንዲያድጉ በክፍሉ ውስጥ ያለው የጸሐይ ብርሃን ስርጭት ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ መቀበያ ቦታውን የመረብ ቤት የማድረጉ አላማ ተክሎቹ ከረዥም ጉዞ በኋላ እንዲያገግሙ ለማድረግና ለመጨረሻው የማጠንከር ስራ ተግባር ቦታ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡ ተክሎቹን የያዙት ብልቃጦች ተቀባዩ ጋር በደረሱ ጊዜ ከካርቶኑ በጥንቃቄ ይወርዱና በአልኮል ይረጫሉ፡፡ ብልቃጦቹን የሚያወርደው ሰውም እንዲሁ አልኮል መቀባትና ጓንት ማድረግ የሚኖርበት ሲሆን ቀጥ አድርጎ በመደርደሪያዎቹ ላይ ያስቀምጣቸዋል፡፡ ማጠንከር: ተክሎቹ የመጎሳቆል ምልክት የሚያሳዩ ከሆነ ዕርጥበቱን ከፍ አድርጎ ለማቆየት ብልቃጦቹ ሳይከፈቱ ከ3 – 7 ቀናት በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡ ተክሎቹ ያልተጎሳቆሉ ከሆኑ ግን ብልቃጦቹን ለአንድ ቀን ብቻ ሳይከፈቱ ማቆየት በቂ ነው፡፡ ከዚያም ጓንት በመጠቀም ከ2 – 4 ቀናት ውስጥ በትንሹ ግጣሙን በመክፈት ቀጥሎም በአምስተኛው ቀን ሙሉ በሙሉ በመክፈት ተክሎቹ ወደመጨረሻው ማጠንከሪያ ቦታ ይወሰዳሉ፡፡ ብልቃጦቹን በጥቂቱ መክፈት ቀስ በቀስ ዕርጥበቱ እንዲቀንስ በማድረግ ቅጠሎች ጠንካራ ገጽ እንዲያወጡና የውሃ ትነትን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ የመጨረሻው የማጠንከር ተግባር ተክሎቹን 10 ሳ.ሜ ቁመት ወዳለውና ኮምፖስት ወደ ተሞላ የላስቲክ ከረጢት ማዛወርና ለነባራዊው የከባቢ ሁኔታ ማጋለጥን ያካትታል፡፡ ይህ ደረጃ ተክሎቹን ለውሃ ትነት፣ ለንጥረ ነገር ብክነትና የስር ወይም ግንድ ጉዳት የሚያጋልጣቸው በመሆኑ በጣም ፈታኝ ደረጃ ነው፡፡ የመጨረሻው ማጠንከሪያ የሚከናወንበት ቦታ፡ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 52  የጸሃይ ብርሃን በሚገባ የሚደርሰው (ጣሪያውን ከዘንባባ ወይም ቀርከሃ ቅጠል መስራት ይቻላል) ፤  ዝናብና ከባድ ንፋስ የማይደርስበት፤  ከምንም አይነት የተባይና በሽታ ብክለት የጸዳ፤  ጥቅም ላይ የሚውሉት እንደ ኮምፖስትና አፈር የመሳሰሉት በሚገባ የታከሙበት፤  ከፍተኛ አንጻራዊ የአየር ዕርጥበት ተጠብቆ የሚቆይበት (በማጠንከሪያው ጣሪያ ላይ የፕላስቲክ ሸራ ማልበስ ይቻላል) መሆን ይኖርበታል፡፡ ተክሎቹን ለማጠንከሪያ የምንጠቀመው የኮምፖስት አፈር ከ1 እጅ የጫካ አፈርና ሁሉም ተህዋሲያንን ለመግደል በሙቀት ከታከመ 5 እጅ አሸዋማ አፈር (ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ግን መቀዝቀዝ ይኖርበታል) ሊዘጋጅ ይችላል፡፡ ተክሎቹን ወደፕላስቲክ ከረጢት በምናዛውርበት ግዜ እጃችንን በሚገባ ማከምና ጓንት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ተክሎቹን በብልቃጥ ውስጥ ለማሳደግ ጥቅም ላይ ውሎ የነበረው አጋር የተባለውን ምግብ የተክሉን ስሮች ደጋግሞ በውሃ በመንከር ማጠብ የሚቻል ሲሆን ቀጥሎም በታከመ ዉሃ ውስጥ በተበጠበጠ ቤንሌት በሚባለው ጸረ-ፈንገስ መድኃኒት ውስጥ ከ3-5 ደቂቃ በመንከር 2 ዕንቡጦችን ከአፈር በታች አድርጎ በፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ መትከል ይቻላል፡፡ ከስሩ በስተቀር ሌላው የተክሉ አካል በውሃ እንዳይረጥብ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የፕላስቲክ ከረጢቶቹ ከእንጨት በተሰራ ማስቀመጫ ተደርገው በፕላስቲክ ሸራ ከመሸፈናቸው በፊት ዕርጥበቱ እየጎለበተ እንዲሄድ ውሃ ይረጭባቸዋል፡፡ ከረጢቶቹ አለመቀደዳቸውንና የዕርጥበት እጥረት አለመከሰቱን በየቀኑ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ከተተከለ ከ3ኛው እስከ 8ተኛው ቀን ድረስ የፕላስቲክ ሸራው ቀስ በቀስ የሚገለጥ ሲሆን ውሃ መርጨቱ ግን ይቀጥላል፡፡ ተክሎቹ ፈጣን ዕድገት እንዲኖራቸው በቅጠል ላይ የሚረጩ ማዳበሪያዎች በደንብ ከጸደቁ በኋላ ይሰጣቸዋል፡፡ ዱርስባን የተባለው ጸረ-ተባይ መድኃኒት 10 ግራም በአንድ ሊትር ውሃ በሆነ መጠን ቆራጭ ተባዮችን፣ ክሽክሽንና ሌሎች ተባዮችን ለመቆጣጠር ይረጫል፡፡ ውሃ የሚሰጠው እንደነባራዊው የአየር ሁኔታ ሲሆን በቂ ዝናብ ካለ መስጠት ላያስፈልግ ይችላል፡፡ ተክሎቹ በጠቅላላው በመጨረሻው የማጠንከር ሂደት ለአንድ ወር ያክል ይቆያሉ፡፡ ማዛወር: ተክሎቹ ምንም አይነት የበሽታ፣ የተባይና የንጥረ-ነገር እጥረት ምልክት ካልታየባቸውና ከ4-6 አዲስ ቅጠል ካወጡ ወደ መስክ የማባዣ መደብ ሊዛወሩ ይችላሉ፡፡ የሚዛወሩበት መስክ ከማንኛውም የስኳር ድንች ማሳ ቢያንስ 100ሜ. የራቀ፣ ውሃ የሚያሰርግ አፈር ያለው፣ እንደ መከዳ ሳር ከመሳሰሉ አስቸጋሪ ከሆኑ አረሞች የጸዳና አስተማማኝ የሆነ የመስኖ ውሃ አቅርቦት ያለበት መሆን አለበት፡፡ ደካማ የአፈር ለምነት ባላቸው ቦታዎች የተክሎቹን ዕድገት ለማፍጠን ከተከላ በፊት የሚደረጉ ሰው ሰራሽ የማደበሪያዎች ውህድ (ኤን.ፒ.ኬ. 25፡5፡5) በአንድ ካሬ 100 ግራም መጠን ከአፈሩ ጋር በማደባለቅ መጠቀም ይመከራል፡፡ የበሽታ ምንጭ እንዳይሆን የተፈጥሮ ኮምፖስትን በዚህ ወቅት መጠቀምን መቀነስ ያስፈልጋል፡፡ በአንድ መደብ ላይ እስከ አምስት መስመሮች በ20 ሳ.ሜ ርቀት እና 10 ሳ.ሜ ርቀት በተክል መካከል ወይም በአጠቃላይ 300 ተክሎች መትከል ይቻላል፡፡ ብዙ ተክሎችን የምናዛውር ከሆነ ተግባሩን በፍጥነት ለማከናወን በቂ ጉልበት መኖሩን ማረጋገጥ ተክሎቹ በበሽታ እንዳይበከሉ ለማድረግ ያስችላል፡፡ የማዛወሩ ተግባር የሚከናወነው በደረቅ ወቅት ከሆነ ውሃ ጥዋትና ማታ ማጠጣት ያስፈልጋል፡፡ የታመሙ ተክሎች እንደታዩ ወዲያውኑ በመንቀስ ማስወገድ ይገባል፡፡ ከቲሹ-ከልቸር ላቦራቶሪ የወጡ ተክሎችን ስለማጠንከር ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከተፈለገ Namanda et al., 2013ን ማየት ይቻላል፡፡ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 53 አባሪ 5.2. መስራች ዘሮችን በመረብ ድንኳን ሳይበከሉ የማቆየት ዘዴ ዘር በማባዛትና ማሰራጨት ተግባር የተሰማሩ አካላት ዘራቸው በቫይረስ ወይም ሌላ ተባይ ያልተጠቃ መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አለበለዚያ ለሚገዟቸው አርሶ አደሮች የበሽታ ስርጭት ምንጭ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ ዘርን ያልተበከለና ንጹህ አድርጎ ለመጠበቅና የማባዣ ፍጥነትን ለመጨመር የመረብ ድንኳን ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ የመረብ ድንኳን ከግሪን ኃውስ ጋር የሚመሳሰል ሲሆን ከግሪን ሃውስ በተቃራኒው የሚሸፈነው በፕላስቲክ ሸራ ሳይሆን በቀጭን መረብ ነው፡፡ የመረብ ድንኳን ክሽክሽና ነጭ ዝንብ የመሳሰሉ ተባዮችን ወደውስጥ እንዳይገቡ በመከላከል ተክሎቹ በቫይረስ እንዳይበከሉ ያደርጋል፡፡ የምርምር ጣቢያዎች ትላልቅና ውድ የመረብ ቤት ቢጠቀሙም ለትናንሽ ዘር አባዢዎች ተስማሚ የሆኑ ትናንሽ የመረብ ድንኳኖችን መገንባት ይቻላል፡፡ ዘርን በንጽህና ለማምረት የሚጠቅም ቀለል ያለ የመረብ ድንኳን አሰራር መመሪያ በሳጥን ኤ5 ውስጥ ተገልጧል (ሙሉ ዝርዝሩን ደግሞ Schulte- Gelderman et al., 2012 ላይ ማግኘት ይቻላል)፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም በኬንያ አንድ የመረብ ድንኳን ለመገንባትና ለመጠገን 120 ዶላር የሚፈጅ የነበረ ሲሆን በድንኳኑ ውስጥ ከተባዙ ዘሮች የተገኘው የስር ምርት በሜዳ ከተባዙት እጅግ የላቀ ነበር፡፡ እንደ ዕድገት ሁኔታዎቹ የስኳር ድንች ሃረጎች በተተከሉ ወይም በተቆረጡ ከ80-100 ቀን ውስጥ ለመሰብሰብ ይደርሳሉ፡፡ ድንኳኑ በሚከፈትበት ጊዜ መረቡ እንዳይጎዳ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሃረጉ በሚሰበሰብበት ወቅት 3 ዕምቡጥ ያለውን የሃረጉን ጫፍ ወስዶ የተወሰነ ዕምቡጥ ያለውን ሃረግ ተመልሶ እንዲያቆጠቁጥ በድንኳኑ ውስጥ መተው ያስፈልጋል፡፡ ከእያንዳንዱ አጨዳ አስከትሎ የናይትሮጂን፣ ፎስፈረስና ፖታሲየም ማዳበሪያ የሚገኝ ከሆነ 17፡17፡17 በሆነ ቅይጥ/እጅ 1 የሻይ ኩባያ (200 ግ) ለአንድ ድንኳን በመስመር መካከል በማድረግ በአፈር መሸፈን ተክሎቹ በፍጥነት እንዲያቆጠቁጡ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ከአጨዳ በኋላ ድንኳኑ ከመዘጋቱ በፊት ክሽክሽንና ነጭ ዝንብን ለመከላከል ጸረ-ተባይ መድኃኒት መረጨት ይኖርበታል፡፡ ለዚህ ተግባር ፓይተሮይድ ዱዱትሪን (1.75EC) የተባለውን ጸረ-ተባይ መድኃኒት 10ግ በ20 ሊትር ውሃ በጥብጦ በሚታዘል ወይም በእጅ መርጫ መርጨት ይቻላል፡፡ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 54 ሳጥን ኤ5. ዘርን ከበሽታ ለመከላከል የመረብ ድንኳን መስራት ቁመት: 1.2 እስከ 1.6 ሜ. ርዝመት: እስከ 3ሜ. ስፋት: በሁሉም በኩል 1.8 ሜ. የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች : መረብ፡ ለአንድ ድንኳን = 4ሜ. x 3.20ሜ ለጣራና ለረዥም ጎኖቹ፤ 2ሜ x 1.7ሜ ለፊት ለፊት፤ 2ሜ x 1.7ሜ ለኋላ ወይም OPTINET 50 Mesh ከሚባለውና 4ሜ በ 100ሜ መጠን ካለው አንድ ጥቅል 20 ድንኳኖችን መስራት ይቻላል ለመዋቅር የሚሆኑ የእንጨት ምሶሶዎች፡ እያንዳንዳቸው 3.6ሜ. ርዝመትና 4ሳ.ሜ ውፍረት ያላቸው 30 ተለማጭ የእንጨት ጨፈቃዎች ማሰሪያ ሽቦ፡ 5 ሜ. ርዝመት ያለው፤ የቃጫ ገመድም መጠቀም የሚቻል ቢሆንም በየአጨዳው ወቅት መተካት ይኖርበታል የቦታ ምርጫ፡ ቦታው ውሃ የሚያጠፍ፣ ለማዘጋጀት ጠንካራ ያልሆነ፣ ለም አፈር ያለበትና የመስኖ ውሃ በቋሚነት ሊያገኝ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡ የአፈሩ ለምነት ደካማ ከሆነ 1 ጋሪ የበሰበሰ ፍግ ለ1 ካሬ ሜትር መጨመር ይቻላል፡፡ አሮጌ የስኳር ድንች ማሳዎች የበሽታና ተባይ ምንጭ ሊሆኑ ስለሚችሉ ከድንኳን መስሪያ ቦታው ማራቅ አስፈላጊ ሲሆን በድንኳኑ ዙሪያ ያሉ አረሞችንም በየጊዜው ማረም አስፈላጊ ነው፡፡ የአሰራር ደረጃዎች: 1. በመካከላቸው ያለው ርቀት 1.8ሜ. ሆኖ 3ሜ. ርዝመት ያላቸው ሁለት ትይዩ መስመሮችን በመሬቱ ላይ ምልክት ማድረግ፤ 2. ተለማጭ ጨፈቃዎቹን በግማሽ ጨረቃ ቅርጽ በማጠፍ ምልክት በተደረጉት ትይዩ መስመሮች ላይ በ 20 ሳ.ሜ ጥልቀት ወደመሬት ውስጥ መቅበር፡፡ በጨፈቃዎቹ መካከል ያለው ርቀት 50 ሳ.ሜ ነው፤ 3. ርዝመቱ 1.7ሜ. የሆነ የእንጨት ምሶሶ በድንኳኑ ፊትና ኋላ በመቅበር ማቆም፤ የድንኳኑን ጥንካሬ ለመጨመር በታጠፉት ጨፈቃዎች ላይ አሸጋግሮ ርዝመቱ 3ሜ. የሆነ እንጨት በማኖር በሽቦ ወይም ቃጫ ገመድ ማሰር፤ 4. ርዝመታቸው 3ሜ የሆነ 4 ተጨማሪ እንጨቶች ሁለቱን በአንድ ጎን በማጋደም ከተለማጭ ጨፈቃዎቹ ጋር በሽቦ ወይም በቃጫ ገመድ ማሰር፤ 5. ከቫይረስ ነጻ የሆኑ 3 ዕምቡጥ ያላቸው ቁርጥራጮችን ሁለቱን ዕምቡጦች አፈር ውስጥ በመቅበር መትከል፤ የተከላ ርቀቱ በ80 ቀናት ሀረጉን ለማጨድ ከተፈለገ 10 ሳ.ሜ በ15 ሳ.ሜ (360 ተክሎች በአንድ ድንኳን) ሲሆን ቶሎ ቶሎ ማጨድ ካልተፈለገ ደግሞ 10ሳ.ሜ በ20 ሳ.ሜ (270 ተክሎች በአንድ ድንኳን) ይሆናል፡፡ በእያንዳንዱ ድንኳን ላይ የዝርያውን ስምና የተከላ ቀን መለያ ይደረግበታል፤ 6. መረቡን በድንኳኑ መዋቅር ላይ በማልበስ በሽቦ ማሰር፤ በድንኳኑ ግራና ቀኝ እንዲሁም ፊትና ኋላ 20 ሳ.ሜ እላፊ መተው፤ 7. ለድንኳኑ ፊትና ኋላ መድፈኛ የተዘጋጁትን የመረብ ቁራጮች ከመዋቅሩ አናትና ከጨፈቃዎቹ ጋር በጥንቃቄ ማሰር፤ ድንኳኑ ንፋስ እንዲቋቋም ለማድረግ መረቡ መሬት በሚነካበት እያንዳንዱ ጎን እላፊ የተተወው መረብ ላይ እንጨት በማጋደም በ20 ሳ.