i ሥርዓተ ፆታን እና ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስን በገበያ መር የግብርና እድገት ውስጥ እንደ ዋናው ተግባር ማየት ለግምባር ቀደም ልማት ሠራተኞች የስልጠና መመሪያ ሥርዓተ ፆታን እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በገበያ መር የግብርና እድገት ውስጥ እንደ ዋናው ተግባር ማየት ለግምባር ቀደም ልማት ሠራተኞች የስልጠና መመሪያ አዘጋጆች ለምለም አረጉ፣ ክሌር ቪሾፕ-ሳምብሩክ፣ ራንጀታ ፑስኩር፣ አረሳውም መንገሻ፣ ኤፍሬም ተሰማና ዛህራ አሊ ምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ፕሮጀክት(IPMS) ዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስትቲዮት(ILRI) ተዛማጅ ደራሲ፦ l.aregu@cgiar.org የደራሲያን ጥምረት ለምለም አረጉ፣ የምርታማነትና ገበያ ስኬት ማሻሻያ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ገበሬዎች (IPMS)፣ ዓለም አቀ ፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲቲዩት (ILRS) አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ክሌር ቢሾፕ-ሳምብሩክ፣ የኤችአይቪ/ኤድስ አማካሪ፣ የምርታማነትና ገበያ ስኬት ማሻሻያ ፕሮጀክት ለኢትዮ ጵያ ገበሬዎች (IPMS)፣ ዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (ILRI) አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ራንጄታ ፑስኩር፣ የፕሮግራሙ መሪ፣ እንስሳት እርባታ ማሻሻያ ዘዴዎች፣ ዓለም ዓቀፍ የእንስሳት ምርም ር ኢንስቲTዮት፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ አረሳውም መንገሻ፣ አሰልጣኝ የግል አማካሪ፣ አዋሳ ኢትዮጵዮያ ኤፍሬም ተሰማ፣ አሰልጣኝ፣ የግል አማካ ሪ፣ አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ ዛሕራ አሊ፣ አሰልጣኝ፣ የግል አማካሪ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጽያ © 2001 ዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (ILRI) ሙሉ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ለንግድ ላልሆነ ሥራ ይህ ሕትመት በከፊል በባለመብቱ በዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት እውቅና ሊባዛ ይችላል። ISBN 92–9146–236–5 iv ማውጫ ገጽ ምህፃር ቃላት vi መቅድም vii ምሥጋና vii ለመደርደሪያነት የቀረበ የአሰልጣኞች መመሪያ 3 ክፍለ ጊዜ 1 እንኳን ደህና መጣችሁና የእርስ በርስ ትውውቅ 6 ክፍለ ጊዜ 2 የቡድን ምስረታ 9 ክፍለ ጊዜ 3 የሥርዓተ ፆታ ትንተና መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች 10 ክፍለ ጊዜ 4 የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ትንተና መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች 13 ክፍለ ጊዜ 5 የሥርዓተ ፆታን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ግንኙነት 16 ክፍለ ጊዜ 6 የሥርዓተ ፆታና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ተፅእኖ በግብርና ምርትና ገበያ ላይ 17 ክፍለ ጊዜ 7 በግብርና ምርቶች ውስጥ የሥርዓተ ፆታ ትንተና ዘዴዎች 19 ክፍለ ጊዜ 8 በገጠሩ ሕብረተሰብ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ትንተና ዘዴዎች 21 ክፍለ ጊዜ 9 የማሳለጥ/የማሰተባበር ጥበብ 23 ክፍለ ጊዜ 10 የመስክ ሥራ ዝግጅት 25 ክፍለ ጊዜ 10 መረጃን መተንተንና መተርጐም 27 ክፍለ ጊዜ 12 በሥርዓተ ፆታን ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ላይ በተነሱ አስተያየቶች ዙሪያ ጥልቅ ሀሳቦችን ማፍራት 29 ክፍለ ጊዜ 13 የድርጊት መርሃ ግብር ዝግጅት 31 ክፍለ ጊዜ 14 የድርጊት መርሃ ግብርን መከታተል 33 ክፍለ ጊዜ 15 ማጠቃለልና ወደፊት መቀጠል 35 v የተዘጋጁ ጽሑፎች የተዘጋጁ ጽሑፎች 1 የወርክ ሾፑ አላማ 38 የተዘጋጁ ጽሑፎች 2 የሥርዓተ ፆታ መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳብና የሥርዓተ ፆታ ትንተና 42 የተዘጋጁ ጽሑፎች 3 የኤች.አይ.ቪ ኤድስን መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች መረዳት 44 የተዘጋጁ ጽሑፎች 4 የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ትንተና መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች በገጠሩ ህስረተሰብ 48 የተዘጋጁ ጽሑፎች 5 ሴቶችን በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ተጠቂ የሚያደርጓቸው ምክንያቶችና ተዛማችነታቸው 55 የተዘጋጁ ጽሑፎች 6 የችግር ምክንያትና ውጤት ትስስር መግለጫ ዛፍ መርሆዎች 56 የተዘጋጁ ጽሑፎች 7 በፆታ የተሰባጠረ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚረዳ አሳታፊ ዘዴ ወይም መሳሪያ 57 የተዘጋጁ ጽሑፎች 8 በማህበረሰቡ የሚሰራ ካርታ 59 የተዘጋጁ ጽሑፎች 9 ሥርዓተ ፆታና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በህብረተሰቡ ውስጥ እንደዋነኛው ተግባር እንዲ ወሰድ የሚረዳ የማሳለጫ ሙያ ዝግጅቶች 60 የተዘጋጁ ጽሑፎች 10 የመስክ ሥራ ሂደት 62 የተዘጋጁ ጽሑፎች 11 በከፊል የተዘጋጁ ቃለመጠይቆችን እንዴት እንደምናቀርብ 63 የተዘጋጁ ጽሑፎች 12 ሥርዓተ ፆታና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በህብረተሰቡ ውስጥ እንደዋነኛ ተግባር እንዲወሰዱ ለማድረግ የሚረዱ ከግብርና ጋር የተያያዙ ሀሳቦችን ማፍለቅ 65 የተዘጋጁ ጽሑፎች 13 የመርሃ ግብር ዝግጅት 73 የተዘጋጁ ጽሑፎች 14 ሥርዓተ ፆታንና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ከክትትልና ግምገማ ዘዴዎች ጋር ማቀናጀት 76 አባሪ 1 የሥልጠና ቅምሻዎች 79 vi ምህፃረ ቃሎች ABC - Abstain, Be faithful and Condom use ...........መታቀብ መታመንና በኮንዶም መጠቀም AIDS - Acquired Immune Deficiency Syndrome ........ከሌላ ሰው የተገኘ የሰውነት የመከላከያ ስርዓት መዳከምና የበሽታዎች ምልክቶች ART - Anti – Retroviral Treatment .........................የፀረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሕክምና ARV - Anti – Retroviral .............................................ፀረ ኤችአይ ቪ DA - Development Agent .........................................የልማት ሰራተኛ FHH - Female Headed Household ............................በእማወራ የሚመራ ቤተሰብ FTC - Farmers Training center .................................የገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከል GO- Government Organization ...............................መንግስታዊ ድርጅት HAPCO - HIV/AIDS Prevention and Control Office .....የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ HEW - Health Extension Worker ................................የጤና ኤክስቴሽን ሠራተኛ HH - Head of Household .........................................የቤተሰብ ኃላፊ HIV - Human Immunodeficiency Virus .....................በሰው ዘር ላይ ብቻ የሚታይ በሽታን የመከላከል ሃይል የሚያደክም ረቂቅ ህዋስ HTP - Harmful Traditional Practice ...........................ባሕላዊ ጎጂ ድርጊቶች IPMS - Improving Productivity & Market ....................የምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ success of Ethiopian farmer’s project ኘሮጀክት ለኢትየጵያ ገበሬዎች MHH - Male Headed Household ................................በወንድ የሚመራ ቤተሰብ NGO - Non-governmental Organization ......................መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት OoARD - Office of Agriculture & Rural Development. የግብርናና የገጠር ልማት ድርጅት PA - Peasant Association ........................................የገበሬ ማህበር PGN - Practical Gender Needs ..................................ተግባራዊ የሥርዓተ ፆታ ፍላጎቶች PLW - Pilot Learning Woreda ....................................ለመማሪያ የተመረጠ ወረዳ PLWHA- Person Living with HIV/AIDS ..........................ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር የሚኖር ሰው PRA - Participatory Rural Appraisal ..........................አሳታፊ የገጠር አሰሳ RDA - Research & Development Assistance ............የምርምርና የልማት ረዳት RDO - Research & Development Officer ..................የምርምርና የልማት ኃላፊ SGN - Strategic Gender Needs .................................ስልታዊ የሥርዓተ ፆታ ፍላጐቶች SS - Semi Structured Interview ...............................በከፊል የተዘጋጀ ቃለ መጠይቅ VCT - Voluntary Canceling and Testing ................... በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የምክር እና የምር ምር አገልግሎት vii መቅድም የገጠሩን ማህበረሰብ ወደ ገበያ መር ግብርና አቅጣጫ እንዲይዝ ልናግዘው ካሰብንና ለውጡ እንዲመጣ ለማ ድረግ፣ ተፅእኖ ለመፍጠርና ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን የለውጥ አራማጆች በቅድሚያ ልናስባቸው ይገባል። ወ ንዶችም ሆኑ ሴቶች በግብዓት አቅርቦት፣ በማምረትና በግብይት ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፣ ይህንን አቅም በአ ግባቡ ለመረዳት የኤክስቴንሽን ሰራተኞች ማን ምን ድርሻ መጫወት እንደሚችል ማን ደግሞ የተለየ ተግባር የመስራት አቅም እንዳለው ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል። በብዙ አጋጣሚዎች በገበያ መር የግብርና እሴት ሰን ሰለት ውስጥ ወንዶች ከፍተኛውን ዋጋ ያለው ድርሻ እንደሚጫወቱ ማስተዋል አያዳግትም ይህ መመሪያ የተመሰረተው ከምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ለኢትዮጽያ ገበሬዎች ፕሮጀክት በ10 የሙ ከራ ወረዳዎች ውስጥ በተገኘ ተሞክሮ ላይ ነው፡፡ አላማው የኤክስቴንሽን ሰራተኞችን የወንዶችንና የሴቶችን ሚና በገበያ ተኮር የግብርና ልማት እሴት ሰንሰለት ውስጥ ምን እንደሚመስል ለመረዳት እንዲችሉና ወደ ተ ሻለና የተጠጋጋ ፆታዊ የሥራ ክፍፍል ወዳለው ገበያ መር የግብርና ልማት መስራት እንዲችሉ ነው። የገበያ መር የግብርና ልማት እንቅስቃሴ በጨመረ ቁጥር የኤችአይቪ/ኤድስ ስጋትም እያደገ እንደሚሄድ በጥ ቅሉ ይታመናል፡፡ የግብዓት ግዥን ለመፈፀምና ምርትን ለገበያ ለማቅረብ የሚደረገው ከፍተኛ እንቅስቃሴ እ ያደገ ከሚሄደው ገንዘብን የማባከን አቅማችን ጋር ተደምሮ ለኤችአይቪ የመጋለጥ አደጋን የሚያሰፋ መሆና ቸው በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ነው ። የምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ፕሮጀክት እንደዚህ አ ይነቱን አቅም ያለው ስጋት ዝም ሊለው ስለማይችል በየወረዳው ባሉ የሙከራ ወረዳዎች ሁኔታዎችን ለመ ተንተንና ለማገናዘብ የሚረዱ ለችግሩ የመፍትሔ ሀሳብ እንድናቀርብ የማያግዙ ዘዴዎችን አዘጋጅቷል። ይህ የስልጠናው አካል በመሆን የኤክስቴንሽን ሰራተኞች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ኤችአይቪ/ኤድስን እን ዴት መታገል እንዳለባቸው አቋማቸውንና ብቃታቸውን በማዳበር ላይ ያተኩራል ። ከዚህ ሌላ ይህንን መመሪያ ያዘጋጁትን ደራሲያን በእጅጉ ማመስገን እየወደድኩ የሥራቸው ፍሬ የሆነውን ሥርዓተ ፆታና ኤችአይቬ/ኤድስን የተገነዘበ ገበያ መር የግብርና ልማት የማምጣትን ሙያ የሚያዳብር እገዛ እንደሚያደርግ ተስፋ አደርጋለሁ ። ድርክ ሆክስትራ የምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ፕሮጀክት ማናጀር viii ምስጋና ይህንን የማሰልጠኛ መመሪያ ስናዘጋጅ በከፍተኛ ደረጃ ለረዱን ለምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ለኢት ዮጵያ ገበሬዎች ኘሮጀክት በተለይም ባሉት ወረዳዎች ሁሉ ከጥቅምት 2001 እስከ ጥር 2001 ድረስ በመስ ክ ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች በማድረስና መመሪያውን በመፈተሽ ላደረገልን አስተዋጽኦ ደራሲያኑ ምስጋናችንን ለኘሮጀክቱ ማቅረብ እንወዳለን ። በሙከራ ወረዳዎች የሚገኙ የምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ፕሮጀክት ሰራተኞች፣ የመንግስት ባልደረ ቦች ላደረጉልን ዋጋ ያለው እገዛና የማሻሻያ ሃሳቦች ምስጋናችንን ልናቀርብ እንወዳለን። ይህ መመሪያ በሙ ከራ ወረዳዎች ሥርዓተ ፆታንና ኤችአይቪ/ኤድስን እንደዋና ተግባር እንዲወሰድ በህብረተሰቡ ውስጥ ከተደረ ጉ እውነተኛ ተሞክሮዎች ትምሕርት ወስዷል። በመጨረሻም ደራሲያኑ ለካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (CIDA) ፣ ላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍና ለምርታ ማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ኘሮጀክት የገንዘብ እርዳታ በማድረግና የሥርዓተ ፆታንና የኤችአይቪ/ኤድስን ጉዳዮች በማጣመር በኩል ላበረከቱት ትስተዋፅኦ ምስጋናችን ይድረሳችሁ እንላለን ። 1 መግቢያ ምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ፕሮጀክትን (IPMS) በሥራ ላይ እያዋሉ ያሉት ዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲቲዮትና (ILRI) የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ናቸው። ምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች (IPMS) በካናዳ አለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (CIDA) የሚረዳ የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ነው። የሚሰራውም በፌደራል፣ በክልልና በወረዳ ደረጃ ተቋማትን በማጠናከር፣ አቅምን በመገንባትና በትምሕርት አመራር ላይ ነው። ፕሮጀክቱ በአራት ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ማለትም በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሔረሰïች ክልል ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች በተመረጡ 10 የሙከራ ወረዳዎች በተግባር የተደገፈ ምርምር ያካሂዳል። የሙከራ ወረዳዎቹ ተግባር የሚያተኩረው ለገበያ በሚውሉ ምርቶች /ሰብሎችና እንስሳት/ ቅድሚያ ሰጥቶ በማስተዋወቅ ላይ ሲሆን የገበያ መር የተቀናጀ የግብርና ልማትን በመደገፍ የግብርና ምርቶችን በተለያየ ዘዴ አሻሽሎ ማቅረቢያ ዘዴን /እሴት መጨመርን/ በማስተዋወቅ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፣ የግብዓት አቅራቢዎችን ተሳትፎ በማበራከት፣ የገጠር ፋይናንስን፤ የገበሬ ማህበራትና የሚያከናውነው ሚዛናዊ በሆነ የፆታ ክፍፍል ላይ በመመርኮዝ የአከባቢን ሥነ ምህዳር በማያዛባ መልኩ ሲሆን እንዲሁም ደግሞ የኤችአይቪ/ኤድስን ስጋትም ለመቀነስ ይጥራል። ኘሮጀክቱ በሚያደርጋቸው የሥራ እንቅስቃሴና ድጋፎች በሙሉ የሥርዓተ ፆታንና የኤችአይቪ/ ኤድስን ጉዳዮችንም እንዲዳሰሱ የሚያስችለውን መረጃና መመሪያ ለማግኘት ኘሮጀክቱ የሥርዓተ ፆታንና የኤችአይቪ ስትራቴጂ ነድፏል፡፡ የመጀመሪያው እርምጃ የነበረው በአሥሩም የሙከራ ወረዳዎች ለእያንዳንዱ የግብና ምርቶች የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ መሰረታዊ መረጃዎችን መሰብሰብ ነበር። ይህ በበኩሉ የተለያዩ የሀሳብ ለሀሳብ መለዋወጫና መማሪያ ሰነዶች ለምሳሌ የሥርዓተ ፆታ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዶችን፣ የኤችአይቪ/ኤድስ ግንባቤ ማስጨበጫ ሰነዶችን፣ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ የእወነታ ሰነዶችን ለማዘጋጀት አስችሏል። ይህ ደግሞ በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተባባሪ ድርጅቶች አማካይነት በብዛት ሊሰራጭ ችሏል። እነዚህ ሰነዶች የምርታማነት ማሻሻያና ገበያ ስኬት ሰራተኞችና የተባባሪ ድርጅቶች ሰራተኞችን ለምን ሥርዓተ ፆታና ኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮችን ማንሳት እንዳስፈለገ ሰፊ ግንዞቤ ከማስጨበጣቸው ባሻገር የሥርዓ ፆታና ኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮችን እንዴት በሥራችን እቅድ ውስጥ ማካተት እንዳለብን የተለያዩ አማራጮችን ለማመላከት አስችሏል። ከግብርና ልማት ሚኒስቴርና ከሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ሰራተኞች ሥርዓተ ፆታንና ኤችአይቪ /ኤድስን ለማህበረሰቡ ለማድረስ የሚረዱ ስልጠናዎችና ተግባር ተኮር የሆኑ ደጋፊ ሰነዶችን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቀርበዋል። በዚህም መሰረት ይህ በጉዳዩ ላይ ከተፃፉ ጽሑፎችና ከ1997 ጀምሮ ሥርዓተ ፆታና ኤችአይቪ/ኤድስን ከፕሮጀክቱ ሥራ ጋር አዋህዶ በመስራት በአሥሩም የሙከራ ወረዳዎች ከተገኘው ተሞክሮ በማቀናጀት ይህ የሰልጠና መመሪያ ሊዘጋጅ ችሏል። ይህ መመሪያ በአሥሩም የሙከራ ወረዳዎች በተዘጋጁ ወርክሾፓችና በስልጠና ትምሕርቶች ተሞክሮ በተገኘው ውጤት መሰረት አስፈላጊ የሆነው ክፍል እንዲሻሻል ተደርጓል። ይህ የማሰልጠኛ መመሪያ የተዘጋጀው ለተለያዩ የገበያ ተኮር የገጠር ልማትን ለሁለቱም ፆታ በእኩልነት ለሚያስተዋውቁ ድርጅቶች /ለምሳሌ የግብርናና የገጠር ልማት ሚኒስቴር፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች/ እንዲሆን ተብሎ የተዘጋጀ ነው። የ5ቀን የስልጠና ትምሕርት ዋና ትኩረት በግምባር ቀደም የሚገኙ የልማት ሰራተኞች በየዕለቱ በገጠሩ ውስጥ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሥርዓተ ፆታንና የኤችአይቪ/ኤድስን ከገበያ መር የገጠር እድገት ጋር አጣጥመው እንዴት መስራት እንዳለባቸው አቅማቸውን በተግባራዊ እውቀት ለመገንባት ነው፡፡ ይህ የማሰልጠኛ መመሪያ የግብርናና የገጠር ልማት የኤክስቴንሽን ሰራተኞችን፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የኤክስቴንሽን ሰራተኞችና ሱፐርቫይዘሮችን፣ የወረዳ ባለሙያዎችና የልማት ሰራተኞችን፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን፣ የፌዴራልና የክልል የምርምር ማዕከሎችን፣ ዩኒቨርስቲዎችን፣ የግብርና ሙያ 2 ማሰልጠኛ ኮሌጆችን፣ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮዎችን፣ ቀደምት አላማው አድርጓል። እንዲሁም ደግሞ በገጠር ልማት ሥራ ላይ የሚሳተፉ የሲቪክስ ማህበራትና የግብርና አገልግሎት ሰጨ ድርጅቶችንም ሊጠቅም ይችላል ። ስልጠናው ሁለቱንም የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስን መሰረታዊ ቁምነገሮችን በጥምረት የሚመለከት ነው። መመሪያው 15 የስልጠና ክፍለ ጊዜ በዝርዝር፣ የየክፍለ ጊዜው አስፈላጊነት፣ ዓላማውንና ዝርዝሩን እንዲሁም ልዩ ልዩ ተግባራትንና አሳታፊ መልመጃዎችን ይዟል። እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ በድምሩ 14 ከሚሆኑ ደጋፊ ጽሑፎች ጋር ተቀናጅተዋል። አባሪ 1 በበኩሉ የአሳታፊ ስልጠናን አሰራር እንደ ቅምሻ ያቀርባል። ይህ መመሪያ ከምርታማነትና ገበያ ስኬት ማሻሻያ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ መሰብሰቢያ ሰነዶች ጋር በማጣመር መጠቀም ያስፈልጋል። ሁለቱንም ከሚከተለው የዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ድህረ ገፅ ማግኘት ይቻላል። http://www.ipms-ethiopia.org/content/files/Documnets/Training%20Materials/Toolkit%20-%20Gender.pdf; http://www.ipms-ethiopia.org/content/files/Documnets/Training%20Materials/Toolkit%20-%20Gender%20(Amharic). pdf http://www.ipms-ethiopia.org/content/files/Documnets/Training%20Materials/Toolkit%20-%20HIV.pdf; http://www.ipms-ethiopia.org/content/files/Documnets/Training%20Materials/Toolkit%20- %20HIV.%20(Amharic).pdf 3 ለመንደርደሪያ የቀረበ የማሰልጠኛ የጊዜ ሰሌዳ ሰንጠረዥ 1- አጠቃላይ የማሰልጠኛ የጊዜ ሰሌዳ ቀን በሰዓት አርዕስት የሚፈጀው ጊዜ 1ኛ ቀን 02:45 እንኳን ደህና መጣችሁ 0:15 ደቂቃ 03:00 1 የፕርግራምና የእርስ በርስ ትውውቅ 1:30 ደቂቃ 04:30 የሻይ ሰዓት 04:45 2 የሥርዓተ ፆታ ትንተና መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች 1:45 06:30 የምሳ ሰዓት 1:15 07:45 3የኤችአይቪ/ኤድስ መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳብ ትንተና 1. 