ግብርና ሚኒስቴር፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የበጎችን እና የፍየሎችን ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር ማስፋፋት የተጠቃሚዎች መመሪያ አስመላሽ በርሄ - የቀይ ሥጋ ዳይሬክተር፣ ግብርና ሚኒስቴር ዳኜ ሙሉነህ - ባለሙያ፣ የእንስሳት ልማት ተቋም ቀጀላ ተሰማ - ባለሙያ፣ ኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ሙላቱ ዳኘው - ባለሙያ፣ አማራ ግብርና ቢሮ ገረመው ሀ/ጊዮርጊስ - ባለሙያ፣ ሲዳማ ግብርና ቢሮ አመልማል ዓለማየሁ - ተመራማሪ፣ ሀዋሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ሻንበል በሱፍቃድ - ብሄራዊ የበግ ምርምር አስተባባሪ፣ ደብረ ብር ሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ዓይናለም ኃይሌ - ዋና ሳይንቲስት፣ ICARDA ብርሃኑ በላይ - ተመራማሪ፣ ICARDA ተስፋዬ ጌታቸው - ተመራማሪ፣ ICARDA አዘጋጆች ስም የሥራ ድርሻና የሚሠሩበት ተቋም የበጎችን እና የፍየሎችን ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር ለማስፋፋት የተዘጋጀ የተጠቃሚዎች መመሪያ ሰኔ 2017, አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ i 2 3 4 5 6 7 8 9 10 1 ©2017 ግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊት ዲሞክራሲያዊት ሪፓብሊክ የሽፋን ገጽ 1.ከላይ - የተሻሻለች የቦንጊቾ እናት በግ ከሦስት ግልገሎቿ ጋር፣ በአላሪጌታ የቦንጋ ማዓዝማ ቦታ (ጣቢያ) (ፎቶ፡ በICARDA/ተስፋዬ ጌታቸው) 2.ከታች በግራ: የርቢ ፍየል ከመንታ ልጆቿ ጋር፣ በቀያፈር የLowland Livelihood Resilience Project ማህበረሰብ-ዓቀፍ የማራቢያ ቦታ አቅራቢያ። (ፎቶ፡ በICARDA/ተስፋዬ ጌታቸው) 3.ከታች በቀኝ እና የኋላ ሽፋን፡ ወ/ሮ አየለች አላቶ፣ በቦንጋ፣ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የ10ኛው ዓመት የማዓዝማ (CBBP) ውድድር ላይ በአንደኛ ደረጃ ተሸላሚ የሆኑ አርሶ አደር። (ፎቶ፡ በILRI/አፖሎ ሃብታሙ). የውስጥ ገጾች፦ 1.ገጽ 1: በጎች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ የአካባቢ ገበያ (ፎቶ፡ ICARDA). 2.ገጽ 2: የአዋሲ እና የዎሎ ድቅል የበግ መንጋዎች፣ በጭሮ፣ ወሎ፣ ማኅበረሰብ ዓቀፍ የማዳቀያ መንደር በተደረገ የማኅበረሰብ ልዩ ዝግጅት ላይ (ፎቶ፡ በICARDA/ተስፋዬ ጌታቸው). 3.ገጽ 3: የአበርጌሌ ፍየሎች በብላቋዋ፣ ዝቋላ፣ ማኅበረሰብ ዓቀፍ የማዳቀያ መንደር። (ፎቶ፡ ታደሰ ምስጋናው/አማራ ክልል የምርምር ተቋም) 4.ገጽ 4: የማዓዝማ ትግበራ አጋሮች በቦንጋ፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የማዓዝማ ዎርኮሾፕ ላይ። (ፎቶ፡ ILRI/አፖሎ ሃብታሙ). 5.ገጽ 15: በቦንጋ፣ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የ10ኛው ዓመት የማዓዝማ (CBBP) ውድድር ላይ ተሸላሚ የሆኑ አርሶ አደር፣ ከተሻሻለ የቦንጋ አውራ በጋቸው ጋር። (ፎቶ፡ ILRI/አፖሎ ሃብታሙ). 6.ገጽ 21: በብላቋዋ፣ ዝቋላ፣ ማኅበረሰብ ዓቀፍ የማዳቀያ መንደር አንድ አርሶ አደር ከተሻሻለ የርቢ አውራው ጋር (Photo credit: ታደሰ ምስጋናው/አማራ ክልል የምርምር ተቋም) 7.ገጽ 22: በብላቋዋ፣ ዝቋላ፣ ማኅበረሰብ ዓቀፍ የማዳቀያ መንደር፣ የአበርጌሌ የተሻሻሉ የርቢ አውራዎቻቸውን በኩራት ሲያሳዩ። (ታደሰ ምስጋናው/አማራ ክልል የምርምር ተቋም). 8.ገጽ 26: የተሻሻለ የቦንጊቾ ኮርማ በቦንጋ ማህበረሰብ ዓቀፍ የርቢ ቦታ። (ፎቶ፡ በICARDA/ተስፋዬ ጌታቸው). 9.ገጽ 27: በሞላሌ የማዓዝማ ጣቢያ፣ ሃብታሙ ጉቻሌ ከስንታየውሁ የበግ መንጋዎች መረጃ ሲሰበስብ። (ፎቶ፡ በICARDA/ተስፋዬ ጌታቸው). 10.ገጽ 28: የICARDA ተመራማሪ እና ሴት የፍየል አርቢ ግልገሏን ይዘው፣ ከኋላቸው ከሚግጡ መንጋዎች ጋር፣ በአንድ የLowland Livelihood Resilience Project ማህበረሰብ ዓቀፍ የማራቢያ ጣቢያ። (ፎቶ፡ በICARDA/ተስፋዬ ጌታቸው). ስንቅነህ እሸቱ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ MOA, 2024. የበጎችን እና የፍየሎችን ማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር ማስፋፋት.የተጠቃሚዎች መምሪያ.ግብርና ሚኒስቴር.አዲስ አበባ.ኢትዮጵያ. ትርጉም፣ አርት ዖት፣ እና የገጽ ቅንብር የፎቶዎች ምንጭ፦ በዋቢነት መጥቀስ ስፈልጉ ይህንን ይጠቀሙ፦ iiማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 ማውጫ መግቢያ አጭር መግለጫ........................................................................................................................01 የማስፋፊያ ማዕቀፍ ................................................................................................................06 ከመንግስት ጥረቶች ጋር ያሉ ትሥሥሮች ....................................................................09 በመከናወን ላይ ካሉ የመንግስት የልማት ዕቅዶች ጋር ማቀናጀት .................09 ተዘዋዋሪ ገንዘብ እና የአርሶ-አደር ተሳትፎ ..................................................................10 ሰው-ሠራሽ የማስጸነሻ ዘዴን በመጠቀም የዘረመል ብልጸጋን ማሳደግ ...10 ክፍል አንድ፦ የማስፋፊያ ማዕቀፉን ለሚፈለገው ዝርያ እንዲስማማ ማድረግ የማዓዝማዎች እና የአምራች ክፍሎች መልክዓምድራዊ ሥርጭት ..............11 የማዓዝማ መርሃግብርን ለማስፋፋት ክለስተርን እንደ ስትራቴጂ መጠቀም..12 የዝርያ ቅድሚያዎችን መወሰን እና የማስፋፊያ ዕምቅ አቅሞችን መገመት...13 ክፍል ሁለት፦ የአተገባበር ሂደት የባለድርሻ አካላት መድረክ እና ዕቅድ ............................................................................18 የማዓዝማ መርሃግብሮች አመሰራረት እና ትግበራ ቅደም-ተከተሎች ...........19 በልማት ወኪሎች እና በወረዳ ባለሙያዎች ኃላፊነት ስር፣ አምራች ክፍሎችን ለማስጀመር እና ለማከናወን የሚያስፈልጉ ቅደም-ተከተላዊ እርምጃዎች................................ .22 የአቅም ግንባታ፣ የተሻለ መኖ ልማትና አመጋገብ እና የጤና እንክብካቤ ጥረቶች ............30 የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ ዘላቂነት ዳራ ....................................................................................................................................................03 የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብር ..........................................................................05 ምሳሌ ...............................................................................................................................................14 በቦንጋቾ ስብስብ ውስጥ የማስፋፋት ዕምቅ አቅም ...............................................15 ማጣቀሻ ........................................................................................................................................32 አባሪ ...................................................................................................................................................33 የማስፋፊያ ማዕቀፉን ትግበራ የሚያስችሉ ነገሮች.................................................09 አጋርነት..............................................................................................................................................28 የምስሎች እና የሠንጠረሾች ዝርዝር .............................................................................iv ምስጋና .............................................................................................................................................v ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 የምሥሎች እና የሠንጠረዦች ዝርዝር ምሥሎች ምሥል 1. ማዓዝማን (ሲቢቢፒን) እና የአምራች ክፍልን የሚወክል ባለ ሁለት ደረጃ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር ምሳሌ .....................................................................................................................................................05 ምሥል 3፡ በኢትዮጵያ የበግ እና የፍየል ማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር ስርጭት። ..............................................................................................................................................................................11 ሰንጠረዥ 2፡ የማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብርን የማስፋፋት ክትትል እና ግምገማ (ሞኒተሪንግ እና ኢቫሉዌሽን) ...........................................................................................................09 ሠንጠረዦች ምሥል 2. የበግ እና የፍየል ማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ የማስፋፊያ ማዕቀፍ። ...................................................................................................................................................................................................08 ሰንጠረዥ 1፡ በቦንጋ ስብስብ ውስጥ የማስፋፋት ዕምቅ አቅም .......................................................09 ምሥል 4፡ በዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ ውስጥ ያሉ የበጎች (በስተግራ) እና የፍየሎች (በስተቀኝ) ስብስቦች (ክላስተሮች)። በምሥሉ ውስጥ፣ ደማቅ ቀለም የተቀቡ ክፍሎች ከወዲሁ የተመሠረቱ ስብስቦችን ሲያሳዩ፣ ነጠብጣባማ እና ፍርግርግ ቅብ ያሉባቸው ቦታዎች ወደፊት ሊመሠረቱ የሚችሉ ስብስቦችን ያመለክታሉ።.............................................................12 ምሥል 5. የበይነ-ባለድርሻ-አካላት ሥነ-ምህዳር፣ የባለድርሻ አካላቱ ሚናዎች እና ኃላፊነቶች .....................................................................................................................................................................................................29 ivማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 ምስጋና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊት ሪፓብሊክ፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የእንስሳት ክፍል ስም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ፣ የፍየሎችን እና የበጎችን ምርታማነት ለማሳደግ ትልቅ ሚና ሲጫወት ለቆየው ለማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር (Community-Based Breeding Program / CBBP) አስተዋጽዖ ላበረከቱ በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። በተለይም፣ ዓለም ዓቀፍ የደረቅ አካባቢዎች የግብርና ምርምር ማዕከል (ICARDA)፣ በአፍሪካ ውስጥ የCGIAR የዓየር-ንብረት ምርምርን ተፅዕኖ ማፋጠን (AICCRA)፣ ለመተዳደሪያዎች፣ ለሥነ-ምግብ፣ እና ለሥርዓተ-ፆታ አካታችነት በዘላቂ የእንስሳት ምርታማነት ላይ የCGIAR ተነሳሽነት (SAPLING) እናየእንስሳትእናየዓሣሀብትሴክተርልማትፕሮጀክት (LFSDP)፣ ይህንን የማዓዝማ (CBBP) ማስፋፊያ የተጠቃሚዎች መምሪያ በማዘጋጀት ለተጫወቱት የመሪነት ሚና በእጅጉ እናመሰግናቸዋለን። ይህ የተጠቃሚዎች መምሪያ የተዘጋጀው፣ የሥርፀት (ኤክስቴንሽን) አጋሮች፣ መዓዝማዎችን (CBBPs) ከብሔራዊ የሥርፀት ሥርዓት ጋር በውጤታማነት እንዲያቀናጁ ለማገዝ ነው። ይህም፣ በእኛ ክፍል (ዘርፍ) እንደተግዳሮት ተለይቶ ለወጣው ለዚህ ወሳኝ ፍላጎት ምላሽ ይሰጣል። በተጨማሪም፣ ግብርና ሚኒስቴርን፣ ክልላዊ የእንስሳት ልማት ቢሮዎችን፣ የእንስሳት ልማት ተቋምን፣ የግብርና ምርምር ተቋማትን እና ኢካርዳን ጨምሮ፣ ከተለያዩ ድርጅቶች ለመጡት ለሚከተሉት ግለሰቦች ቅን ምስጋናችንን ልንገልፅ እንወድዳለን፦ አስመላሽ በርሄ፣ ዳኜ ሙሉነህ፣ ቀጀላ ተሰማ፣ ሙላቱ ዳኜው፣ ገረመው ኃ/ጊዮርጊስ፣ አመልማል ዓለማየሁ፣ ሻንበል በሱፈቃድ፣ ዓይናለም ኃይሌ፣ ብርሃኑ በላይ፣ እና ተስፋዬ ጌታቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የበጎችን እና የፍየሎችን ማዓዝማ መርሃግብሮች (CBBPs) ለማስፋፋት የተዘጋጀውን ይህንን የተጠቃሚዎች መምሪያ እውን በማድረግ ረገድ የእነሱ አስተዋጽዖ እጅግ ወሳኝ ነበር። በመጨረሻም፣ በግምገማው እና በማጽደቁ (ቫሊዴሽን) ሂደት ውስጥ፣ የተጠቃሚዎችን መምሪያ በማርታት እና በማቅናት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ግለሰቦች እና ተቋማት በሙሉ አድናቆታችንን እንገልጻለን። ለዘላቂ የእንስሳት ልማት ለሚደረገው የጋራ ጥረት የማይናወጥ መሰጠታችሁን እና ጽናታችሁን ስላሳያችሁ፣ ሁላችሁንም እጅግ አድርገን እናመሰግናችኋለን! vማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 ምህጻረ-ቃላት Artificial Insemination Accelerating Impacts of CGIAR Climate Research in Africa Borana, Omo, and Konso (goat cluster for breeds in southern lowlands) Community-Based Breeding Program Consultative Group on International Agricultural Research Central Statistical Agency Development Agent Debub Maekelawi Initiative, A Small Ruminant Cluster in the Central and Southern Ethiopia Region Data Tree, A Genetic Database developed by ICARDA and Abacusbio Estimated Breeding Value Food System Research Project Finisher Unit International Center for Agricultural Research in the Dry Areas International Livestock Research Institute Livestock and Fisheries Sector Development Project Lowland Livelihood Resilience Project Ministry of Agriculture (assumed) Market Unit Non-Governmental Organization Production Unit Southern Agricultural Research Institute (Ethiopia-specific) Subject Matter Specialist Training of Trainers Washera Wollo (sheep cluster for Washera and Wollo sheep breeds) AI AICCRA BOOM CBBP CGIAR CSA DA DMI DTREO EBV FSRP FU ICARDA ILRI LFSDP LLRP MOA MU NGO PU SARI SMS TOT WaWo ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 01 በኢትዮጵያ፣ የበግ እና የፍየል፣ ማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃ-ግብር፣ ወይም Community- Based Breeding Program (CBBP) ከተጀመረበት ከ2001 ዓ.ም. ጀምሮ፣ የተሳካ የዘረመል ማሻሻያ ፕሮጀክት ሆኖ እስከዛሬ ዘልቋል። ይህ መርሀ-ግብር፣ የማህበረሰቡን የበግ እና የፍየል መንጋ ለማሻሻል፣ የእንስሳትን መረጃ መለየትን እና ማሰባሰብን፣ የተሻሻሉ የእርባታ አውራዎችን እና ኮርማዎችን አያያዝን እና አጠቃቀምን፣ የባህላዊ እውቀት አጠቃቀምን፣ እና የማህበረሰብ መንጋዎችን ማሰባሰብን በመሳሰሉ የመርሃግብሩ የተለያዩ ገጽታዎች ውስጥ ማህበረሰቡን በውጤታማነት ያሳትፋል። ይህንንም የሚያከናወነው፣ የህብረተሰቡን ልዩ ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የማህበረሰቡን አባላት፣ የእንስሳቱን የዘረ-መል እሴት ወይም ዋጋ (breeding value) መሰረት ባደረገ አሳታፊ የመረጣ ሂደቶች ውስጥ በማሳተፍ ነው። የዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብሩ (CBBP)፣ በእስከዛሬው ጉዞው፣ የማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሀ- ግብሮችን ቁጥር በማሳደግ እና የተሻለ ጥራት ያላቸው የእርባታ አውራዎችን/ኮርማዎችን በማፍራት ጉልህ ስኬቶችን አስመዝግቧል። ይህም፣ ከፍ ወዳለ የባለድርሻ አካላት እና ወደተሻለ የማህበረሰብ ተሳትፎ መርቷል።የእንስሳት እና የዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት ፕሮጀክት (LFSDP)፣ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP)፣ እንዲሁም የምርምር ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የኢትዮጵያ ብዝሃ-ሕይወት ተቋም፣ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለሲቢቢፒዎች ስኬቶች እውቅና ሰጥተዋል፣ የፕሮጄክቶቻቸው አካልም አድርገዋቸዋል። ስኬታማ ሲቢፒፒዎችን በማበራከት እና የተሻሻሉ የርቢ አውራ/ኮርማዎችን በአቅራቢያዎቻቸው ለሚገኙ፣ አምራች ክፍሎች (PUs) ተብለው ለሚጠሩ፣ መንጋዎች በማሰራጨት፣ መርሀ-ግብሩ የሚያሳድረውን አዎንታዊ ተጽዕኖ ለማስፋፋት፣ የማስፋፊያ ማዕቀፍ ወይም scaling framework ተዘጋጅቶ እየተተገበረ ይገኛል። በአምራች ክፍሎች (PUs) የሚስተዋሉ ከማስተዳደር ጋር የተያያዙ፣ በሥራው ጸንቶ የመዝለቅ ችግሮችን (የቁርጠኝነት ስጋቶችን) እና የብቃት ክፍተቶችን የመሳሰሉ ተግዳሮቶች፣ ቀለል ያሉ የአጠቃቀም መመሪያዎችን በመጠቀም እንደሚቀረፍ ይታመናል። አጭር መግለጫ ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 02 ይህ የአጠቃቀም መምሪያ ሁለት ክፍሎች አሉት፦ 1. ለአንድ የተወሰነ የእንስሳት ዝርያ፣ አንድ የማስፋፊያ ማዕቀፍን ተግባራዊ ማድረግ፦ ይህክፍል የሚያተኩረው ለአንድ ለተወሰነዝርያ በተለይ የተነደፈን አንድ የማስፋፋትስትራቴጂ በጥንቃቄ እና በዝርዝር በማዘጋጀትእና በመተግበር ላይ ነው።ይህም፣ አሁን ባሉት ማህበረሰብ-ዓቀፍየዝርያ ማሻሻያ መርሀ- ግብሮች (CBBPs) እናአምራች ክፍሎች (PUs) መልክዓ-ምድራዊሥርጭት ላይ አጠቃላይ ግምገማ ማድረግንያካትታል። ይህሂደት፣ በተፈለገው ስብስብ (ክላስተር) ወይም ዝርያ ውስጥ፣ "ምን ያህልተጨማሪ CBBPዎች እና አምራች ክፍሎችይኑሩ? ተጨማሪዎችስየት የት ቦታዎች ላይስይመሥረቱ?" ለሚሉ ጥያቄዎች ምላሽበመስጠት፣ ይበልጥ ውጤታማ የሆነን የCBBPዎችንእና የአምራች ክፍሎችን ብዛት ለማወቅእና ስትራቴጂያዊ የቦታ ምደባዎችንለማድረግ ያስችላል። 2. የአተገባበር ሂደት፦ ይህሰነድ፣ በባለድርሻ አካላትንተሳትፎ CBBPዎችንእና አምራች ክፍሎችን ለማስጀመር እናለማካኼድ የሚያስችል አጠቃላይ መመሪያምይሰጣል። እንስሳትን መለየትን፣ የመረጃአሰባሰብን፣ የማዳቀል መረጣን፣ የኮርማ አያያዝን፣እና የገበያ ቅንጅትን ለመሳሰሉ ተግባራትምዝርዝር መመሪያዎችን ይይዛል። ይህየአጠቃቀም መመሪያ፣ ድርጊቶችንየሚያቀላጥፉ፣ እቀዳን እና ትግበራን የሚያሻሽሉ፣ እና በሁሉም ደረጃዎች ውስጥ የዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብሩን ውጤታማ ክትትል የሚያስችሉ ግልጽ እና አጫጭር መመሪያዎችን ይሰጣሉ።እነዚህ መሳሪያዎች፣ የመርሀ- ግብሩን በጎ ተፅእኖ ከፍ በማድረግ፣ የመንግስት እርምጃዎችን በማጠናከር፣ እና አጋሮችን በማብቃት እና ግንዛቤአቸውንና አቅማቸውን በማጎልበት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የበግ እና የፍየል የዝርያ ማሻሻልመርሃ-ግብርን ዕመርታ እና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ያልማሉ። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 03 እ.ኤ.አ. ከ1940ዎቹ ጀምሮ፣ ኢትዮጵያ፣ለበጎች እና ለፍየሎች፣ ባደጉ ሀገራት የተለመዱትን "ኑክሊየስ" እና "ክሮስ-ብሪድንግ" የማዳቀል መርሃ-ግብርን ተግባራዊ አድርጋለች። እነዚህ ስራዎች ያተኮሩት በመንግሥት እርሻዎች ላይ በመረጣ የዝርያ ማሻሻል ስራን በማከናዎን እንዲሁም በምርታማነታቸው የታወቁ ዝርያዎችን በማምጣት በእርሻዎቹ ውስጥ በማባዛትና የተሻሻለ አውራዎችን ወይም ኮርማዎችን ለማህበረሰብ መንጋዎች ማሰራጨት ነበር። ዳሩ ግን፣ ሁለቱም አቀራረቦችዋና ዋና ተግዳሮቶች ገጥመዋቸዋል፣ ይህም ወደ ማህበረሰቡ የሚደርሱ ዲቃላዎች (ክሮስ- ብሪድስ) እና የተሻሻሉ መንጋዎች/አውራዎች ቁጥር ትንሽ እንዲሆን አድርጓል (Getachew et., 2016)። በተጨማሪም፣ የተሰራጩት ድቅል መንጋዎች ዝቅተኛ ተፅእኖ ነበራቸው። ያም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት በጎች እና ፍየሎች ውስጥ፣ በዲቃላዎቹ ላይ የ0.35% እና በመጤ ዝርያዎች ላይ ደግሞ የ0.10% ተጽዕኖ ብቻ ነበር። ለዚህ አካሄድ አለመሳካት በርካታ ምክንያቶችአስተዋጽኦ አድርገዋል። ለምሳሌ፣ እንስሳቱን ከውጭ ለማስመጣትና ለመንከባከብ ከፍተኛ ወጪ መጠየቁ፣ የበሽታ ወረርሽኝ በተደጋጋሚ መከሰት፣ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ያለመጣጣም፣ የውጭእንስ ሳት ያላቸው ዝቅተኛ አካባቢን የመላመድ ችሎታተገቢ የዝርያ ማሻሻያ እቅድ አለመኖር፣ እና እንደ የኢትዮጵያ የበግ እና የፍየል ምርታማነት ማሻሻያ ፕሮጀክትንለመሳሰሉ ስኬታማ ፕሮጄክቶች ማስቀጠል ያለመቻል የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። በ2001 ዓ.ም. ከተተዋወቀበት ጊዜ ጀምሮ በበግ እና በፍየል ላይ የሚደረገው ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃ-ግብር (ሲቢቢፒ) በኢትዮጵያውስጥ አማራጭ የዘረመል ማሻሻያ ዘዴ ሆኖ ብቅ ብሏል። ይህ መርሀ-ግብር፣ አገር-በቀል ዕውቀትን እያካተተ እና የተሰባሰቡ የማህበረሰብ መንጋዎችን እየተጠቀመ፣ ማህበረሰቡን በመረጃ አሰባሰብ እና በትግበራ ላይ በንቃት በማሳተፍ በልዩነቱ ጎልህ ሆኖ ይታያል። በባለፉት ዓመታት ውስጥ፣ ሲቢቢፒ አስደናቂ ስኬቶችን ተቀዳጅቷል። ይህም ስኬት፣ በተመሠረቱት ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያዎች ቁጥር እና የተሻሻሉ ኮርማዎችን/አውራዎችን ለማምረት ባላቸው ብቃት ውስጥ በግልጽ ይታያል። የመርሀ-ግብሩ ውጤታማነት ከፍተኛ ትኩረት ያገኘ ሲሆን፣ ይህም የባለድርሻ አካላት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲጎለብት አስችሏል (Haile et al., 2011, 2020, 2023)። በተለይም የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ሴክተር ልማት ፕሮጀክትን (LFSDP) እና የቆላ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክትን (LLRP) የመሳሰሉ ዳራ ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 04 የመንግስት ተነሳሽነቶች ለእነዚህ ስኬቶች እውቅና በመስጠት የፕሮጀክቶቻቸው አካላት በማድረግ መርሀ- ግብሩ በአገር-አቀፍ ደረጃ እንዲስፋፋ አስችለዋል። ነገር ግን፣ አሁንም፣ መርሀ-ግብሩ ለሀገሪቱ ሰፊ የበግ እና የፍየል ቁጥር ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ በዝርያ- ደረጃ የዘረመል መሻሻልን ለማሳካት፣የስብስብ (የክላስተር) አቀራረብን በመጠቀም የፕሮግራሙን ተደራሽነት ማስፋት ያስፈልጋል።ለዚህ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት እና ሰፋ ያለ የህዝብ ቁጥርን ለመድረስ የሚያስችል አንድ የማስፋፊያማዕቀፍ ተዘጋጅቷል። የሲቢፒዎችን ቁጥር ማበራከት እና በእነዚህ ሲቢቢፒዎች ውስጥ የሚዳቀሉ የተሻሻሉ ኮርማዎችን/ አውራዎችን፣ በዙሪያቸው ላሉ፣ አምራች ክፍሎች (PUs) ተብለው ለሚጠሩ፣ የአካባቢው መንጋዎች ማሰራጨት፣ እንደ ቁልፍ ስልት ተለይቶ ተቀምጧል። ዓለም አቀፍ የደረቅ አካባቢዎች የግብርና ምርምር ማዕከል (ICARDA) እና የምርምር፣የኤክስቴንሽን፣ እና የዩኒቨርሲቲ አጋሮቹ፣ በሲቢቢፒዎች እና በአምራች ክፍሎች (PUs) መካከል ያለውን ቁርኝት ለማጎልበት እና በዚያ ሥርዓት ውስጥ የተጨማሪ እንስሳትንሽያጭ ለማመቻቸት የሚያስችል የማስፋፊያ ማዕቀፍ ፈጥረዋል። የምርምር ተቋማት እና ዩኒቨርሲቲዎች በዓይነተኛነት የሲቢቢፒዎችን አስተዳደር በበላይነት ክፍሎች ጋርም ያቆራኛሉ። ነገር ግን፣ አሁንም፣ ደካማ ቁርጠኝነትን፣ የክህሎት ክፍተቶችን፣ የሀብት ውስንነትን፣ በቂ እቅድ አለማውጣትን፣ እንቅስቃሴዎቹ እስከታችኞቹ የአካባቢ ደረጃዎች እንዲወርዱ ማድረግን አለመቻልን፣ እና ደካማ ክትትል እና ግምገማን የመሳሰሉ በርካታ ተግዳሮቶችአሉ። በመርሀ-ግብሩ አተገባበር ላይ የሚሳተፉ ሰዎች እነዚህን ተግዳሮቶች ለይተው አውጥተዋል። ሲቢቢፒዎችን፣ አምራች ክፍሎችን፣እና ገበያን በማገናኘት ረገድ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ቀለል ያሉ መመሪያዎችን እና በተለይም ለልማት እና ለኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሚሆኑ የአጠቃቀም መምሪያዎችን ማዘጋጀት አለብን። እነዚህን ሀብቶች አሁን ካለው የኤክስቴንሽን ዕቅድ ጋር በማቀናጀት፣ ባለሙያዎች ሲቢቢፒዎችን እና አምራች ክፍሎችን ለማስተዳደር የሚያስችሏቸውን ግንዛቤዎች፣ ክህሎቶች፣ እና ብቃት ማሳደግ እንችላለን። የአጠቃቀም መምሪያዎቹ፣ የተፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ፈለግ ለመጥረግ፣ እቀዳን እና ትግበራን ለማሻሻል፣ እንዲሁም በሁሉም ደረጃዎች ውጤታማ ክትትልን እና ግምገማን ለማመቻቸት የሚያስችሉ፣ ለተጠቃሚዎች ምቹ የሆኑ መመሪያዎችን ያቀርባሉ። ይህ፣ በእነዚህ መርሀ-ግብሮች እና በመንግስት ተነሳሽነቶች መካከል የሚቆጣጠሩ ሲሆን፣ የማህበረሰብ አርቢ ማህበራት፣የልማት አጋሮች፣ እና የኤክስቴንሽን አጋሮች ለአምራች ክፍሎቹ ስኬት በንቃት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። በሃይሌ እና በሌሎች (Haile et al. 2011, 2018) ተመራማሪዎች እንደተሰነደው፣ ሲቢቢፒዎቹ የአሠራር መመሪያዎችን ያዘጋጁ መሆናቸውን መጥቀሱ ተገቢ ነው። ሆኖም፣ በአሁኑ ጊዜ፣ በተለይ ለአምራች ክፍሎች እንዲስማሙ ተደርገው የተዘጋጁ የአካታች የተጠቃሚዎች መምሪያውቾ እጥረት አለ። አንዳንድ አካባቢዎች የአምራች ክፍል መንደሮችን በውጤታማነት ያስተዳድራሉ፣ ሲቢቢፕዎችን ከአምራች ያለውን ትስስር በማጠናከር፣ ለእንስሳቱ ዘርፍ እና ለአጠቃላይ የመረሀ-ግብሩ ስኬት ትልቅ ጠቀሜታ ይሰጣል። አጠቃላይ መመሪያ፣ የስልጠና ማጣቀሻ፣ እና የእውቀት ማጋሪያ መሳሪያ ሆነውም ያገለግላሉ፣ ወጥነት ላለው ትግበራም ደረጃቸውን የጠበቁ መመሪያዎችን ይሰጣሉ። በተጨማሪም፣ አጋሮች ውጤታማ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ፣ ተሞክሮዎቻቸውን እንዲያስተላልፉ፣ ተግዳሮቶችን እንዲቀርፉ፣ እና የመርሀ-ግብሩን ተፅእኖ እና ዘላቂነት ከፍ እንዲያደርጉ ኃይል ይሰጧቸዋል። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብር 05 ምሥል 1. ማዓዝማን (ሲቢቢፒን) እና የአምራች ክፍልን የሚወክል ባለ ሁለት ደረጃ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር ምሳሌ ለገበያ የሚቀርቡ መንጋዎች ዘረመል ይቀበላሉ አስኳል ሥርጭት ልኬት እና የዘረመል ምዘና ዘረመል ያቀርባል የዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብር ተፈላጊ ባህሪያት ያሏቸውን እንስሳት ከመንጋው በመምረጥና እርስ በርስ እንዲዳቀሉ በማድረግ የተተኪውን ትውለድ ዘረመል ለማሻሻል እና የተመረጡ ባህሪያቶቻቸውንም ጥራት ለመጨመር፣ የሚደረግን ስልታዊ የእርባታ ዘዴወይም ስትራቴጂ ነው። ይህም የተፈላጊ ዘረመሎችን ብዛት ለመጨመር እና የማይፈለጉ ባህሪያቶችን ክስተት ለመቀነስ፣ የተመረጠውን እንስሳ (አውራ ወይም ኮርማ) በመንጋው ውስጥ ካሉ እንስቶች ጋር ማዳቀልን ያካትታል። የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብር የሚከናወነው፣ ቀጣዮቹ የእንስሳቱ ትውልዶች ከአካባቢያዊ ሁኔታዎች ጋር ይበልጥ ተላምደውምርታማነትን ለመጨመር እና የበሽታ መቋቋም ችሎታቸውን ከፍ ለማድረግ፤ እንዲሁም የቆዳ ቀለምን እና ተክለ-ቁመናን የመሰሉ የተፈላጊ ባህሪያት ዘረመሎችን ለማሻሻል ነው። በእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብር ወላጅ ዝርያዎችን በጥንቃቄ መምረጥን፣የዘረመል ባህሪያትን መከታተልን፣ እና የሚፈለጉትን ግቦች ለማሳካት የተለያዩ የማዳቀያ ዘዴዎችን መተግበርን ያካትታል። የዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብር በዓይነተኛነት ሁለት ወይም ሶስት ደረጃ ያለውን የመራቢያ ሥርዓት ይጠቀማል። ይህም በአንድ የእንስሳት መንጋ ውስጥ ውጤታማ የሆነ የዘረመል መሻሻል እንዲኖር ያስችላል። በዚህ ሥርዓት የመጀመሪያው ደረጃ ውስጥ በአስኳሉ መንጋስብስብ ውስጥ መረጃንመሰረት ያደረገ ምርጫን በማከናወን ምርጥ ዘሮችን የመፍጠር ሰራዎች የሚከናወኑ ሲሆን፣ በሁለተኛው ደረጃ ወይም በማባዣ ክፍል ውስጥ ደግሞ በመጀመሪያው ክፍል ብልጫ ያላቸው ዘረመሎችን በማባዛት፣ እና በመጨረሻምየተሻሻሉ እንስሳትን ወደ ወደ ሰፊው አምራች ክፍል በማሰራጨት ላይ ያተኩራል። ሂደቱ፣ የዘረመል መሻሻሉ፣ ከምርጥ የርቢ ዝርያዎች እስከ ሽያጭ ምርቶች ድረስ በውጤታማነት የሚደርስበትን ፍሰት ያቀላጥፋል። በዚህም፣ አርቢዎችንም፣ ሸማቾችንም ተጠቃሚ ያደርጋል። በሁለት ደረጃዎች (በአስኳል እና በአምራች) ወይም በሦስት ደረጃዎች (በአስኳል፣ በማባዣ እና በአምራችከሚሠራው ተለምዷዊው የዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብር ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ፣ በአነስተኛ አምራቾች ዘንድ የሚደረገው የዝርያ ማሻሻያ መርሃ- ግብርም ባለ ሁለት ደረጃ ነው። ይህም፣ በምሥል 1 ላይ እንደሚታየው፣ ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብርን (ሲቢቢፒ) እና የአምራችክፍልን ያካትታል። ሲቢቢፒዎች በአስኳልነት የሚያገለግሉ ሲሆን፣ በዋነኝነት የተመረጡ እና ስለጥራታቸው ማረጋገጫ የሚሰጣቸው አውራዎችን ወይም ኮርማዎችን በማምረት ላይ ያተኩራሉ። ከዚያም፣ እነዚህን የርቢ አውራዎች ወደ አምራች ክፍል (PU) ያሰራጫሉ። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 የማስፋፊያ ማዕቀፍ 06 በኢትዮጵያ በመተግበር ላይ ባለው ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሀ-ግብር (ሲቢቢፒ) አውድ ውስጥ፣ የማስፋፊያ ማዕቀፉ የተነደፈው፣ በዋነኝነት እጅግ ምርጡን ዘረመል በማባዛት እና በማሰራጨት ይበልጥ ሰፊ የሆኑ መንጋዎችን ለመድረስ፣ ምርታማነትን ለማሻሻል፣ እናም ሰፋ ያለ ተፅእኖን ለመፍጠር በማሰብ ነው። የማስፋፋት ሰራው የሚከናወነው፣ በሲቢቢዎች ውስጥ የሚመረቱ የርቢ አውራዎችን ወይም ኮርማዎችን፣ በተፈጥሮአዊ ስሪያ ወይም ሠው-ሠራሽ ማዳቀያ በመጠቀም፣ ለሌሎች ሰፊ መንጋዎች በማሰራጨት ነው። ይህ ማዕቀፍ የሚያልመው፣ በበጎች እና በፍየሎች ላይ፣ በሙከራ ቦታዎች እና በማህበረሰብ-ደረጃ የተደረገውን በፈጠራ የተሞላ የዝርያ ማሻሻያ ጥረት ወደሰፊ የመንጋ ወይም የዝርያ ደረጃ ለማሸጋገር ነው። ሲቢቢዎችን እንደ አስኳል የማራቢያ ዝርያ የሚወስድን የስብስብ (የክላስተር) አቀራረብን ይከተላል። ዓለም አቀፍ የደረቅ አካባቢዎች የእርሻ ምርምር ማዕከል (ICARDA)፣ በአፍሪካ ውስጥ የዓለም አቀፍ የግብርናምርምር የመማክርት ቡድንን (CGIAR)ን የምርምር ተፅእኖን ማፋጠን (AICCRA) እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔራዊ የምርምር እና የልማት አጋሮች ይህንን የማስፋፊያ ማዕቀፍ አዘጋጅተዋል (Mueller et al., 2019; Mueller et al., 2023)። ማዕቀፉ አራት ዋና ዋና ክፍሎችን የያዘ ነው፦ እነዚህም ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ (CBBP)፣ የአምራች ክፍል (PU)፣ የማደለቢያ ክፍል (FU) እና የገበያ ክፍል (MU) ናቸው (ምሥል 2)። የማስፋፊያ ማዕቀፉ፣ ሲቢቢፒዎችን ከማራቢያ ክፍሎች ጋር ለማገናኘት፣ በመንጋ ደረጃ ምርጥ ዘረሞሎችን ለማሰራጨት፣ በእሴት ጭማሪ አማካኝነት ተጨባጭ ተፅእኖዎችን ለመፍጠር፣ እና ለተጠቃሚዎች የሥጋ በግ እና ፍየሎችን ለመሸጥ ያገለግላል። የማስፋፊያ ማዕቀፉ አራት ክፍሎች እንደሚከተለው ይብራራሉ፦ 1. ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ (ማዓዝማ) መርሃ-ግብር፦ የማዓዝማ መንደሮች፣ ለማዳቀል ዓላማዎች የሚውሉ፣ የጥራት ማረጋገጫ የተሰጣቸው፣ እና ከፍተኛ ተመራጭነት ያላቸውን አውራዎች እና ኮርማዎች ለማምረት፣ ጥብቅ የመረጃ አሰባሰብ፣ የዘረመል ግምገማ፣ እና መረጣ የሚካሄድባቸው ቦታዎች ናቸው። ማዓዝማዎች አስኳል ክፍሎች በመሆን ያገለግላሉ። ይህም በሥርዓቱ ውስጥ አስፈላጊ ደረጃ ሲሆን፣ በመረጃ ስነዳ፣ በመረጣ፣ በማዳቀል፣ እና በዘረመል ማሻሻል ላይ ያተኩራል። ይህ ክፍል፣ ለተፈላጊ ባህሪያቶቻቸው በጥንቃቄ የተመረጡ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን እጅግ ምርጥ የእንስሳት ቡድን ያቀፈ ነው። በማዓዝማ መንደሮች ውስጥ፣ ተሳታፊ አርሶ አደሮች፣ በጋራ ከ500 እስከ 1,000 የሚደርሱ ሴት በጎችን ወይም ፍየሎችን በሚይዙ የአርቢዎች ማህበራት በመደራጀት፣ በዝርያ ማሻሻያው መርሀ-ግብር ውስጥ በአውራ ወይም ኮርማ መጋራት መርሃ-ግብር አማካኝንት ተሳትፎ ያደርጋሉ። በማዓዝማ ውስጥ የሚሳተፉ አርሶ-አደሮች ቁጥር፣ እንደየመንጋው መጠን ይለያያል። አንድ ማዓዝማ፣ በዓይነተኛነት፣ ከ50 እስከ 150 የሚደርሱ አባላትን ይይዛል። ይህ ክፍል በዋነኝነት የሚተዳደረው በምርምር ማዕከላት እና/ወይም በዩኒቨርሲቲዎች ነው። የጥራት ማረጋገጫ የሚሰጣቸው አውራዎች ወይም ኮርማዎች፣ የእንስሳውን የዘረመል ዋጋ፣ የማስወለድ ብቃት፣ የወንድ ዘር ጥራት እና ብዛት በሚገመግም፣ እና ለዋና ዋና በሽታዎች የመከላከያ ክትባት ማግኘታቸውን በሚያረጋግጥ የብቃት ማረጋገጫ ሂደት ውስጥ ያልፋሉ። በማዓዝማዎች ውስጥ የሚራቡት የጥራት ማረጋገጫ የሚሰጣቸው ኮርማዎች ወይም አውራዎች ለእርባታዓላማዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ። ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው አውራዎች/ኮርማዎች በማዓዝማ መንደሮች ውስጥ ይሰማራሉ። በጥራት ደረጃቸው ቀጣይ የሆኑ አውራዎች/ኮርማዎች ደግሞ ወደ አምራች ክፍሎች (PUs) ይሰራጫሉ። የጥራት ማረጋገጫውን ሂደት የማያልፉ አውራዎች/ኮርማዎች ተቀናሽ በመሆን ለዕርድ ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 07 ይሸጣል። ማዓዝማዎች በዋነኝነት በምርምር ማዕከላት እና በዩኒቨርሲቲዎች የሚተዳደር ቢሆንም፣ የወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤቶች (DAs) እና የኤክስቴንሽን አጋሮች በማህበረሰቡ ውስጥ ማዓዝማዎችን (ሲቢቢፒዎችን) በመደገፍ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። የዝርያ ማሻሻያ ማህበራትን አፈፃፀም መከታተልን፣ የማራቢያ አውራዎችን/ኮርማዎችን አጠቃቀም እና አያያዝን መቆጣጠርን፣ እና በእርባታ፣ በመኖ አቅርቦት፣ በጤና አጠባበቅ፣ እና በግብይት ውስጥ ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ እገዛ ያደርጋሉ። ስለ ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃ-ግብሮች (ሲቢቢፒስ) አመሠራረት እና አስተዳደር ተጨማሪ መረጃ የሚሰጥ፣ አጠቃላይ የአጠቃቀም መመሪያ አለ (Haile et al., 2020)። ይህ መመሪያ፣ የርቢያ እንስሳትን መረጣን፣ የዝርያ ማሻሻያ ስልቶችን፣ የማህበረሰብ ተሳትፎን፣ የመረጃ አሰባሰብን፣ እና አጠቃላይ የፕሮግራም አስተዳደርን ጨምሮ በማዓዝማ መርሃግብር (CBBP) ትግበራ የተለያዩ ገጽታዎች ላይ ጥልቅ እና ዝርዝር መመሪያዎችን ይሰጣል። 2. የአምራች ክፍል (PU)፦ ይህ የማስፋፊያ ማዕቀፉ ሁለተኛው አካል ነው። ይህ ክፍል፣ የጥራት ማረጋገጫ የተሰጣቸው አውራዎችን/ኮርማዎችን ከማዓዝማዎች (ሲቢቢፒ) በመቀበል ለሥጋ ገበያ እና ለፍጆታ የሚሆኑ የበግና ፍዬልጠቦቶችን እና ግልገሎችን ለማምረት፣ እንዲሁም የተሻሻሉ የሴቶች ዝርያዎችን ለምትክነት ማዘጋጀት እና ለሌሎች አርቢዎች ለእርባታ የመሸጥ ስራዎችን ያከናውናል። በዚህ ክፍል ውስጥ፣ አርሶ አደሮች እራሳቸውን በአምራች ማህበራት ያደራጃሉ። የአምራች ክፍሉ ስፋት፣ በቀበሌው ስፋት የሚወሰን ይሆናል። ይህ በዓይነተኛነት ከ400 እስከ 1,000 የሚያህሉ አባ/እማ-ወራዎችን የሚያካትት ቢሆንም፣ ቁጥሩ ተለዋዋጭ ሊሆን ይችላል። እንደየተሳታፊዎች አቅም፣ እንደየርቢያ አውራዎች/ኮርማዎች መኖር ወይም አለመኖር፣ እና አርሶ አደሮች እነሱን ለማግኘት እንዳላቸው ፍላጎት፣ ቁጥሩ ሊለያይ ሊሆን ይችላል። ቀበሌዎቹ ሰፋፊ ከሆኑ፣ ስኬታማ ለሆነ አስተዳደር፣ ለአያያዝ ወደሚመቹ ስብስብቦች ሊከፋፈሉ ይችላሉ። ለአስተዳደር እንዲያመቹ ተደርገው በተፈጠሩ ስብስቦብ ውስጥ፣ የርቢያ አውራዎቹን/ኮርማዎቹን አጠቃቀም እና ዝውውር ቀልጣፋ ለማድረግ፣ የስሪያ ቡድኖች ይቋቋማሉ። በማራቢያ ክፍሎች ውስጥ የሚመረቱት ወንዶች አንዳቸውም ለመራቢያ ዓላማዎች ጥቅም ላይ መዋል የለባቸውም። ይልቁንም፣ መኮላሸት፣ ከመንጋው መነጠል፣ መደለብ፣ እና በቀጥታ ለሸማቾች ወይም ለማደለቢያ ክፍሎች መሸጥ አለባቸው። የአምራች ክፍሉ በዋናነት የእንስሳት ኤክስቴንሽን ክፍል የሚመራው ሲሆን ከግል ባለሀብቶችና አድላቢዎች ጋር ጥምረት እንዶፈጥሩ ቢደረግ ገበያው ውጤታማ እንዲሆንና ትርፋማ ሆነው እንዲቀጥሉ ያደርጋል። 3. የማደለቢያ ክፍል (FU)፦ ይህ ክፍል ከማዓዝማዎች (ሲቢቢፒዎች) እና ከማራቢያ ክፍሎች፣ ለርቢ የማይሆኑ ወንድ እንስሳትን ይቀበላል፣ ውጤታማና የሥጋ ጥራታቸው የተሻሉ እንዲሆኑ ተገቢ አመጋገብን እና የጤና እንክብካቤን ያደርጋል፣ ከአገር- ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሸማቾች ጋርም የገበያ ትሥሥሮችን ይፈጥራል። ማናቸውም ፍላጎቱ ያላቸው (የወጣቶች ወይም የሴቶች ቡድኖችን የመሳሰሉ) ቡድኖች፣ ወንድ ጠቦቶችን ወይም ግልገሎችን ለጥቅም ለማብቃት ሊደራጅ ይችላል፤ በዚህም በማዓዝማዎች ወይም በማራቢያ ክፍሎች ውስጥ በሚመረተው ሥጋ ላይ እሴት ይጨምራሉ። እነዚህ ቡድኖች፣ ከማዓዝማው (ሲቢቢፒ) እና ከአምራች ክፍሉ (ፒዩ) ጋር በተጓዳኝነት ጎን-ለጎን ሊቋቋሙ ይችላሉ፣ ወይም ከማዓዝማዎቹ እና ከአምራች ክፍሎቹ ጋር ቁርኝት ያሏቸው ልዩ አካላት (ለምሳሌ፣ የወጣት ቡድኖች፣ የሴቶች ቡድኖች፣ ወይም የግል ድርጅቶች) ሆነው ሊካሄዱ ይችላሉ (Wamatu et., 2021)። 4. የግብይት ክፍል (MU)፦ ለሥጋ ዝግጁ የሆኑ ጠቦቶችን/ግልገሎችን ለገበያ ማቅረብ፦ ይህ ክፍል፣ ከማዓዝማዎች (ሲቢቢፒ)፣ ከአምራች ክፍሎች (ፒዩ)፣ ወይም ከማደለቢያ ክፍሎች (ኤፍዩ) የተገኙ፣ ለሥጋ ዝግጁ የሆኑ፣ እንስሳትን ለአገር- ውስጥ እና ለባህር ማዶ ሸማቾች ያስተላልፋል። በአድላቢዎችና እና በሸማቾች መካከል ጠንካራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል። የግል ባለሀብቶች እና የተደራጁ ቡድኖች፣ በጥሩ ሁኔታ የተደራጁ የግብይት መዋቅሮች ያሉትን አንድ የዲጂታል መገበያያ መድረክ በመፍጠር እና ከአድላቢዎች ጋር የስምምነት ውሎችን በመፈራረም፣ በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ሊሳተፉ ይችላሉ። ይህ፣ የግብይት ሂደቶችን በማመቻቸት እና ቀልጣፋ ግብይቶች መፈጠራቸውን በማረጋገጥ፣ አምራቾችን ሰፋ ካሉ ገበያዎች ጋር ለማገናኘት፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እና መድረኮችን መጠቀምን ይጠይቃል። አምራቾች፣ የዲጂታል ግብይት ስትራቴጂዎችን በመጠቀም፣ ሰፋ ያለ የሸማቾችን መሠረት ማግኘት፣ በገበያ ውስጥ የመታየትና የመታወቅ ዕድላቸውን መጨመር፣ እና ትርፋማነታቸውን ማሳደግ ይችላሉ። የዲጂታል ግብይት ተነሳሽነቶችን ተግባራዊ ማድረግ የተለያዩ አቀራረቦችን ሊያካትት ይችላል። ለምሳሌ፣ ለዝርያ ማሻሻያ መርሃ- ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 08 ግብሩ በተለይ የተዘጋጀ የመስመር ላይ የገበያ ቦታን ወይም መድረኮችን ማዘጋጀት፣ በአምራቾች እና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛ ግንኙነቶችን ሊያመቻች ይችላል። እነዚህ መድረኮች፣ ለገበያ የቀረቡ የእርባታ እና የሥጋ እንስሳትን ማሳየት፣ ዝርዝር መረጃ መስጠት፣ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ግብይት እንዲደረግ ማመቻቸት ይችላሉ። በተጨማሪም፣ የማህበራዊ ትሥሥር ገጾችን፣ ድረ-ገጾችኝ፣ እና የመስመር ላይ ማስታወቂያዎችን መጠቀም፣ መርሃ-ግብሩን እና ምርቶቹን ሰፋ ላሉ ታዳሚዎች ለማስተዋወቅ ይረዳል። CB BP ማ ዓ ዝ ማ (C B B P ) ም ክ (P U) ማ ክ (F U) ግ ክ (M U) የአ ም ራ ች ክ ፍ ል (P U ) የማ ደ ለ ቢ ያ ክ ፍ ል (F U ) የግ ብ ይ ት ክ ፍ ል (M U ) Aዘ ረ መ ል የተ ቀ በ ሉ የሥ ጋ እ ን ስ ሳ ት የዕ ሴ ት እ ከ ላ ለ ሚ ፈ ለ ገ ው አ ገ ል ግ ሎ ት የተ ዘ ጋ ጁ / የደ ለ ቡ እ ን ስ ሳ ት በ አ ካ ባ ቢ ው በ ት ል ል ቅ ከ ተ ሞ ች ኤ ክ ስ ፖ ር ት የዘ ረ መ ል ም ዘ ና እ ና መ ረ ጣ የአ ው ራ ዎ ች ን ብ ቃ ት ማ ረ ጋ ገ ጥ የአ ባ ለ ዘ ር አ ቅ ር ቦ ት ም ትክ ሴ ቶ ች ♀ ♂ ♀ ♀ ♂ ♀ ም ሥ ል 2 . የ በ ግ እ ና የፍ የል ማ ህ በ ረ ሰ ብ -ዓ ቀ ፍ የ ዝ ርያ ማ ሻ ሻ ያ መ ርሃ ግ ብ ሩ የ ማ ስ ፋ ፊ ያ ማ ዕ ቀ ፍ ። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ ዘላቂነት 09 የረጅም ጊዜ ስኬታማነቱን እና ተፅእኖውን ለማረጋገጥ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ ዘላቂነት በጣም አስፈላጊ ነው። አንድ ማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር (CBBP) ዘላቂ ነው ተብሎ የሚታሰበው በዋናነት፣ ማህበረሰቡ በንቃት የሚሳተፍበትና ተገቢውን ትርፍ በተከታታይ የሚያገኝበትናበህብረት ሰራ ማህበራቸው የሚመራ እና የሚተዳደር ከሆነ እና በኤክስቴንሽን ሥርዓት የሚደገፍ ከሆነ ነው። የመርሃግብሩን ዘላቂ የማስፋፊያ ማዕቀፍ ለማቋቋም፣ በርካታ ቁልፍ ነገሮች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር ዘላቂነት በሚከተሉት ነገሮች ይወሰናል፦ የማስፋፊያ ማዕቀፉን ትግበራ የሚያስችሉ ነገሮች፦ መኖ፣ የጤና አጠባበቅ፣ እና ጋጦች (ጉረኖዎች) የመኖ ልማት እና ስልታዊ ምገባ ምርጥ ዘረመሎችን (ዝርያዎችን) መጠቀምን ያበረታታል። ስትራቴጂካዊ የጤና አጠባበው የበጎችን እና የፍየሎችን እምቅ የዘረመል አቅም መገለጥ ያረጋግጣል። የአርቢዎች ማህበራት የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን ተቋማዊነት ያሻሽላሉ፣ ለዘላቂነቱም አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። ስለዚህ፣ እነዚህ አስቻይ ነገሮች የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን የሚያበረታቱ በመሆናቸው፣ ለተግባራዊነታቸው ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን ዘላቂነት ለማረጋገጥ፣ በመርሃግብሩ ክፍች እና፣ የልማት ትሩፋትን፣ የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት ፕሮጄክትን፣ የቆላ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጄክትን፣ የምግብ ሥርዓት ምርምር ፕሮጀክትን፣ የቀይ ስጋ መርሃግብርን፣ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ክፍሎችን፣ የሥጋ ማቀነባበሪያ ክፍሎችን፣ እና ቄራዎች በመሳሰሉ፣ በመካሄድ ላይ ባሉ፣ የመንግስት ተነሳሽነቶች መካከል ጠንካራ ትስስር መመስረት አስፈላጊ ነው። ይህ ቅንጅት መኖሩ፣ በእነዚህ ተነሳሽነት የሚቀርቡትን ሀብቶች፣ አውታረ- መረቦች፣ እና የድጋፍ ስልቶች ለመጠቀም ያስችላል። ከመንግስት ጥረቶች ጋር ያሉ ትሥሥሮች እንደ ዶሮ እርባታ እና የወተት ልማት ካሉ ሌሎች የእንስሳት ምርት ዘርፎች ጋር ሲነፃፀር፣ የበጎች እና የፍየሎች እርባታ፣ ለግል ባለሀብቶች ብዙም ማራኪ ሆኖ ላይታይ ስለሚችል፣ የአርቢዎችን እና የአምራቾችን ህብረት ስራ ማህበራትን ማጠናከር ወሳኝ ነው። እነዚህን የህብረት ሥራ ማህበራት ማጎልበት፣ ራሳቸውን ወደቻሉ ዘላቂ የንግድ ድርጅትነት እንዲያድጉ ማድረግ ይቻላል። ነባር እና አዳዲስ የንግድ ሥራ ሞዴሎችን በመጠቀምም የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን ኢኮኖሚያዊ ሕልውና ያረጋግጣሉ። የማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን የማስፋፋት ትልም፣ ከነባር የኤክስቴንሽን እቅዶች ጋር ማቀናጀት እና ወደታችኞቹ የአካባቢ ደረጃዎች እንዲዘልቅ ማስቻል ሰፋ ያሉ ተጠቃሚዎችን ለመድረስ እና የመርሃግብሩን ተፅእኖ ከፍ ለማድረግ አስፈላጊ ነው። ማዓዝማውን (ሲቢቢፒውን) ከዞን፣ ከወረዳ፣ እና ከቀበሌ የእንቅስቃሴ ዕቅዶች ጋር ማቀናጀት፣ የልማት ሠራተኞችን (DA) እና የSMS የሥራ አፈጻፀም ግምገማ፣ ከሚያከናውኗቸው የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሮች ውጤታማነት አንጻር ማድረግ ለመርሃግብሩ ዘላቂነት በጣም አስፈላጊ ነው። በመከናወን ላይ ካሉ የመንግስት የልማት ዕቅዶች ጋር ማቀናጀት ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 10 የማኅበረሰብ ቅስቃሳዎችን እና የመገናኛ ብዙኃን ዘመቻዎችን ማቀድ፣ እንዲሁም የመስክ ቀናትን እና የእንስሳት ትርዒቶችን ማደራጀትን ጨምሮ፣ ለመርሃግብሩ ጥብቅና መቆም እና የማስተዋወቂያ ጥረቶችን ማድረግ፤ የፖሊሲ አውጪዎችን፣ አጋሮችን እና ማህበረሰቦችን በማነሳሳት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። እነዚህ ተግባራት፣ በዋና ባለድርሻ አካላት ዘንድ፣ ግንዛቤን ለማሳደግ፣ ድጋፍን እና ተሳትፎንም ለማበረታታት ያስችላሉ። በማስፋፋት መዕቀፉ ክፍሎች መካከል ቋሚ ትስስርን መመስረት እና የአምራች ክፍሉን ውጤታማ አስተዳደር ማረጋገጥ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው። የባለብዙ ድርሻ አካል መድረክ ማቋቋምና ለመርሃግብሩ ዘላቂነት በጋራ መሥራት ተገቢ ነው። ውጤታማየምገባ፣ የጤና ክብካቤ፣ እና የገበያ ስትራቴጂዎችን እንደመጠቀም ያሉ አስቻዮችን (ወሳኝ ግብዓቶችን) ከመጠቀም ጎን ለጎን፣ የጥራት ማረጋገጫ የተሰጣቸውን አውራዎች/ ኮርማዎች መጠቀምን እና ለተሻሻሉ ዝርያዎች ከፍ ያለ የዋጋ ተመን መወሰንን የመሳሰሉ ተግባራዊ እርምጃዎችን ማስተዋወቅ፣ ለመርሃግብሩ ዘላቂነት ቁልፍ ምክንያቶች ናቸው። የኤክስቴንሽን ሂደቱን በባለቤትነት መያዝ፣ ከኤክስቴንሽን ክፍልጠንካራ ቁርጠኝነት እና ክትትል ማግኘት፣ እና የእንስሳት ትርዒቶችን እና የሬዲዮ ስርጭቶችን በመሳሰሉ መንገዶች ንቁ የጥብቅና እና የማስተዋወቂያ ጥረቶችን ማድረግ ለመርሃግብሩ ዘላቂነት ዘዋሪ ኃይሎች በመሆን ያገለግላሉ። የአርሶ-አደሮች ተሳትፎ እና ለዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ የሚያደርጓቸው አስተዋፅዖዎች የመርሃግብሩን ዘላቂነትን በእጅጉ ያሻሽላል። አርሶ-አደሮች አስተዋፅዖ ማድረግ የሚችሉበት አንዱ መንገድ፣ በመርሃግብሩ ውስጥ በንቃት በመሳተፍ እና የመጀመሪያውን የእርባታ አውራ/ኮርማ በመግዛት ነው። ይህ በመንጋው ውስጥ በቂና ጥሩ ኮርማዎች እንዲኖሩ ከማረጋገጡም ባሻገር፣ የተዘዋዋሪ ገንዘብ (ፈንድ) ዘዴን ይመሠርታል። አርቢዎች ለመርሃግብሩ የእርባታአውራዎችን/ ኮርማዎችን ለመግዛት የገንዘብ መዋጮ ማድረግ ወይም ከሌላ አካል በድጋፍ መልክ ሊያገኙ ይችላሉ። ይህ ምርሶ አደሮቹ የመንጋዎቻቸውን ምርታማነት እንዲያሳድጉ የሚስችሉ ጥራት ያላቸው የእርባታ እንስሳትንም እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር በተጨማሪ ለመርሃ-ግብሩ የመነሻ ካፒታል በመፍጠር የሥራ ሂደቱን ይደግፋል። የእርባታ አውራዎች/ ኮርማዎች አንዴ አገልግሎታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ፣ ለሥጋ ሊሸጡ ይችላሉ። ይህም፣ ከመንጋው የሚወለዱና የሚመረጡ ምርጥ ምትክ አውራዎችን/ኮርማዎችን ለመግዛት ወይም ሌሎች ፍላጎቶችን ለማሟላት ያገለግላል። አርሶ አደሮችን በሂደቱ ውስጥ ማሳተፍ እና ተዘዋዋሪ ገንዘብ ለመፍጠር መዋጮዎቻቸውን መጠቀም፣ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ የበለጠ በገንዘብ ራሱን የቻለ እና ዘላቂ እንዲሆን ያስችላል። ይህ አሰራርም በአርሶ- አደሮች ዘንድ ለመርሃግብሩ ስኬት የኃላፊነት እና የተጠያቂነት ስሜት እንዲፈጠረ ያደርጋል። በዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሮች ውስጥ የዘረመል ብልጸጋን (መሻሻልን) ለማፋጠን፣ ተፈላጊ ግብዓቶች የሚገኙ ከሆነ፣ ሰው-ሠራሽ የማስጸነሻ ዘዴን (አርቲፊሻል ኢንሲሚኔሽን ወይም AI) መጠቀም ይቻላል። በአሁኑ ጊዜ፣ ኢካርዳ (ICARDA) እና የምርምር እና የዩኒቨርሲቲ አጋሮቹ፣ በመላ አገሪቱ ውስጥ፣ ወጪ ቆጣቢ የሆኑ የሰው-ሠራሽ ማስጸነሻ ላቦራቶሪዎችን አቋቁመዋል። በዩኒቨርሲቲዎች እና በምርምር ማዕከላት የሚካሄዱት እነዚህ ላቦራቶሪዎች፣ የዘረመል ማሻሻያውን በማስተዋወቅ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ተንቀሳቃሽ የኃይል ማመንጫዎችን (ጀነሬተሮችን)፣ አልትራሳውንዶችን፣ ስፔክትሮፎቶሜትሮችን፣ ማይክሮስኮፖችን፣ እና ሌሎች የወንድ ዘር መሰብሰብያ፣ ማዘጋጃ፣ እና የወንዴውን ዘር ወደሴቷ ማሕጸን የማስገቢያ መሳሪያዎችን ጨምሮ፣ አስፈላጊ መገልገያዎች የተገጠሙባቸው እነዚህ ላቦራቶሪዎች፣ የውስን ጊዜ የሰው-ሠራሽ ማስጸነሻ ሥነ-ሥርዓቶችን (ፕሮቶኮሎችን) ተግባራዊ ማድረግ ያስችላሉ። ይህ፣ ሴት እንስሳት ለጽንስ ዝግጁ የሚሆኑበትን ዑደት መጠበቅን እና አዲስ የወንድ የዘር ፍሬዎችን ለማስጸነስ መጠቀምን ያካትታል። በተጨማሪም፣ ማቀዝቀዣ ሳጥኖችን የያዙት የሰው-ሠራሽ የማስጸነሻ ቴክኖሎጂ ጥቅሎች፣ ትኩስ የወንዴ ዘር ሳይበላሽ የሚቀመጥበት ጊዜ ወደስድስት ሰዓት አካባቢ እንዲረዝም ያግዛሉ። ይህም፣ ራቅ ወዳሉ የገጠር አካባቢዎች በሚጓጓዙበት ጊዜ፣ የዘረመል ሕዋሶቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲቆይ በማድረግ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ዘረመሎች እንዲሠራጩ ያደርጋል። ስለዚህም፣ የህ ሠው-ሠራሽ የማስጸነስ ዘዴ፣ በተፈጥሮአዊው መንገድ ከሚደረገው የማስጸነስ ሂደት የተሻለ ውጤታማነት ይኖረዋል። ተዘዋዋሪ ገንዘብ እና የአርሶ-አደር ተሳትፎ ሰው-ሠራሽ የማስጸነሻ ዘዴን በመጠቀም የዘረመል ብልጸጋን ማሳደግ ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 ቁልፍ ክፍል አንድ፦ የማስፋፊያ ማዕቀፉን ለሚፈለገው ዝርያ እንዲስማማ ማድረግ 11 የማስፋፊያ ማዕቀፉን ተቀብሎ ለመተግበር በተመረጠው ዝርያ ላይ በመከናወን ላይ ያሉ የማህበረሰብ- ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር (ሲቢቢፒ) እና አምራች ክፍል (PU) ቦታዎች፣ በሌሎች ተዛማጅ ተነሳሽነቶች ላይ ሁሉን-አካታች ግንዛቤ መኖሩ፣ እንዲሁም በአካባቢው ያሉ ተሳታፊና ሊሳተፉ የሚችሉ አጋሮች ለይቶ ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ወቅት፣ የበጎች እና የፍየሎች ማዓዝማ መርሃግብር፣ በመላው ሀገሪቱ 188 መንደሮችን የሚገኙ ሲሆን፤ እነዚህ ማዓዝማዎች (ሲቢቢፒዎች)፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ መካከለኛው ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ሲዳማ፣ ትግራይ፣ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ይገኛሉ (ምሥል 3)። የማዓዝማዎች እና የአምራች ክፍሎች መልክዓምድራዊ ሥርጭት ምሥል 3፡ በኢትዮጵያ የበግ እና የፍየል ማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር ስርጭት። ፍየል በግ ኢትዮ-ዞኖች ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 12 እነዚህ መርሃግብሮች የሚመሩት በግብርና ምርምር ማዕከላት፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ እና እንደ LLRP ምርምር እና የኦሮሚያ ኤክስቴንሽን እና ምርምር ጥምረት ባሉ የጋራ ተነሳሽነቶች ነው። በተጨማሪም፣ እንደ የውሃ እና የመሬት ሀብት ማዕከል (WLRC) ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ተሳትፈዋል። በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ የተለያዩ ተቋማት በተመሳሳይ ወይም አንድ ዝርያ ላይ የሚመሳሰሉየምርት አከባቢዎች እና የርቢያ ዓላማዎች ያሏቸውን ማህበረሰቦችን ዒላማ በማድረግ በመስራት ላይ ይገኛሉ። ከ188 የማዓዝማ መንደሮች በተጨማሪ፣ወደ 200 የሚጠጉ የማምረቻ ጣቢያ መንደሮች በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ተሰራጭተው ይገኛሉ። እነዚህ ጣቢያዎች የተመሠረቱት እና የሚተዳደሩት በዋናነት በእንስሳት የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ በእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ሴክተር ልማት ፕሮግራም (LFSDP)፣ እና በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጄክ (LLRP) ነው። ማሥፋፋትን ለማቀላጠፍ እና ቅንጅትን ለማሻሻል፣ በተለያዩ ተቋማት የሚተዳደሩ ድንበርተኛ (አጎራባች) ማዓዝማዎችን (CBBPs) እና የእርባታ ክፍል (PUs) ቦታዎችንእንደ አንድ ስብስብ መቁጠር (ክላስተሪንግ) እንደ ቁልፍ ስትራቴጂ በጥቅም ላይ ውሏል። ይህ የክለስተሪንግ (ስብስብ) አሰራር ማዓዝማዎችን ለማስፋፋት ያግዛሉ፣ በተወሰኑ መልክዓምድራዊ አካባቢዎች ውስጥ፣ ውጤታማነታቸው የተረጋገጡ የመኖ ምገባ፣ የጤና ክብካቤ፣ እና የገበያ ሥርዓቶች ጥረቶች እንዲቀናጁ ያስችላሉ። በውስን አካባቢ የሚከናወን ስብስበን መሰረት ያደረገ የማስፋፋት ስራ በአካባቢውያሉ የበጎች እና የፍየሎች ጠቅላላ መንጋዎችን ዒላማቸው በማድረግ ስለሚሰሩ፤ በሌሎች አካባቢዎች ተደግመው የሚተገበሩና ሊስፋፉ የሚችሉ ሞዴል የማስፋት ዘዴዎች እንዲጎለብቱ ያደርጋል። ስብስቦችን መፍጠር (ክላስተሪንግ)፣ ሀብቶችን፣ ሙያዊ-ብቃቶችን እና ተቋማትን፣ የምርምር ማዕከላትን፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ እና የልማት አጋሮች ጨምሮ፣ በባለድርሻ አካላት መካከል የሚደረጉ ትብብሮችን፣ ወደሚፈለገው ቦታ ለማሰባሰብ (ለማከማቸት) ያስችላሉ። ይህ ትብብራዊ አቀራረብ፣ ውጤታማነትን ያሻሽላል፣ የጥረቶችን አላስፈላጊ ድግግሞሽ ይቀንሳል፣ እንዲሁም የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን ውጤታማነት ከፍ ያደርጋል። እንዲሁም ተመሳሳይ የምርት አከባቢዎች እና ዕርባታ ዓላማዎች ባላቸው ማህበረሰቦች መካከል የሚፈጠረውን የውህደት ኃይል ለመለየት እና ለመጠቀም ያስችላል። በስብስብ ውስጥ ባሉ በተወሰኑ ዝርያዎች ላይ በማተኮር፣ መርሃግብሩ የተለመዱ የጋራ ተግዳሮቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ መፍታት፣ የመፍትሔ እርምጃዎችንም መውሰድ ይችላል። ይህም የተሻሻለ ምርታማነትን እና የዘረመል ውጤትን መፍጠር ያስችላል። ምሥል 4፡ በዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ ውስጥ ያሉ የበጎች (በስተግራ) እና የፍየሎች (በስተቀኝ) ስብስቦች (ክላስተሮች)። በምሥሉ ውስጥ፣ ደማቅ ቀለም የተቀቡ ክፍሎች ከወዲሁ የተመሠረቱ ስብስቦችን ሲያሳዩ፣ ነጠብጣባማ እና ፍርግርግ ቅብ ያሉባቸው ቦታዎች ወደፊት ሊመሠረቱ የሚችሉ ስብስቦችን ያመለክታሉ። የማዓዝማ መርሃግብርን ለማስፋፋት ክለስተርን እንደ ስትራቴጂ መጠቀም ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 13 ስብስቦችን መፍጠር እና የማስፋፋት ማዕቀፉን ማካሄድ፣ ሰፋ ያለ የዘረመል ኩሬ (ስብስብ) እና የዘረመል ብዝሃነትእንዲኖር ያደርጋል፣ ይህም በመሆኑ ካለው ሰፊ የዘረመል ክምችትና መለያየት (ብዝሃነት) ውስጥ ከፍተኛ የዘረ-መል አቅም ያላቸውን እንስሳት በመምረጥ ከፍተኛ የምርታማነት መሻሻል ማምጣት ከማስቻሉም በላይ፤ ጥቅምን መሠረት ያደረገ የዝርያ ጥበቃ ስራ እንዲኖር ያደርጋል። በዝርያ ደረጃ ለሚደረግ መሻሻል የማስፋፊያ ስብስቦችን መፍጠር፣ የየራሳቸውን ዝርያዎች ጥራት ለማሻሻል በጋራ ለመሥራት ፈቃደኛ በሆኑ አጋሮች የጋራ ፍላጎትእና ትብብር ላይ የተመሠረተ ነው። የማስፋፊያ ስብስቦች (ክላስተሮች) ወሰን በፖለቲካም ሆነ በሌሎች የልማት ስራዎች ማዕቀፍ የተገደበ አለመሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። በእነዚህ ጥረቶች አማካኝነት፣ የማስፋፋት ማዕቀፉ ዓላማ ምርታማነትን ማሳደግ፣ የዘረመል ብዝሃነትን ማበልጸግ፣ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የበግ እና የፍየል መንጋዎችን አጠቃላይ ተለዋዋጭ የአየር ንብረትና አካባቢን የመቋቋም አቅምን ማሻሻል ነው። ክላስተሮችእንደ የእውቀት እና የሙያዊ-ብቃት ማዕከል ሆነው ያገለግላሉ፤ በባለድርሻ አካላት መካከል ትብብርን ያጎልበታሉ፣ የተሻሉ ልምዶችን እና ስኬታማ የዝርያ ማሻሻያ ስልቶችን በውጤታማነት ማሰራጨትንም ያስችላሉ። እነዚህን የመስፋፋት ዓቅም ያላቸው ሞዴሎች በመተግበር እና የበለጠ በማሻሻል፣ በመላ አገሪቱ ውስጥ ባለው የበግ እና የፍየል እርባታ ተሞክሮ ላይ ዘላቂነት እና ጉልህ ተፅእኖ ያላቸው ማሻሻያዎችን ለማሳካት ያልማሉ። ባሏቸው ሰፊ መልከዓምድራዊ ሽፋን እና የተለያዩ ዝርያዎች በአንድ ክልል ውስጥ በሚኖሩበት ጊዜ በአንድ ክልል ውስጥ በርካታ ስብስቦችን ማቋቋም ይቻላል። በተቃራኒው ደግሞ፣ የተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይ የበግ እና የፍየል ዝርያዎችን የሚይዙ እና ትናንሽ መልክዓምድራዊ አካባቢዎችን የሚሸፍኑ ሆነው ሲገኙ፣ አንድ ስብስብ ከአንድ በላይ ክልሎችን ሊያካትት ይችላል። ይህ ቅንብር፣ በበርካታ ክልሎች መካከል የተቀናጁ እርምጃዎችን እና የሀብት ምደባዎችን ያመቻቻል፣ አንድ የተለያዩ ዝርያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሁሉን-አካታቸ የሆነ አሰራር እንዲፈጠርም ያስችላል። እስካሁን ድረስ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለበጎች በድምሩ አምስት ስብስቦች የተቋቋሙ ሲሆን፣ ለፍየሎች ደግሞ አንድ ስብስብ ተቋቁሟል። እነዚህም፦ በዋሸራ እና በወሎ በጎች ላይ ትኩረት የሚያደርገው የዋሸራ-ወሎ (ዋዎ) ስብስብ፤ በመንዝ በግ ዝርያ ላይ ትኩረት የሚያደርገው የመንዝ-ሸዋ ስብስብ፤ በቦንጋ የበግ ዝርያዎች ላይ ትኩረት የሚያደርገው የቦንጋቾ ስብስብ፣ በማዕካላዊ እና በደቡባዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ባሉ የበግ ዝርያዎች ላይ ትኩረት የሚያደርገው የደቡብ ማዕከላዊ ስብስብ፣ በሆሮ የበግ ዝርያዎች ላይ ትኩረት የሚያደርገው የሆሮ-ወንጪስብስብ፣እና በደቡብ ኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች ውስጥ ባሉ የቦረና፣ የኦሞ፣ እና የኮንሶ የፍየል መንጋዎች ላይ ትኩረት የሚያደርገው የቡም ስብስብ ናቸው። (ምሥል 4) ማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሮችን ስኬታማ ለማድረግ፣ በተወሰኑ መስፈርቶች ላይ በመመርኮዝ፣ በቅድሚያ ትኩረት የሚደረግበትን ዝርያ መወሰን አስፈላጊ ነው። እነዚህ መመዘኛዎች፣ የዝርያውን የመንጋ ብዛት፣ ለቤተሰብ መተዳደሪያ እና ለሀገር ገቢ የሚያበረከተውን አስተዋፅኦ፣ እንዲሁም በመካኼድ ላይ ያሉ ማዓዝማ መርሃግብሮች (CBBPs) እና ሌሎች ተዛማጅ ተነሳሽነት መኖር-አለመኖር እና ያሉበትንም ሁኔታ መረዳትን ያካትታል። የአምራችክፍሎችን (PU) ማቋቋም፣ አሁን ባሉት ማዓዝማዎች ውስጥ ያሉ የርቢያ አውራዎችን/ ኮርማዎችን የማምረት አቅም በመገምገም መርህ መሠረት መመራት አለበት። ሆኖም፣ አሁን ያሉት ማዓዝማዎች የዝርያውን አጠቃላይ ቁጥር ለመሸፈን በቂ ላይሆኑ እንደሚችሉ ልብ ማለት ያስፈልጋል። አሁን ያሉት ማዓዝማዎች በቂ ባልሆነበት ሁኔታ ውስጥ፣ መላውን የዝርያውን የመንጋ ብዛት ለመሸፈን የሚያስፈልገውን የተጨማሪ ማዓዝማዎች (CBBPs) ብዛት መወሰን ቀላል እና ቀጥተኛ በሆነ ስሌት አማካኝነት ሊከናወን ይችላል። ይህ ስሌት ማዓዝማዎች አውራዎችን/ኮርማዎችን ለማምረት ያላቸው አቅምን፣ የአውራው/የኮርማው የአገልግሎት ዓመታት ርዝመትን፣ የወንድ-ሴት ጥምርታን (አንድ ወንድ ለስንት ሴት እንደሚዳረስ)፣ ዝርያው በቦታው ውስጥ ያለውን ጠቅላላ የመንጋ ብዛት፣ በመሳሰሉ ነገሮች ዙሪያ ያጠነጥናል። እነዚህን ነገሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት እና ጥንቃቄ የተሞላቸው ስሌቶችን በማድረግ፣ አሁን ያሉት ማዓዝማዎች (ሲቢቢፒዎች) መሰረት በማድረግ ሊቋቋሙ የሚገባቸውን የአምራች ክፍሎች (PU) ቁጥር የዝርያ ቅድሚያዎችን መወሰን እና የማስፋፊያ ዕምቅ አቅሞችን መገመት ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 14 መወሰን ይቻላል። በተጨማሪም፣ ይህ ትንታኔ፣ የዝርያው አጠቃላይ የመንጋ ብዛት ሙሉ ሽፋን ያገኝ ዘንድ የሚያስፈልጉትን ተጨማሪ ማዓዝማዎች ብዛት ለመወሰንም ይረዳል። ይህንን ስትራቴጂካዊ አቀራረብ መከተል ማዓዝማዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማቀድን እና መተግበርን ያስችላል፣ የማስፋፊያ ጥረቶችም ከታለመው ዝርያ እና ከማህበረሰቡ ልዩ ፍላጎቶች እና አቅም ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን ያረጋግጣል። 500 ያህል የእርባታ ሴቶች ያሉትን የቦንጋ የበግ ማዓዝማ (ሲቢቢፒ) እንመልከት። የእርባታ ክፉልን መጠን እና በየዓመቱ ሊመረቱ የሚችሉ የሥጋ እንስሳት ብዛት እንገምታለን። ደረጃዎች፦ 1. ሥነ-ሕይወታዊ (ባዮሎጂካዊ) እና የመንጋ ልኬቶችን ከነባር መረጃዎች (የሚገኝ ከሆነ)፣ ከጥናት ጽሑፎች፣ እና ከማዕከላዊ የስታቲስቲክስ ባለሥልጣን መረጃ መሰብሰብ። ይህ የሚከተሉትን ያካትታል፦ የመፀነስ መጠን በውልደቶች (በጽንስ) መካከል ያለ የጊዜ ክፍተት መንታ የመውለድ መጠን የጠቦት እና የአዋቂዎች በሕይወት የመቆየት መጠን የአውራው/የኮርማው የአገልግሎት ጊዜ ርዝመት ሴቶችን የመተካት ፍጥነት የመረጣ መጠን የወንድ-ለሴት ጥምርታ የዝርያው ጠቅላላ የመንጋ ቁጥር (ብዛት) 2. በመካሄድ ላይ ባለው የቦንጋ በግ ማዓዝማ እና በታተሙ ጽሑፎች ላይ በመመርኮዝ፣ የሚከተሉት እሴቶች ተገኝተዋል፦ የመፀነስ መጠን (መቶኛ) = 90% በውልደቶች (በጽንስ) መካከል ያለ የጊዜ ክፍተት (ቀናት) = 228 መንታ የመውለድ መጠን (በአንድ ውልጃ ጊዜ የተወለደ በግ ቁጥር) = 1.45 አንድ በግ፣ ከውልደት እስከ መረጣ ዕድሜ ድረስ ያለው የመኖር ዕድል (በመቶ) = 90% የትላልቅ እንስሳት አመታዊ የመኖር ዕድል (በመቶ) = 95% የዕርባታ አውራው/ኮርማው የአገልግሎት ዘመን ርዝመት (ዓመታት) = 3 ሴቶችን የመተካት ፍጥነት መጠን (በመቶ) = 15% በአካላዊ አቋም የመቀነስ (የማስወገድ) መጠን (መቶኛ) = 5% የመረጣ ምጣኔ (በመቶ) = 0.5% የወንድ-ለሴት ጥምርታ - 1:25 በተመለከተው አካባቢ የዝርያው አጠቃላይ የርቢ ሴቶች ቁጥር = 471,285 3. ከላይ በተሰጠው መረጃ መሠረት፦ 1.አንዲት እናት በግ በዓመት የምትወልዳቸው ግልገሎች ቁጥር (አመታዊ የውልደት መጠን) እንደሚከተለው ሊሰላ ይችላል፦ = 365/በውልደት መካከል ያል የጊዜ ክፍተት * የመጸነስ መጠን * መንታ የመውለድ መጠን = 365/228 ቀናት * 0.9 * 1.45 = 2.09 ግልገሎች 2.ከ500 የርቢ እናት በጎች የሚወለዱ ግልገሎች ጠቅላላ ብዛት እንደሚከተለው ይሰላል፦ የርቢያ ሴቶች ብዛት * አመታዊ የውልደት መጠን = 500 * 2.09 = 1044 ግልገሎች በዓመት 3.በማዓዝማው ውስጥ ያሉ (የሚፈለጉ) የርቢ አውራዎች/ኮርማዎች ጠቅላላ ብዛት፦ = የርቢ ሴቶች/በአንድ ወንድ የሚሰረሩ ሴቶች ብዛት = 500/25 = 20 4.የጥራት ማረጋገጫ ያላቸው አውራዎችን/ኮርማዎችን ማምረት ከሚወለዱ በጎች ውስጥ 50% የሚሆኑት ወንዶች ናቸው ብሎ በማሰብ እና ለመረጣ ዕድሜ የመድረስ መጠንን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የመረጣው ምጣኔ እንደሚከተለው ይሰላል፦ = በየዓመቱ የሚወለዱ ግልገሎች ብዛት * የወንድ ጠቦቶች መጠን * የበግ ጠቦቶች እስከመረጣ በሕይወት የመቆየት ዕድል * በአካላዊ ገጽታ ምክንያት ከሚደረግ ቅነሳ የመትረፍ መጠን * የመረጣ መጠን የጥራት ማረጋገጫ የሚሰጣቸው አውራ በጎች ብዛት = 1044 * 0.5 * 0.90 * 0.95 * 0.5 = 223 5.በአንድ ማዓዝማ ውስጥ በዓመት የሚያስፈልገው የአውራ/ኮርማ ብዛት አንድ አውራ/ኮራም 25 የርቢ ሴቶችን ያገለግላል፣ ምሳሌ፦ ቦንጋ የበግ ማዓዝማ ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 15 5.በአንድ ማዓዝማ ውስጥ በዓመት የሚያስፈልገው የአውራ/ኮርማ ብዛት አንድ አውራ/ኮራም 25 የርቢ ሴቶችን ያገለግላል፣ የአገልግሎት ዘመኑም 3 ዓመት ነው፣ አንድ አውራ/ ኮርማ በሕይወት የመቆየት ዕድሉም 95% ነው ብንል፣ በአንድ ማዓዝማ በዓመት የሚያስፈልገው የአውራ/ ኮርማ ቁጥር እንደሚከተለው ይሰላል፦ ((በማዓዝማው ውስጥ ያሉ ሴቶች ቁጥር/ በአንድ አውራ የሚገለገሉ ሴቶች ቁጥር)/ የአውራው የአገልግሎት ዘመን) * (1/የአዋቂዎች በሕይወት የመቆየት ዕድል) ((500/25)/3) * (1/0.95) = 7 ምትክ አውራ በየአመቱ በማዓዝማው ያስፈልጋል 6.ለአምራቹ ክፍል የሚያስፈልጉ የርቢ አውራዎች/ ኮርማዎች ብዛት = የጥራት ማረጋገጫ ያላቸው አውራዎች/ኮርማዎች ጠቅላላ ብዛት - ለማዓዝማ የሚፈለገው የምትክ ቁጥር = 223 – 7 = 216 7.በአምራቹ ክፍል ውስጥ የርቢ ሴቶች ብዛት ይህ ከማዓዝማው በሚመረተው የአውራዎች ቁጥር መሠረት ሊታለም ይችላል፣ እንደሚከተለውም ይሰላል፦ = ለአምራቹ ክፍሉ የተዘጋጁ አውራዎች/ኮርማዎች ብዛት * በአምራቹ ክፍሉ ውስጥ የአውራዎች/ ኮርማዎች የአገልግሎት ዘመን * በአንድ አውራ/ኮርማ የሚጠቁ ሴቶች ብዛት = 216 * 3 * 25 ~ 16,220 8.በአምራቹ ክፍል ውስጥ የሚመረቱ ጠቦቶች ጠቅላላ ብዛት = በአምራቹ ክፍል ውስጥ ያሉ የርቢ ሴቶች ብዛት * አመታዊ የውልደት መጠን = 16,220 * 2.09~ 33,885 9.ከአምራቹ ክፍል ውስጥ ለሽያጭ የሚቀርቡ ወንዶች ጠቅላላ ብዛት በመሠረቱ፣ በአምራቹ ክፍል ውስጥ የሚመረቱ ወንዶች በሙሉ ለሽያጭ ዝግጁ መሆን አለባቸው = በአምራቹ ክፍል ውስጥ የሚወለዱ በጎች ጠቅላላ ብዛት * የወንድ መጠን * እስከ መረጣ ዕድሜ በሕይወት የመቆየት ዕድል = 33,885 * 0.5* 0.9 ~ 15,248 10. ከአምራቹ ክፍል ውስጥ ለሽያጭ የሚቀርቡ ሴቶች ጠቅላላ ብዛት 15% ሴቶች ለምትክነት ስለሚፈለጉ፣ 85% ሴቶች ለሽያጭ ዝግጁ ይሆናሉ = የሚወለዱ በጎች ጠቅላላ ብዛት * የሴት መጠን * እስከመረጣ ጊዜ የመቆየት ዕድል - (ጠቅላላ በጎች * የምትክ በጎች መጠን) = 33,885* 0.5* 0.9 – (16,220*0.15) = 12,815 11. ለሽያጭ የሚቀረቡ የአዋቂ ወንዶች ጠቅላላ ቁጥር = ለምትክነት በየዓመቱ የሚፈለጉ በጎች ቁጥር = (በማምረቻው ክፍል ውስጥ ያሉ ጠቅላላ የርቢ አውራዎች ብዛት/ የአውራዎች የአገልግሎት ዘመን) * (1/የአዋቂዎች የሞት መጠን) = (216 / 3)* (1/0.95) = 76 12. ከአምራችክፍል ውስጥ ለሽያጭ የሚቀርቡ የአዋቂ ሴቶች ጠቅላላ ብዛት ይህ በእርጅና ምክንያት ለሽያጭ ከሚቀርቡ የሴቶች ቁጥር ማለት ሲሆን፣ ይህም ከሴት በጎች ውስጥ 15% ነው = በአምራች ክፍል ውስጥ ያሉ የአዋቂ ሴት በጎች ብዛት * የምትክ መጠን =16,220* 0.15 = 2,432 13. ከማዓዝማው ክፍል ውስጥ ለሽያጭ የሚቀርቡ የወንድ በጎች ጠቅላላ ብዛት = በማዓዝማ ውስጥ የሚወለዱ በጎች ጠቅላላ ብዛት * የወንድ መጠን * ለመረጣ ዕድሜ የሚደርሱ በጎች መጠን) - የጥራት ማረጋገጫ የሚሰጣቸው አውራዎች ብዛት = (1044 * 0.5 * 0.90) – 223 = 247 14. በማዓዝማው ውስጥ ለሽያጭ የሚቀርቡ ሴቶች ጠቅላላ ብዛት = የተወለዱ በጎች ጠቅላላ ብዛት * የሴት መጠን * እስከመረጣ ጊዜ በሕይወት የመቆየት ዕድል * (1- የምትክ በጎች መጠን) = 1044 * 0.5 * 0.90 – (500*0.15) = 395 15. ለሽያጭ የሚቀረቡ የአዋቂ ወንዶች ጠቅላላ ቁጥር = ለምትክነት በየዓመቱ የሚፈለጉ በጎች ቁጥር = (በማዓዝማ ውስጥ ያሉ የርቢ አውራዎች ብዛት/ የአውራዎች የአገልግሎት ዘመን) * (1/የአዋቂዎች የሞት መጠን) = 20 / 3 * (1/0.95) = 7 16. ከማዓዝማ ውስጥ ለሽያጭ የሚቀርቡ የአዋቂ ሴቶች ጠቅላላ ብዛት ይህ በእርጅና ምክንያት ለሽያጭ ከሚቀርቡ የሴቶች ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 16 ቁጥር ማለት ሲሆንይህም ከሴት በጎች ውስጥ 15% ነው = በማራቢያ ክፍል ውስጥ ያሉ የአዋቂ ሴት በጎች ብዛት * የምትክ መጠን =500 * 0.15 = 75 17. በአምራቹ ክፍል ውስጥ ጠቅላላ የሽያጭ መጠን = ከ9 እስከ 12 ያሉት ጠቅላላ ድምር = 15,248 + 12,815 + 76 + 2433 = 30,572 18. በማዓዝማ ውስጥ ጠቅላላ ሽያጭ = ከ13 እስከ 16 ጠቅላላ ድምር = 247 + 395 + 7 + 75 = 724 19. በማዓዝማ እና በአምራች ክፍል ውስጥ ጠቅላላ ዓመታዊ ሽያጭ = 30,571 + 724 = 31,296 20. ጠቅላላ የርቢ ሴቶች ብዛት = ከጠቅላላው በጎች 60% ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ባለሥልጣን በተገኘው መረጃ መሠረት፣ በሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች-ማጂ፣ እና ዳውሮ ውስጥ ያሉ ጠቅላላ በጎች ብዛት = 812,509 = 812,509 * 0.6 = 487,505 ከላይ በተጠቀሱት ስሌቶች መሠረት እና እና በሠንጠረዥ 1 ውስጥ እንደተገለጸው፣ አንድ ማህበረሰብ ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ (ሲቢቢፒ) 216 የርቢ አውራዎችን የማምረት አቅም ሲኖረው፣ እነዚህም 16,220 የርቢ ሴቶችን በውጤታማነት ሊያስጸንሱ ይችላል። በታለመው አካባቢ ያሉ 487,505 የርቢ በጎችን በሙሉ ለማስተናገድ፣ አሁን ካለው ማዓዝማ ጋር ተመጣጣኝ አቅም ያላቸው ወደ 30 የሚጠጉ ማዓዝማዎች (CBBPs) ያስፈልጋሉ። ይህም የተሰላው፣ 487,505ን በ16,220 በማካፈል ነው። በአሁኑ ጊዜ፣ በአምራች ክፍል ውስጥ 389,267 የርቢ ሴት በጎችን መሸፈን የሚችል፣ ለቦንጋ በጎች የሚሆኑ፣ 24 ማዓዝማዎች አሉ። ይህ የሚያሳየው፣ በቦንጋ ውስጥ ያለውን የመንጋ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ውስጥ ያሉ ሌሎች በጎችን በበቂ ሁኔታ ለመሸፈን ተጨማሪ 6 ማዓዝማዎች ያስፈልጋሉ ማለት ነው። በቀደሙት ስሌቶች ላይ በመመርኮዝ፣ እያንዳንዱ ማዓዝማ (CBBP) በግምት 31,296 የሚሆኑ እንስሳት ለሽያጭ የማምረት አቅም አለው። በአጠቃላይ ከ24ቱ ነባር ማዓዝማዎች ጋር፣ ጥምሩ አቅም፣ 31,296 በ24 ተባዝቶ፣ በግምት 751,104 አካባቢ እንስሳትን በየአመቱ ለሽያጭ በቦንጋቾ ስብስብ ውስጥ የማስፋፋት ዕምቅ አቅም ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 17 ሰንጠረዥ 1፡ በቦንጋ ስብስብ ውስጥ የማስፋፋት ዕምቅ አቅም ልኬት የማዓዝማዎች ብዛት በማዓዝማ ውስጥ ያሉ ሴቶች ብዛት የተረጋገጡ አውራዎች ለማዓዝማው የሚፈለጉ ምትክ አውራዎች አምራች ክፍል ውስጣ ያሉ አውራዎች አምራችክፍሉ ውስጥ ያሉ የርቢ ሴቶች ብዛት ለሽያጭ የሚቀርቡ ጠቅላላ እንስሳት ብዛት በየዓመቱ በማዓዝማ ውስጥ የሚመረቱ ወንድ የሥጋ በግ ከማዓዝማው ለሽያጭ የሚቀርቡ ሴት በግ/ግልገልከማዓዝማው ተቀናሽ ሆነው የሚሸጡ ወንዶች ብዛት ከማዓዝማው ተቀንሰው ለሥጋ የሚሸጡ የርቢ ሴቶች (በየአመቱ 15%) ከታለሙ አምራች ክፍሎች የሚመረተው ወንድ የሥጋ እንስሳት ከታለሙ አምራች ክፍሎች የሚመረቱ ሴት የሥጋ እንስሳት ከአምራች ክፍሉ ተከልተው የሚሸጡ ወንዶች ብዛት ከአምራች ክፍሉ ተከልተው የሚሸጡ የርቢ ሴቶች ብዛት (በየአመቱ 15%) ከማዓዝማውና ከአምራቹ ለሽያጭ የሚቀርቡ ጠ. የወንድ በጎች ብዛት ከማዓዝማው እና ከአምቹ ለሽያጭ የሚቀርቡ ጠ. የሴት በጎች ብዛት ከማዓዝማውና ከአምራቹ ክፍሉ ተቀናሽ ሆነው የሚሸጡ ወንዶች ብዛት ከማዓዝማው እና ከአምራቹ ክፍሉ ተቀናሽ ሆነው የሚሸጡ ሴቶች ብዛት በታለመው አካባቢ ውስጥ ያሉ ጠቅላላ የበግ/ፍየል መንጋ ብዛት ጠቅላላ የታለሙ የርቢ ሴቶች ብዛት (ከጠቅላላው መንጋ 60% ) መላውን የመንጋ ቁጥር ለመሸፈን የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ማዓዝማዎች 24 12000 5359 168 5190 389268 751106 5923 9481 168 1800 365956 307566 1821 58390 371879 317048 1990 60190 812509 487505 6 1 500 223 7 216 16219 31296 247 395 7 75 15248 12815 76 2433 15495 13210 83 2508 812509 487505 29 30 15028 6711 211 6500 487505 940660 7417 11874 211 2254 458311 385185 2281 73126 465729 397060 2492 75380 812509 487505 0 ነጠላ ማዓዝማ ሉማ ዓዝማዎች ሙሉ ዕምቅ አቅም ቦንጋ ቦንጋ ቦንጋ አቅርቦት ማምረት ያስችላል። እነዚህ እንስሳት ወንድና ሴት ጠቦቶችን፣ የተቀነሱ የርቢ ሴት በጎችን፣ እና ከዕርባታ የተወገዱ አውራ በጎችን ይጨምራል። በተመሳሳይ መልኩ፣ ከላይ የተጠቀሱትን የስሌት ደረጃዎችን በመከተል፣ የሌሎችንም የሚታለሙ ስብስቦች ወይም መንጋዎች የማስፋፋት ዕምቅ አቅም ማወቅ ይቻላል። ስሌቶቹ ለዚህ ዓላማ በተዘጋጁትን የኤክሴል ሰንጠረዦች በመጠቀም ቀላል እንዲሆን ማድረግ ይቻላል (ይህንን ሰንጠረዥ ከግብርና ሚኒስቴር በመጠየቅ ማግኘት ይቻላል)። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 ክፍል ሁለት የአተገባበር ሂደት 18 ለአንድ የተወሰነ ዝርያ ወይም መንጋ፣ አንድ ልዩ ማዕቀፍ (መዋቅር) ተቀባይነት ካገኘ በኋላ፣ የአካባቢውን የበግ እና የፍየል ዝርያዎችን ለማሻሻል ማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብርን እንደስትራቴጂ መመወሰዱን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ በክልል እና በወረዳ ደረጃዎች የሚገኙ፣ የተመራማሪዎች፣ የኤክስቴንሽን ሠራተኞች፣ የዩኒቨርሲቲዎች፣ እና የሌሎች የልማት አጋሮች ቡድን፣ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን በየክልላቸው ውስጥ ለማስፋፋት እና ለመተግበር እቅድ ለማውጣት መሰባሰባቸው እጅግ አስፈላጊ ነው። በባለድርሻዎች ተሳትዎ ውስጥ የስብስብ (ክለስተሪንግ) አቀራረብ (ምሥል 3) ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።እነዚህ ዕቅዶች፣ አስፈላጊ የሆነውን የሰው እና የገንዘብ ሀብት ማሰባሰብና መጠቀምን ማካተት አለባቸው። የባለድርሻ አካላት መድረክ እና ዕቅድ የማስፋፋት ሂደቱን ለማቀላጠፍ በእያንዳንዱ ክላስተር ውስጥ የባለድርሻ አካላትን መድረክ መመስረት አስፈላጊ ነው። ይህ መድረክ የምርምር ተቋማትን፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ የኤክስቴንሽን አገልግሎቶችን፣ እንደ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የግል ተቋማት ያሉ የልማት አጋሮችን ጨምሮ፣ የተለያዩ አጋሮችን ሊያሰባስብ ይገባል። መድረኩን የመመሥረት ሂደት፣ የማስፋፊያ ማዕቀፉን ለማሳደግ የሚያስችል አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም፣ በክልል የእንስሳት ልማት ቢሮ እና በምርምር ተቋማት በጣምራ ይከናወናል። የበጎች አምስቱ ስብስቦች እና የፍየሎች አንድ ስብስብ፣ መድረኩን በመፍጠር ረገድ ጠቃሚ ተሞክሮ የሚያበረክቱ በርካታ ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ ተቋቋመዋል። በመድረኩ ውስጥ ያለው አስተባባሪ ኮሚቴ፣ በርካታ ዝርዝር ተግባራትን በአደራ የተሰጡት ሲሆን፣ ይህም የሚከተሉትን ያካትታል፦ ስለማስፋፊያ ማዕቀፉ እና ስለ ስብስብ አ ፈጣጠሩ (ክላስተሪንግ) ግንዛቤን ማሳደግን ግባቸው ባደረጉ አውደ-ጥናቶች አማካኝነት፣ የአቅም ግንባታ ሥልጠናን ማካሄድ። ለማካተት የሚታለሙትን ዝርያ/መንጋ እና ስብስቦችን መወሰን። ከላይ በተጠቀሱት የአሠራር ቅደም-ተከተሎች መሠረት፣ በኤክሴል ሰንጠረዡ በመታገዝ፣ የማስፋፊያ ማዕቀፉን እና ዝርያ-ተኮር ስታቲስቲክስን ማዘጋጀት ወይም ማስማማት። ስምምነት የተደረገባቸውን ተግባራት በማቀድ እና በመተግበር ላይ መመሪያ እና አቅጣጫ መስጠት። ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ማቀድ፣ ዕቅድን መገምገም እና ማፅደቅ። የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን የሚመለከቱ መረጃዎችን መሰብሰብ እና መገምገም፣ የዝርያ መሻሻልን ከግብ ለማድረስ እና የምርሃግብር ግቦችን እና ውጤቶችን ለማስፋፋት የሚያስችሉ መመሪያዎችን እና ምክረ-ሀሳቦችን መስጠት። የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን የአካሄድ ህብር (መጣጣም) መጠበቅ እና በተለያዩ የዝርያ ማሻሻያ አስኳሎች ውስጥ ባሉ አተገባበሮች መካከል ትስስርን ማጎልበት። በተለያዩ አስፈጻሚ ተቋማት እና ቡድኖች መካከል ያለውን ተግባቦት ማቀላጠፍ። ለተግባሪዎች የባለሙያ ምክር መስጠት። ስብሰባዎች እንዲደረጉ ሃሳብ ማቅረብ እና ማዘጋጀት። በአባሪው ውስጥ የተቀመጡትን መሰረት በማድረግ ቀላል የመረጃ መሰብሰቢያ እና የዘገባ ቅጾችን ማዘጋጀት። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 19 የመርሃግብሩን አጠቃላይ አፈጻጸም፣ ከዓመታዊ ዕቅዱ አንጻር፣ ከኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በተሰበሰቡ የመስክ ምዘናዎች እና ዘገባዎች አማካኝነት በመከታተል እና መገምገም። የሀብት ማሰባሰብን እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን መደገፍ። ለፕሮጀክቱ ትልቅ አንድምታ ያላቸውን ማናቸውንም የሚያጋጥሙ ችግሮች መፍታት። መደበኛ የአሠራር ሂደት ደረጃዎችን መመሥረት። የ አምራች ክፍሎችን በብቃት ያስተዳድሩ ዘንድ፣ በምርምር ማዕከላት እና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ባሉ ተመራማሪዎች እና በክልል እና በዞን ባለሙያዎች አማካኝነት፣ በወረዳ ያሉ ባለሥልጣናትን አቅም መገንባት። ከፍተኛ ደረጃ ግንዛቤን መፍጠር። የማህበረሰብ-ዓቀፍ የዝርያ ማሻሻያ (ማዓዝማ) መርሃግብር (ሲቢቢፒ) መንደሮች፣ የማዓዝማ (ሲቢቢፒ) መመሪያዎችን በመከተል መመሥረት እና መተግበር አለባቸው (Haile et al., 2011, 2018)።የማዓዝማ ቁልፍ እሳቤዎች እንስሳቱን መለየት፣ የዝርያ ማሻሻያ ዓላማዎችን እና የመረጣ መስፈርቶችን መበየን፣ በመረጣ መስፈርቶች መሠረት መረጃ መሰብሰብ፣ የእንስሳት የዘረመል (ጄኔቲክ) ግምገማ እና ደረጃ ምደባ፣ የማዳቀል ስልቶችን እና የአስተዳደር ስትራቴጂዎችን ጨምሮ የዝርያ ማሻሻያ መዋቅሮችን ማዳበር (ማዘጋጀት)ን ያካትታሉ፡ ። መዓዝማዎችን ለማቋቋም እና ለማስተዳደር አስፈላጊ የሆኑት ቅደም-ተከተላዊ እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦ 1. የቦታ እና የዝርያ መረጣ፦ የምርምር ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ወይም የማስፋፊያ መድረኩ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ ለመዓዝማው የሚታለመውን ዝርያ እና መንጋ ይወስናሉ። ከመርሃግብሩ ግቦች እና ከማህበረሰቡ ፍላጎቶች ጋር የሚስማሙ ግልጽ የዝርያ ማሻሻያ ዓላማዎችን እና የመረጣ መስፈርቶችን ይበይናሉ (ይወስናሉ)። 2. የማህበረሰብ ተሳትፎን ማረጋገጥ፦ በማህበረሰቡ አባላት መካከል ስለ ማዓዝማ (CBBP) ግንዛቤ ማሳደግ አስፈላጊ ነው። ይህ፣ በማህበረሰቡ ዘንድ በመርሃግብሩ ላይ የባለቤትነት መንፈስ መፈጠሩን እና ለንቁ ተሳትፎ መነሳሳታቸውን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ የውይይት እና የምክክር ሂደቶች ይከናወናል። 3. የህብረት ሥራ ማህበራት ምሥረታ፦ የጋራ እርምጃዎችን ለማስፋፋትና ንቁ የማህበረሰብ ተሳትፎን ለማበረታታት፣ የባለድርሻ አካላቱ መድረክ እና አስፈጻሚዎች፣ ከግዜ በኋላ ወደመደበኛ የህብረት ሥራ ማህበራትነት መለወጥ የሚችሉ፣ መደበኛ ያልሆኑ የህብረት ሥራ ማህበራት እንዲመሠረቱ ያግዛሉ። እነዚህ የህብረት ሥራ ማህበራት የማህበረሰብ አባላት፣ የማህበረሰቡ አባላት የሚተባበሩባቸው እና ሀብቶች የሚሰባሰቡባቸው መድረኮች በመሆን ያገለግላሉ፣ ማዓዝማውን በተመለከተም በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ይሳተፉባቸዋል። 4. መረጃ መዝጋቢ መረጣ እና ምልመላ፦ ከማህበረሰቡ ውስጥ መረጃ መዝጋቢ በመሆን ለማገልገል ተስማሚ የሆኑ ግለሰቦችን መለየት እና መመልመል ወሳኝ ነው። መረጃ መዝጋቢ፣ ለእንስሳቱ መለያ ቁጥር መስጠት፣ መረጃ በመሰብሰብ፣ እና የመረጃውን ትክክለኛነት እና አስተማማኝነት በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። በቀድሞው የደቡብ ግብርና ምርምር ተቋም (SARI)፣ መረጃ ሰብሳቢዎች፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ለእነሱ የተወሰኑ የሥራ ድርሻዎችን በማቋቋም፣ ወደ ሙሉ-ጊዜ የመንግስት የምርምር ሠራተኛነት እንዲያድጉ ተደርገዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ እንደ ደቡብ ኦሞ እና አንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ባሉ ቦታዎች ውስጥ፣ የኤክስቴንሽን ቢሮው፣ መደበኛ የልማት ወኪሎችን የሙሉ ጊዜ መረጃ ሰብሳቢዎች አድርጎ ለመመደብ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ስራው የዕለት ከዕለት ክትትልን ስለሚጠይቅ መረጃ መዝጋቢዎች ለመዓዝማው (ሲቢቢፒ) የሙሉ ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው። 5. የአውራ/ኮራማ ቡድኖች ምሥረታ፦ ቁጥጥር የሚደረግባቸው እና ስትራቴጂካዊ የሆኑ ስሪያዎች (ማዳቀሎች) መከናወናቸውን በማረጋገጥ የዝርያውን አጠቃላይ የዘረመል እሴት ለማሻሻል፣ የማዓዝማ መርሃግብሮች አመሰራረት እና ትግበራ ቅደም-ተከተሎች ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 20 የአውራ ቡድኖች መመሥረት አለባቸው። የአውራ ቡድኖች ምርጥ አውራዎችን ወይም ኮርማዎች በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ስርዓት በመፍጠር የዝርያ ማሻሻል ስራው እንዲሳለጥ ያደርጋሉ። 6. የእንስሳት መለያ መፍጠር እና መሠረታዊ መረጃ መሰብሰብ፦ መሰብሰብ፦ይህ፣ ለእያንዳንዱ እንስሳ ተለይቶ የሚታወቅበትን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ወይም መለያ መስጠትን እናእንደ አካላዊ (ፊኖታይፒክ) ባህሪዎች፣ የዘር ሐረግ፣ እና የምርታማነትመለኪያ ያሉመሠረታዊ መረጃዎችን መሰብሰብን ያካትታል። በአባሪ 2 ላይየቀረበው ቅጽ መረጃዎችን ለመሰብሰብ እንደ መመሪያ ሆኖ ያገለግላል። ተመራማሪዎች፣ ከኤክስቴንሽን አጋሮች፣ ከመረጃ መዝጋቢዎች፣ እና ከአርቢዎች ኮሚቴ ጋር በመተባበር ይህንን ወሳኝ ተግባር ይቆጣጠራሉ። 7. የአውራዎች/ኮርማዎች ግዢ እና ምደባ፦ ከፍተኛ ጥራት ያለው የርቢ ዝርያዎችን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ፣ በቁጥር በቂ የሆኑና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አውራዎች/ኮርማዎች ገዝቶ ለማዓዝማ መንደሮች መመደብ አስፈላጊ ነው። የሚመረጡት አውራዎች ከሚፈለገው የዝርያ ማሻሻያ ዓላማዎች ጋር የሚጣጣሙ ሊሆኑ እና ተፈላጊ የዘረመል (ጄኔቲክ) ባህሪዎች ሊኖራቸው ይገባል። 8. ያልተመረጡ አውራዎች ድቅያን መከላከል፦ ያልተመረጡ አውራዎች/ኮርማዎች ስሪያ እንዳይፈጽሙ መከላከል የሚቻልባቸውን ስልቶችን መተግበር በቁጥጥር ሥር ለሆነ የዝርያ ማሻሻያ እና የአጠቃላዩን መንጋ የዘረመል ጥራት ለመቆጣጠር ወሳኝ ነው። እነዚህን ስልቶች፣ ከህብረተሰቡ ጋር በመመካከር ማዘጋጀት እና መተግበር ወሳኝ ነው። ጥቅም ላይ ሊውሉ ከሚችሉ ዘዴዎች ውስጥ፣ ያልተመረጡ አውራዎችን ማኮላሸት፣ መለየት፣ ወይም ሽርጥ መጠቀም ይገኙባቸዋል። 9. የዘር እና የአፈጻጸም መረጃ ስነዳ፦ የዝርያ ማሻሻያውን እድገትን ለመከታተል ስልታዊ የሰነድ አያያዝ ሂደት መመስረት ወሳኝ ነው። መረጃው፣ የወላጅነት፣ የወሊድ ክብደት፣ የእድገት ፍጥነት፣ የወተት ምርት መጠን፣ የመራባት አፈፃፀም፣ እና ሌሎች ተዛማጅ ባህሪያትን ያጠቃልላል። የትውልድ እና የአፈፃፀም ስነዳው ከበአባሪ 3ሀ እስከ 3ሐ የቀረቡን ቅጾች በመጠቀም ሊደረግ ይችላል። 10. የዘረመል (ጄኔቲክ) የመረጃ ቋት፦ በኢካርዳ (ICARDA) እና በአባከስባዮ (Abacusbio) የግል ኩባንያ የበለጸገውን፣ ዲትሪዮ (DTREO) የተባለ ዲጂታል የጄኔቲክየመረጃ ቋትን መጠቀም ይመከራል። ይህ የዘረመል ግምገማን እና ውሳኔ-አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የውሂብ (ዳታ) አያያዝን፣ ተገቢ አቀማመጥን፣ አደረጃጀት፣ እና የተሰበሰበውን መረጃን መተንተንን ያስችላል። 11. የዘረመል ግምገማ፦ ይህ ግምታዊ የዘረ-መል እሴቶችን (EBVs)፣ የጥራት ማረጋገጫን፣ እና የርቢ እንስሳት መረጣን ያካትታል። በዘረመል ምዘናው ሂደት ውስጥ ተመራማሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን ይህ ሂደትም የነፍስወከፍ እንስሳን ግምታዊ የመራባት እሴቶች ማስላትን እና በዘረመል ጠቀሜታቸው ላይ ተመስርቶ የእንስሳቱን ደረጃ መስጠትን ያካትታል። ከዚያ በኋላ ምርጥ አውራዎች/ ኮርማዎች የጥራት ማረጋገጫ ወረቀት ይሰጣቸዋል፣ ይህም የተፈላጊ የዘረመል ባህሪያትን መሰራጨት ያረጋግጣል። 12. የማህበረሰብ ማረጋገጫ፦ በአፈፃፀም ስነዳው መሠረት የእንስሳት መረጣ በሚደረግበት ሂደት ውስጥ የማህበረሰቡን ይሁንታ ማግኘት ወሳኝ እርምጃ ነው። የተመረጡ እንስሳት የማህበረሰቡን መስፈርቶች እና ምርጫዎች ማሟላት አለባቸው፣ ይህም እንደ ቆዳ ቀለም እና ሌሎች ሥነ- አካላዊ ባህሪያትን ሊያካትት ይችላል። የማህበረሰቡን ይሁንታ ለማግኘት መጣር፣ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ ከማህበረሰቡ አባላት ፍላጎቶች እና ምርጫዎች ጋር የሚስማማ መሆኑን ያረጋግጣል፣ ንቁ ተሳትፎ እና የባለቤትነት ስሜትንም ያበረታታል። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 21 13. አውራዎች/ኮርማዎችን መተካት፦ በዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ ውስጥ ቀጣይነት ያለው መሻሻልን እና የዘረመል ብዝሃነት መኖሩን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። የአውራዎች/ኮርማዎች አፈፃፀም፣ የዘረመል ጠቀሜታ፣ ጤና፣ እድሜ ፣እና ማናቸውም ዓይነት ጉድለቶች በየጊዜው መገምገም አለበት። በተወሰነው የአገልግሎት ዘመናቸው መሠረት እንደዚህ ያሉ ችግሮችን የሚያሳዩ ወይም የሚያረጁ አውራዎች/ ኮርማዎች መተካት አለባቸው። ይህ አሠራር ከፍተኛ የእንስሳት ጤና ደረጃን ለመጠበቅ ይረዳል፣ እንዲሁም የዘረመል ወይም አካላዊ ጉድለቶች ወደቀጣይ ትውልዶች እንዳይተላለፉ ያደርጋል። 14. የህብረት ሥራ ማህበራት አመራር፦ የማህበረሰቡን አባላት፣ በውሳኔ አሰጣጥ እና በሀብት ምደባ ውስጥ በማሳተፍ፣ የህብረት ሥራ ማህበራትን ማቋቋም እና ተግባራዊነታቸውን ማሳደግ ለማዓዝማ እንቅስቃሴዎች ውጤታማ አስተዳደር አስፈላጊ ነው። ይህም በ አካባቢው ያሉ የህብረት ሰራ ማህበር ጽ/ቤት ባለሙያዎች በሚሰጡት መመሪያ መሰረት ይከናወናል። 15. ሥልጠና እና ክትትል፦ የአቅም ግንባታ እና ለማዓዝማ ተሳታፊዎች እና ለባለድርሻ አካላት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ መስጠት፣ ክህሎትን እና እውቀትን ለማሳደግ ወሳኝ ናቸው። ይህ ከዕውቀት እና ከህሎት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ፣ መልካም አሠራሮችን ለማጠናከር፣ እና መማርን እና ፈጠራን ለማሳደግ ይረዳል። 16. የአመጋገብ፣ የጤና ክብካቤ፣ እና የገበያን ማሻሻል፦ የእንስሳት አመጋገብን፣ ጤናን እና የገበያ ተደራሽነትን ለማሻሻል ስልቶችን መተግበር አስፈላጊ ነው። ከእንስሳት መኖ፣ ጤና፣ የገበያ ትሥሥር ጋር የተዛመዱ ጥረቶችን ለመተግበር እና ተሳታፊ ማህበረሰቦች ለተገቢ የአመጋገብ ልምዶች፣ የእንስሳት እንክብካቤዎች፣ እና ለተሻሻሉ የገቢያ ዕድሎችን ተደራሽ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ አርቢዎች ከእንስሳት ጤና አገልግሎቶች፣ ከኤክስቴንሽን ሠራተኞች፣ እና ከገቢያ ተዋናዮች ጋር መተባበር አለባቸው። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 22 የስብስብ እና የማስፋፊያ ማዕቀፉን መረዳት የልማት አጋሮች፣ የልማት ወኪሎች (DAs)፣እና የወረዳ-ደረጃ የኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የዚህን መምሪያ የመጀመሪያ ምዕራፎች በማንበብ እና እነሱን ከሚመሯቸው ተቆጣጣሪዎች እና ተመራማሪዎች ጋር በመመካከር፣ የማስፋፊያ ማዕቀፉን እና የስብስብ (ክላስተር) ምንነትና አቀራረቡን መረዳት አለባቸው። የአምራች ክፍል ጣቢያዎችን እና ተሳታፊዎችን/ ባለድርሻ አካላትን መለየት አምራች ጣቢያዎች ተመርጠው የሚለዩት፣ የማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሮች አውራዎችን ለማምረት ባላቸው አቅም፣ መነሻ የሚሆኑ የእርባታ አውራዎችን//ኮርማዎችን ለመግዛት የሚያስፈልገው ሀብት መኖር ወይም አለመኖሩን፣ እና ማህበረሰቡ የእርባታ ወንዶችን ለማበርከት እና ለመግዛት ያለው ፈቃደኝነትን በመሳሰሉ ምክንያቶች ላይ በመመርኮዝ ነው። በአምራቹ ክፍል (PU) ውስጥ የሚሳተፉት አርሶ አደሮች ብዛት የሚወሰነው በበእንስሳቱ የወንድ-ለ-ሴት የስሪያ ጥምርታ (ምጥጥን) ነው። ወደ 25 ለሚጠጉ የርቢ ሴቶች፣ አንድ የርቢ ወንድ መጠቀም ይመከራል። ሆኖም፣ ይህ እንደ ዝርያው ተበታትኖ መገኘት እና እንደ ወቅታዊነት ባሉ የተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ሊስተካከል ይችላል። ለምሳሌ፣ የዝናብ ወቅቱ በጣም አጭር በሆነበት በአበርጌል አካባቢ፣ ገበሬዎች አንድ ወንድ ለ አስር ሴት ፍዬሎች ይጠቀማሉ። ይህም ባለው አጭር የጥቂያ ጊዜ ዝግጁ የሆኑት ሁሉም እንስቶች መጠቃት እንዲችሉ ያደርጋል። በእርባታ ክፍሉ ውስጥ ጥብቅ የመረጃ አሰባሰብ ባለመኖሩ ምክንያት፣ የአምራች ክፍሉ ከማዓዝማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተሳታፊዎችን ሊይዝ ይችላል። ይሁን እንጂ፣ በጣቢያው የተመደቡት የግብርና ልማት ወኪሎች (DA)፣ውጤታማ ክትትል ማድረግ እና ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት መሥራት ይችሉ ዘንድ፣ የአምራች ክፍሉ ስፋትበአቅማቸው ሥር መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በልማት ወኪሎች እና በወረዳ ባለሙያዎች ኃላፊነት ስር፣ አምራች ክፍሎችን ለማስጀመር እና ለማከናወን የሚያስፈልጉ ቅደም-ተከተላዊ እርምጃዎች ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 23 የማህበረሰቡን ግንዛቤ እና አቅም መገንባት ግንዛቤን መፍጠር፣ ሥልጠናን መስጠት፣ እና ከአርሶ አደሮች ፈቃደኛነትን ማግኘት አምራች ቦታዎችን ለመመሥረት ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው። የሥልጠናው ይዘት የሚከተሉትን ጨምሮ የተለያዩ ገጽታዎችን መሸፈን አለበት፦ የአገሬው ዝርያዎች ለመሻሻል ያላቸውን ዕምቅ አቅም። የመንጋዎቻቸውን የዘረመል ጥራት ለማሻሻል የተሻሻሉ ወንዶችን መጠቀምን። የርቢ አውራ/ኮርማ አያያዝን። ዝቅተኛ ጥራት ያላቸውን እና የማይፈለጉ እንስሳትን የመቀነስ ወይም የማኮላሸት አስፈላጊነትን። የግብዓት ተደራሽነትን እና የምርት ሽያጭን ለማቀላጠፍ የትብብር አስፈላጊነትን። አንዴ አርሶ አደሮች ለመሳተፍ ከተስማሙ በኋላ፣ ማህበረሰቡን ለመደገፍ፣ መደበኛ ያልሆነ የአርሶ አደር ኮሚቴ ይቋቋማል። የኮሚቴው ዋና ኃላፊነት፣ መደበኛ የአምራቾች ህብረት ሥራ ማህበር እስኪደራጅ ድረስ፣ አምራች ክፍሉን በማስተዳደር ረገድ ማህበረሰቡን መደገፍ ነው። የማዳቀል (የስሪያ) ቡድን ምሥረታ የስሪያ ቡድን፣ በአንድ አውራ በግ የሚደቀሉ (የሚሰረሩ) የርቢ ሴቶች ያሏቸው ገበሬዎችን ያቀፈ ነው። በአንድ ቤተሰብ (አባ/እማ-ወራ) የሚረቡ ሴቶች ቁጥር ከአውራው አቅም በላይ ከሆነ (ብዙውን ጊዜ ለአንድ አውራ ወደ 25 ገደማ ሴቶች ይመደባሉ)፣ አውራዎች በርቢያ ሴቶች ብዛት ላይ በመመርኮዝ ይመደባሉ። ይህ በአርብቶ አደሮች ምህዳር ውስጥ በጣም የተለመደ ነው። የአሰፋፈር ሥርዓቶችን፣ የርቢ ሴቶች ቁጥርን፣ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥን፣ እና አርሶ- አደሮች ለመተባበር ያላቸውን ፈቃደኛ መሠረት በማድረግ የስሪያ ቡድኖች ይቋቋማሉ። ቡድኑ የተመረጡ አውራ//ኮርማን በጋራ ለመጠቅም ያስችላል። ይህም ጥቂትና በጣም መርጦቹን አውራ// ኮርማን በመጠቀም የዝርያ መሻሻሉ ፈጣን እንዲሆን ያስችላል። የርቢ አውራዎች/ኮርማዎች ግዢ ለአምራች ክፍሉ መጠቀሚያ የሚሆኑ፣ የጥራት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት የተሰጣቸው፣አውራዎች/ ኮርማዎች በዋነኝነት በስብስቡ ውስጥ ካሉ የማዓዝማ (CBBP) ጣቢያዎች ቢገኙ ይመረጣሉ። በማዓዝማዎች ውስጥ የጥራት ማረጋገጫ የተሰጣቸው አውራዎች/ኮርማዎች የማይገኙ ከሆነ፣ አውራዎቹ ከማህበረሰቡ መንጋዎች ውስጥ፣ ወይም በአቅራቢያ ካሉ ገበያዎች፣ ተለይተው ሊመረጡ ይችላሉ። ከልማት አጋሮች የተውጣጡ ባለሞያዎችን እና አርሶ አደሮችን ያካተተ፣ ከ3 እስከ 5 አባላት ያሉት፣ ኮሚቴ የርቢ አውራዎችን የመለየት፣ የመምረጥ፣ እና የመግዛት ኃላፊነት ይሰጠዋል። የርቢ አውራዎችን ተስማሚነት ማረጋገጥ:- የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶች፣ የአውራውን የዘረመል (ጄኔቲክ) ብቁነት በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፣ ለርቢ ተስማሚነታቸውም እንደ ማስረጃ ያገለግላሉ። የጥራት ማረጋገጫ የሚሰጣቸው አውራዎች/ኮርማዎች የዘረመል ዋጋቸውን፣ የርቢያ ብቃታቸውን፣ ያላቸውን የወንዴ-ዘር ጥራት እና ብዛት፣ እና ከዋና-ዋና በሽታዎች መከላከያ ክትባቶችን መውሰዳቸውን ጨምሮ የተለያዩ የብቃት መሥፈርቶችን በሚገመግም ጥብቅ የምርመራ ሂደት ውስጥ ያልፋሉ። እነዚህ ግምገማዎች፣ አስፈላጊዎቹን ደረጃዎች የሚያሟሉ አውራዎች/ኮርማዎች ብቻ ለርቢ ዓላማዎች የሚመረጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። የተመረጡ አውራዎችን/ኮርማዎችን በማዓዝማዎች (ሲቢቢፒ) ማስፈተሽ እና የምስክር ወረቀት ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው። ዋናው (ኦርጂናሌው) የምስክር ወረቀት በአምራቹ የሕብረት ሥራ ጽ/ቤት ውስጥ መቀመጥ ያለበት ሲሆን፣ ቅጂው ለማመሳከሪያ ይውል ዘንድ በሚመለከተው ወረዳ ጽ/ቤት ውስጥ ሊቆይ ይችላል። የርቢ አውራዎች/ኮርማዎች ምደባ የተገዙ የርቢ አውራዎች/ኮርማዎች ለእያንዳንዱ የስሪያ ቡድን መመደብ አለባቸው። ይህ ሲደረግ፣ አድልዖ እንዳይፈጠር በወንድ-ለ-ሴት ጥምርታ መሠረት በማድረግ በዕጣመመደብ ያስፈልጋል ። በዓይነተኛነት፣ የጎለመሰ እርባታ አውራ ከ25 እስከ 40 ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 24 የርቢ ሴቶችን ሊያገለግል ይችላል፣ ምንም እንኳን ይህ ቁጥር በተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ሊለያይ ቢችልም። ለምሳሌ፣ የስሪያው ወቅት ከዝናብ ወቅት ጋር በሚገጣጠምበት እና ዝናቡ ለአጭር ጊዜ ብቻ በሚቆይበት በአበርጌሌ ውስጥ፣ በዚያ ውስን የጊዜ ገደብ ውስጥ ስኬታማ ስሪያ መከናወኑን ለማረጋገጥ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አውራዎች መመደብ ወሳኝ ይሆናል። አሁን በመተግበር ላይ ያለው አሰራር ለእያንዳንዱ 10 የርቢ ሴቶች አንድ አውራ መመደብን ይመክራል። የአውራ/የኮርማ አጠቃቀም እና አያያዝ ሁሉም የተገዙ የርቢ አውራዎች/ኮርማዎች የአምራቾች የህብረት ሥራ ማህበራት የጋራ ንብረት በመሆናቸው፣ ለማህበሩ ይዞታ መተላለፍ አለባቸው። በአውራ/ኮርማ አጠቃቀም እና አስተዳደር ውስጥ መሰረታዊ መርሆዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ የአውራ/ኮርማ ማጋራት፣ አውራዎቹን በስሪያ ቡድኖች ውስጥ ማዘዋወር፣ በአባላቱ ኃላፊነቶች እና ጥቅሞች ላይ መስማማት፣ እና የአውራውን የአገልግሎት ዘመን መወሰን። እያንዳንዱ የስሪያ ቡድን፣ በቡድኑ አባላት መካከል የርቢ አውራውን ትክክለኛ አጠቃቀም በተመለከተ ኃላፊነት ያለው፣ የተመረጠ መሪ ይኖረዋል። የቡድን አባላት፣ የርቢ አውራውን የመንከባከብ ኃላፊነት ላለበት መሪ በሚሰጡ ልዩ ጥቅሞች ላይ ሊወያዩ እና ሊወስኑ ይገባል። የርቢ አውራዎችን መሸጥን፣ ማረድን፣ ወይም ደካማ በሆነ መንገድ መያዝን የመሳሰሉ አግባብነት የሌላቸ አጠቃቀሞች፣ ስምምነት በተደረገበት የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት ይዳኛሉ። የርቢያ አውራዎች/ኮርማዎች የርቢ አቅማቸውን ሊያዳክሙ የሚችሉ ጉድለቶች እንደሌሉባቸው ለማረጋገጥ በየጊዜው መፈተሽ አለባቸው።ማንኛውም ጉድለት ያለበት አውራ፣ ወዲያውኑ መከላት (መወገድ) እና የጥራት ማረጋገጫ ባላቸው አውራዎች መተካት አለበት። በዝምደ ርቢ ምክንያት የሚመጣ የዝርያ መዳከምን ለመቀነስ አውራዎችን በዙር መጠቀም በመንጋው ውስጥ የዘረመል ብዝሃነትን መጠበቅ፣ በቅርብ ቤተሰብ ዝርያዎች ውስጥ በሚደረግ መዋለድ ምክንያት የሚመጣውን የዝርያ ጥራት መመናመን (ኢንብሪዲንግ) አሉታዊ ተፅእኖዎች ለመከላከል ወሳኝ ነው። ይህ የጥራት መቀነስ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤታማነትን እና ተመራጭ ባህሪያትን ሊቀንስ ይችላል። ይህንን ለማስቀረት፣ በዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩ ውስጥ፣ በቅርበት የተዛመዱ እንስሳትን እርስ-በእርስ ከማዋለድ መቆጠብ አስፈላጊ ነው። ውጤታማ ከሆኑ ስትራቴጂ ውስጥ አንዱ፣ አውራዎችን/ኮርማዎችን በማዘዋወር የመጠቀም ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ነው። የርቢ አውራዎች/ ኮርማዎች በአንድ የስሪያ ቡድን ውስጥ ከአንድ ዓመት በላይ ጥቅም ላይ መዋል የለባቸውም። ይህ አሰራር ከመጠን በላይ የሆነ የዝርያ መመናመንን ይከላከላል፣ የዘረመል ልዩነትንም (ብዝሃነትን) ያበረታታል። በማዓዝማው ወይም በአምራች ክፍሉ ውስጥ በርካታ የስሪያ ቡድኖች መኖራቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ አንድ አውራ ከአንድ ዓመት በላይ ጥቅም ላይ እንዲውል የታሰበ ከሆነ፣ በእነዚህ ቡድኖች ውስጥ አውራዎችን በማቀያየር መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል። የርቢ ያልሆኑ ወንዶችን መክላት/ማኮላሸት:- በአምራችክፍል ውስጥ የሚመረቱ ወንዶች በሙሉ መኮላሸት፣ እና ከደለቡ ወይም በገበያ ፍላጎቶች መሠረት ከተዘጋጁ በኋላ፣ ለገበያ መቅረብ አለባቸው። አንድ የርቢ አውራ/ኮርማ የአገልግሎት ዘመኑን ሲያጠናቅቅ ወይም በጉድለት ምክንያት ሲከላ፣ ተዘጋጅቶ ወይም ደልቦ ለሥጋ መሸጥ አለበት። ያረጁ ሴት በጎች፣ ከ7 ውልደቶች በኋላ፣ እንዲከሉ እና በልጅእግር ሴቶች ወይም ቄቦች እንዲተኩ ይመከራል። የልማት ወኪሎች መንጋውን በመደበኛነት መከታተል እና፣ አርሶ-አደሮች፣ የእርባታ ያልሆኑ አውራዎችን/ ኮርማዎችን፣ የአገልግሎት ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የእርባታ አውራዎችን፣ እና በእርጅና ወይም፣ መካንነትን፣ የጤና ችግሮችን፣ አካላዊ ጉዳትን፣ በመሳሰሉ እንከኖች ምክንያት ምርታማነታቸው የቀነሱ ሴት የርቢ በጎችን እንዲከሉ ይመክራሉ። ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ያልወለዱ ሴት በጎችም እንዲሁ መከላት ወይምከዕርባታ ውጭ መሆን አለባቸው። የርቢ እንስሳትን የመተካት እቅድ የርቢ እንስሳትን ቀጣይነት ያለው አቅርቦት እና የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን ዘላቂነት ለማረጋገጥ፣ የመተካት እቅድ ማዘጋጀት ወሳኝ ነው። የርቢ አውራዎች/ ኮርማዎች፣ ስምምነት የተደረገበትን የአገልግሎት ዘመናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ መተካት አለባቸው። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 25 ማንኛውም ዓይነት ጉድለት ከተከሰተባቸውም እንዲሁ ወዲያውኑ መወገድና መተካት አለባቸው። የርቢ አውራ/ኮርማ የአገልግሎት ዘመን በአጠቃላይ ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት መሆን ያለበት ሲሆን፣ በአንድ የስሪያ ቡድን ውስጥ ለአንድ ዓመት ብቻ ጥቅም ላይ መዋል አለበት። በአምራች ክፍሎች ውስጥ የአውራ ምትክ በዋነኝነት ከማዓዝማዎች (ከሲቢቢፒዎች) መምጣት አለበት። ይህም፣ የልማት ወኪሎች እና የኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በማዓዝማዎች እና በአምራች ክፍሎች (ፒዩ) መካከል ውጤታማ ትስስር ለመፍጠር መሥራት ይጠይቃል። በመንጋው ውስጥ ያሉ ያረጁ ወይም ጉድለት ያለባቸው እናቶችን ለመተካት፣ ጥሩ የሚመስሉ ሴት ጠቦቶችን መምረጥ አስፈላጊ ነው። እነዚህን ተስፋ ሰጪ ጠቦቶች በምትክነት በመጠቀም፣ የመንጋው ጥራት እና ምርታማነት ሊጠበቅ እና ሊሻሻል ይችላል። እንስሳቱ በተገቢው መንገድ ከተገመገሙ በኋላ፣ ከገበያ ምትክ መንጋዎችን መግዛትም ሌላው አማራጭ ነው። የገበያ ትስስር:- አምራቹ ክፍል (PU) አንዴ ከተቋቋመ እና የርቢ አውራ ከተመደበ በኋላ፣ የስሪያ ዕድሜ ላይ የደረሱ ነባር ወንዶች በሙሉ መኮላሸት እና ከማድለቢያ ው ክፍል ጋር መገናኘት አለባቸው። አርሶ አደሮች፣ እነዚህን ለርቢ የማይፈለጉ ወንዶች ለማኮላሸት ፈቃደኛ ካልሆኑ፣ በማግለል፣ ሽርጥ በመጠቀም፣ ወይም በሌላ መንገድ ስሪያ እንዳይፈጽሙ መከላከል አለባቸው። በማራቢያው ክፍል ውስጥ የተመረተ ማንኛውም ወንድ፣ የጥራት ማረጋገጫ የተሰጠው አውራ/ኮራማ እስካለ ድረስ ለርቢ ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። በመርህ ደረጃ፣ በአምራች ክፍሉ ውስጥ የተወለዱ ወንዶች በሙሉ መኮላሸት፣ መድለብ እና ለሸማቾች መሸጥ አለባቸው። በተጨማሪም፣ ያረጁ እናት በጎች፣ ለምትክነት የማይፈለጉ ወጣት ሴቶች፣ እና የተከሉ የርቢ ወንዶች፣ ከመንጋው በተገቢው መንገድ መወገድ አለባቸው። እነዚህ እንስሳት፣ በቀጥታ ለጨራሾች (ለአደላቢዎች) ሊሸጡ ወይም በራሳቸው በገበሬዎች ደልበው በመጨረሻም ለገበያ ሊቀርቡ ይችላሉ። ለረጅም ጊዜ በማደለብ (በመጨረስ) የመቆየት ልማድ መበረታታ የለበትም። እንስሳት ለገበያ ዕድሜ እንደደረሱ መሸጥ አለባቸው። ይህ ዕድሜ ግን እንደ ዝርያው እና እንደ አከባቢው ሁኔታ ሊለያይ ይችላል። ይህ፣ በተሻሻለ የመመገቢያ እና የማጠናቀቂያ ቴክኖሎጂዎች መታገዝ አለበት። ለምትክነት ለማይፈለጉ ሴቶች፣ ለተከሉ የርቢ ሴቶች፣ እና ለተከሉ የርቢ ወንዶች ትክክለኛውን የገበያ ትስስር መፍጠር አስፈላጊ ነው። የልማት ወኪሎች እና የእንስሳት ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ በማድለብ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ለመደገፍ እና ከገበያ ጋር ለማገናኘት ከህብረት ስራ ማህበራትና ከንግድ ቢሮዎች ጋር በቅርበት መስራት አለባቸው። እንዲሁም፣ ከግምት ይልቅ በክብደት እና በጥራት ደረጃ መሠረት መሸጥን፣ የዲጂታል የገበያ መረጃ ሥርዓቶችን መጠቀምን የመሳሰሉ ዘመናዊ የገበያ ልውውጥ ዘዴዎችን ማስተዋወቅም አለባቸው። ይህም፣ አርሶ አደሮች እንስሳታቸውን በተገቢው ጊዜ በከፍተኛ ዋጋ እንዲሸጡ፣ እንዲሁም የእንስሳት ሽያጭን ድርቅን የመሳሰሉ አደጋዎችን እንደ መቋቋሚያ ዘዴ አድርገው እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል። የትርፍ እንስሳትን ሽያጭ ማቀላጠፍ በአምራች ክፍሉ ሥርዓት ውስጥ ለሥጋ የሚመረቱትን ወንድ በጎችን በሙሉ መሸጥ በጣም አስፈላጊ ነው። ትርፋማነትን ለማሻሻል፣ እንስሳትን ለማዘጋጀት፣ እና ከተገቢ ገበያዎች ጋር ለማገናኘት የሚመከሩ ልምዶችን መከተል ያሻል። እነዚህን እንስሳት በሚመከረው የገበያ ዕድሜ ላይ፣ በተለይም ከ4 እስከ 10 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ፣ መሸጥ ጥሩ ነው። እንደ ቦንጋ፣ ዶዮጌና፣ እና ዋሸራ ያሉ በፍጥነት የሚያድጉ የበግ ዝርያዎች፣ ከ4 እስከ 6 ወር ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ሊሸጡ ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ፣ እንደ መንዝ፣ ወሎ፣ እና ጎንደር አካባቢዎች ውስጥ ያሉ አነስተኛመጠን ያላቸው የበግ እና አብዛኛዎቹ የፍየል ዝርያዎች፣ በተለምዶ ከ6 እስከ 10 ወር ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሽያጭ ይቀርባሉ። የተወሰነው የመሸጫ የዕድሜ ክልል ምንም ይሁን ምን፣ እንስሳቱ፣ ሊሸጡባቸው የታሰቡ ገበያዎች የሚፈለጉትን የጥራት ደረጃዎች እና የገበያ ምርጫዎች ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ መዘጋጀት፣ የሚፈለገውን ጥራት እና የገበያ ምርጫ ማሟላታቸውን ማረጋገጥ፣ አስፈላጊ ነው። ይህ፣ እድገታቸውን እና ተክለ- ቁመናቸውን ለማስተካከል፣ ተስማሚ የአመጋገብ እና የአያያዝ ልምዶችን መተግበርን ሊጠይቅ ይችላል። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 26 የአገልግሎት ዘመናቸው ከተጠናቀቀ በኋላ - (ለርቢ ወንዶች ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት ሲሆን፣ ለርቢ ሴቶች ደግሞ ሰባት ውልጃዎችን የሚያክል ነው) - በገበያ ምክረ-ሀሳቦች መሠረት፣ የማብቃት ወይም የማደለብ ጥቅሎችን በመከተል፣ ለሽያጭ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም፣ ትርፍ ሴት ቄቦችም ከገበያ ጋር የተሳሰሩ መሆን አለባቸው። በተወሰኑ ዓላማዎች መሠረት፣ እነዚህ ሴት ቄቦች ለርቢ ሊሸጡ ወይም የታለመውን የሥጋ ገበያ መስፈርቶች ለማሟላት በመዘጋጃ ወይም በተሻለ የ አመጋገብ ሂደት አልፈው ለስጋ ዝግጁ ሊሆኑይችላሉ። ሕጋዊ የአምራቾች የህብረት ሥራ ማህበር:- የአምራቾች ማህበራት፣ መደበኛ ካልሆነ አደረጃጀት ወደ መደበኛ አደረጃጀት መሸጋገር፣ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን በውጤታማነት ለማካሄድ፣ ለግብዓት አቅርቦት፣ ለምርት ግብይት፣ የብድር ተደራሽነትን ለማመቻቸት፣ እና የመሰረተልማት ሥራ ለማከናወን ወሳኝ ነው። የልማት ወኪሎች እና ባለሙያዎች አምራቾችን ህጋዊ ለማድረግ እና ህጋዊ ሂደቶችን ለመከተል ከህብረት ሥራ ቢሮዎች ጋር መተባበር አለባቸው። መደበኛ ድጋፍ (ሥልጠና፣ ኦዲት) እና የአፈፃፀም ግምገማም አስፈላጊዎች ናቸው። የመረጃ አሰባሰብ እና ዘገባ:- በአምራች ክፍሎች ውስጥ፣ በመደበኛነት የእንስሳት መለያዎችን መስጠት እና የመረጃ ስብሰባ፣ የመዓዝማውን ያህል አስፈላጊ አይደሉም። ምክንያቱም፣ በእነዚህ የአምራች ክፍሎች ውስጥ መረጣ አይካሄድም። የልማት ወኪሎች እና የኤክስቴንሽን ባለሙያ ተቀዳሚ ኃላፊነት፣ የተሰራጩ የርቢ አውራዎችን ቀጣይነት ያለው እና ዘላቂ የሆነ አጠቃቀም ማረጋገጥ ነው። ስለዚህ፣ ሁኔታውን መከታተል፣ እና ከግልገል/ጠቦት ምርት አንፃር፣ የርቢ አውራ በጎችን አቅም እና አፈፃፀም በየጊዜው መገምገም አስፈላጊ ነው። በአንድ የርቢ አውራ አማካኝነት የተወለዱ የበግ ጠቦቶችን/ግልገሎችን ብዛት ለመመዝገብ፣ የርቢያ አውራ ክትትልእና የሩብ ዓመት ዘገባ (ሪፖርት) ማቅረቢያ ቅጾችን መጠቀም ያስፈልጋል (አባሪዎች 3 እና 4)። የርቢ አውራዎችን የማሰራጨት መርሃግብር አፈፃፀም እና ስኬቶችን መገምገም ከተፈለገ፣ የልማት ወኪሎች እና የኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ቀለል ያሉ ቅጾን በመጠቀም የአፈፃፀም መረጃዎችን ሊሰበስቡ ይችላሉ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ፣ የምርምር ተቋማትን እና የዩኒቨርሲቲዎችን ምክር መሻት አስፈላጊ ነው። የመረጃ (ውሂብ) ስብሰባው በጥቂት የተመረጡ መንጋዎች ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 27 ውስጥ ሊተገበር ይችላል፣ ይህም የአምራች ክፍሉን መጠን ከ5% እስከ 10% ያህል ዒላማ ሊያደርግ ይችላል። የበግ/ፍየል የመነሻ መረጃ (ቤዝላይን) የምርታማነት መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ (አባሪ 1)፣ ለአምራቹ ጣቢያ የእድገት አፈፃፀም ወይም ውጤታማነትንለመለካት የሚያስችል መረጃ አሰባሰብ ቅጽ (አባሪ 5) እና የወተት ምርት መመዝገቢያ ቅጽ (አባሪ 2ለ) ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። የዘረመል መሻሻያውን ተፅእኖን ለመገምገም፣ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ፣ የቤዝላይን (የመነሻ) መረጃ ስብሰባን ተከትሎ፣ የአንድ ጊዜ ግምገማ ማካሄድ ውጤታማነትን ለመለካት ሊያገለግል ይችላል። ይህ ግምገማ፣ መርሃግብሩ የዘረመል መሻሻልን በመዘወር ረገድ ያለውን ውጤታማነት ለመወሰን የሚያስችለውን ንፅፅራዊ ትንተና ለማድረግ ያስችላል። የሀብት ምደባ የገንዘብ ሀብት፣ የአምራች ክፍሉን ለማስኬድ፣ በተለይም የመነሻ የርቢ አውራን/ኮርማን ለማግኘት፣ ወሳኝ ነው። ቁልፍ የገንዘብ ምንጮች፣ የአባላት መዋጮዎችን፣ የአርሶ-አደሮች ነፍስ-ወከፋዊ መዋጮዎችን፣ በአገልግሎት ዘመናቸው መጨረሻ ላይ የርቢ አውራዎችን ከመሸጥ የሚገኝ ገቢን፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና ከግብርና ልማት ፕሮጄክቶች የሚገኙ ድጋፎችን፣ እና ከመንግስት የሚገኝ የገንዘብ ድጋፍን ያካትታሉ። የኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና የልማት ወኪሎች የገንዘብ ሀብቶችን እና ሌሎች የድጋፍ ዓይነቶችን ለማግኘት የሚያስችሉ ዕድሎችን በንቃት መመርመር አለባቸው። የውጭ ምንጮች ለመርሃግብሩ እንደ መነሻ ግፊት (ማበረታቻ) ሊያገለግሉ ቢችሉም፣የመርሃግብሩን የረጅም ጊዜ ዘላቂነት ለማረጋገጥ፣ ዋናው ትኩረት፣ እንደ አርሶ አደሮች መዋጮ ባሉ የውስጥ የገቢ ምንጮች ላይ መሆን አለበት። ስለዚህ፣ ውስጣዊ የገቢ ምንጮችን በመጠቀም ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ ነው። ማስተዋወቅ የፖሊሲ አውጪዎችን፣ የልማት አጋሮችን፣ እና የፋይናንስ ተቋማትን ትኩረት ለመሳብ ማስተዋወቅ (ፕሮሞሽን) ወሳኝ ነው። በተጨማሪም፣ በማህበረሰቦች ውስጥ ለርቢ አውራዎች/ኮርማዎች ያለውን ፍላጎት ከፍ ለማድረግ፣ እና የሸማቾችን የሥጋ እንስሳት ፍላጎት ለማነቃቃት ይረዳል። ይህንን ከግብ ለማድረስ፣ ውጤታማ የማስተዋወቂያ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል። ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ውጤታማ ስልቶች፦ የመስክ ቀኖችን እና የእንስሳት ትርኢቶችን ማደራጀትን፣ በግብርና ኤግዚቢሽኖች እና ትርኢቶች ላይ መሳተፍን፣ እና የላቀ ስኬት ላስመዘገቡ ገበሬዎች እውቅና ለመስጠት አወዳድሮ መምረጥን፣ ማበረታቻዎችን እና ሽልማቶችንም መስጠትን፣ ሊያካትቱ ይችላሉ። በተጨማሪም፣ በተለያዩ መደበኛመገናኛ ብዟሃን እና በማህበራዊ ትሥሥር መድረኮች አማካኝነት ልዩ ዝግጅቶችን ማስተዋወቅ፣ ከተጠቃሚዎች ግብረመልስ መሰብሰብ፣ እና በአርቢዎች፣ በአምራቾች፣ እና በርቢና በሥጋ እንስሳት ጨራሾች መካከል ጥብቅ ቁርኝትን መፍጠር ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ስልቶች ናቸው። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 28 አጋሮችን ለይቶ ማወቅ፣ ማሳተፍ፣ እና ሚናቸውን በግልጽ ማብራራት፣ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብሩን አካላት (ማዓዝማ/CBBP፣ አምራች ክፍል/PU፣ጨራሽ ክፍል/FU፣ እና የግብይት ክፍል/MU) በአግባቡ ለማካሄድ አስፈላጊ ናቸው። አጋሮች የተወሰኑ የማስፋፊያውን ማዕቀፍ ክፍሎች በማስተዳደር ረገድ የመሪነት ሚና አላቸው። ለምሳሌ፣ የእንስሳት ኤክስቴንሽን፣ በአምራች ክፍሎች ውስጥ ግንባር ቀደም ሚና ይጫወታል። በእያንዳንዱ ስብስብ (ክላስተር) ውስጥ፣ በበጎች እና በፍየሎች ላይ የሚሰሩ አጋሮች በሙሉ፣ የመርሃግብሩ አካል ይሆኑ ዘንድ፣ መገምገም ፣ መቀረብ፣ እና እንዲሳተፉ መጋበዝ አለባቸው። የባለድርሻ አካላት መድረክ መመሥረት እና በአስተባባሪ ኮሚቴ መመራት አለበት። አጋርነት የሚከተለው፣ ሊታሰቡ የሚችሉ አጋሮች እና ሚናዎቻቸው ዝርዝር ነው። የአጋሮች ዓይነቶች አሁን እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ ላይ በመመርኮዝ በተለያዩ ስብስቦች ሊለያዩ ይችላሉ፦ የእንስሳት ልማት ቢሮዎች በተለያዩ ደረጃዎች (የፌደራል፣ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ፣ እና የቀበሌ) የምርምር ተቋማት ዩኒቨርስቲዎች ፕሮጀክቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እና የልማት አጋሮች የህብረት ስራ ማህበራት እና የንግድ ቢሮዎች የክህሎትና ስራ ፈጠራ ቢሮዎች የገንዘብ ተቋማት ነጋዴዎች አርቢዎች፣ አምራቾች፣ እና የማደለቢያ ህብረት ሥራ ማህበራት ሸማቾች የማስፋፊያ ማዕቀፍ እና የስብስብ የትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ የማስፋፊያ ማዕቀፉ በተገቢው ሁኔታ መተዳደር አለበት። ይህ፣ የባለድርሻ አካላት ገጽታ እና የሚናዎቻቸውን እና የኃላፊነቶቻቸውን አቅጣጫ በግልጽ መረዳትን፣ እና በሥርዓቱ ውስጥ በተገነባ የክትትል እና የግምገማ መርሃግብሮች መታገዝን ይጠይቃል። የባለድርሻ አካላት ኃላፊነቶች እና ሚናዎች በሰንጠረዥ 2 ውስጥ ቀርበዋል። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 29 ምሥል 5. የበይነ-ባለድርሻ-አካላት ሥነ-ምህዳር፣ የባለድርሻ አካላቱ ሚናዎች እና ኃላፊነቶች የግ ብ ር ና ቢ ሮ ዎ ች ፣ L D O ፖ ሊ ሲ ዎ ች ን እ ና መ መ ሪ ያ ዎ ች ን ለ የክ ል ላ ቸ ው ነ ባ ራ ዊ ሁ ኔ ታ ማ ስ ማ ማ ት ፣ በ ዋ ና ነት አ ም ራ ች ክ ፍ ሎ ች ን ማ ስ ተ ዳ ደ ር ፣ በ ክ ል ል ደ ረ ጃ የ ሚ ደ ረ ጉ ዕ ን ቅ ስ ቃ ሴ ዎ ች ን በ ሙ ሉ መ ከ ታ ተ ል N G O S, L LR P, L FS D P, F SR , IC A R D A የቴ ክ ኒ ክ እ ና የ ፋ ይ ና ን ስ ድ ጋ ፍ ማ ድ ረ ግ ፣ በ ክ ል ል እ ና በ ፌ ዴ ራ ል ደ ረ ጃ ዎ ች የ ዓ ቅ ም ግ ን ባ ታ ጥ ረ ቶ ች ን ማ ገ ዝ ጥ ቃ ቅ ን እ ና መ ካ ከ ለ ኛ ኢ ን ተ ር ፕ ራ ይ ዞ ች የፋ ይ ና ን ስ አ ቅ ር ቦ ት ማ ህ በ ረ ሰ ብ ፌ ዴ ራ ል ግ ብ ር ና ሚ .፣ LD I, EB I ፖ ሊ ሲ እ ና መ መ ሪ ያ ማ ዘ ጋ ጀ ት ፣ የ ገ ን ዘ ብ ድ ጋ ፎ ች ን ማ ፈ ላ ለ ግ ፣ የ ፌ ደ ራ ል ደ ረ ጃ ዕ ቅ ድ ፣ በ ፈ ተ ኛ ደ ረ ጃ የ ዓ ቅ ም ግ ን ባ ታ ፣ በ ፌ ዴ ራ ል ደ ረ ጃ ያ ሉ እ ን ቅ ስ ቃ ሴ ዎ ች ን መ ም ራ ት የም ር ም ር ተ ቋ ማ ት ፦ EI A R , R A R IS መ ዓ ዝ ማ ዎ ች ን መ ም ራ ት ክ ል ላ ዊ ም ር ም ር ሸ ማ ቾ ች ለ አ ም ራ ቾ ች እ ና ለ አ ስ ቻ ዮ ች ግ ብ ረ መ ል ስ (አ ስ ተ ያ የት ) መ ስ ጠ ት ክ ሕ ሎ ቶ ች ፡ የ ሸ ማ ቾ ች ም ር ጫ እ ና ግ ብ ረ መ ል ስ ዩ ኒ ቨ ር ሲ ቲ ዎ ች መ ዓ ዝ ማ ዎ ች ን ማ ስ ተ ዳ ደ ር ክ ሕ ሎ ቶ ች ፦ ለ ው ሳ ኔ አ ሰ ጣ ጥ የ መ ረ ጃ አ ያ ያ ዝ የል ማ ት አ ጋ ሮ ች ክ ሕ ሎ ቶ ች ፦ የ ባ ለ ድ ር ሻ አ ካ ላ ት አ ያ ያ ዝ ጥ መ ኢ ክ ሕ ሎ ት ፦ ት ን ን ሽ የ ን ግ ድ ድ ር ጅ ቶ ች ን መ ም ራ ት ክ ሕ ሎ ት ፦ ተ ቋ ማ ዊ ዐ ቅ ም ግ ን ባ ታ ፣ ክ ት ት ል እ ና ግ ም ገ ማ ክ ሕ ሎ ቶ ች ፦ ለ ው ሳ ኔ አ ሰ ጣ ጥ መ ረ ጃ (ው ሂ ብ ) አ ያ ያ ዝ ክ ሕ ሎ ቶ ች ፦ ተ ቋ ማ ዊ ል ማ ት ፣ ክ ት ት ል እ ና ግ ም ገ ማ ዩ ኒ ቨ ር ሲ ቲ ዎ ች ሸ ማ ቾ ች የበ ይ ነ- ባ ለ ድ ር ሻ -አ ካ ላ ት ስ ነ ዝ ም ዶ ሽ ሚ ና ዎ ች እ ና ኃ ላ ፊ ነቶ ች ግ ብ ራ ና ሚ .፣ LD I፣ E B I ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 30 ትሎችን፣ ስትራቴጂያዊ ክትባትን፣ ስትራቴጂያዊ ሕክምናን፣ አዲስ የተወለዱ እንስሳት አያያዝን፣ እና ያልተመረጡ እንስሳትን ማኮላሸትን የመሳሰሉ ትልሞችን—መተግበር በጣም አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ፣ ጥራት ያላቸው የእንስሳት ጤና አገልግሎቶች እና የመድኃኒቶች መገኘት እና ተደራሽነት ይህንን ጥረት የሚወስኑ ተግዳሮቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ስለሆነም፣ በተለያዩ መንገዶች ለምሳሌ የግል ባለሃብቶችን ወይም በአካባቢው ያሉ ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን በማሰልጠንና በማሳተፍ የእንስሳት ጤና አገልግሎቶችን ማድረስ ለመርሃግብሩ ስኬት ወሳኝ ነው። የርቢ መንጋውን በአግባቡ መመገብ፣ በዝርያ ማሻሻያው ውስጥ የታቀፉ እንስሳት የዘረ-መል አቅማቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲከስቱ ያስችላቸዋል። የእርባታ ሴቶች እና ወንዶች በዋነኝነት የሚያዙት ለርቢ እና ለገበያ ጠቦቶችን እና ግልገሎችን ለማምረት ነው። ለርቢ ዓላማ የማይስማሙ ሆነው የተገኙ እንስሳት፣ እንዲሁም ትርፍ የሆኑ ወንድ እና ሴት እንስሳት፣ እርባታውን ትርፋማነት ከፍ ለማድረግ፣ በአፋጣኝ መሸጥ አለባቸው። ለተወሰኑ የእንስሳት ዓይነቶች፣ ይበልጥ ተስማሚ የሆኑ ጉሮኖዎች (በረቶችን) መፈለግ፣ መንደፍ፣ እና መገንባት አለባቸው። ምክንያቱም፣ መኖሪያ ቤት በምግብ አያያዝ እና በእንስሳት ጤና ቁጥጥር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራልና። በፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር፣ በክልል የግብርና ቢሮዎች፣ እና በእንስሳት ልማት ቢሮዎች—እንዲሁም እንደ ICARDA እና ILRI ባሉ ድርጅቶች— የተዘጋጁት የኤክስቴንሽን የጤና እና የመመገቢያ የተጠቃሚዎች መመሪያዎች፣ እነዚህን ጥረቶች በመተግበር ረገድ ለኤክስቴንሽን እና ለልማት ወኪሎች ጠቃሚ መመሪያ ሊሰጡ ይችላሉ (Wamatu et al., 2021; Fetal et al., 2023; Temesgen et al., 2023)። የአቅም ግንባታ፣ የተሻለ መኖ ልማትናአመጋገብ እና የጤና እንክብካቤ ጥረቶች የአቅም ግንባታ እንቅስቃሴዎች እና፣ ስትራቴጂያዊ የጤና እንክብካቤን፣ አመጋገብን፣ የሥራ-ፈጣሪነትን፣ እና ግብይትን የመሳሰሉ ፈጠራ-መር ጥረቶች፣ ከዝርያ ማሻሻል ባሻገር ያሉ የማስፋፊያውን ማዕቀፍ አካላት ዘላቂነት ባለው መንገድ ለመተግበር እና ለማካሄድ እጅግ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ አስቻዮች ናቸው። የአቅም ግንባታ አስፈላጊ ነው። ይህም፣ ለተወሰኑ ባለድርሻ አካላት እና ተግባሪዎች ፍላጎቶች እንዲስማሙ ተደርገው የተዘጋጁ እና የተደራጁ ክፍል- ተኮር ይዘቶችን ማጠናቀርን ይጠይቃል። ይህ ይዘት፣ የተጠቃሚዎች መምሪያዎችን፣ በራሪ ወረቀቶችን፣ እና ፖስተሮችን በመሳሰሉ፣ ለተግባቦት እና ለመረዳት ቀላል በሆኑ፣ ቅርጾች መቅረብ አለባቸው። የአሠልጣኞችን ሥልጠና (TOT) መርሃግብሮች ማካሄድ እና በተለያዩ ደረጃዎች ቀጣይነት ያላቸው የንድፈ-ሀሳብ እና ተግባራዊ ሥልጠናዎችን መስጠት፣ የማስፋፊያ ማዕቀፉን ትግበራ ለማቀላጠፍ የአቅም ግንባታው ወሳኝ ገጽታዎች ናቸው። ስትራቴጂያዊ የመኖ እና የጤና ክብካቤ ጥረቶችም እንዲሁ አስፈላጊ ናቸው። ለርቢ እንስሳትም ሆኑ ለሽያጭ የተዘጋጁ እንስሳት፣ ተገቢ እርባታን ለማስገኘት እና በገበያው ውስጥም የተሻሉ ዋጋዎችን ለማግኘት በጥሩ የጤንነት እና የሰውነት ሁኔታ ላይ መሆን አለባቸው። ስለዚህ፣ የተሻሻሉ የጤና እና የአመጋገብ ጥቅሎችን (ፓኬጆችን) ማዳበር እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ የመርሃግብሩ ቁልፍ አካላት ናቸው። በተሻሻሉ የእንስሳት ጤና እና የግብርና ልምምዶች የበሽታዎችን ተፅእኖ በመቀነስ፣ የእንስሳት ጤና እንክብካቤ ጥረቶችን ማሻሻል፣ የ አርቢዎችን ምርታማነትን እንዲያሳድጉ፣ የሕክምና ወጪዎችን እና የመድኃኒቶን መላመድ እንዲቀንሱ፣ የድርጅት/የማህበር ትርፋማነትን እንዲያሻሽሉ፣ እና የእንስሳትን ደህንነት እንዲያሳድጉ ለማድረግ ይረዳል። የተለያዩ የእንስሳት ጤና እንክብካቤ ጥረቶችን — ስትራቴጂያዊ ጸረ- ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 31 ሰ ን ጠ ረ ዥ 2 ፡ የ ማ ህ በ ረ ሰ ብ -አ ቀ ፍ የ ዝ ርያ ማ ሻ ሻ ያ መ ርሃ ግ ብ ርን የ ማ ስ ፋ ፋ ት ክ ት ት ል እ ና ግ ም ገ ማ (ሞ ኒ ተ ሪ ንግ እ ና ኢ ቫ ሉ ዌ ሽ ን) ክትትል እና ግምገማ የተ ሻ ሻ ሉ አ ው ራ ዎ ች /ኮ ር ማ ዎ ች አ ጠ ቃ ቀ ም እ ና አ ያ ያ ዝ ዋ ና ተ ግ ባ ራ ት መ ግ ለ ጫ አ መ ል ካ ች /ቾ ች የማ ረ ጋ ገ ጫ ዘ ዴ ዎ ች አ ባ ላ ቱ የ ተ ሻ ሻ ሉ እ ና የጥ ራ ት ማ ረ ጋ ገ ጫ የም ስ ክ ር ወ ረ ቀ ት ያ ላ ቸ ው ን አ ው ራ ዎ ች /ኮ ርማ ዎ ች ያለ ማ ቋ ረ ጥ እ ንደ ሚ ጠ ቀ ሙ ይ ጠ በ ቃ ል ። የተ ሻ ሻ ሉ እ ና የተ ረ ጋ ገ ጡ (የ ተ ፈ ቀ ደ ላ ቸ ው ) አ ው ራ ዎ ች ን/ ኮ ርማ ዎ ች ን ያለ ማ ቋ ረ ጥ መ ጠ ቀ ም ። የፈ ቃ ድ እ ና የጥ ራ ት ማ ረ ጋ ገ ጫ ሁ ኔታ ው ን ሪ ፖ ርት ማ ድ ረ ግ ፣ ማ ረ ጋ ገ ጥ በ ት ግ በ ራ ላ ይ ያ ሉ ማ ህ በ ራ ት እ ና ቆ ጣ ሪ ዎ ች ዝ ቅ ተ ኛ ፍ ሬ ያ ማ ነት ያ ላ ቸ ው ን ሴ ት የር ቢ እ ን ስ ሳ ት ን መ ክ ላ ት (ማ ስ ወ ገ ድ ) ዝ ቅ ተ ኛ ፍ ሬ ያ ማ ነት ያ ላ ቸ ው ን ሴ ት የር ቢ እ ን ስ ሳ ት ን መ ክ ላ ት (ማ ስ ወ ገ ድ ) የአ ፈ ጻ ጸ ም መ ረ ጃ (ው ሂ ብ ) የዘ ረ መ ል (ጄ ኔ ቲ ክ ) መ ሻ ሻ ል እ ና ሥ ነ- አ ካ ላ ዊ (የ ሞ ር ፎ ሎ ጂ ) ለ ው ጥ የአ ቅ ም ግ ን ባ ታ በ ተ ወ ሰ ኑ ቦ ታ ዎ ች ላ ይ ያ ሉ ፣ ሕ ጋ ዊ ነት ያ ላ ቸ ው ፣ በ ተ ግ ባ ር ላ ይ ያ ሉ ማ ህ በ ራ ት ፣ እ ና በ መ ደ በ ኛ ነት ኦ ዲ ት የ ሚ ደ ረ ጉ የ ሰ ለ ጠ ኑ መ ረ ጃ መ ዝ ጋ ቢ ዎ ች ። ፈ ቃ ድ /የ ጥ ራ ት ማ ረ ጋ ገ ጫ ፣ ዘ ገ ባ ፡(ሪ ፖ ርት )፣ ካ ፒ ታ ል ። የፈ ቃ ድ እ ና የጥ ራ ት ማ ረ ጋ ገ ጫ ሁ ኔታ ው ን ሪ ፖ ርት ማ ድ ረ ግ ፣ ማ ረ ጋ ገ ጥ ከ 7 በ ላ ይ የ ጸ ነሱ /የ ወ ለ ዱ እ ና መ ካ ን የሆ ኑ የ ርቢ በ ጎ ች በ ሙ ሉ ይ ከ ላ ሉ ። ከ 7 በ ላ ይ የ ወ ለ ዱ እ ንስ ሳ ት አ ለ መ ኖ ራ ቸ ው ። በ መ ጨ ረ ሻ ከ ወ ለ ዱ በ ኋ ላ ለ ሁ ለ ት ዓ መ ት መ ው ለ ድ ያቆ ሙ ፣ ደ ካ ማ የ እ ናት ነት ች ሎ ታ ፣ ደ ካ ማ ሁ ኔታ ፣ በ ሽ ታ ፣ አ ካ ላ ዊ ጉ ዳ ት የ ሚ ታ ይ ባ ቸ ው የ እ ርባ ታ ሴ ቶ ች አ ለ መ ኖ ራ ቸ ው ። ሪ ፖ ርት እ ና የመ ስ ክ ጉ ብ ኝ ት / ክ ት ት ል ። በ አ ም ራ ች ክ ፍ ሉ ው ስ ጥ የ ተ መ ረ ተ ማ ንኛ ው ም እ ንስ ሳ ፣ እ ና ም ርታ ማ ያ ል ሆ ኑ እ ንስ ሳ ት በ ሙ ሉ ፣ ከ ጨ ራ ሽ /አ ድ ላ ቢ ዎ ች /የ ገ በ ያ ክ ፍ ል ጋ ር በ ወ ቅ ቱ መ ቆ ራ ኘ ት አ ለ ባ ቸ ው ። ከ ጨ ራ ሽ /አ ድ ላ ቢ /የ ገ በ ያ ክ ፍ ል ጋ ር የተ ገ ናኙ የ በ ግ ጠ ቦ ቶ ች መ ቶ ኛ ፤ በ መ ደ በ ኛ ነት ከ ዘ መ ናዊ የ ግ ብ ይ ት ክ ፍ ሎ ች ጋ ር የተ ገ ናኙ እ ንስ ሳ ት መ ቶ ኛ ፤ የ ተ ፈ ጠ ሩ ገ በ ያዎ ች ብ ዛ ት ። ዘ ገ ባ (ሪ ፖ ርት ማ ድ ረ ግ )። ከ መ ንጋ ው ከ 5 እ ስ ከ 1 0% ው ሂብ መ ያዝ ፣ ተ ፅ እ ኖ ን ለ መ ገ ም ገ ም ቀ ላ ል የ መ ሰ ነጃ ቅ ጾ ች ን ማ ዘ ጋ ጀ ት ። የው ሂብ ቅ ጾ ች ን መ ሙ ላ ት ። ቅ ጹ ን ማ ረ ጋ ገ ጥ / መ መ ርመ ር። በ ባ ለ ፉ ት ዓ መ ታ ት ው ስ ጥ የ ታ የው ም ርታ ማ ነት (ክ ብ ደ ት ፣የ እ ርባ ታ አ ቅ ም የ ወ ተ ት ም ርት )። ው ሂቡ ን መ ፈ ተ ሽ እ ና መ ተ ንተ ን። - ለ ኤ ክ ስ ቴ ንሽ ን (የ ስ ርፀ ት ) ባ ለ ሙ ያዎ ች ፣ ለ ል ማ ት ወ ኪ ሎ ች ፣ እ ና ለ አ ርሶ -አ ደ ሮ ች ለ እ ያን ዳ ንዱ ደ ረ ጃ የሚ ሆ ኑ የ ተ ጠ ቃ ሚ ዎ ች መ ም ሪ ያዎ ች እ ና ሥ ል ጠ ናዎ ች መ ኖ ራ ቸ ው ። የተ ጠ ቃ ሚ ዎ ች መ ም ሪ ያዎ ች ለ ሁ ሉ ም መ ዳ ረ ሳ ቸ ው ፣ የ ሥ ል ጠ ናዎ ች ብ ዛ ት ፣ የሥ ል ጠ ናዎ ች ተ ፅ እ ኖ ። ማ ረ ጋ ገ ጥ እ ና ዘ ገ ባ ማ ድ ረ ግ ። ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 32 1.CSA. (2015). Agricultural sample survey 2014/2015(2007 E.C.): Volume II, Report on livestock and livestock characteristics. Statistical Bulletin 578. 2.Fatalo, T., Yitagesu, E., Aydefruhm, D., Lemma, M. and Temesgen, W. 2023. Training report on small ruminant flock health and welfare management in Ethiopia. Nairobi, Kenya: International Livestock Research Institute (ILRI). 3.Getachew, T., Haile, A., Wurzinger, M., RischB, R., Gizaw, S., Abebe, A., & Sölkner, J. (2016). Review of sheep crossbreeding based on exotic sires and among indigenous breeds in the tropics: An Ethiopian perspective. African Journal of Agricultural Research, 11(11), 901–911. https://doi.org/10.5897/AJAR2013.10626 4.Gizaw, S., & Getachew, T. (2009). The Awassi × Menz Sheep Crossbreeding Project in Ethiopia : Achievements , Challenges and Lessons Learned. 53–62. 