ሜ ጥልቀት አፈር ውስጥ መቅበር፤ 8. ዝናብ በበቂ መጠን እየዘነበ ካልሆነ በስተቀር ተክሎቹ በቀን ሁለት ግዜ (ጥዋትና ማታ) በድንኳኑ አናት በኩል በአትክልት ውሃ ማጠጫ ውሃ እንዲያገኙ ይደረጋል፤ መረቡ መገለጥ የሚኖርበት በአጨዳ ወቅት ብቻ ሲሆን መልሶ ከመልበሱ በፊትም ጸረ-ተባይ መድኃኒት መርጨት ባልታጨዱት ሃረጎች ላይ ያረፉ ክሽክሽና ነጭ ዝንብን ለመቆጣጠር ይረዳል፤ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 55 አባሪ 6. የአፈር አይነትን ማወቅ ሰንጠረዥ 6ሀ.1 ዋና ዋና አፈር አይነቶች ፣ ጠባያቸውና አይነታቸውን ለመለየት የሚደረግ የመስክ ጥናት የአፈር አይነት ጠባይ የመስክ ጥናት ማሻሻያ ዘዴዎች እንደ የሰብል ቅሪት፣ ብስባሽና ፍግ በትንሹ ወይም ፈጽሞ አይያያዝም፣ የመሳሰሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ በጥንቃቄ ከተጠቀለለ የተደላደለ ኳስ ሊሰራ ይችላል፣ አሸዋማ ማዳበሪያዎችን በቋሚነት እንደ ቋሊማ ሊጠቀለል አይችልም፣ መጨመር፣ የሸክላ ይዘቱ ከ10 በመቶ ያነሰ ነው፣ አረንጓዴ ብስባሾችን መጠቀም፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ያለምንም ችግር የተደላደለ ኳስ ይሰራል፣ ማዳበሪያዎችን በቋሚነት በጥንቃቄ ከተጠቀለለ ወፍራም ቋሊማ ሊሰራ ይችላል፡፡ አሸዋማ ለም መጨመር፣ ቋሊማው በትንሽ ግፊት ይሰበራል፣ አረንጓዴ ብስባሾችን መጠቀም፣ የሸክላ ይዘቱ ከ10 እስከ 20 በመቶ ይሆናል፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መጨመር ጠቀሜታው ትንሽ ነው፣ ወደ ተደላደለ ቋሊማ ሊጠቀለል ይችላል፣ አሸዋማ -ሸክላማ - የትኛውን ሰው ሰራሽ የማዳበሪያ በ"ሀ" ቅርጽ በሚታጠፍበት ግዜ መሃሉ ላይ ይሰበራል፣ ለም ፕሮግራም መጠቀም የሸክላ ይዘቱ ከ20 እስከ 35 በመቶ ይሆናል፣ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን የአፈር ትንተና ውጤት ያስፈልጋል፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መጨመር የተደላደለ ቋሊማ ይሰራል፣ ጠቀሜታው ትንሽ ነው፣ የትኛውን ሰው ሰራሽ የማዳበሪያ ሸክላማ ለም በጥንቃቄ ከተያዘ የተደላደለ "ሀ ቅርጽ ይሰራል፣ ፕሮግራም መጠቀም የሸክላ ይዘቱ ከ27 እስከ 40 በመቶ ይሆናል፣ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን የአፈር ትንተና ውጤት ያስፈልጋል፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መጨመር የሸክላ አፈር አጠቃላይ ጠባያትን ይይዛል፣ ቋሊማው ወደ ክብ ቅርጽ ሊሰራ ሲሞከር ይሰበራል፣ አሸዋማ ሸክላ ጠንከር ተደረጎ ጫን ሲደረግ ወይም በመዳፍና በጣት ሲታሽ ያጣብቃል፣ የሸክላ ይዘቱ ከ35 እስከ 55 በመቶ ይሆናል፣ ቋሊማው የተደላደለ ክብ ሳይሰበር ይሰራል፣ እንደ ብስባሽ ያሉ የተፈጥሮ አያጣብቅም፣. ማዳበሪያና ጂፕሰም መጨመር እንደፕላስቲክ ወጥነት አለው፣ ሸክላ ጥሩ የሆነ ውሃ የመያዝ ችሎታ፣ አንዳንድ ሸክላማ አፈሮች ሲደርቁ በጣም ጠንካራና ለመጠቅለል አስቸጋሪ ናቸው፣ የሸክላ ይዘቱ ከ55 በመቶ በላይ ይሆናል፣ ደካማ ቅርጽ ግን ጥሩ ለምነት፣ ለስለስ ያለ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለስላሳ ደቃቅና በትንሹ የሚያጣብቅ፣ መጨመር፣ ደለል በአጠቃላይ የሸክላ አፈር ጠባይ ያለው፣ አረንጓዴ ብስባሾችን መጠቀም፣ የሸክላ ይዘቱ ከ80 በመቶ በላይ ይሆናል፣ ምንጭ: Faber et al., 2010 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 56 አባሪ 11. የሥርዓተ-ጾታ የሁኔታዎች ትንተና ቢጋር አባሪ 11ሀ. ለቡድን ቃለ-መጠይቆች የሥርዓተ-ጾታ የሁኔታዎች ትንተና ቢጋር የተለያዩ የስኳር ድንች አምራች አርሶአደሮችን ሊወክሉ የሚችሉ ቡድኖች የሚታደሙበት ስብሰባ ማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡ ፍሊፕ ቻርት ከነመቆሚያው እና ማርከሮች የመልመጃው ዓላማ፡ የመልመጃው ዋና ዓላማ ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን የተሻለ ስኳር ድንች ምርት እንዲያመርቱ በመርዳት በምግብ ወይም በገቢ ወይም ደግሞ በሁለቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም ከስብሰባው ማወቅ የተፈለገው ወንዶችና ሴቶች እንዴት በስኳር ድንች ሰብል ምርት ላይ አንደሚሳተፉ፣ እንዴት የአመራረት ተግባራቶቻቸው ሊመሳሰሉ ወይም ሊለያዩ እንደሚችሉ እና በአመራረት ላይ የሚገጥሟቸው ችግሮች ተመሳሳይ ወይም የተለያዩ እንደሆኑ ለማወቅ እንደሆነ ለተሳታፊዎቹ ማብራራት፡፡ የሚከተሉትን መረጃዎች መመዝገብ፡ ቦታ 1. ቀን 2. የመንደሩ ስም፣ ወረዳ፣ ዞን ወዘተ. 3.