1:45 09:30 የሻይ ሰዓት 15 ደቂቃ 09:45 4 የኤችአይቪ/ኤድስ መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብ ትንተና 2 1:00 ሰዓት 10:45 5 የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ግንኙነት 30 ደቂቃ 11:15 ቡድን ምስረታ 15 ደቂቃ 2ኛቀን 02:30 በቀደመው ትምሕርት ላይ የተሳታፊዎች አስተያየት 30 ደቂቃ 03:00 6 የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ተፅዕኖ በግብርና 1:30 ደቂቃ ምርትና ገበያ ላይ 04:30 የሻይ ሰዓት 15 ደቂቃ 04:45 7 በግብርና ምርቶች ላይ የሥርዓተ ፆታ ትንተና ስልቶች 1:45 ደቂቃ 06:30 ምሳ 1:15 ደቂቃ 07:45 የሥርዓተ ፆታ ትንተና /የቀጠለ/ 30 ደቂቃ 08:15 8 በገጠሩ ህብረተሰብ የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና 1:15 ደቂቃ 09:45 የሻይ ሰዓት 09:45 የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና /የቀጠለ/ 1:00 ሰዓት 10:45 9 የመስክ ሥራ ትውውቅና ራስን መገምገም 45 ደቂቃ 3ኛ ቀን 02:30 በቀደመው ትምሕርት ላይ የተሳታፊዎች አስተያየት 30 ደቂቃ 03:00 10 የማሳለጥ/የማስተባበር ጥበብ 1:30 ደቂቃ 04:30 የሻይ ሰዓት 15 ደቂቃ 04:45 የመስክ ሥራ ዝግጅት 1:45 ደቂቃ 06:30 ምሳ 1:15 ደቂቃ 07:45 የመስክ ሥራ 4 ሰዓት 4ኛቀን 02:45 የተሳታፊዎች አስተያየት 30 ደቂቃ 03:00 11 መረጃ መተንተንና መተርጐም 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ 04:30 የሻይ ሰዓት 15 ደቂቃ 04:45 መረጃ መተንተንና መተርጐም /የቀጠለ/ 1 ሰዓት ከ15 ደቂቃ 06:00 ራስን መመዘንና መገምገም 30 ደቂቃ 06:30 ምሳ 1 ሰዓት ከ15 ደቂቃ 07:45 ከመስክ የተገኘውንና የተጠናቀቀውን ውጤት ማቅረብ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ 09:30 የሻይ ሰዓት 15 ደቂቃ 09:45 12 ሀሳቦችን ማፍለቅ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ 4 5ኛ ቀን 02:30 የተሳታፊዎቹ አስተያየት 30ደቂቃ 03:00 13 የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ 04:30 የሻይ ሰዓት 15 ደቂቃ 04:45 የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት የቀጠለ 1 ሰዓት 05:45 የድርጊት መርሃ ግብሩን ማቅረብ 45 ደቂቃ 06:30 ምሳ 1ሰዓት ከ15 ደቂቃ 07:45 መርሃ ግብር ማቅረብ /የቀጠለ/ 45 ደቂቃ 08:30 ግምገማና ምዘና 1 ሰዓት 09:30 የሻይ ሰዓት 15 ደቂቃ 09:45 ግምገማና ምዘና /የቀጠለ/ 45 ደቂቃ 10:30 የተሳታፊዎች አስተያየት 20 ደቂቃ 10:50 14 ማጠቃለልና ወደፊት መቀጠል 1ሰዓት 5 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለጊዜ1 እንኳን ደህና መጣችሁና የዕርስ በዕርስ መተዋወቅ ክፍለጊዜ2 የቡድን ምስረታ ክፍለጊዜ3 የሥርዓተ ፆታ ትንተና መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች ክፍለጊዜ4 የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች ክፍለጊዜ5 የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ግንኙነት ክፍለጊዜ6 የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ተፅእኖ በግብርና ምርትና ገበያ ላይ ክፍለጊዜ7 በግብርና ምርት የአመራር ሂደት ውስጥ የሥርዓተ ፆታ ትንተና መንገዶች ክፍለጊዜ8 በገጠሩ ህብረተሰብ የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና መንገዶች ክፍለጊዜ9 የማስተባበር ወይም የማሳለጥ ክህሎት ክፍለ ጊዜ 10 የመስክ ሥራ ዝግጅት ክፍለ ገዜ 11 መረጃን መተንተንና መተርጐም ክፍለ ጊዜ 12 በሥርዓተ ፆታና ኤችአይቪ/ኤድስ በቀረቡ አስተያየቶተች ላይ የተለያዩ ጥልቅ ሀሳቦችን ማፍለቅ ክፍለ ጊዜ 13 የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት ክፍለ ጊዜ 14 የድርጊት መርሃ ግብሩን መገምገም ክፍለ ጊዜ 15 ማጠቃለያ እና ቀጣይ ሥራዎች 6 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 1 እንኳን ደህና መጣችሁና የእርስ በርስ ትውውቅ የክፍለ ጊዜው ያስፈለገበ ት ምክንያት ይህ ክፍለ ጊዜ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ተሳታፊዎች የተዘጋጀውን የጊዜ ሰሌዳ ማሳወቅ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ተሳታፊዎች እርስ በርስ መተዋወቅና ልምድ መለዋወጥ የሚጀምሩበት ጊዜ ነው፡፡ ይህም በተሳታፊዎች መሃል ያለ ውን ዝምታ በመስበር ልምዳቸውንና አስተያየታቸውን በግልፅ ለመለዋወጥ እ ንደሚረዳቸው ይታሰባል ። የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች የሚከተሉትን ነጥቦች ይጨብጣ ሉ ፣ ሌሎች ተሳታፊዎችን መለየትና የኋላ ታሪካቸውን መረዳት• ከስልጣናው የሚጠብቁትን ለሌሎች ማካፈልና እነሱ ደግሞ • ከስልጠናው ምን እንደሚጠብቁ ማወቅ የሥልጠናውን አስፈላጊነትና ዓላማ መረዳት• በአምስቱ ቀን ሥልጠናው የሚዳስሷቸውን አርዕስቶችና ቁምነገሮች• እንዲሁም የሚቀስሙትን ሙያ በአግባቡ መረዳት መቻል የክፍለ ጊዜው ዋና ዋና ተግባራት እንኳን ደህና መጣችሁ• እርስ በርስ መተዋወቅ• ተሳታፊዎች ምን ይጠብቃሉ• የትምሕርቱ ዓላማና ፕሮግራም• አስፈላጊ ቁሳቁሶች የ A4 ወይም በ21*30 ሳ.ሜ. መጠን የተቆረጡ ወረቀቶች• ካርዶች • እስኪሪፕቶዎች• የመሸፈኛ ኘላስተሮች• የማሳያ ሰሌዳ/ቦርድ• የሚፈጀው ጊዜ 105 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት እንኳን ደህና መጣችሁ አስተባባሪው/ዋ/ የክብር እንግዳው የእንኳን ደህና መጣ ችሁና የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ ይጋብዛል/ትጋብ ዛለች 15 ደቂቃ 7 መልመጃ ሀ. የእርስ በርስ ትውውቅ ለተሳታፊዎች ስልጠናው አሳታፊ እንደመሆኑ• አንዱ ከሌላው ተሳታፊ የሚማርበትና ልምድ የሚ ለዋወጥበት መሆኑን እንዲረዱት ማድረግና ለዚህም የርስ በርስ ትውውቅና ቅርርብ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን መግለፅ ይህንን ለማሳካት አዳዲስ ዘዴዎችን መጠቀም፤ ም• ክንያቱም ታሳታፊዎች ገና ከወዲሁ ጉጉት እንዲያ ድርባቸውና ፍላጎት እንዲያዳብሩ ስለሚያደርግ ተሳታፊዎች ስለሥርዓተ ፆታና ስለኤችአይቪ/ ኤድ• ስ የዕውቀትና የክህሎት ደረጃ ቢያንስ አምስት ቢበ ዛ አስር ነጥቦችን /5-10/ በመስጠት እራሳቸውን እ ንዲመዝኑ ማድረግ ከ 5-10 ያሉትን ቁጥሮች በተለያዩ ቁርጥራጭ ወረ• ቀቶች ፃፉና በክፍሉ ዙሪያ ግድግዳ ላይ ለጥፋቸው ተሳታፊዎች እራሳቸውን ባስቀመጡት ነጥብ ቁጥር • አጠገብ እንዲቆሙ ወይም ቁጥሮችን በማቧደን ለ ምሳሌ ከ5-6፣ ከ7-8፣ ከ9-10 ያሉትን ባንድ ላይ በ ማድረግ በየቡድኑ የተመጣጠነ የአባላት ቁጥር እን ዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡ እዛው በቆሙበት እያንዳንዱ ተሳታፊ ለቡድን አባ• ል ራሱን እንዲያስተዋውቅ ማድረግ፡፡ ተሳታፊዎች ሁሉም በተገኙበት ስማቸውን፣ የሥ• ራ ቦታ፣ የኃላፊነት ደረጃና የጋብቻ ሁኔታ በአንድ ገፅ ወረቀት ላይ እንዲፅፉ አድርግና ግድግዳ ላይ ለ ጥፈው ። 30 ደቂቃ ለ/ ከስልጠናው ምን ይጠበቃል ? በካርድ ላይ የአፃፃፍ ደንብን አስረዳ/ጂ• ተሳታፈዎች በየቡድናቸው የሚከተሉትን ጥያቄዎ• ች በማንሳት ከስልጠናው ምን እንደሚጠብቁ እን ዲወያዩና መልሳቸውንም በካርዳቸው ላይ እንዲጽ ፉ ጠይቅ በዚህ ስልጠና ምን መማር ይፈልጋሉ?• ከስልጠናው ዝግጅትና አቅርቦት መመቻቸት አንፃር • ምን ይጠብቃሉ፣ ካርዶቹን በሚገባ ከልሳቸው የሀ ሳብ ተመሳሳይነትን ወይም ልዩነትን የማሳያ ዘዴ አድርገህ ተጠቀምባ ቸው 20 ደቂቃ 8 ሐ. የትምሕርቱ ዓላማና ኘሮግራም የስልጠናውን ዝርዝር ዓላማ አስረዳ/ጂ• የስልጠናው ተሳታፊዎች ከስልጠናው የሚጠብቁት• ንና የስልጠናውን ዓላማ ተመሳሳይ መሆናቸውን አ ነፃፅር/ሪ የስልጠናውን ዝርዝር ኘሮግራም በፅሑፍ 1 በተዘ• ጋጀ Flow chart በመጠቀም ምክንያታዊ ትስስራቸ ውን አስርዳ/ጂ 25 ደቂቃ መ. መሰረታዊ ሕጐች ተሳታፊዎች ሥልጠናው የተሳካና ውጤታማ እን• ዲሆን ምን ዓይነት አካሄድ እንደሚፈልጉ ጠይቅ/ቂ። ሁሉንም አስተያየቶች በተገላጭ ቻርት ላይ መዝ• ግቧቸው በተገላጭ ቻርት የተፃፉትን በደንብ ሊታዩ በሚች• ሉበት ቦታ ለጥፋቸው/ለጥፊያቸው ተሳታፊዎችም ሆኑ አዘጋጁ የተዘረዘሩትን ህጐች • ምንግዜም እንደመመሪያ ሊያከብራቸው የሚገቡና አዎንታዊ የሆነ ልምድ ይዘን እንድንወጣ የሚያደ ርጉን መሆኑን አስረዳ/ጂ። 10 ደቂቃ ሽግግር ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ• 5 ደቂቃ የተዘጋጀ ጽሑፍ የተዘጋጀ ፍሑፍ 1 የወርክሾፕ ዓላማ• ተጨማሪ ንባብ አባሪ 1 የስልጠና ቅምሻዎች• 9 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 2 ቡድን መገንባት የክፍለ ጊዜው ያስፈለገበት ምክንያት የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ዓላማ በያንዳንዱ ቀን የተሰጡትን የትምሕርትና የተ ግባር ክፍለ ጊዜ የሚከልስና የሚገመግም የሥራ ቡድን ማቋቋም ነው። የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች ቡድኖችን መመስረትና ሐላፊነቶችን መከፋፈል፣ ትምሕርቶችንና• ተግባራትን መከለስና ሌሎች ድርጊቶችን ይማራሉ። አስፈላጊ ቁሳቁሶች የመፃፊያ ማርከር• የማሳያ ሰሌዳ/ቦርዶች• የተለያየ ቀለም ያላቸው ካርዶች• የክፍለ ጊዜው ዝርዝር ተግባራት ቡድን ምስረታ• መሰረታዊ ሕጎች• የሚፈጀው ጊዜ 20 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት ቡድን ምስረታ ሀ. ቡድን ማቋቋም አዘጋጁ 5 ወይም 6 አባላት ያሉት ቡድኖችን በተሻለ• ና ለየት ባለ አመራረጥ ዘዴ ያቡዋድናል/ታቡ ዋድናለች ለያንዳንዱ ቡድን ሥራውን ያስረዳል/ታስረዳለ• ች፣ እያንዳንዱ ቡድን ለሚከተሉት ተግባራት ሐላፊነቱን ይወስዳል። ሰዓት መቆጣጠርና የሰልጣኞች አቀማመጥ ማ• ስተካከል ተሳታፊዎች የእለቱን ስሜታወቸውን በስሜት • መለኪያ ሜትር ተጠቅመው እንዲመዘግቡ ማ ድረግ ። 15 ደቋቃ ሽግግር የተዘጋጀ ጽሑፍ የራሳቸውን የመገምገሚያ መስፈርት ከገለፁ • በኋላ የዕለቱን ክፍለ ጊዜና ተግባሩን እንዲገመግሙ ማድረግ፣ በሚቀጥለው ጥዋት ግምገማውን በተመለከተ• አጭር ማብራሪያ መስጠት ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ• የተዘጋጀ ጽሑፍ 1 የስሜት መለኪያ ሜትር• 5 ደቂቃ 10 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 3 የሥርዓተ ፆታ ትንተና መሰታዊ ፅንሰ ሀሳቦች የክፍለ ጊዜው የዚህ ክፍለ ጊዜ ያስፈለገበት ምክንያት ተሳታፊዎች የሥርዓተ ፆታንና ያስፈለገበት መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳብን እና ትንተና በመረዳት በግብርና ልማት ምክንያት ውስጥ የሥርዓተ ፆታን ጉዳይ ማካተት እንዲችሉ ለማስተማር ነው፡፡ የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች ከሥርዓተ ፆታ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች ይረዳ• ሉ። በፆታ ልዩነትና በስርዓተ ፆታ መሀከል ያለውን ልዩነት ግንዛቤ • ይይዛሉ። በወንድና በሴት መሀከል ያለውን ያልተመጣጠነ ልዩነት እንዲፈጠር የ• ሚያደርጉ የህብረሰባዊ ምክንያቶች ለይቶ ማወቅ፣ ከሥርዓተ ፆታ ዕይታ አንፃር የሥን ድርሻንና ሀላፊነትን መተንተን• ሀብትና ጥቅማጥቅምን በመቆጣጠር በኩል ያለውን ፆታዊ ልዩነት መ• ረዳት ይቻላል የክፍለ ጊዜው ትንተና የሥርዓተ ፆታና የፆታ ልዩነቶች• የሥርዓተ ፆታ ትንተና• ፆታዊ የሥራ ድርሻና ሀላፊነቶች• ሀብትን የመቆጣጠር ዕድል• ጥቅማ ጥቅም የመቆጣጠር ዕድል• በውሳኔ አሰጣጥ ያላቸው ፆታዊ ተሳትፎ• አስፈላጊ ቁሳቁሶች - የተለያየ ቀለም ያላቸው ካርዶች መፃፊያ ማርከር • ተገላጭ ቻርት • የተለያየ ቀለም ያላቸው ወረቀቶች • ማጣበቂ ፕላስተር• የማሳያ ሰሌዳ• የሚፈጀው ጊዜ 105 ደቂቃዎች ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት መልመጃ አስተባባሪው/ዋ ክፍለ ጊዜው ያስፈለገበት ምክንያትና ዓላማውን 5 ደቂቃ ምን ምንን እንደሚመለከት መግለፅ በስርዓተ ፆታና በፆታ መሀል ያለው ልዩነት የስርዓተ ፆታ ትንተና• ሀ/ በስርዓተ ፆታና በፆታ መሃል ያለው ልዩነት 40 ደቂቃ ተሳታፊዎች ጥንድ ጥንድ ሆነው ሚስጥራዊ ምኞቶቻቸውን • እንዲለዋወጡ አድርግ፡፡ ለማድረግ የምመኘው ነገርና ሴት ወይም 11 ወንድ በመሆኔ ሳላደርግ የቀረሁት ፣ ድብቅ ምኞቶቻቸውን በተለያየ ካርድ ላይ እንዲጽፉ አድርግ/ጊ። • አንዱን ቀለም ለወንዶች ሌላውን ደግሞ ለሴቶች አድርግ/ጊ፡፡ በግድግዳ ዙሪያ ላይ ለጥፋቸው/ፊያቸው ከመልመጃው በኋላ ተሳታፊዎችን የሥርዓተ ፆታንና የፆታ ልዩነትን • እንዲያብራሩ አድርግ/ጊ። አስተባባሪው/ዋ የሥርዓተ ፆታንና የፆታን ምንነት መግለጫ ይሰጣል/ትሰጣለች። አንድ ወይም ሁለት ተሳታፈዎችን በመጋበዝ በግድግዳ ላይ የተለጠፉትን• ድብቅ ፍላጐቶች እንዲያነቡ አድርግ/ጊ፡፡ ከዛም የተቀሩትን ተሳታፊዎች እያንዳንዱን ድብቅ ፍላጐት ፆታዊ ወይም ሥርዓተ ፆታዊ ተዛምዶ እንዳላቸው መጠየቅ ሥርዓተ ፆታን የተመለከቱ ማህበረሰቡ አንዳንድ 1. ማህበራዊ ደንቦቹን ቢለውጥ ሚስጥራዊው ምኞት ሊሳካ የሚችል መሆኑን ወይም በፆታ/በቀጥታ ተፈጥሮአዊ የሚመለከቱና ሁኔታዎች ምንም 2. ቢደረግ ሚስጥራዊ ምኞት የማያሳኩ መሆናቸውን እንዲለዩ አድርግ። በመጨረሻም ተሳታፊዎች ከዚህ መልመጃ ምን ሊማሩ እንደሚችሉ • ጠይቅ። የበለጠ ወደ ትንተናው ለመግባት ድብቅ ፍላጐታቸው ለምን ሊሟሉ እንዳልቻሉ እንዲያብራሩ መጠየቅ ትችላለህ/ሽ፡፡ ሃሳባቸውንም በተገላጭ ቻርቱ ላይ በመፃፍ ለሚቀጥለውየሥርዓተ ፆታ ትንተና ትምህርት መጠቀም ይቻላል፡፡ ለ/ የሥርዓተ ፆታ ትንተና 60 ደቂቃ አስተባባሪው/ዋ የሥርዓተ ፆታ መሰረተ ሀሳቦችን ያብራራል/ለች 15 ደቂቃ ፆታዊ የሥራ ድርሻና ሐላፊነቶች 1. ፆታን መሠረት ያደረገ ንብረት ላይ የማዘዝና የመቆጣጠር ድርሻ 2. ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቅማጥቅምን የመካፈል 3. በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ፆታዊ ድርሻ4. ተሳታፊዎች በአምስት ቡድን እንዲከፋፈሉ አድርግ/ጊና 20 ደቂቃ እያንዳንዱ ቡድን በሚከተሉት የሥርዓተ ፆታ ትንታኔ ሰነዶችን እንዲሞክሩ አድርግ/ጊ፣ ግሩፕ 1 እና 2 ፆታዊ ሥራ ድርሻንና ሀላፊነቶችን ይሞክሩ• ማን ምን ይሰራል /በሶስቱ ሥርዓተ ፆታ የሥራ ድርሻዎችና • ሃላፊነቶች – በቤት ውስጥ፣ በማምረትና በማህበረሰቡ ውስጥ ግሩፕ 3 ደግሞ ፆታን መሠረት በማድረግ ንብረት ላይ የማዘዝና • የመቆጣጠር ድርሻ ላይ እንዲሰሩ አድርግ - ማን ምን ላይ ማዘዝ/መጠቀም ይችላል ? ማን ምን መቆጣጠር ይችላል ?• ግሩፕ 5 ደግሞ ፆታን መሠት በማድረግ ጥቅማ ጥቅም የመካፈልና • የውሳኔ አሰጣጥ ድርሻ ላይ ይሰራል ። ማን ከየትኛው ገቢ ውስጥ የተገኘውን ጥቅም መካፈል ይችላል ? - በቤት ውስጥ ሆነ በማህበራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ማን ምን- ይሣተፋል ? ማንስ ይመራል ? 12 ሁሉም ቡድኖች በአንድ ላይ በመሆን የውይይታቸውን• ነጥቦች ለአምስት አምስት ደቂቃ እንዲያቀርቡ ማድረግ፣ የያንዳንዱን አቀራረብ ተከትሎ ተሳታፊዎች ምን 15 ደቂቃ እንደተረዱ መጠየቅ? አስተባባሪው/ዋ በስርዓተ ፆታ ሚዛናዊ አለመሆንና በዚሁም • ላይ መሰራት ስላለባቸው ማስተካከያዎች የማጠቃለያ 10 ደቂቃ አስተያየቱን/ቷን ይሰጣል/ተሰጣለች፣ ሽግግር - ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ 5 ደቂቃ የተዘጋጀ ጽሑፍ - ተዘጋጁ ጽሑፎች ቁጥር 2 የስርዓተ ፆታ መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦችና ትንተና ተጨማሪ ንባብ - የሥርዓተ ፆታ መረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20 Materials/ Toolki t%20-%20Gender.pdf) (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Mate- rials/Toolki t%20-%20Gender%20(Amharic).pdf) 13 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 4. የኤችአይቪ/ኤድስ መሰረታዊ ፅንስ ሀሳቦች ትንተና የክፍለ ጊዜው ክፍለ ጊዜው ያስፈለገበት ምክንያት ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ጠቅለል ያለ ያስፈለገበት ሃሳብ ለመስጠትና በገጠሩ ህብረተሰብ የኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ትንተና ቁልፍ ምክንያት መሰረተ ሀሳቦች ለማስጨበጥ ነው ። የክፍለ ጊዜው በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ሰልጣኞች ዓላማ • በግለሰብ ደረጃ ለኤችአይቪ የሚያጋልጡ ስጋትን እና እንዲሁም ወደ ኤድስ ደረጃ የሚያደርሱ ተያያዥ ምክንያቶችንና ኤድስ በሚያስከትለው ህመም/ሞት ምክንያት ለሚመጣው ተፅዕኖ ተጋላጭነትን ይለያሉ። በሽታውን ለመከላከል ያሉትን መልካም አጋጣሚዎችን ይለያሉ።• በገጠሩ ህብረተሰብ በኤችአይቪ የመያዝ የስጋት ምንጮችን ይረዳሉ።• በገጠሩ ህብረተሰብ የኤድስ ተፅዕኖ ጠቋሚዎችን ይለያሉ ።• የክፍለ ጊዜው ኤችአይቪ/ኤድስ የሚተላለፍበት መንገድ ዝርዝር • በገጠሩ ህብረተሰብ ውስጥ የበሽታውን አስከፊነትና ተለዋዋጭ ደረጃዎች መረዳት አስፈላጊ ቁሳቁስ ተገላጭ ቻርት የተለያዩ ካርዶች • እስኪሪፕቶዎች• ማጣበቂያ ኘላስተር• የማሳያ ሰሌዳ• የሚፈጀው ጊዜ 165 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት መልመጃ አስተባባሪው/ዋ የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተናን ማስተማር 100 ደቂቃ ለምን እንዳስፈለገና የክፍለ ጊዜውን ይዘት ያስረዳል/ታስረዳለች። ሀ/ የኤችአይቪ/ኤድስ መተላለፊያ መንገድ አስተባባሪው ተገላጭ ቻርቱን በመጠቀም /ስዕል1፣ ጽሑፍ3/ • የኤችአይቪ/ኤድስን መተላለፊያ መንገዶች ያስረዳል ። የኤችአይቪ/ኤድስ ዋና መተላለፊያ • መንገዶችንና ከኤድስ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው በሽታዎችና ምልክቶችን ተሳታፊዎች ምሳሌ እንዲያቀርቡ ይጠይቃል/ትጠይቃለች። በሽታውን ለሚያባብሱ ነገሮችና በሽታውን ለመከላከል በሚረዱ• መልካም አጋጣሚዎች መሃል ያለውን ልዩነት ማስረዳት ተሳታፊዎች በቡድን ከሚከተሉት አንዱን • እንዲለዩ ይጠይቃል /ስዕል 2፣ ጽሑፍ 4/ በበሽታው የመያዝ የአደጋ ምንጭ፣ - 14 አንድ ሰው በበሽታው እንዳይያዝ የሚረዱ- መንገዶችን ፣ ከኤድስ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው በሽታዎችና- ሞትን የሚያፋጥኑ ምክንያቶችን፣ በበሽታው የተያዘን ሰው ከሞት የሚከላከሉ ወይም- ህመሙ እንዳይባባስ የሚደርጉ ምክንያቶችን፣ በኤድስ ሞት ምክንያት ለሚመጣ ተፅዕኖ ቀሪውን- ቤተሰብ ተጠቂ የሚያደርጉ ምክንያቶችን በኤድስ ሞት ምክንያት ለሚመጣው ተፅዕኖ ቀሪው • የቤተሰብ አባላት ተጠቂ እንዳይሆኑ ያሉ መልካም አጋጣሚዎች ተሳታፊዎች በአንድ ላይ የሚመልሱት፣ በህብረተሰቡ • ውስጥ የመተላለፊያ መንገዶቹን በሦስቱ የበሽታው ደረጃዎች /ኤድስ ሲጀምር፣ ኤድስ ሲስፋፋና የኤድስ ተፅዕኖ/ እንዲያስረዱ ማድረግ። ይህ መረጃ ለበሽታው ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል። የሚቀጥለው ጥያቄ ተስቦውን በማህበረሰብ ደረጃ መተንተን ነው። ለ/ በገጠሩ ህብረተሰብ ውስጥ የበሽታውን አስከፊነትና 60 ደቂቃ የተለያየ ገፅታውን መረዳት አስtባባሪው/ዋ ለኤችአይቪ/ኤድስ ወረርሽኝ ተገቢውን ምላሽ• መስጠት እንዲቻል፣ ለበሽታው የሚያጋልጡ ምንጮችን የማወቅና በህብረተሰቡ ውስጥ ወረርሽኙ ያለውን ደረጃ መረዳት አስፈላጊ መሆኑን ማስረዳት በወረዳ ከተሞችና በገጠሩ ሕብረተሰብ መሐከል • የኤችአይቪ የጥቃት ደረጃን አወዳድር። መጀመሪያው ማለትም ከተማው ከገጠሩ ሕብረተሰብ የበለጠ የተጠቃ ነው። ይህ ማለት የገጠሩ ሕብረተሰብም አደጋ ላይ አይደለም ማለት ነው? አይደለም። የገጠሩ ሕብረተሰብም አደጋ ላይ ነው፣ ምክንያቱም የበሽታው አስተላላፊ ድልድይ የሆኑ ሰዎች በሚጫወቱት ሚናና በባሕላችንና ጐጂ ልማዶችና ደንቦች ምክንያት የተነሳ፣ ኤችአይቪ/ኤድስ የመተላለፊያ እድሉ በጣም የሰፋ ነው ። በወረዳው ውስጥ ለኤችአይቪ/ኤድስ ስጋት የሆኑ ቦታዎችን • የሚመለከት ካርታ በመጠቀም፤ ተሳታፊዎች የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንዲመልሱ አድርግ/ጊ፡፡ /ስዕል2. ጽሑፍ 4/ በወረዳው የኤችአይቪ/አደገኛ ቦታዎችን - አስተላላፊ ድልድይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን- /ወደገጠሩ የሚገቡና የሚወጡ እንዲሁም በገጠሩ የሚዘዋወሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች/፣ የበሽታውን ስርጭት የሚያባብሱ የሕብረተሰቡ ሕጐች- ልማዶች ደንቦችና ባሕላዊ ስርዓቶችን፣ በማጠቃለያም ማንኛውም በገጠር የሚኖር ሰው እንደ- እድሜው፣ ፆታው፣ የኑሮ ደረጃውና ማንነቱ የተለያየ ይሁን እንጂ በኤችአይቪ/ኤድስ የመያዝ ሠፊ አደጋ 15 እንዳለው ማስረዳት ያስፈልጋል፣ የኤድስን ተፅዕኖ በበለጠ ለመረዳት ተዛማጅ - ምልክቶችን መጠቀም ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስረዳ/ጂ፡፡ ምክንያቱም ስለበሽታው ተጠናክሮ የተቀመጠ በቂ የጽሑፍ መረጃ ባለመኖሩ፣ የአሟሟት ሁኔታን የሚገልፅ የሞት ምስክር ወረቀት ስለሌና ሕብረተሰቡ የበሽታውን መኖር አምኖ ስላልተቀበለ ማስረዳት ተገቢ ነው /ስዕል 3፣ ፅሑፍ 4/ ተሳታፊዎችን በአንድ ላይ ወይም በየቡድናቸው • በኤድስ የተያዘና የተጐዳ/በተፅEኖው ሥር የወደቀ ሕብረተሰብ ጠቋሚ የሆኑ ጉዳዮችን የሚቀጥሉትን ጥያቄዎች በማንሳት እንዲወያዩ ማድረግ፣ በአንድ ሕብረተሰብ ውስጥ የሚገኝ የኤድስ ተፅዕኖ • ምክንያት የባሕሪ ለውጥ–ከበሽታውና በሽታው 1. የሚያስከትለው ሞት ጋር አብሮ ለመኖር የሕብረተሰቡ የባሕሪ ለውጥ ወይም የአስተሳሰብ ለውጥን፣ በቤተሰብ አባላት ስብጥር ያለውን ለውጥ 2. በግብርና በመሳሰሉት የመተዳደሪያ ሥራዎች3. ላይ ስላለው ለውጥ ሽግግር - ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ 5 ደቂቃ የተዘጋጀ ጽሑፍ - የተዘጋጀ ጽሑፍ 3 የኤችAይቪ ኤድስን መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች መረዳት ተጨማሪ ንባብ - ተዘጋጀ ጽሑፍ 4 የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና መሰረታዊ ፆንሰ ሀሳቦች በገጠሩ ሕብረተሰብ (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Mate rials/Toolkit% 20-%20HIV.pdf); (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Mate rials/Toolkit% 20-%20HIV.%20(Amharic).pdf ) 16 የሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 5 በሥርዓተ ፆታና በኤችአይቪ/ኤድስ መሃከል ያለ ግንኙነት የክፍለ ጊዜው ሴቶች ለኤችአይ/ኤድስ እንዲጋለጡ የሚያደረጉ ምክንያቶችንና ያላቸው ሥራ ያስፈለገበት ድርሻ እንዲት በኤድስ እንዲጠቁ እንደሚያደርጋቸው መረዳት፣ ምክንያት የክፍለ ጊዜው በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች ዓላማ - ሴቶችን ለኤችአይቪ/ኤድስ የሚያጋልጡ ምክንያቶችን መግለፅ ይችላሉ በሥርዓተ ፆታና በኤችአይቪ/ኤድስ መሐከል ያለ ግንኙነትን ይረዳሉ ፣- የክፍለ ጊዜው - በሥርዓተ ፆታና በኤችአይቪ/ኤድስ መሐከል ያለ ግንኙነት ዝርዝር አስፈላጊ ቁሳቁስ - የተለያየ ቀለም ያላቸው መፃፊያ ወረቀት ተገላጭ ቻርት - መፃፊያ ማርከር- የሚፈጀው ጊዜ 30 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት ማቅረብ በሥርዓተ ፆታና በኤችአይቪ/ኤድስ መሃል ያለ ግንኙነት 30 ደቂቃ አስተባባሪው/ዋ የክፍለ ጊዜውን አስፈላጊነት ያብራራል • ሴቶችን ለኤችአይቪ/ኤድስ የሚያጋልጡ• ምክንያቶችንና ግንኙነቶችን ይገልፃል በወንዶችና በሴቶች መሃከል በኤችአይቪ/ኤድስ• የመጋለጫ አደጋ መንገዶች እንዴት ሊያዩ እንደሚችሉ አያይዞ ማቅረብና ሴቶችና ልጃገረዶች እንዴት ከጐልማሶችና ወጣት ወንዶች የበለጠ አስቀድሞ የተጋለጡ እንደሆኑ መጠቆም ። የተዘጋጀ ጽሑፍ ፅሑፍ 5፣ ሴቶችን ለኤችአይቪ/ኤድስ የሚያጋልጡ • ምክንያቶችና ተዛማጅነት፣ ሀሳቦች መረዳት 17 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 6 ሥርዓተ ፆታና ኤችአይቪ/ኤድስ በግብርና ምርትና ገበያ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ የክፍለ ጊዜው የዚህ ክፍለ ጊዜ አስፈላጊት የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮችን ያስፈለገበት በግብርና ክፍል ኤኮኖሚ ያለውን አስፈላጊነት በጥቅሉ እና በተለይም በገበያ ምክንያት መር የግብርና ምርት ማልማት ላይ የተለያዩ ጥልቅ ሀሳቦችን ለማመንጨት ነው። የክፍለ ጊዜው በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች ዓላማ - በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ የሚታየውን ኢ-ሚዛናዊ የፆታ ልዩነት መረዳትና በኤችአይቪ/ኤድስ ወረርሽኝ እየተከሰተ ያለውን አደጋ ይገነዘባል በግብርና ልማት እንቅስቃሴ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮችን መመልከ- ትና ጣልቃ በጉዳዩ ላይ መግባት አስፈላጊ መሆኑን ይረዳሉ፡፡ የክፍለ ጊዜው • የቡድን ውይይት ማቅረብ ዝርዝር አስፈላጊ ቁሳቁስ • ተገላጭ ቻርት የተለያዩ ካርዶች• መፃፊያ ማርከር • መለጠፊያ ማስቲሽ• የሚፈጀው ጊዜ 90 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት የቡድን ሥራ አስተባባሪው/ዋ የክፍለ ጊዜውን አስፈላጊነት ያስረዳል/ታስረዳለች • 5 ደቂቃ 6 ቡድኖችን መስርቶ የሥራ ድርሻቸውን • ይመድብላቸዋል እያንዳንዱ ቡድን በሥርዓተ ፆታ ወይም • 30 ደቂቃ በኤችአይቪ/ኤድስ ላይ መወያያ የሚሆን አርእስት ይሰጠውና ምክንያቱንና ውጤቱን እንዲገልፅ ያደርጋል። / የምክንያትና ውጤት ተዛምዶ ማሳያ ዛፍ ለመስራት ይረዳል/ ለቡድን ውይይት የሚረዱ ጥያቄዎች • ፆታዊ የሥራ ድርሻዎችና ሃላፊነቶች ኤችአይቪ/ኤድስ- እንዴት ነው ለዝቅተኛ የግብርና ምርታማነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉት? /ቡድን1 እና 2/ ፆታዊ ድርሻዎችና ሃላፊነቶች ኤችአይቪ/ኤድስ እንዴት- ነው ለግብርና ምርቶች ግብይት ደካማነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉት? /ቡድን 3 እና 4/ ኤችአይቪ/ኤድስ እንዴት ነው ለግብርና ምርት- ዝቅተኛነትና ለግብይት ድክመት ምክንያት የሚሆኑት? /ቡድን 5/ የግብርና ምርቶችና የገበያ መሻሻል ለኤችአይቪ- ስርጭት መጨመርና ለበሽታው ተፅዕኖ ተጋላጭነትን 18 እንዴት ይጨምራል? ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በካርዶች ላይ እንዲጽፉ • 30 ደቂቃ ማድረግና የምክንያትና ውጤት ተዛምዶ አመላካች ዛፍ መስራት በዚህም አስተባባሪው የምክንያትና ውጤት ተዛምዶ አመላካች ዛፍ በመስራት ፆታዊ የሥራ ድርሻና ሀላፊነት እንዲሁም ኤችአይቪ/ኤድስ እንዴት ከግብርና ምርታማነትና ግብይት ጋር እንደሚቆራኝ ተሳታፊዎች እንዲረዱ ያደርጋል/ታደርጋለች፡፡ ሁሉም ቡድኖች ግኝታቸውን ተሳታፊዎች በተገኙበት - 20 ደቂቃ ያቀርባሉ ማጠቃለያ ተሳታፊዎች ካቀረቡት ላይ ማጠቃለያ መስጠት 5 ደቂቃ ተጨማሪ ንባብ ፅሑፍ 5፣ ሴቶችን ለኤችአይቪ/ኤድስ የሚያጋልጡ ምክንያቶችና ተዛማጅ፣ ሀሳቦች መረዳት 19 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 7 በግብርና ልማቶች ውስጥ ለሥርዓተ ፆታ ትንተና የሚረዱ ሰነዶች የክፍለ ጊዜው የዚህ ክፍለ ጊዜ ዓላማ በግብርና ልማት እንቅስቃሰ ውስጥ ፆታን ያስፈለገበት ባሰባጠረ መልኩ የግብርና ሥራዎችን በተመለከተ መረጃዎችን ምክንያት ለመሰብሰብና ለመተንተን ከሚረዱ አሳታፊ ሰነዶ ጋር ተሳታፊዎችን ለማስተዋወቅ ነው። የክፍለ ጊዜው በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች የማከተሉትን እንዲያውቁ ዓላማ ይደረጋል ፆታን ባሰባጠረ መልኩ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚረዱ አሳታፊ የመረጃ ሰነዶች• ን እንዲያውቁና እንዲጠቀሙ ይደረጋል የክፍለ ጊዜው - የሀብት ደረጃ ማውጣትን ትንተና - በመጠን ማደራጀትን መረጃ ሰነድ 1. የቤተሰብ ገቢን መመልከትን እና ማሰስ • መረጃ ሰነድ 2. በማሕበረሰቡ ያለው አዳዲስ ቴክኖሎጂና አሰራርን• መመልከትን እና ማሰስ ወቅታዊ የጊዜ መቁጠሪያን • ሰነድ 3 እስከ 5 የሥርዓተ ፆታ ትንተና በግብርና ምርቶች ላይ ይደረጋል• አስፈላጊ ቁሳቁሶች ተገላጭ ቻርት መፃፊያ ማርከር • የተለያዩ ቀለም ያላቸው መፃፊያ ወረቀቶች • ማስመሪያ • መለጠፊያ ማስቲሽ • ማሳያ ሰሌዳ• የሚፈጀው ጊዜ 135 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት መልመጃ 1. የሀብት ደረጃ ማውጣት 35 ደቂቃ አስtባባሪው/ዋ ተሳታፊዎች እንደ ማህበረሰብ ሆነው ራሳቸውን• እንዲያዩና የማህበረሰቡን ድርሻ እንዲጫወቱ ያደርጋል/ለች በማህበረሰቡ ተቀባይነት ያለውን የሀብት ደረጃ መግለጫ• መስፈርቶችን ቡድኑን በመጠየቅ ማህበረተሰቡ በተለያየ የሀብት ደረጃ መመደብ፡፡ ለምሳሌ /ሐብታም ቤተሰብ፣ መካከለኛ ቤተሰብና ድሀ ቤተሰብ/ ክፍፍሉን በየቤተሰብ ዓይነት ከጠቅላላ የቤተሰብ ብዛት • ጋር በማነፃፀር በጠጠር ወይም በባቄላ ፍሬ ለይቶ 20 ማስቀመጥ በየቤተሰቡ የሀብት መጠን የተለየውን ከጠቅላላው በመቶኛ ማስላት በእማወራ የሚመራ በየሐብት መጠን ስንት ቤተሰብ • እንዳለና ከመቶኛ ስንት እንደሚሆን ተሳታፊዎች እንዲያሰሉት መጠየቅ 2. የቤተሰብ ሀብትን መመልከት ከሥርዓተ ፆታ ትንተና መረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ 25 ደቂቃ• ውስጥ ሰነድ1. የቤተሰብ የሀብት ደረጃ መጠቆሚያ የሚለውን በተገላጭ ቻርት ላይ በማሳየት ምን አይነት መረጃዎችን ቅጽ አንድን ለመሙላት እንደሚጠቀሙበት ማስረዳት ቅጹ ሲሞላ ተጨማሪ መረጃዎች ለየት ያሉ ጥያቄዎችን• በመጠየቅ እንዴት ሊገኙ እንደሚችሉ ማሳየት 3. በማሕበረሰቡ ውስጥ ያለውን አዳዲስ ቴክኖሎጂና አሰራር ምልከታና ዳሰሳ አስtባባሪው/ዋ፦ 15 ደቂቃ ከሥርዓተ-ፆታ ትንተና መረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ• ውስጥ ሰነድ ሁለትን በማሳየት በወረዳው ውስጥ የገባውን የአዳዲስ ቴክኖሎጂና አስራርን መረጃ መሰብሰብ እንዴት እንደሚቻል ያስረዳል/ታስረዳለች ቅጹ ሲሞላ አንዳንድ በሰነዱ ላይ የተሰረዘሩ ጥያቄዎች• መረጃ ለመሰብሰብ እንዴት እንደሚረዱን ያስረዳል/ታሰረዳለች 4. በግብርና ምርቶች ላይ የሥርዓተ ፆታ ትንታኔና የጊዜ መቁጠሪያ 55 ደቂቃ አስተባባሪው/ዋ ተሳታፊዎች ወቅታዊ የዝናብ ጊዜያቶችን በተገላጭ• ቻርቱ ላይ እንዲያመለክቱና በወረዳው ወይም በገበሬ ማህበሩ ውስጥ በያንዳንዱ ወቅት ያለውን የሥራ አይነት፣ የሰብል ምርትና የእንስሳት አያያዝ እንዲያሳዩ ይጠይቃል። በፆታ ላይ የተመሰረተ የሥራ ክፍፍልን፣ የጥቅማ ጥቅምና• የሀብት ድርሻና ክፍፍልን እንዲሁም በውሳኔ አሰጣጥ ላይ በያንዳንዱ የሰብል፣ የዛፍ ተክልና እንስሳት ዕርባታ ሰነድ 3፣ 4 እና 5ን በመጠቀም እንዲተነትኑ ያደርጋል/ታደርጋለች ። ሽግግር - ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ 5 ደቂቃ የተዘጋጀ ጽሑፍ - የተዘጋጀ ጽሑፍ 7 ፆታን ባሰባጠረ መልኩ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚረዱ አሳታፊ ሰነዶች ተጨማሪ ንባብ - የሥርዓተ ፆታ መረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ በአማርኛ (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Materials/ Toolkit% 20-%20Gender%20(Amharic).pdf) ሥርዓተ ፆታ በግብርና ምርቶች ላይ ያለውን እውነታ ሰነድ ምሳሌ• የአሰልጣኞች መመሪያ 21 ክፍለ ጊዜ 8 በገጠሩ ህብረተሰብ ለኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና የሚረዱ ሰነዶች የክፍለ ጊዜው የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ዓላማው ተሳታፊዎች በገጠሩ ህብረተሰብ ውስጥ ያስፈለገበት የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና መረጃ ሰነዶች ጋር ለማስተዋወቅ ነው። ምክንያት የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች፡- አሳታፊ ሰነዶችን አውቀውና ተረድተው የኤችአይቪ/ኤድስ መረጃዎችን ለመሰ• ብሰብ ይጠቀሙበታል የክፍለ ጊዜው ኤችአይቪ/ኤድስ የስጋት አካባቢ የሆኑትንና አስተላላፊ ድልድይ ትንተና የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎች ይለያሉ /ሰነድ 1, 2 እና 3 በመጠቀም/ የኤችአይቪ/ኤድስ ተፅዕኖ ትንተና /ሰነድ 4 5 እና 6 በመጠቀምና በመጠን ማ• ደርጃ ዘዴ መጠቀም/ አስፈላጊ ቁሳቁሶች ተገላጭ ቻርት መፃፊያ ማርከር • የባቄላ ፍሬዎች/ጠጠሮች • ማስመሪያ• ማጣበቂያ ኘላስተር • ማሳያ ሰሌዳ• የሚፈጀው ጊዜ 135 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት መልመጃ 1. /የኤችአይቪ/ኤድስ/ የስጋት አካባቢንና አስተላላፊ 60 ደቂቃ ድልድይ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን መለየት አስተባባሪው/ዋ-- ተሳታፊዎች የማሕበረሰብ አባላትን ተመስለው• እንዲጫወቱ ያደርጋል/ታደርጋለች ተሳታፊዎች የወረዳውን ካርታ እንዲስሉ በማድርግ • በካርታው ላይ የኤችአይቪ ስጋት የሆኑ ቦታዎችን እንዲያመለክቱ ይጠይቃል/ትጠይቃለች። የኤችአይቪ ስጋት የሆኑት የገበያ ቦታዎች ለምን እንደ• ኤችአይቪ ምንጭ ሊታሰቡ እንደቻሉ ያውጣጣል/ታውጣጣለች። እንደ አስተላላፊ ድልድይ ስለሚገመቱ ሰዎች መጠየቅና• ከገጠር ስጋት ወደ ሆኑ የወረዳው ቦታዎች የሚመላለሱ እንዲሁም ከከተማ ወደ ስጋት የሆኑ ቦታዎች ወደ ገጠሩ ማህበረሰብ ምልልስ የሚያበዙ በገጠሩ ውስጥም የሚዘዋወሩ ሰዎችን እንዲለዩና መልሱን በካርታው ላይ እንዲመዘግቡ ያደርጋል/ታደርጋለ ች። ከኤችአይቬ/ኤድስ መረጃ ውስጥ በተገላጭ ቻርቱ ላይ ሰነድ • 1፣2 እና 3ን በማሳየት ከካርታ ልምምዱ ላይ የተገኙ መረጃዎችን እንዴት በቅጽ 1፣2 እና 3 እንደሚሞሉና እግረመንገድ የተነሱ ጥያቄዎችን አስፈላጊ ከሆነ እንዴት 22 እንደሚጠቀሙ ያስረዳል/ታስረዳለች። 2/ የኤችአይቪ/ኤድስ ተፅዕኖ ትንትና /በቤተሰብ ስብጥር ላይ የሚመጣው ለውጥ 35 ደቂቃ የኤድስ ተፅዕኖ ለመገንዘብ እንዲቻል ምን ዓይነት • መረጃዎች መሰብሰብ እንዳለባቸው ማስረዳት ተሳታፊዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ምን ዓይነት የቤተሰብ• አይነቶች እንዳሉ ጠይቅ/ቂ /ሰነድ 4/ ተሳታፊዎች በማህበረሰቡ የሚኖሩትን የቤተሰብ ዓይነቶችን• በመጠን በመለየት እንዲያሳዩ ጠይቅ/ቂ ከአምስት ወይም አስር ዓመታት በፊት ምን ምን ዓይነት • ቤተሰቦች ይኖሩ ምንደነበር ጠይቅ። በደረጃ በደረጃቸው እዲለዩ አድርግ/ጊ የአሁኑን የአንድ ቤተሰብ ብዛት እንዲጠቁሙ አድርግና• ከአምስት እና አሥር ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር እንዲያነፃፅሩ አድርግ/ጊ 3/ የኤችአይቪ/ኤድስ ተፅዕኖ ትንተና /በግብርና አሰራር ላይ 35 ደቂቃ የሚያመጣው ለውጥ፣ የማሕበረሰቡ መላሽና የባህሪ ለውጥ አስተባባሪው/ዋ ሰነድ 5፣ 6 እና 7ን በማሳየት • አጠቃቀሙን መግለጽ። ለማውጣጣት የሚረዱ ጥያቄዎችን በመጠቀም እንዴት መረጃ መሰብሰብ እንደሚቻል ለተሳታፊዎች ያስረዳል። በከፊል የተዘጋጁ ጥያቄዎችንም መጠቀም እንደሚቻል• ለተሳታፊዎች ያስታውሳል። ሽግግር - ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ 5 ደቂቃ የተዘጋጀ ጽሑፍ - የተዘጋጀ ጽሑፍ 8. አሳታፊ የማህበረሰብ ካርታ መስራት ተጨማሪ ንባብ - የኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ በአማርኛ (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Mate- rials/ Toolkit% 20-%20HIV.%20(Amharic).pdf ) የወረዳ የኤችአይቪ/ኤድስ የእውነታ ገጾች ምሳሌዎች• 23 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 9 የማስተባበር/የማሳለጫ ሙያ የክፍለ ጊዜው ክፍለ ጊዜው ያስፈለገበት ምንክያት የባለሙያዎች አመለካከትና ጠባይ ያስፈለገበት ከገጠሩ ማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነትና ቅርርቦሽ እንዴት ሊጎዳው ምክንያት እንደሚችል ለማሳወቅና አስፈላጊውን ውጤታማ የማስተባበር ሙያን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው። የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች የባለሙያዎች አመለካከትና ጠባይ ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸውን ግንኙነት• እንዴት እንደሚጐዳ ውይይት ያደርጋሉ ለተሳካ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና አስፈላጊ የሆኑ አንዳንድ የ• ውይይት ማሳለጫ/የማስተባበሪያ ሙያ ባሕርያትን ይዘረዘራሉ በከፊል የተዘጋጁ ቃለመጠይቆችን እንዴት መጠቀም እንደሚገባ በሙከራ ያሳያ• ሉ የክፍለ ጊዜው ትንተና የባለሙያዎች አመለካከትና ጠባይ ለስኬት የሚጠበቁ ዋና ዋና ውጤቶች• በከፊል የተዘጋጀ ቃለመጠይቅ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል• Aስፈላጊ ቁሳቁሶች 21*30 የሆነ መፃፊያ ወረቀት ካርዶች • እስክርቢቶች • ማስመሪያ • ማጣበቂያ ኘላስተር • የማሳያ ሰሌዳ • የሚፈጀው ጊዜ 120 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት የቡድን ሥራ 1/ አመለካከትና ጠባይ 50 ደቂቃ አስተባባሪው/ዋ ያለፉትን ክፍለ ጊዜያት ከአሁኑ ጋር በማያያዝ • ያስተዋውቅና የክፍለ ጊዜውን ዓላማና ዝርዝር በሰሌዳ ላይ ያሳያል/ታሳያለች። በአጭሩ ስለ አመለካከትና ጠባይ ገለፃ• ያደርጋል/ታደርጋለች። አምስት ወይም ስድስት ቡድኖችን በዘዴ• ይመሰርታል/ትመሰርታች። ለምሳሌ ተሳታፊዎች ስማቸውን ጽፈው በማጠራቀሚያ ኩባያ ውስጥ እንዲያስቀምጡ ማድረግ። ሌሎች አምስት ስድስት ሰዎች ደግሞ በየተራ የተፃፈውን ወረቀት በማውጣት የየራሳቸውን ቡድን እንዲመሰርቱ ማድረግ። የተለያዩ የእንስሳት ስዕሎችን ለቡድኑ ያድላል።