5.Haile, A., Getachew, T., Mirkena, T., Duguma, G., Gizaw, S., Wurzinger, M., Soelkner, J., Mwai, O., Dessie, T., Abebe, A., Abate, Z., Jembere, T., Rekik, M., Lobo, R. N. B., Mwacharo, J. M., Terfa, Z. G., Kassie, G. T., Mueller, J. P., & Rischkowsky, B. (2020). Community-based sheep breeding programs generated substantial genetic gains and socioeconomic benefits. Animal, 1–9. https://doi.org/10.1017/S1751731120000269 6.Haile, A., Getachew, T., Rekik, M., Abebe, A., Abate, Z., Jimma, A., Mwacharo, J. M., Mueller, J., Belay, B., Solomon, D., Hyera, E., Nguluma, A. S., Gondwe, T., & Rischkowsky, B. (2023). How to succeed in implementing programs : Lessons from the fi eld in Eastern and Southern Africa. March, 1–9. https://doi.org/10.3389/fgene.2023.1119024 7.Haile, A., Wurzinger, M., Mirkena, T., Duguma, G., Mwai, O., & Rischkowsky, B. (2011). Guidelines for Setting up Community-based Sheep Breeding Programs in Ethiopia. ICARDA - tools and guidelines. ICARDA. 8.Haile, A., Wurzinger, M., Mueller, J., Mirkena, T., Duguma, G., Rekik, M., Mwacharo, J. M., Okeyo, M., Soelkner, J., & Rischkowsky, B. (2018). Guidelines for setting up community-based small ruminants breeding programs Second edition. 9.Mueller, J., Haile, A., Getachew, T., Santos, B., Rekik, M., Belay, B., Solomon, D., Yeheyis, L., & Rischkowsky, B. (2023). Going to scale—From community-based to population-wide genetic improvement and commercialized sheep meat supply in Ethiopia. Frontiers in Genetics, 14(March). https://doi.org/10.3389/fgene.2023.1114381 10.Mueller, J. P., Haile, A., Getachew, T., Rekik, M., & Rischkowsky, B. (2019). Genetic progress and economic benefit of community-based breeding programs for sheep out- and upscaling options in Ethiopia. Small Ruminant Research, 177(June), 124–132. https://doi.org/10.1016/j.smallrumres.2019.06.025 11.Mueller, J. P. P., Haile, A., Getachew, T., Rekik, M., & Rischkowsky, B. (2019). Genetic progress and economic benefit of community-based breeding programs for sheep out- and upscaling options in Ethiopia. Small Ruminant Research, 177(June), 124–132. https://doi.org/10.1016/j.smallrumres.2019.06.025 12.Temesgen, W., Lemma, M., Yitagesu, E., Fatalo, T., Doyle, R. and Knight-Jones, T. 2023. Community-based training on small ruminant flock health and welfare management. Nairobi, Kenya: International Livestock Research Institute (ILRI). 13.Wamatu, J., Zeleke, M., Abiso, T. and Ephrem, N. 2021. Sheep Fattening: A Training Manual for Livestock Farmers and Extension Workers in Ethiopia. Addis Ababa, Ethiopia: International Center for Agricultural Research in the Dry Areas (ICARDA). ማጣቀሻ ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 33 አባሪ 1. ለማዓዝማዎች (CBBPs) የመሠረት ውሂብ (መረጃ) ማሰባሰቢያ ቅጽ የመ ሠ ረ ት ው ሂ ብ (መ ረ ጃ ) ማ ሰ ባ ሰ ቢ ያ ቅ ጽ ወ ረ ዳ _ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ መ ን ደ ር _ __ __ __ __ __ __ _ ቀ ን _ __ __ __ __ __ __ _ BT = bi rt h ty pe = D en t = n um be r of p ai rs o f p er m an en t i nc is or , B C = bo dy c on di tio n sc or e (1 ve ry fa t a nd 5 v er y th in ), NL B = nu m be r of la m bs /k id sb or n in a ni m al s lif e tim e, N LW = n um be r of la m bs /k id s w ea ne d አባሪዎች S. No. Owner’s Name የባለቤቱ ስም Animal መለያ ቁጥር Sire የኮርማ መለያ ቁጥ Dam የእናት መለያ ቁጥር Sex ጾታ Coat Color መልክ Dent ጥርስ Age ዕድሜ Birth Type የውልደት ዓይነት Bc የሰውነት አቋም Parity ስንተኛ ጊዜ ወለደች Nlb/Nkb / የተወለዱ ግልገሎች ብዛት Nlw/Nkw ጡት የጣሉ ግልገሎች ብዛት Wattle / አንገት ላይ የተንጠለጠለ/ሉ Ruff የደረት ጸጉር Ear Size የጆሮ መጠን Horn Size የቀንድ መጠን Beard ጺም Body Weight ክብደት ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 34 አባሪ 2ሀ፡ የአፈጻጸም መከታተያ ቅጽ – ውልጃ፣ ዕድገት፣ እና መክላት የው ል ጃ እ ና የ ዕ ድ ከ ት ው ሂ ብ (በ ረ ጃ ) መ ሰ ብ ሰ ቢ ያ ሠ ን ጠ ረ ዥ L = la m b/ la m bi ng , K = K id /K id di ng , L S= li tt er s iz e, B iw t = B ir th w ig ht , W t = W ei gh t, Co l = c oa t c ol oa r, PP W T= po st -p ar tu m w ei gh t o f d oe ; S. No. Producer’s Name የባለቤቱ ስም Sire የኮርማ መለያ ቁጥ Dam የእናትመለያ ቁጥር Par ስንተኛ ጊዜ ወለደች Coat Color መልክ Dent ጥርስ LS/የተወለዱ ግልገሎች ብዛት L/K ID የግልገል መለያ Bc የሰውነት አቋም L/k Sex የግልገል ጾታ L/k col የግልገል መልክ Biwt/የግልገል የውልደት ክብደት PPWT/ከውልደት በኋላ የእናት ክብደት L/KDate የውልደት ቀን W ea ni ng ግ ል ገ ል ጡ ት የጣ ለ በ ት Si x m on th s የ 6 ወ ር Ye ar lin g የአ መ ት Di sp os al የተ ወ ገ ደ በ ት Date ቀን Wt ክብደት Reason ምክንያት Date ቀን Date ቀን Date ቀን Wt ክብደት Wt ክብደት ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 35 አባሪ 2ለ፡ የአፈጻጸም መከታተያ ቅጽ - የወተት መመዝገቢያ Mi lk re co rd sh ee t የወ ተ ት ም ር ት መ መ ዝ ገ ቢ ያ S. No. Ow ne r N am e የባ ለ ቤ ቱ ስ ም Dam ID የእናት መለያ Lambing Date የውልደት ቀን Milking Date ማለቢያ ቀን Morning Milk የጠዋት ወተት መጠን Night Milk የማታ ወተት መጠን Te st D ay 1 የአ ለ ባ ቀ ን 1 Milking Date ማለቢያ ቀን Morning Milk የጠዋት ወተት መጠን Night Milk የማታ ወተት መጠን Milking Date ማለቢያ ቀን Morning Milk የጠዋት ወተት መጠን Night Milk የማታ ወተት መጠን Te st D ay 2 የአ ለ ባ ቀ ን 2 Te st D ay 3 የአ ለ ባ ቀ ን 3 Dried Date አለባ የቆመበት ቀን ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 36 አባሪ 3፡ በአምራች ቦታዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል የአውራ/ኮርማ መከታተያ ቅጽ Br ee din g s ire in ve nt or y f or ma t ኮ ርማ በ ግ /ፍ የል መ ከ ታ ተ ያ ቅ ጽ Na m e of c oo pe ra tiv es : _ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ D is tr ic t: __ __ __ __ __ __ __ _ Vi lla ge /C BB P: _ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ _ የማ ህ በ ሩ ስ ም ፣ ወ ረ ዳ ፣ ቀ በ ሌ Ma tin g gr ou ps a nd s ir e al lo ca tio n to m at in g gr ou ps የኮ ርማ ተ ጠ ቃ ሚ ቡ ድ ን የኮ ርማ አ ጠ ቃ ቀ ም መ ከ ታ ተ ያ። ኮ ርማ ው የ ተ ገ ኘ በ ት የ ሚ ለ ው በ ግ ዥ ፣ በ ስ ጦ ታ ፣ ወ ይ ም የ ተ ወ ለ ደ ተ ብ ሎ የ ሞ ላ ። የው ል ደ ት ቀ ን/ ዕ ድ ሜ /ጥ ርስ = የ ሚ ታ ወ ቅ ከ ሆ ነ የው ል ደ ት ቀ ኑ የ ሞ ላ ፡ ካ ል ሆ ነ ግ ን ዕ ድ ሜ በ ግ ም ት ወ ይ ም የ ጥ ርስ ሁ ኔታ 1 ጥ ንድ ፣ 2 ጥ ንድ ፣ 3ጥ ንድ ፣ 4 ጥ ንድ ተ በ ሎ ይ ሞ ላ ። የተ ወ ገ ደ በ ት ም ክ ንያ ት = በ ሞ ት ፣ በ ሽ ያጭ ፣ የታ ረ ደ ፣ ስ ጦ ታ ፣ ወ ዘ ተ ተ ብ ሎ ይ ሞ ላ S. No. Mating group members የኮርማ ተጠቃሚ ቡድን አባላት ስም Sire/s ID የኮርማዎች መለያ ቁጥር Name of group leader የቡድኑ መሪ Source of sire /purchased, gift, own) ኮርማው የተገኘበት Date of acquisition ኮርማው የገባበት ቀን Price purchased የተገዛ ከሆነ ዋጋው Birth date/Age/dent at purchase የውልደት ቀን/ዕድሜ/ጥርስ Entry weight ሲገባ ያለው ክብደት Disposal date የተወገደበት ቀን Disposal wt ሲወገድ ክብደት Disposal reason የተወገደበት ምክንያት Price if sold ከተሸጠ ዋጋው Remarks አስተያየት ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 37 አባሪ 4፡ በአምራች ጣቢያዎች (ቦታዎች) ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል የሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ Qu ar te rly re po rt ing fo r n um be r o f l am bs /k ids bo rn pe r b re ed ing si re fo rm at ኮ ርማ በ ግ /ፍ የል መ ከ ታ ተ ያ ቅ ጽ Na m e of c oo pe ra tiv es : _ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ D is tr ic t: __ __ __ __ __ __ __ _ Vi lla ge /C BB P: _ __ __ __ __ __ __ __ __ _ Re po rt in g Ye ar _ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ __ የማ ህ በ ሩ ስ ም ወ ረ ዳ ቀ በ ሌ S. No. Mating Group Members የኮርማ ተጠቃሚ ቡድን አባላት ስም Name of group leader የቡድኑ መሪ Sire/s ID የኮርማዎች መለያ ቁጥር Entry date ኮርማው የገባበት ቀን Ha m le to M es ke re m ከ ሐ ም ሌ እ ስ ከ መ ስ ከ ረ ም Ti ki m t t o Ta hs as ከ ጥ ቅ ም ት እ ስ ከ ታ ህ ሳ ስ Ti r t o M eg ab it ከ ጥ ር እ ስ ከ መ ጋ ቢ ት M ia zi a to S en e ከ ሚ ያ ዝ ያ እ ስ ከ ሰ ኔ If d is po se d የሚ ወ ገ ደ ከ ሆ ነ M ወ ን ድ M ወ ን ድ M ወ ን ድ M ወ ን ድ Da te ቀ ን F ሴ ት F ሴ ት F ሴ ት F ሴ ት Re as on ም ክ ን ያ ት ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 38 አባሪ 5. በአምራች ጣቢያዎች ውስጥ በጥቅም ላይ የሚውል የሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ Da ta co lle ct ion fo rm at fo r p ro du ct ion si te /t his ne ed to be do ne in se lec te d h hs on ly. 5 to 10 % of th e h hs ca n b e c on sid er ed . የው ል ደ ት ና ክ ብ ደ ት መ ከ ታ ት ያ ቅ ጽ ። ከ ጠ ቅ ላ ላ ተ ሳ ታ ፊ ዎ ች በ ተ መ ረ ጡ ከ 5 - 10 % የ ሚ ሆ ኑ አ ርሶ አ ደ ሮ ች ላ ይ ብ ቻ የ ሚ ወ ሰ ድ ግ ል ገ ል በ ተ ወ ለ ደ በ 2 4 ሰ ዓ ት ው ስ ጥ መ ለ ያ ቁ ጥ ር ተ ሰ ጥ ቶ ት በ ዚ ህ ቅ ጽ ላ ይ መ መ ዝ ገ ብ የ ኖ ርበ ታ ል ። የው ል ደ ት ዓ ይ ነት = ነ ጠ ላ ፣ መ ንታ ወ ይ ም 3 ተ በ ሎ ይ ሞ ላ ። የተ ወ ገ ደ በ ት ም ክ ንያ ት = በ ሞ ት ፣ በ ሽ ያጭ ፣ የታ ረ ደ ፣ ስ ጦ ታ ፣ ወ ዘ ተ ተ ብ ሎ ይ ሞ ላ ። የ 6 ወ ር/ የአ መ ት ክ ብ ደ ት = የ መ ረ ጣ መ ስ ፈ ርት ን መ ሰ ረ ት በ ማ ድ ረ ግ የ 6 ወ ር ወ ይ ም የአ መ ት ክ ብ ደ ት ይ ወ ሰ ድ ። የአ ባ ት መ ለ ያ ቁ ጥ ር = ተ ክ ክ ለ ኛ ው ን አ ባ ት ማ ወ ቅ ካ ለ ተ ቻ ለ እ ስ ከ 3 በ አ ባ ት ነት የ ሚ ጠ ረ ጠ ሩ ት ይ ሞ ላ ሉ ። S. No. Owner Name የባለቤቱ ስም 6 Months/Yearling Weight የ 6 ወር/ የአመት ክብደት Disposal Date የተወገደበት ቀን Disposal Weight ሲወገድ ክብደት Disposal Reason የተወገደበት ምክንያት Price If Sold ከተሸጠ ዋጋው 6 Months/ Yearling Date ክብደት የተወሰደበት ቀን La m b/ Ki d የግ ል ገ ል Da m / እ ና ት Si re Id / የአ ባ ት መ ለ ያ ቁ ጥ ር Id የመለያ ቁጥር Sex ጾታ Birth Type የውልደት ዓይነት Coat Color መልክ Birth Date የውልደት ቀን Id መለያ ቁጥር Parity ስንተኛ ጊዜ ወለደች 1 2 3 ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 39 ግብርና ሚኒስቴር፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ የበጎችን እና የፍየሎችን ማህበረሰብ-አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ መርሃግብር ማስፋፋት እናመሰግናለን ለተጨማሪ መረጃ ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ስልክ/Phone: +251 11 646 0746 ኢሜል/Email info@moa.gov.et ድረገጽ/WEBSITE: www.moa.gov.et FACEBOOK: https://www.facebook.com/MoAEthiopia YouTube: https://www.youtube.com/@AgricultureEthiopia TELEGRAM: https://t.me/MoAEthiopianews X: https://x.com/MoA_Ethiopia ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 mailto:info@moa.gov.et https://l.facebook.com/l.php?u=http%3A%2F%2Fwww.moa.gov.et%2F%3Ffbclid%3DIwZXh0bgNhZW0CMTAAAR0vuZ46RzMX7qDsYmNhn-00Fc6qvJtjrxckFdXnMQavekeUnK_0L7mDmBU_aem_-LjP5UmVDeMFELdHXv7OKw&h=AT2nT0zL6jxdJBujfSx9dxP5cKnXqQ2uKC_vZr1CAf3CgqQWESHHUXfgD9N4wUDvXUzRf-90f1f8vUhRkhvAyHrv7uQWoipYVtEoixmV8aOt-TlBWIjJfJUcjpp3A_bDcQ&__tn__=-UK-R&c%5b0%5d=AT20V3a1YQS1pMOaYCVqTzDxVRjdg1dBRwUe-xkd_cmy0FYEmEhcCoxW2TcafTHoN6HiOJMv2ztfGURWzoiVe4L4gxbi_Xb507pkPpAH13Gf7lFIF4BcLVr2RemxuDqdcA8KV-B9b-OjJRXd6EgVyU4jrer75r-kux86BG3vgE2ybopbGnhJ5XF7gaT5D7C7TGUD0ueCwfODOXDyVTsUL72tCQ https://web.facebook.com/MoAEthiopia?__cft__%5b0%5d=AZUhQSErbdVt1tEgB6HSPnUXZhtOsOUhhrrIySnUZ0ziKgFzrVfuroRQSkQnn5gRYLxqVTHl_kBcgHqdxnxttfaMBoD2lJVvDvkXFEIo5LH45Eam3jfMts2AGrIpKjbiavYNPZ7cBLl1rJzwOcciclRVxpOeP1dK52cajcpvaOz-h2Ufwm_sM41tDOVatS5shA8&__tn__=-%5dK-R https://www.youtube.com/@AgricultureEthiopia?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTAAAR0FuGQ_X5aYxo-tbYkYjRqlj2qjYc4OyE7NYaCqLDT8nMrnscmakKRP0I0_aem_ix_ZlyVP_GNX4XNYbzYpwQ https://l.facebook.com/l.php?u=https%3A%2F%2Ft.me%2FMoAEthiopianews%3Ffbclid%3DIwZXh0bgNhZW0CMTAAAR0sTrNQKf09jDu7D3rZZFPNc6vq8JY6MAH0eaVCTZ39iDcnz7kffaEXueI_aem_3MxcnZIT0gAMHSJMCBf7MA&h=AT1B58xW0g2ouhI6suEBhmUj7tlduGp6A6Th2tBn_E7EbgH34jWILm1HX3qWp0ntQmZNuyxlWOQx_3ilvgWsvYAMk_knMFab8d48PDvu_kXVa7ShLg5qLCWyiv2n-9EUeg&__tn__=-UK-R&c%5b0%5d=AT20V3a1YQS1pMOaYCVqTzDxVRjdg1dBRwUe-xkd_cmy0FYEmEhcCoxW2TcafTHoN6HiOJMv2ztfGURWzoiVe4L4gxbi_Xb507pkPpAH13Gf7lFIF4BcLVr2RemxuDqdcA8KV-B9b-OjJRXd6EgVyU4jrer75r-kux86BG3vgE2ybopbGnhJ5XF7gaT5D7C7TGUD0ueCwfODOXDyVTsUL72tCQ https://x.com/MoA_Ethiopia?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTAAAR1TlU3S1_u00AbWIf0cxB-dr4Ep4Voj52NQAPCy1Jm1zMOD1uuQUhCrF-I_aem_Xwsb8KYW6jA9DkePIWw-rw የተጠቃሚ ማስታወሻ የተጠቃሚ ገጽ 02 0301 ማዓዝማዎችን ማስፋፋት፡ በግ እና ፍየል ግ.ሚ.፡ የተጠቃሚዎች መምሪያ፣ 2017 48