የመምረጫ መስፈርት 4. በቦታው የሚገኝ ዋና ነገድ 5. በአብላጫ የሚገኘው ኃይማኖት 6. ሌሎች ምልከታዎች (ምሳሌ፡ በአቅራቢያው በአርሶ አደር ማሳ ላይ የተካሄደ የብርቱካንማ ስኳር ድንች የመስክ ሙከራ) ቡድን 7. የተገኘ የአርሶ አደር ብዛት፤ ወንድ/ሴት 8. የትኛው ባለስልጣን ወይም እንግዳ ተገኘ 9. የውይይቱ ቦታ 10. በአርሶአደሮች ምርጫ ወቅት የታየ ማዳላት (ምሳሌ፡ በአብዛኛው ሃብታም፣ ለንግድ የሚያመርቱ አርሶአደሮች፣ የተወከሉ የኃይማኖት ቡድኖች ወዘተ.) አጠቃላይ የቃል ውይይት 1. በአካባቢው ለምግብና ለገበያ የሚመረቱ ዋና ዋና ሰብሎች እነማን ናቸው? ማንኛውም ሰብል የሚመረተው በዋነኝነት ለገበያ ነው? ሰብሉ በባሎችና ሚስቶች እንዴት ነው የሚመረተው? በቤተስብ መሬት ላይ ነው? ለራሳቸው በተለየ መሬት ላይ ነው? በባሎች መሬት ላይ ነው? በሚስቶች መሬት ላይ ነው? ጉልበት የሚያቀርበው ማነው? ሰብል በአብዛኛው ለገበያ የሚመረቱ ሰብሎች መሬት ያለው ማነው ጉልበት የሚያቀርበው ማነው መሬት ዝግጅት ወንዶች መስመር/ቦይ ማውጣት ሴቶች ተከላ ሁለቱም አረም ምርት መሰብሰብ ማጓጓዝ መሸጥ ወንዶች፣ ሴቶች፣ ወንድ ልጆች፣ ሴት ልጆች፣ ተቀጣሪ ወንድ ልጆች፣ ተቀጣሪ ሴት ልጆች ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 57 2. የአካባቢው ዋና ምግብ/ቦች ማነው/እነማናቸው? ስኳር ድንች 3. በአካባቢው ስኳር ድንች እንዴት ነው የሚበላው? ስኳር ድንች እንዴት ነው የሚቀነባበረው? የስኳር ድንች ቅጠል ለምን ተግባር ይውላል? 4. ምን ያክል ቤተሰቦች ስኳር ድንችን ያመርታሉ (10 ጠጠሮችን በመጠቀም የመቶኛ መጠን እንዲያወጡ ማድረግ ይቻላል)? 5. የስኳር ድንች ማሳቸውን ራሳቸው ከሚንከባከቡ የስኳር ድንች አርሶአደሮች መካከል ምንያክሉ ወንዶች ምንያክሉ ደግሞ ሴቶች ናቸው (ማሳሰቢያ: ለቤት ፍጆታም ሆነ ለገበያ የሚያመርቱት መካተት ይኖርባቸዋል፤ 10 ጠጠሮችን በመጠቀም የመቶኛ መጠን እንዲያወጡ ማድረግ ይቻላል) ወንዶች: ሴቶች: ጠቅላላ=10 6. ባሎችና ሚስቶች ስኳር ድንችን በአካባቢው እንዴት ያመርታሉ? ሀ. ለየብቻ፤ ባሎችም ሆኑ ሚስቶች በራሳቸው መሬት ላይ ለ. ሚስቶች ብቻ የራሳቸው የስኳር ድንች ማሳ አላቸው ሐ. ባሎች ብቻ የራሳቸው የስኳር ድንች ማሳ አላቸው መ. የሚያመርቱት በቤተሰብ ማሳ ላይ ነው 7. የስኳር ድንች አምራች አርሶአደሮች ቁጥር ለውጥ አሳይቷል: ከ10 አመት በፊት? ከ20 አመት በፊት? የቁጥር ለውጥ ከታየ፤ ለውጡ እንዴትና ለምን ሆነ? የትኛው ጾታ ነው የቁጥር ለውጥ ያሳየው ወንድ ወይስ ሴት ወይስ ሁለቱም? 8. አርሶአደሮች ለስኳር ድንች ያላቸው ማሳ አንድ ብቻ ነው ወይስ ብዙ? 9. ከ10 ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲወዳደር አሁን ያለው የስኳር ድንች ማሳ መጠን ልዩነት አለው? እንዴትና ለምን? 10. ስኳር ድንችን ለማምረት መሬት የሚከራይ አርሶአደር አለ? ለምንድነው መሬቱን የሚከራዩት? መሬት የሚከራዩት ወንዶች ናቸው ወይስ ሴቶች? 11. አርሶአደሮች ስኳር ድንችን እንዴት ነው የሚተክሉት፤ በጉብታ፣ በመደብ/ቦይ፣ ለጥ ባለ መሬት ላይ? 12. በአመት ስንት ጊዜ ስኳር ድንችን ያመርታሉ? ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 58 አባሪ 11ለ. ለወንድና ሴት የመሬት ባለቤቶች ቡድን የተዘጋጀ ቢጋር (ወንዶችና ሴቶች የተለያየ የስኳር ድንች ማሳ ያላቸው እንደሆነ) የሴቶች ቡድን 1. ለስኳር ድንች መትከያ የሚሆን መሬት ሴቶች ለማግኘት ይቸገራሉ? ለሌሎች ሰብሎችስ? 