/ለምሳሌ • አንበሳ፣ ነብር፣ አህያ፣ ዔሊ፣ ቀጭኔ የመሳሰሉትን/ ተሳታፊዎች የፃፉትን ካርድ በሙሉ እንዲሰጡ ይጠይቅና • 24 ግርግዳ ላይ በመለጠፍ መልካም ጥሩና መጥፎ ጠባያትን ለመለየት እንዲረዳው ያደርጋል በመጨረሻም በተሳታፊዎች የተነሱትን ጥሩና መጥፎ• ጠባያትን በማንሳት ባለሙያዎችና የኤክስቴንሽን ሰራተኞች ምን ዓይነት ጠባይ ለማህበረሰቡ ማሳየት እንዳለባቸው፤ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ጠባያትን እንዴት ማስተናገድ እንደሚገባቸው ያስረዳል/ታስርዳለች። 2/ ቡድኖቹ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንሳት ይወያያሉ 30 ደቂቃ የሚከተሉት ሁኔታ ቢያጋጥሙት ምን ያደርጋሉ አንድ የቡድን አባል የበላይነት ተሰምቶት/ቷት • ከማድመጥ ይልቅ እኔ ያልኩትን ተቀበሉ ቢል/ብትል አንድ ሀላፊ ከቡድኑ ጋር አብሮ የመጣ/ች/ የጥናቱን • ዓላማ በተሳሳተ መንገድ ለማህበረሰቡ ቢያስረዳ/ብታስረዳ በማህበረሰብ ስብሰባ ላይ የአካባቢው መሪ የውይይቱን • ሂደት ውጤት ሊያዛባው ቢፈልግ በቃለ መጠይቅ ወቅት ተጠያቂው/ዋ/ መልስ ለመስጠት • ባይፈልግ/ባትፈልግ ወይም ቢያቅማማ/ብታቅማማ ሁሉም ቡድኖች አንድ ላይ በመሆን ውጤታቸውን 20 ደቂቃ• ያቀርባሉ። 3/ በከፊል የተዘጋጁ ቃለመጠይቆችን እንዴት መጠቀም 25 ደቂቃ እንደሚቻል በከፊል የተዘጋጁ ቃለ መጠይቆችን ለሥርዓተ ፆታና • ለኤችአይቪ ትንተና መቼና ለምን እንደምንጠቀም ማስረዳት ። ለሥርዓት ፆታና ኤችአይቪ ትንተና ምን ምን ጥያቄዎን • ማካተት እንዳለብን ማስረዳት ቡድኑን ለሁለት ለሁለት ክፈላቸው። አንዱ ጠያቂ • ሁለተኛው ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርግ/ጊ አንዳንድ አርዕስት ስጣቸውና ተፈላጊውን ሚና • እንዲጫወቱ አድርግ/ጊ። ለጥቂት ቡድኖች እድሉን ሰጥ/ጭ በሁሉም • ተሳታፊ ፊት ጥያቄዎቻቸውን እንዲያቀርቡና እንዲመልሱ እድል ስጣቸው/ስጫቸው ጠያቂዎች የማያውጣጣ ዓይነት ጥያቄዎችን እንዲጠቀሙ • መሪ ጥያቄዎችን እንዳይጠቀሙ መምከርና ማበረታታት ሽግግር - ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ 5 ደቂቃ የተዘጋጀ ጽሑፍ - የተዘጋጀ ጽሑፍ 9: ለመስክ ሰራተኞች የማስተባበር ሙያ ተጨማሪ ንባብ - የተዘጋጀ ጽሑፍ 11: በከፊል የተዘጋጁ ቃለመጠይቆች አጠቃቀም የአሰልጣኞች መመሪያ 25 ክፍለ ጊዜ 10 የመስክ ሥራ ዝግጅት የክፍለ ጊዜው የዚህ ክፍለ ጊዜ አስፈላጊነት ተግባር በገበያ መር የግብርና ልማት ያስፈለገበት ውስጥ አሳታፊ ሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ሰነዶችን አጠቃቀም ምክንያት ለመለማመድ ነው። የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች የመስክ ሥራ ሂደትን መግለፅ ይችላሉ • የሥርዓተ ፆታና ኤችአይቪ መረጃ ሰነዶችን ለመጠቀም በቡድን ይዘጋጃሉ። • አሳታፊ በሆነ መንገድ የመስክ ሥራ ያካሂዳሉ • አንድ ወይም ሁለት የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ መሰብሰቢያ ሰነ• ዶችን ይጠቀማሉ። የክፍለ ጊዜው ትንተና የመስክ ሥራ አሰራር ሂደት የመስክ ሥራ ዝግጅት• አስፈላጊ ቁሳቁሶች ካርዶች መፃፊያ ማርከር • መለጠፊያ ኘላስተር• የሚፈጀው ጊዜ 120 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት የቡድን ሥራ 1/ የመስክ ሥራ አመራር ሂደት 20 ደቂቃ አስተባባሪው/ዋ የክፍለ ጊዜውን ዓላማ ያስረዳል/ታስረዳለች የክፍለ ጊዜውን አስፈላጊነት ያስረዳል/ታስረዳለች• የመስክ ሥራ ዓላማን፤ ከመሥብ ሥራዉ የሚጠበቀው• ውጤትንና የአሰራር ሂደቱን በግልፅ ያስረዳል/ታስረዳለች። ከተለያዩ የማሰልጠኛ ጣቢያዎች የመጡና የተለያየ ሙያ• ያላቸውን አምስት ቡድኖችን ይመሰርታል። በመስክ ሥራ ላይ ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም • ለማስቻል ሦስቱ ቡድኖች በሥርዓተ ፆታ ላይ ሁለቱ ደግሞ በኤችአይቪ ላይ ይሰራሉ ። / 5 ደቂቃ/ ድርሻን 2/ ለመስክ ሥራ ዝግጅት ድርሻን መተወን/መጫወት 90 ደቂቃ መተወን/መጫወት ተሳታፊዎች በየቡድናቸው እንዲቀመጡ አድርግ/ጊ አስፈላጊዎች ቅጾችን ለየቡድኑ አድል/ይ• ቡድን 1 በሥርዓተ ፆታና ትንተና የቤተሰብ የሀብት- ደረጃ መጠቆሚያ /ቅጽ 1/ እና ወቅታዊ የጊዜ ሰሌዳ። ቡድን 2፦ በስነ-ፆታ ትንተና በየሰብሉ አመራረት - ቡድን 3፦ በሥርዓተ ፆታና ትንተና በከብት ዕርባታ - ቡድን 4፦ የኤችአይቪ የስጋት ትንተና /ሰነድ1፣2 እና 3/ - 26 ቡድን 5፦ የኤድስ ተፅዕኖ ትንተና /ሰነድ 4፣ 5፣6 እና 7/ - የመስክ ሥራውን ሃላፊነት እንዴት መከፋፈል• እንዳለባቸው ማስረዳትና /ለምሳሌ አንዱን ሰነድ ቀድሞ ማን እንደሚጠቀም፣ ማን እንደሚመዘግብና ማን ደግሞ እንደሚከታተል የመሳሰሉትን/ ተሳታፊዎቹ ሀላፊነቶቹን በቡድን መሃል እንደ አስተባባሪ፣ እንደ ማስታወሻ ያዥና እንደታዛቢ እስከሚከፋፈሉ በቂ ጊዜ መስጠት ተሳታፊዎች በቡድናቸው መሃል የተሰጣቸውን የሥራ• ድርሻ በትወና መልክ እንዲሰሩ ማድረግ የተዘጋጀ ጽሑፍ የተዘጋጀ ጽሑፍ 9 የመስክ ሥራ ዝግጅት የአሰራር • ሂደት፣ • ሥርዓተ ፆታ ሰነድ 1 ለቡድን 1 • ሥርዓተ ፆታ ሰነድ 3 እና 2 ለቡድን 2• ሥርዓተ ፆታ ሰነድ 5 እና 2 ለቡድን 3 • ኤችአይቪ ሰነድ1\2 እና 3 ለቡድን 4 • ኤችአይቪ/ኤድስ ሰነድ 4\5/6 እና 7 ለቡድን 5• ተጨማሪ ንባብ • የሥርዓተ ፆታ መረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ በአማርኛ (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Materi- als/ Toolkit% 20-%20Gender%20(Amharic).pdf) የኤችአይቪ መረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ በአማርኛ • (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Mate rials/Toolkit%20-%20HIV.%20(Amharic).pdf ) 27 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 11 መረጃ መተንተንና መተርጐም የክፍለ ጊዜው የዚህ ክፍለ ጊዜ አስፈላጊነት ከገጠሩ ማህበረሰብ የተሰበሰበውን ያስፈለገበት የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ አተናተንና አተረጓጐም ምክንያት ሙያን ለማዳበር ተብሎ ነው። የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች ከሥርዓተ ፆታ ዕይታ አንፃር መረጃን ይተነትናሉ ይተረጉማሉ፣ • ከኤችአይቪ/ኤድስ ዕይታ አንፃር መረጃን ይተነትናሉ ይተረጉማሉ። • ከመስክ ሥራ ሂደት ተጨባጭ ግብረመልሶችን ይሰበስባል • ከማህበረሰቡ ጋር የነበረውን የቡድኑን ግንኙነትና የቡድኑን • አመለካከትና ጠባይ ይዳስሳሉ።• በቡድን አባላት መሃል ያለውን ግንኙነት ይመረምራሉ • ለወደፊቱ የማስተባበር ችሎታቸውን የሚሻሽሉበት ዘዴ ላይ አስተያየት• ይሰጣሉ።• የክፍለ ጊዜው ትንተና መረጃ መተንተንና መተርጉም የመስክ የሥራ ሂደትን መከታተል፣ ማቅረብ• አስፈላጊ ቁሳቁሶች ተገላጭ ቻርት ባለቀለም ወረቀቶች • መፃፊያ ማርከር • ማስመሪያ • ማጣበቂያ/ኘላስተር• የሚፈጀው ጊዜ 300 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት መልመጃ 1/ መረጃ መተንተንና መተርጐም 160 ደቂቃ አስተባባሪው/ዋ ከመስክ የተሰበሰበውን መረጃ የሥርዓተ ፆታ ትንተና • ዘዴን /ሰነድ6፣7 እና 8/ በመጠቀም እንዴት መተንተንና መተርጐም እንደሚቻል ያስረዳል/ታስረዳለች ። ከመስክ የተሰበሰበውን የኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ • የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና ዘዴን /ሰነድ 8 እና 9/ በመጠቀም እንዴት መተንተን እንደሚቻል ያስረዳል/ታስረዳለች። የመስክ ሥራ ቡድኖች መረጃ ሲተነትኑና ሲተረጉሙ • ድጋፍ ይሰጣል/ትሰጣለች ። 2/ የመስክ ሥራ ሂደትን መታዘብ 30 ደቂቃ አስተባባሪው/ዋ የክፍለ ጊዜውን ዓላማና የመስክ ሥራ ሂደትን ግምገማ እንዴት ማካሄድ እንዳለባቸው ያስረዳል/ታስረዳለች። 28 ተሳታፊዎች የቡድኑን የማስተባበር ሙያ ከ10• ነጥብ እንዲሰጡት አድርግ/ጊ /1=ዝቅተኛ - 10= ከፍተኛ / ለሚሰጡት ነጥብ ከታች የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች በመንተራስ በቂ ምክንያት እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል። የቡድኑ የእርስ በርስ ግንኙነት ከማህበረሰቡ ጋር• የነበረው ከስብሰባ በፊት፣ በስብሰባው ላይና ከስብሰባው በኋላ እንዴት ነበር? ከማህበረሰቡ ጋር በነበረው ውይይት የወንዶችና • የሴቶች የተሳትፎ ደረጃ ምን ይመስል ነበር? ዝምተኛውን የማህበረሰብ አባል እንዲሳተፍ • እንዴት አበረታታችሁት ? ሀይለኛ ተናጋሪውንስ እንዴት ተቆጣጠራችሁት? • የቡድኑና የማህበረሰቡ ግንኙነትና ቅርርብ ምን• ይመስል ነበር? የማስተባበር ሙያችሁስ እንዴት ታሻሽሉታላችሁ• 3/ ማቅረብ 105 ደቂቃ እያንዳንዱ ቡድን የደረሰበትን ውጤት ያቀርባል• /እያንዳንዱ ቡድን 10የደቂቃ/ እንዲሁም የመስክ ስራ ሂደት ግብረ መልስ /Feedback/ ያቀርባሉ /እያንዳንዱ ቡድን 5 ደቂቃ/ ግብረ መልስና ውይይት /30 ደቂቃ/• ሽግግር - ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ 5 ደቂቃ ተጨማሪ ንባብ - የሥርዓተ ፆታ ትንተና ቅፅ ሰነድ 6,7 እና 8 የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና ቅጽ ሰነድ 8 እና 9• (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Materials/Tool- kit% 20-%20Gender%20(Amharic).pdf) (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Materials/Tool- kit% 20-%20HIV.%20(Amharic).pdf ) 29 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 12 በሥርዓተ ፆታና በኤችአይቪ/ኤድስ ምላሾች ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን ማፍለቅ የክፍለ ጊዜው ለሥርዓተ ፆታና ኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ የሚሆን በርካታ የተወሰኑ ያስፈለገበት ከግብርና ጋር የተያያዙ ተግባራት ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን ማፍለቅ ምክንያት የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ግዜ መጨረሻ ላይ የኤክትቴንሽን ሰራትኞች በርካታ የሥርዓተ ፆታ ተግባራትን ከዕለት • ተዕለት ተግባራቸው ጋር ተቀብለው የሚያዋህዱትን መለየት ይችላሉ። የኤክስቴንሽን ሰራተኞች በርካታ የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮችን ከዕለት • ተግባራቸው ጋር ተቀብለው የሚያዋህዱትን መለየት ይችላሉ። yክፍለ ጊዜው ትንተና - ለሥርዓተ ፆታ ምላሽ የተለያዩ ሀሳቦችን ማፍለቅ ለኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ የተለያዩ ሀሳቦችን ማፍለቅ• Aስፈላጊ ቁሳቁሶች ተገለላጭ ቻርት ካርዶች• መፃፊያ ማርከር • ማጣበቂያ/ኘላስተር• የሚፈጀው ጊዜ 105 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት የቡድን ሥራ 1/ ለሥርዓተ ፆታ የተለያዩ ሀሳቦችን ማፍለቅ 45 ደቂቃ የክፍለ ጊዜውን አስፈላጊነት ማስረዳት ስለ ሥነ-ፆታ ወይም ስለኤችአይቪ ኤድስ ጥያቄዎችን የያዙ ካርዶችን ለተሳታፊዎች ማደል /እያንዳንዱ ጥንድ አንድ ካርድ በመስጠት/ /በአባሪ 2 ቅጽ 5 እና 6ን ተመልከት/ እንደ አንድ የኤክስቴንሽን ሰራተኛ ወይም እንደ - የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ ወይም የወረዳ ሰራተኛ ምን ማድረግ አለብኝ? በሚለው