2. በአካባቢው ሴቶች በአብዛኛው ምን ያክል የስኳር ድንች ማሳ አላቸው? የሚቻል ከሆነ በአማካይ በስኳር ድንች የሚሸፍኑትን የማሳ መጠን ማግኘት (በአካባቢው በተለመደ የመለኪያ ዘዴ ወስዶ ወደ ሄክታር መቀየር)? 3. ሴቶች ስኳር ድንችን ከሌሎች ሰብሎች ጋር አሰባጥረው ይተክላሉ? የሚሰባጠሩት ሰብሎች እነማን ናቸው? 4. በአጠቃላይ ግምገማ በወንዶች እንክብካቤ የሚደረግለት ማሳ በሴቶች ከተያዘው የተለየ ነው? ለምን እና እንዴት ሊለይ ቻለ? 5. ለሴቶች የገቢ ድጎማ የሚያደርጉ ጠቃሚ ሰብሎችን በቅደም ተከተል ማስቀመጥ (ከገቢ መጠን፣ ገቢው ከሚገኝበት ጊዜ ወዘተ. አንጻር በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ ምክንያቶቹን መግለጽ) 6. የስኳር ድንች የእርሻ ተግባር ቀን መቁጠሪያ በወርና በጾታ (በሴቶች እንክብካቤ ለሚደረግለት ማሳ) (ከታች በተዘረዘሩት ተግባራት በሙሉ አርሶአደሮቹ መስማማታቸውን በቅድሚያ ማረጋገጥ ያስፈልጋል) ወር ማነው የሚተገብረው? ወንዶች፣ ሴቶች፣ወንድ ሌሎች ተግባራት/ በወቅቱ ጥ የ መ ሚ ግ ሰ ሐ ነ መስ ጥቅ ሕ ታ ልጆች፣ ሴት ልጆች፣ የሴቶችን ጉልበት የሚሻሙ ተቀጣሪ ወንድ ልጆች፣ ሌሎች ሰብሎች እነማናቸው? ተግባራት ተቀጣሪ ሴት ልጆች መሬት ዝግጅት የማሳ ጽዳት ጉብታ/መደብ/ቦይ መስራት ዘር ማግኘት ዘር ማጓጓዝ ተከላ አረም ማዳበሪያ መጨመር ምርት መሰብሰብ ምርት ወደ ገበያ ማጓጓዝ መሸጥ ማቀነባበር 7. አብዛኞቹ ሴቶች ስኳር ድንችን የት ነው የሚሸጡት (ወደ መንደራቸው ለሚመጡ ነጋዴዎች፣ ለአካባቢ ገበያ፣ በቅርብ ላለ ገበያ፤በመጠናቸው ደረጃ ማውጣት)? በቅርብ ላለ ገበያ የሚሸጡ ከሆነ ማን በምንድነው የሚያጓጉዘው? 8. በአካባቢ ገበያ ስኳር ድንችን በአብዛኛው የሚሸጠው ማነው፤ ወንዶች፣ ሴቶች ወይስ ሁለቱም? ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 59 9. የሰኳር ድንች ዝርያዎችና ተመራጭ ጠባያቸው (ዝ) 9. 1ለ0አ.መቻቹ: 11. 1የ2ስ.ኳር ድንች ጠባያት ምሳሌዎች: 1የ3ስ.ርና ቅጠል ጣዕም 14. 1የ5ደ.ራቆት መጠን (ጠንካራ/ውሃማ) 16. 1የ7መ. ብሰያ ጊዜ 18. 1የ9ስ.ር ስጋ ቀለም 20. 21.  የስር ምርት ብዛትና መጠን  የመድረሻ ጊዜ  የሃረግ ምርት  የምርት አሰባሰብ አይነት (ትንሽ በትንሽ፣ሁሉንም በአንድ ጊዜ)  አከማችቶ በማቆየት ዙሪያ ያላቸው ጠባይ  በሽታና ተባይ የመቋቋም ችሎታ  ድርቅ የመቋቋም ችሎታ  ለገበያ ተፈላጊነት  የግብዓት መጠን/የማምረቻ ወጪ  የጉልበት ፍላጎት ዝ1. በአካባቢው/በመንደሩ አርሶአደሮች ምን ዓይነት የስኳር ድንች ዝርያ ነው የሚያመርቱት? ለእያንዳንዱ ዝርያ ከዚህ በታች ለተጠቀሱ ጉዳዮች ዝርዝሮችን ማግኘት:  የስር ስጋ ቀለም  የምርት ዓላማ (ለምግብ፣ ለእንስሳት መኖ፣ ለገበያ?)  የእያንዳንዱ ዝርያ ጥሩ ጎን ምንድነው? መጥፎ ጎንስ?  ዝርያው እንዴት ነው ጥቅም ላይ የሚውለው(ምሳሌ፡ ተቀቅሎ፣ ተጠብሶ፣ዱቄት ሆኖ ወዘተ) ዝ2. ለዝርያዎቹ እንደቅቡልነታቸው ደረጃ ማውጣትና ምክንያቱን መግለጽ (አርሶአደሮቹ ከአራት በላይ ዝርያዎችን ከመረጡ ደረጃ ለማውጣት ወደ 4 ዝቅ እንዲያደርጓቸው መጠየቅ) ዝርያ 1 ዝርያ 2 ዝርያ 3 የስር ስጋ ቀለም የምርት ዓላማ የዝርያው የሚወደዱ ጠባያት የዝርያው የሚጠሉ ጠባያት ዋና ጥቅሙ በአጠቃላይ ለተቀባይነታቸው ደረጃ መስጠት ዝ3. ሴቶች በአማካይ ምን ያክል የስኳር ድንች ዝርያዎችን ያመርታሉ? የተለያዩ ዝርያዎችን በአንድ ማሳ/ጉብታ/መስመር ይተክላሉ? ከሆነ ለምን? ዝ4. አርሶአደሮች ሊያመርቷቸው የማይፈልጓቸው የስኳር ድንች ዝርያዎች አሉ? የእነዚህ ዝርያዎች ስም ማነው? ለምንድነው ሊያመርቷቸው የማይፈልጉት? ዝ5. ብርቱካንማ ስኳር ድንች አይታችሁ/አምርታችሁ ታውቃላችሁ? ዝ6. ብርቱካንማ ስኳር ድንች የሚያመርቱ ከሆነ ማነው የሚያመርተው፤ወንዶች፣ ሴቶች ወይስ ሁለቱም? (የማያመርተው ወገን ለምን እንደማያመርት ማወቅ) ዝ7. አርሶአደሮች የብርቱካንማ ስኳር ድንች ስሮችን ምን ያደርጉታል: ይመገባሉ፣ ይሸጣሉ፣ ሁለቱም፣ ያቀነባብራሉ? ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 60 ሴቶች የግብርና ቴክኖሎጂዎች መረጃ ለማግኘት ማንን እንደምንጭነት ይጠቀማሉ? የዘር ሥርዓት (ዘስ) ለአመቻቹ: የስኳር ድንች ሃረግ ዋና ምንጮች:  የራስ እርሻ  በመንደሩ ካሉ ሌሎች አርሶአደሮች በስጦታ  በሌላ መንደር ከሚኖሩ አርሶአደሮች በስጦታ  በመንደሩ ካሉ አርሶአደሮች በግዢ  በሌላ መንደር ከሚኖሩ አርሶአደሮች በግዢ  ከምርምር ወይም ከግብርና ቢሮዎች  መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ፕሮጀክቶች በማሳ ላይ ሃረግ የማባዛት ዘዴዎች: ዝናብ በሚጀምርበት ወቅት እንዲያቆጠቁጥ የተወሰኑ ስሮችን በማሳ ውስጥ መተው የተወሰኑ ሃረጎችን ውሃ ባለበት ወይም በመኖሪያ ቤት አካባቢ መትከል የማሳውን የተወሰነ ክፍል ምርት ሳይሰበሰብ ማቆየት ዘስ1. በአብዛኞቹ አመታት ሴቶች ለተከላ የሚሆኑ ሃረጎችን ከየት ያገኛሉ? የትኛው ዘር ማግኛ ምንጭ በጣም ጠቃሚ ነው (በተደጋጋሚ ከመጠቀም አንጻር)፣ ብዙ የማይጠቅመውስ? ከጠቀሜታ አንጻር ደረጃ መስጠት፤ ዘስ2. አብዛኛው አርሶአደር የስኳር ድንች ዘር ያላገኘበት ሁኔታ ተከስቶ ያውቃል? ሁኔታውን የፈጠረው ነገር ምን ነበር? ይህ ሁኔታ በሚከሰትበት ወቅት አርሶአደሮች ዘር ከየት ያገኛሉ? ዘስ3. አርሶአደሮች ከራሳቸው ማሳ የስኳር ድንች ዘር ለማግኘት የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ በአካባቢው የትኞቹን ዘዴዎች ነው የሚጠቀሙት? ዘስ4.:አርሶአደሮች ከሌሎች አርሶአደሮች ዘር እንዴት ያገኛሉ፡ በግዢ፣ በስጦታ፣ በብድር? ዘስ5. በአካባቢው የዘር ዋጋ ስንት ነው? (የሽያጭ መጠኑን መገንዘብ)? ዘስ6. ከሌሎች አርሶአደሮች ዘር በስጦታና በብድር የሚያገኙ ከሆነ ብዙ ጊዜ ከማን ነው የሚያገኙት? ከሴቶች፣ ከወንዶች፣ ከሁለቱም? ከአንዱ ብቻ ከሆነ ለምን? ዘስ7. ጥራት ያለው የስኳር ድንች ዘር በመያዝ የታወቁ ወይም እያባዙ ለሌሎች የሚያሰራጩ አርሶአደሮች በአካባቢው አሉ? ካሉ ወንዶች ናቸው ሴቶች? ከእነዚህ ውስጥ ምን ያክሎቹን ታውቃላችሁ? የምርት ማነቆዎች (ምማ) ምማ1. ሰብሉን በማምረት ሂደት ሴቶች የሚገጥሟቸው ዋና ዋና ችግሮች ምንድናቸው? ከጠቀሜታቸው አንጻር በደረጃ ማስቀመጥ የውሳኔ አሰጣጥ (ውአ) ውአ1. የአገባች ሴት ከምትንከባከበው ማሳ ላይ በተሰበሰበ ስኳር ድንች ምን መደረግ እንዳለበት የሚወስነው ማነው? ውአ2. የአገቡ ሴቶች ስኳር ድንች በሚሸጡባቸው አካባቢዎች ገንዘቡን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው የሚወሰነው ማነው? ውአ3. ብዙ ጊዜ የአገቡ ሴቶች ከሚያመርቱት ስኳር ድንች ምንያክሉ ለምግብነት እና ለሽያጭ ይውላል? ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 61 ውአ4. ብዙ ጊዜ የአገቡ ወንዶች ከሚያመርቱት ስኳር ድንች ምንያክሉ ለምግብነት እና ለሽያጭ ይውላል? (በወንዶችና በሴቶች መካከል ያለው የመጠን ልዩነት ከፍተኛ ከሆነ ለምን ብሎ መጠየቅ) የቤተሰብ የምግብ ፍጆታ (ምፍ) ምፍ1. በአንዳንድ አካባቢዎች ቤተሰባቸው በሚገባ መመገቡን የማረጋገጥ ኃላፊነት የሴቶች ብቻ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ በዚህ አካባቢ የማህበረሰቡ አስተሳሰብ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይመስላል? ወንዶች ቤተሰባቸው ምን መመገብ እንዳለበት በመወሰን ረገድ ምን ሚና ይጫወታሉ? ምፍ2. በአጠቃላይ በአካባቢው በቤት ውስጥ ለቤተሰቡ በማምረትም ይሁን በግዢ ምግብ የማቅረብ ኃላፊነት የማነው? ምግብ ባል ከማሳ ባል ሚስት ከማሳ ሚስት በራሷ ሁለቱም ከማሳ ሁለቱም በራሳቸው የሚያቀርበው የሚገዛው የምታቀርበው ገንዘብ የሚያቀርቡት ገንዘብ የሚገዙት የምትገዛው ዋና ሰብል (ካሳቫ፣ በቆሎ፣ ሩዝ ወዘተ.) የእንስሳት ፕሮቲን (ስጋ፣ አሳ) የምግብ ዘይትl ምፍ3. በአካባቢው በብዙ ቤተሰቦች በየቀኑ የሚሰራውን የምግብ ዓይነት የሚወስነው ማነው? ምፍ4. ሕጻናት እንዴት መመገብ እንዳለባቸው በመወሰን ረገድ ወንዶች ሚና አላቸው? ከሆነስ ምን አይነት ሚና ይጫወታሉ? ምፍ5. ከወላጆች ባሻገር ሕጻናት እንዴትና ምን መመገብ እንዳለባቸው ምክር የሚሰጥ አለ (ጤና ጣቢያ፣አያቶች ወዘተ.)? ምፍ6.በአካባቢው እናቶች ስኳር ድንችን ለሕጻናት ይመግባሉ? ሕጻናቱ በስንት አመት ዕድሜያቸው ስኳር ድንችን መመገብ ይጀምራሉ? እስከ 5 ዓመት ያሉ ሕጻናት ስኳር ድንችን በምን መልክ ነው የሚመገቡት? ስኳር ድንችን ማቀነባበር 1. በቡድኑ ውስጥ ስንት ሰዎች ስኳር ድንችን ለቤት ፍጆታ ወይም ለገበያ ያቀናብራሉ? 2. በአካባቢው ሴቶች የትኛውን የተቀነባበረ ምርት ከስኳር ድንች ይሰራሉ? (ለቤት ፍጆታ (ምሳሌ ዱቄት) እና ለገበያ (ምሳሌ ጁስ፣ ቂጣ፣ ኬክ ወዘተ) በማለት መለየት) 3. ወንዶች ስኳር ድንችን ያቀነባብራሉ? ከሆነስ ምን አይነት ምርቶችን ያመርታሉ? 4. በአካባቢው ሴቶች የስኳር ድንች ምርቶችን የት ይሸጣሉ (ከቤት፣ መንገድ ዳር፣ገበያ ወዘተ.)? የስኳር ድንች የተቀነባበሩ ምርቶችን ማነው የሚሸጠው (ሴቶች፣ ወንዶች፣ ልጆች)? 5. የስኳር ድንች የተቀነባበሩ ምርቶችን ማነው የሚገዛው (ሁሉም ሰው፣ ተማሪዎች፣ የጉልበት ሰራተኞች ወዘተ.)? 6. ስኳር ድንችን የማያመርቱ ግን የሚያቀነባብሩ አንዳንድ ሴቶች አሉ? ስሩን ከየት ያገኛሉ? ሁሉም ሴቶች ስር ከባሎቻቸው ያገኛሉ? ስሩን ከባሎቻቸው እንዴት ነው የሚያገኙት (በግዢ፣ በለውጥ ወዘተ.) ማሳሰቢያ፡ ቢጋሩ ለወንዶች በሚያመች ሁኔታ ተሻሽሎ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 62 አባሪ 12. የስኳር ድንች መሰረታዊ መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 63 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 64 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 65 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 66 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 67 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 68 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 69 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 70 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 71 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 72 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 73 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 74 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 75 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 76 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 77 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 78 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 79 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 80 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 81 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 82 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 83 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 84 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 85 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 86 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 87 ርዕስ 14 - ግብረ-መልስና አባሪዎች - 88