ዋና ጥያቄ ሥር በስልጠና ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ- ሴቶችን በሀብት፣ ለሥልጣን፣ አቅም እንዲኖራቸው - ለማድረግ የሴቶችን ጉልህነት ለመጨመር - የሴቶችን የሥራ ጫና ለመቀነስ - ገበሬዎች ስለኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ - የሚጋኙበትን መንገድ ለማስፋት ነጋዴዎች፣ አጓጓዦች፣ ተራ ሰራተኞች፣ ደላሎች- ስለኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ የሚያገኙበትን መንገድ ለማስፋት፣ የገበሬዎችን ወደ ገበያ ምልልስ ለመቀነስ - 30 ገበሬዎችና ሰራተኞች ገቢያቸውን በአግባቡ- እንዲጠቀው ለማበረታታት ከኤችአይቬ/ኤድስ ጋር የሚኖሩትንና የቤተሰብ- መሪያቸውን የሚደገፉ ድርጅቶችን ለማስተዋወቅ ስለ ጥያቄዎቹ ተሳታፊዎቹ ለ10 ደቂቃ የተለያዩ• ሀሳብ እንዲያፈልቁ አድርግና እያንዳንዱን አስተያየት በተለያየ ካርድ ላይ መዝግብ ሁሉም ተሳታፊ ባንድ ላይ አስተያየታቸውን• እንዲያክሉበት አድርግ በምርታማነትና ገበያ ስኬት ማሻሻያና በሌሎች• ድርጅቶች የተለዩ ሀሳቦች ካሉዋቸው እንዲታከልበት ማድረግ በስልታዊ የሥርዓተ ፆታ ፍላጐትና በተግባራዊ• የሥግዓተ ፆታ ፍላጐት መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ 2/ ስለኤችአይቪ/ኤድሰ ምላሽ የተለዩ ሀሳቦችን ማፍለቅ 55 ደቂቃ ሁሉም ተሳታፊ ባለበት ስለኤችአይቪ/ኤድስ• አስትያየታቸውን እንዲሰጡ አድርግ በምርታመነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ ፕሮጀክት • የተለዩ ተጨማሪ አስያየቶች ካሉ እንዲታከልበት• አድርግ ሽግግር - የትምሕርቱ ሂደት ወደሚቀጥለው ማሸጋገር 5 ደቂቃ የተዘጋጀ ጽሑፍ - የተዘጋጀ ጽሑፍ 12 ለሥርዓተ ፆታና ኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ ከግብርና ጋር የተያያዙ ሀሳቦች ማፍለቅ የምርታማነት መሻሻያና ገበያ ስኬት ፕሮጀክት• የሥርዓተ ፆታ እውነታዎች የምርታማነት መሻሻያና ገበያ ስኬት ፕሮጀክት• የኤችአይቪ /ኤድስ ፖስተሮች ተጨማሪ ንባብ IPMS የወረዳ ኤችአይቪ/ኤድስ እውነታ ገጾች “ “ ፖስተሮች • “ “ የሥርዓተ ፆታ እውነታዎች• 31 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 13 መርሃ ግብር ማዘጋጀት የክፍለ ጊዜው የዚህ ክፍለ ጊዜ አስፈላጊነት በተግባር ሊተረጐም የሚችል ያስፈለገበት መርሃ ግብር በገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከልና በወረዳ ደረጃ ምክንያት ለማዘጋጀት ነው ። የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች በግብርናው ዘርፍ ሥርዓተ ፆታንና የኤችአይቪ/ኤድስን ጉዳዮችን • ለማሳካት ያሉትን መልካም አጋጣማዎች በመጠቀም መርሃ ግብር ያዘጋጃሉ ኤችአይቪ/ኤድስንና ሥርዓተ ፆታን ከዕለት ተዕለት ተግባራቸው ጋር• ያዋህዳሉ የክፍለ ጊዜው ትንተና መርሃ ግብር ዝግጅት መርሃ ግብር ማቅረብ አስፈላጊ ቁሳቁሶች ተገላጭ ቻርት በቀለም መፃፊያ ወረቀቶች • መፃፊያ ማርከር • ማስመሪያ • ማጣበቂያ/ ኘላስተር• የሚፈጀው ጊዜ 245 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት መልመጃ 1/ መርሃ ግብር ማዘጋጀት 150 ደቂቃ አስተባባሪው/ዋ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ መርሃ ግብር• አዘገጃጀት ቅፆችን ያስረዳል/ታስረዳለች ተሳታፊዎችን በገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከላቸውን • ያቧድናል/ታቧድናለች ፣ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ መርሃ ግብር• ማዘጋጃ ቅፆችን ለያንዳንዱ ቡድን አድሎ መርሃ ግብር በማሰልጠኛ ማዕከል ደረጃ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል/ታደርጋለች ። /2 ሰዓት/ 2/ ማቅረብ 90 ደቂቃ ተሳታፊዎች በሙሉ በተገኙበት የሥርዓተ ፆታና• የኤችአይቪ/ኤድስ መርሃ ግብ ማቅረብ /ለያንዳንዱ ቡድን 10 ደቂቃ በጥቅሉ በግምት 1 ሰዓት/ በቀረበው ላይ የቡድን ውይይት (20 ደቂቃ) • የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ /ኤድስን በማካተት• ለመስራት ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች በመርሃ ግብር ዝግጅት ጊዜ መጠቀም አስፈላጊነቱን ያስረዳል/ታስረዳለች ። /20 ደቂቃ/ 32 ሽግግር - ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ 5 ደቂቃ የተዘጋጀ ጽሑፍ - የተዘጋጀ ጽሑፍ 13 መርሃ ግብር ተጨማሪ ንባብ - የሥርዓተ ፆታ መርሃ ግብር ዝግጅት ቅፅ የኤችአይ/ኤድስ መርሃ ግብር ዝግጅት ቅጽ • የሥርዓተ ፆታ መረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ በአማርኛ • የኤችአይቪ መረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ በአማርኛ• (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Materials/ To olkit%20-%20Gender%20(Amharic).pdf) (http://www.ipms- ethiopia.org/content/files/documnets/training%20Materials/ To olkit%20-%20HIV.%20(Amharic).pdf ) 33 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 14 የድርጊት መርሃ ግብርን መከታተል የክፍለ ጊዜው ይህ ክፍለ ጊዜ ያስፈለገበት ምክንያት በገበሬዎች ማሰልጠኛ ያስፈለገበት ማዕከልና በወረዳ ደረጃ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብርን እንዴት ምክንያት መከታተል እንደሚቻል ሙያዊ ብቃት ለማሳደግ ነው። የክፍለ ጊዜው ዓላማ በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ተግባራት በታቀደላቸው መሰረትና• በተያዘላቸው ጊዜ መፈፀማቸውን ያረጋግጣሉ። ክትትል ሊደረግባቸው የሚገቡ የሥርዓት ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ• ጠቋሚዎችን ይለያሉ። የትኛው ዘዴና የትኛው መሳሪያ የበለጠ ሴቶችን ለማግኘትና• የኤችአይቪ/ኤድስ ተግባራትን ለመፈፀም እንዳስቻለ ይለያሉ። የሥነ-ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ተግባራት ምን ያህል እንደተካሄደበት• ይመዘግባሉ። አንዳንድ ጉዳዮች በተፈለገውና በሚጠበቀው መንገድና መጠን ካልተሰሩ• አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳሉ። ሴቶችና ወንዶችን በእኩል ደረጃ ለማስተናገድ ያስቻሉትን ተሞክሮዎችና• ትምሕርቶችን መዝግበው ይይዛሉ። የክፍለ ጊዜው ትንተና የክትትል ዘዴን ማዘጋጀት ለተሳታፊዎች ማቅረብ• Aስፈላጊ ቁሳቁሶች ተገላጭ ቻርት የተለያየ ቀለም ያላቸው መፃፊያ ወረቀቶች • መፃፊያ ማርከር • ማስመሪያ • ማጣበቂያ/ኘላስተር• የሚፈጀው ጊዜ 105 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት መልመጃ 1/ የክትትል ዘዴ ማዘጋጃ 40 ደቂቃ አስተባባሪው/ዋ እንዴት የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ የድርጊት 20 ደቂቃ• መርሃ ግብር የሚከተሉትን ነጥቦች በመጠቀም መከታተል እንደሚቻል አስረዳ/ረጂ፦ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ ጠቋሚዎችን - በኤችአይቪ/ኤድስ የተጠቁና የተጐዱ ሰዎችና- ቤተሰቦችን እንዲሁም ሴቶችን ያሳተፈና ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘዴና ስልቶችን፣ የተከናወኑ ተግባራትንና ሂደታቸውን መመዝገብና- ማሳወቅ ። በፊት ለመርሃ ግብሩ ከተመሰረተው ቡድን ጋር አብሮ• መስራትና መቀጠል፣ 34 አንድ የተሻለ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ መርሃ• ግብር መርጦ ተገላጭ ቻርት ላይ ወይም ግድግዳ ላይ መለጠፍ፣ ሁሉም ቡድኖች በአንድ መርሃ ግብር ላይ እንዲሰሩ 20 ደቂቃ• ነገር ግን የተለያየ ተግባር እንዲይዙ /ለምሳሌ አንድ ወይም ሁለት ቡድን በአንድ ጥያቄ ላይ እንዲሰሩ እንደ ሰው ብዛት እየታየ/ በተለጠፈው መርሃ ግብር ላይ የሥርዓተ ፆታና- የኤችአይቪ ጠቋሚዎች ምን ምን ናቸው? ምን ዓይነት ዘዴዎች ወይም አቀራረቦች የሴቶችን ተሳትፎ ሊያሳዳግ ይችላል። በገበያ መር የግብርና ልማት ውስጥ የኤችአይቪ/- ኤድስ ተደራሽነትን በምን ዓይነት ዘዴዎችና አቀራረቦች የበለጠ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል። 2/ ለተሳታፊዎች ማቅረብ 65 ደቂቃ ግኝታቸው ለተሳታፊዎች ማቅረብ /ለያንዳንዱ ቡድን 40 ደቂቃ• 5 ደቂቃ በጥቅሉ 30 ደቂቃ/ ቡድኑ ባቀረበው የቡድን ውይይት ማድረግ• አስተባባሪው/ዋ 20 ደቂቃ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ/ኤድስ መርሃ ግብርና• ክትትል ያላቸውን ምክንያታዊ ግንኙቶችንና በተለይም የታቀደውን ውጤት ለማምጣት በሚረዱ ጠቋሚዎች፣ ዘዴዎችና የመረጃ ሰነዶች በመጠቀም እንዴት እንደሚሰራ ያሳያል/ታሳያለች። በመርሃ ግብር ወቅት የተዘለሉ አስፈላጊ ጠቋሚዎችን- ዘዴዎችንና መረጃ ሰነዶችን ያሰገነዝባል። በመጨረሻም ተሳታፈዎች በአንድ የጊዜ ገደብ ላይ • እንዲስማሙ ይረዳል። የመጨረሻው የድርጊት መርሃ ግብር ለግብርና - ገጠር ልማት ቢሮዎች ለማስገባት ፣ ከመርሃ ግብሩ ግብ አኳያ እየተደረገ ያለውን ሂደት- ለማሳወቅ ሽግግር ወደሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መተላለፍ 5 ደቂቃ የተዘጋጀ ጽሑፍ የተዘጋጀ ፅሑፍ 14 የሥርዓተ ፆታንና ኤችአይቪ/ኤድስን ከክትትልና ግምገማ ጋር ማዋሀድ ተጨማሪ ንባብ አባሪ 1፡ የአይፒኤምስ የሥርዓተ ፆታ እና ኤችአይቪኤድስ መከታተያ ቅፅ 35 የአሰልጣኞች መመሪያ ክፍለ ጊዜ 15 ማጠቃለያና ቀጣይ ሥራዎች የክፍለ ጊዜው የዚህ ክፍለ ጊዜ አስፈላጊነት የተሰጡትን ትምሕርቶች ከተለያዩ ያስፈለገበት አቅጣጫዎች ለመመዘንና ለአስተባባሪዎችና አዘጋጆች ግብረ መልስ ምክንያት /feed back/ እንዲያገኙ ለማስቻል ነው። የክፍለ ጊዜው ዓላማ ከዚህ ክፍለ ጊዜ በኋላ ተሳታፊዎች ስልጠናው የተሰጠበት ስልትና የስልጠናው ሂደት ትምሕርቶችን መመዝገብ ይ• ችላሉ ። ስለስልጠናው ይዘት የተሰጡትን ዋና ዋና ትምሕርቶች መመዝገብ ይችላሉ። • ቀጣይ ሥልጠናዎቸ የሚሻሻሉበትን ሀሳብ መስጠት ይችላሉ።• የክፍለ ጊዜው ትንተና • የትምሕርቱ ምዘና ማጠቃለያ• አስፈላጊ ቁሳቁሶች ካርዶች መፃፊያ ማርከሮች • ማጣበቂያ ማስቲሽ• የሚፈጀው ጊዜ 60 ደቂቃ ተግባራት ተፈላጊ ሰዓት መልመጃ 30 ደቂቃ 1/ የትምሕርቱ ምዘና ተሳታፊዎች በሚቀጥሉት ሀሳቦች ላይ አስተያየታቸውን• እንዲሰጡ ጠይቅ/ቂ ሀ/ በስልጠናው ከተሰጡት ትምሕርቶች ሦስት በጣም ጠቃሚ ትምህርቶችን ጥቀስ/ሽ ለ/ ስልጠናው ከተሰጠበት ስልትና ሂደት ሦስት በጣም ጠቃሚ ትምህርቶችን ጥቀስ/ሽ ሐ/ ስልጠናውን ለማሻሻል ያላችሁን አስትያየት ስጡ ሶስት ወይም ሁለት ተሳታፊዎች ስለስልጠናው ይዘት• ያላቸውን ግብረ መልስ /feedback/ እንዲያቀርቡ ጠይቅ/ቂ ስለስልጠናው አካሄድ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡ• ሁለት ወይም ሶስት ተሳታፊዎችን ጠይቅ/ቂ ሁለት ወይም ሶስት ተሳታፊዎች ቀጣይ ስልጠናዎች• ስለሚሻሻሉበት ሁኔታ አስተያየታቸውን ጠይቅ/ቂ በሦስት ጥያቄዎች የተሰጡትን አስተያየቶች በተለያዩ • ፖስታዎች መሰብሰብ፡፡ (የእያንዳንዱ ጥያቄ በአንድ ፖስታ ለብቻ) ስልጠናው ካበቃ በኋላ ሀሳቦችን ማጤን ውጤቱን በስልጠናው ሪፖርት ላይ ማቅርብ• 2/ ማጠቃለያ 30 ደቂቃ ተሳታፊዎችን፣ አስተባባሪዎችን፣ አዘጋጆችን፣ • 36 እንዲሁም ለስልጠና ድጋፍ ያደረጉ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን ማመስገን አዘጋጆች በስልጠናው ላይ ያላቸውን አስተያየት • እንዲሰጡ መጋበዝ የተዘጋጀውን ሰርተፊኬት ለሰልጣኞች መስጠት • በመጨረሻም ተጋባዥ የድርጅት ተወካይ የመዝጊያ ንግግር እንዲያደርጉ መጋበዝ 37 የተዘጋጁ ጽሑፎች የተዘጋጀ ጽሁፍ 1፡ የወርክሾፑ ዓላማ የተዘጋጀ ጽሁፍ 2፡ የሥርዓተ ፆታ ትንተና መሠረተ ሀሳቦች የተዘጋጀ ጽሁፍ 3፡ የኤች አይቪና የኤድስን መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች መረዳት የተዘጋጀ ጽሁፍ 4፡ በገጠሩ ህብረተሰብ የኤች አይቪ/ኤድስ መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች ትንተና የተዘጋጀ ጽሁፍ 5፡ ሴቶችን ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጠቂ የሚያደርጓቸው ምክንያቶችና ተዛማጅነታቸው የተዘጋጀ ጽሁፍ 6፡ የችግር ምክንያትና ውጤት ትስስር መግለጫ ዛፍ መርሆዎች የተዘጋጀ ጽሁፍ 7፡ በፆታ የተሰባጠረ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚረዱ አሳታፊ ሰነዶች የተዘጋጀ ጽሁፍ 8፡ በማህበረሰብ የሚሰራ ካርታ የተዘጋጀ ጽሁፍ 9፡ የሥርዓተ ፆታና ኤች አይቪ/ኤድስ እንደዋና ተግባር እንዲወሰድ ለማድረግ የሚረዳ የ ማሳለጫ ሙያ የተዘጋጀ ጽሁፍ 10፡ የመስክ ሥራ አሠራር የተዘጋጀ ጽሁፍ 11፡ በከፊል የተዘጋጁ ቃለ መጠይቆችን እንዴት እንደምናቀርብ የተዘጋጀ ጽሁፍ 12፡ ከግብርና ጋር ተዛማጅነት ባላቸው ተግባሮች ውስጥ ሥርዓተ ፆታንና ኤች አይቪ/ኤድስ ን እንደዋና ተግባር እንዲወሰድ ለማድረግ ጥልቅ ሀሳቦችን ማፍለቅ የተዘጋጀ ጽሁፍ 13፡ የድርጊት መርሐ ግብር የተዘጋጀ ጽሁፍ 14፡ ኤች አይቪ/ ኤድስንና ሥርዓተ ፆታን ከክትትልና ግምገማ ጋር ማቀናጀት 38 የተዘጋጀ ጽሁፍ 1፡ የወርክሾፑ ዓላማ የወርክሾፑ ዓላማ እና አስፈላጊነት ግንባር ቀደም ተሰላፊ የሆኑትን የመስክ ሠራተኞች በሥርዓተ ፆታንና ኤችአይቪ/ኤድስ በገበያ መር የግብርና ል ማት አካተውና ከእለት ተዕለት የገጠር ልማት ሥራቸው ጋር ለማዋሀድ እንዲችሉ አቅማቸውን ክህሎታቸውን ለማጐልበትና ተግባራዊ ችሎታቸውን ለማሳደግ ነው። የወርክሾፑ ዓላማ ተሳታፊዎች፡- የሥርዓተ ፆታ መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳብን ከግብርና ሥራ ጋር አያይዘው እንዲረዱ ለማድረግ፣• የኤች አይቪ/ኤድስ መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳብን ከግብርና ሥራ ጋር አያይዘው እንዲረዱ• ለማድረግ፣ በገጠሩ ህብረተሰብ ውስጥ በፆታ የሰበጣጠረ የሥርዓተ ፆታ መረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችና• መረጃ ሰነዶችን አጠቃቀም እንዲያውቁ፣ በገጠሩ ህብረተሰብ በኤች አይቪ የመያዝ አደጋንና የኤድስ ተጋላጭነት መረጃን ለመሰብሰብ• የምንጠቀምበት ዘዴና መረጃ ሰነዶችን አጠቃቀም ግንዛቤ እንዲያውቁ፣ የሥርዓተ ፆታና የኤች አይቪ/ኤድስ መረጃ አተናተን ዘዴ እንዲረዱ፣ • የሥርዓተ ፆታና የኤች አይቪ/ኤድስን የተግባር መርሃ ግብር የማዘጋጀት ክህሎት• እንዲኖራቸው የሥርዓተ ፆታና ኤች አይቪ/ኤድስን ከእለት ተዕለት ተግባራቸው ጋር የማዋሃድ ክህሎት• እንዲያዳብሩ ለማድረግ ነው፣ 39 የወርክ ሾፑ ፕሮግራም አ ን ደ ኛ ቀ ን ሁ ለ ተ ኛ ቀ ን ስ ተ ኛ ቀ ን አ ራ ተ ኛ ቀ ን አ ም ስ ተ ኛ ቀ ን የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ ኤድስ ግንኙነት የሥርዓተ ፆታና ኤች አይቪ/ኤድስ ተፅዕኖ በገበያ መር፣ ግብርና ልማት ላይ የኤች አይቪ/ኤድስ መረጃ መተንተኛ የሥርዓተ ፆታ መረጃ መተንተኛ ሰነዶች የሥርዓተ ፆታና ኤች አይቪ/ኤድስ እንደ ዋና ተግባር እንዲወሰድ ጥልቅ ሀሳቦችን ማፍለቅ ክትትልና ግምገማ መግቢያ የሥርዓተ ፆታ ፅንሰ ሀሳብ የኤች አይቪና የኤድስ መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳብ የማስተባበር/ የማሳለጫ ክህሎት መርሃ ግብር የመስክ ሥራ ዝግጅት የመስክ ሥራ/ መረጃ መሰብሰብ መረጃ መተንተንና መተርጎም 40 በካርድ ላይ እንዴት እንደሚፃፍ፡- በአንድ ካርድ ላይ አንድ ሀሳብ ብቻ ፅፉ፡፡ እያንዳንዱ ሀሳብ ማቡዋደን እንዲቻል• በያንዳንዱ ካርድ ላይ ሦስት መስመር ብቻ ፃፉ፣ • ከሙሉ ዓረፍተነገር ይልቅ ቁልፍ ቃላትን ተጠቀሙ፣ • ፊደሎቹን ጎላ ጎላ አድርጋችሁ ፃፉ፣ • የመፃፊያ ማርከሩን ቀጭን ጎን ሳይሆን ሰፊውን ጎን ተጠቅማችሁ• በትልልቁ መጻፍ ልመዱ፣ የራሳችሁን ፈጠራ ተጠቅማችሁ የተለያየ መጠን ቅርጽና ቀለም ያላቸው ካርዶችን ተጠቀሙ፣• ሦስት መስመር አንድ ካርድ ላይ ቁልፍ ቃላት ተጠቀሙ አንድ ሃሳብ አንድ ካርድ ላይ ስዕል1. በካርድ ላይ የአፃፃፍ ዘዴ የስሜት መለኪያ ይህ የስሜት መለኪያ ስለተዘጋጀው የስልጠና ወርክሾፕ ተሳታፊዎች ስሜታቸውን የሚገልፁበት መሳሪያ/ዘዴ ነ ው። ተሳታፊዎች በተዘጋጀው የስሜት መለኪያ ላይ ስለግማሽ ቀን ወይም ሙሉ ቀን የስልጠና ውሎአቸው ስሜ ታቸውን እንዲገልፁ ይደረጋል። ይኸ ደግሞ ለስልጠናው አዘጋጆችና አስተባባሪዎች ግብረ መልስ ሆኖ ያገለግላ ል። ስለዚህ በዚህ በሰልጣኞች ስሜት ላይ ተሞርክዞ ስልጠናው ባለበት እንዲቀጥል ወይም እንዲሻሻል ዘዴ መቀ የስ ያስችላል። መለኪያው በመውጫ በር አጠገብ ሁሉም ሰው በቀላሉ ሊያየውና አስተያየቱን በነፃነት እንዲሰጥ የሚያስችል ቦታ ላይ መለጠፍ አለበት። እንዲነበብ በትልቁ ፃፉ የተለያየ ቀለም ተጠቀሙ ጎላ ጎላ ያሉ ፊደላትን ፃፉ የካርድ አፃፃፍ ሕጎች 41 የስሜት መለኪያ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ሀሙስ አርብ ጧት ከሰዓት ጧት ከሰዓት ጧት ከሰዓት ጧት ከሰዓት ጧት ከሰዓት በጣም ደስተኛ ደስተኛ ምንም ያልተሰማው የተከፋ ስዕል 2፡ የስሜት መለኪያ ተምሳሌት ለተሳታፊዎች 42 የተዘጋጀ ጽሑፍ 2፡- የሥርዓተ ፆታ መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳብና የሥርዓተ ፆታ ትንታኔ ሥርዓተ ፆታና ፆታ ፆታ በወንድና በሴት መካከል ያለውን ተፈጥሯዊ ልዩነት የሚያሳይ ነው። ሥርዓተ ፆታ በወንድና በሴት መካከ ል ያለውን ማህበራዊ ግንኙነት የሚያመለክት ነው። የሥርዓተ ፆታ ግንኙነቶች ከቦታ የሚለያዩና እንደ ወቅቱ የ ኢኮኖሚ ሁኔታ የሚለዋወጡ ናቸው። ፆታ ሥርዓተ ፆታ ተፈጥሮአዊ በማህበረሰቡ የተገነቡ የሥራ ድርሻና ኃላፊነቶች አብሮ የሚወለድ አብሮ የማይለይ በተፈጥሮ የተወሰነ/የተገኘ የሚማሩት ዓለም አቀፋዊ ባህላዊ ሊለወጥ የማይችል ሊለወጥ የሚችል ከባህል ባህልና ከጊዜ አኳያ ልዩነት የሌለው ከባህል ባህል ከጊዜ ጋር ተለዋዋጭ የሆነ ለምሳሌ መውለድ የሚችሉት ሴቶች ብቻ ናቸው ለምሳሌ ሴቶች የወንዶችን ሥራ መስራት መቻል ስዕል 1፡ በፆታና በሥርዓተ ፆታ መሐል ያለ ልዩነት የሥርዓተ ፆታ ትንተና የሥርዓተ ፆታ ትንተና የሁለቱንም ፆታ ፍላጎት፣ አመለካከትና ግብ ለመረዳትና በፕሮጀክት ወይም ልማታዊ እ ንቅስቃሴ ውስጥ ፍላጐተቸውንና ግባቸውን በአግባቡ ለማቀናጀት ይጠቅማል። የ‘ማነው’ ጥያቄዎች ማነው የሚሳተፍ? • ማነው ውሳኔ የሚሰጥ? • ማነው ተጨማሪ ሸክሙን የሚሸከም? • ማነው ምን የሚሠራ፣ ወይም የተለየ ሥራ ያለው? • ማነው ሀብትን የሚጠቀም? • ማነው ሀብትን የሚቆጣጠር? • ማነው ተጠቃሚው?• ሦስት እጥፉ የሥርዓተ ፆታ ድርሻ በህብረተሰብ ውስጥ ያለው የሥራ ክፍፍል ተፈጥሯዊና የሥርዓተ ፆታ ልዩነትን የሚያሳይ ነው። በብዙ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ሴቶች ሦስት እጥፍ ድርሻ እለባቸው፣ የመውለድ የማምረትና የማህበራዊ ተሳትፎ ድርሻ። ወንዶች በአብዛኛው የማምረትና የማህበራዊ ተሳትፎ ድርሻ ላይ ብቻ ነው የሚገኙት። የመውለድና የመንከባከብ ድርሻ፡- ይህ ድርሻ ልጅ የመውለድና የማሳደግ ኃላፊነትንና የሴቶች የቤት ውስጥ ሥ ራ ማለትም አምራች ኃይሉን በአስተማማኝ ደግፎ መያዝንና መጨነርብ ይመለከታል። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ አ ርግዞ መውለድን ብቻ ሳይሆነ ቤተሰቡን በሥራ የሚደግፈውን ኃይል (የወንድ ጓደኛንና አምራች ልጆችን) የመን ከባከብ ኃላፊነት ማለት ነው፡፡ እንዲሁም የወደፊት የሥራ ኃይል የሚሆኑትን ህፃናትና ትምህርት ቤት የሚሄዱ ትን ልጆች ይጨምራል። 43 የአምራችነት ድርሻ፡- በዓይነት ወይም በገንዘብ ክፍያ ለማግኘት ወንዶችም ሴቶችም የሚሰሩት ሥራ ነው፡፡ ይህ ወደ ገበያ ተወስዶ ዋጋ የሚያወጣን፣ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ውሎ ጠቀሜታ የሚያስገኝንና ሊሽጥም ሊለወጥም የ ሚችለውን ምርት ያካትታል። በግብርና ምርት ለተሰማሩ ሴቶች ራሳቸውን ችለው ገበሬ መሆንን፣ ጭሰኝነትን ወ ይም ተቀጥሮ መስራትን ይጨምራል። የማህበራዊ አገልገሎት ድርሻ፡- በማህበረሰቡ ውስጥ ሴቶች የሚሰሯቸው ሥራዎች አብዛኛውን ጊዜ የመውለድ ና የመንከባከብ ድርሻ ተቀጥላዎች ናቸው። እጥረት ያላቸውን የጋራ ጠቀሜታ ያላቸውን ሀብቶች በእንክብካቤ የ መያዝና የማቅረብ። (ለምሳሌ ውሃ፣ ጤናና ትምህርት የመሳሰሉትን) ይህ ያለምንም ክፍያ በትርፍ ጊዜያቸው የ ሚሰሩት ሥራ ነው። ማህበራዊ የፓለቲካ ጉዳዮች ድርሻ፡- በአገር አቀፍ የፖለቲካ መስመር ሥር በማህበረሰብም ደረጃ በተለያዩ የፖለ ቲካ ድርጅቶች በተለያየ ደረጃ መሳተፍ በአብዛኛው በወንዶች የሚዘወተር ነው፡፡ ይህ ሥራ በቀጥታ ወይም በተዘ ዋዋሪ መንገድ በሥልጣን ወይም በደረጃ የማደግ ጥቅም ሊያስገኝ ይችላል። በሀብትና በጥቅማ ጥቅም የመገልገልና የማዘዝ ፆታዊ ድርሻ፡- በጥቅሉ ሲታዩ በመገልገልና በማዘዝ መሃል ያለ ው ልዩነት ግልፅ ነው። መገልገል የሚያመለክተው በሀብቱ ወይም በጥቅሙ መጠቀም መቻልን ሲሆን ማዘዝ ደ ግሞ መቼና እንዴት መጠቀም እንዳለብን መወሰን መቻልን ነው። ስለዚህ አንድ ሴት ለአረም ሥራ የቤተሰብ አባ ልን እገዛ ማግኘት መብቷ ነው። ነገር ግን ማን ሊያግዛት እንደሚገባ፤ መቼ መታገዝ እንዳለባት የሚወስነው ወ ንድየው ነው። ወንዶችና ሴቶች በማምረቻ ንብረትና በጥቅማ ጥቅም ላይ አንድ ዓይነት መብት ወይም እኩል መብት የላቸውም። ይህ ፆታን መሠረት ያደረገ ኢ-ሚዛናዊ ልዩነት መኖሩ የልማት ሥራ ሲታቀድ በጥንቃቄ ካልታየ የራሱ የሆነ ተ ፅዕኖ እንደሚኖረው እሙን ነው። ስለዚህ የሥርዓተ ፆታ ትንተና ሲሰራ እቅድ አውጭዎች በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ፆታን መሠረት ያደረገ ልዩነት በንብረት የመጠቀምና የማዘዝ መብት ምን እንደሚመስል መረጃ ሊኖራቸ ው ይገባል። በንብረት የመጠቀምና የማዘዝ ባህልን መረዳትና መረጃዎችን መሰብሰብ የሥርዓተ ፆታን ሁኔታ/ክፍ ፍልን ማወቂያ መሳሪያ ነው። ምን ዓይነት ሀብት ነው ወንዶችም ሴቶችም የሚሠሩበት? • ማነው የዚህ ሀብት ባለቤት/ተቆጣጣሪ/ ተጠቃሚ? ማንስ ነው ከተጠቃሚነትና ባለቤትነት የተገለለው? • ወንዶችና ሴቶች ምን ዓይነት ውሳኔ ይሰጣሉ፤ በቤት ውስጥ? በማህበረሰቡ ውስጥ?• በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ፆታዊ ድርሻ ፡- በቤተሰብ፣ በማህበረሰብና በተቋማት ደረጃ ውሳኔዎች ይወሰናሉ። የሴቶች በነዚህ ውሳኔዎች መካፈልና፤ ውጤቱ ላይ ለውጥ ማምጣት ድምጻቸውን ከፍ እንዲያደርጉና አመለካከታቸው ተቀባይነት ያለው መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት። በዚህ ሂደት ውስጥ በበቂ ሁኔታ እንዲሳተፉ ካልተደረገ ፍላጎቶቻቸውና ምኞቶቻቸው ሳይታዩ ሊታለፉ ይችላሉ። 44 የተዘጋጀ ጽሑፍ 3፡- የኤች አይ ቪና የኤድስ መሠረተ ሀሳቦችን መረዳት ይህ ጽሑፍ የኤች አይ ቪ/ኤድስ በሽታን መሠረታዊ እውነታዎችን እያስተዋወቀ በኤች አይ ቪ እና በኤድስ መሃ ል ያለውን ቁርኝት፣ የበሽታው መንስኤዎችንና በሽታው የማይተላለፍበትን መንገዶች እንዲሁም በግለሰብ ወይም በቤተሰብ ውስጥ የበሽታውን ዑደት ምን እንደሚመስል ያስረዳል። ኤች አይ ቪ ምንድነው? ሰዎችስ እንዴት ይያዛሉ? ኤችአይቪ/ኤድስ የሰው ልጆች የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል ኃይል የሚያዳክም ነው፡፡ ምንም እንኳን ግልፅ የሆነ ምልክት ባይኖርም በኤችአይቪ የተለከፈ ሰው ወደ ሌላ ሰው ረቂቅ ተህዋሱን ሊያስተላልፍ ይችላል። የሚተላለፍባቸው መንገዶች ቫይረሱ ካለበት ወይም ከኤድስ በሽተኛ ጋር ልቅ • የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ በበሽታው ከተበከለ ደም ወይም ከሌሎች የሰውነት • ፈሳሾች ጋር መነካካት (ለምሳሌ ከወንድ ብልት ወይም ከ ሴት ብልት የሚወጣ ፈሳሽ)፣ ስለታምና ሹል ነገሮችን እን ደ ሕክምና መርፌ፣ የመላጫ ምላጭ፣ መርፌ በጋራ መ ጠቀም ወይም በቆዳችን ላይ በሚገኝ ስንጥቅና ቁስል የተ በከለ ደም በመጋራት፣ • ቫይረሱ ካለባት እናት ወደ ልጅ (በእርግዝና፣ በመውለጃ ጊዜ ወይም በጡት ማጥባት አማካይነት) ኤድስ ምንድን ነው? ኤድስ በበሽታው የመጠቃት የመጨረሻ ደረጃ ነው። ኤች አይ ቪ የሰውነት የመከላከል አቅምን ቀስ በቀስ እያደከ መ ስለሚሄድ ሰውነታችን በሽታዎችን ሆነ ሌሎች ተላላፊዎችን ለመከላከል አቅም ያንሰዋል። በመጨረሻም ኤችአ ይቪ/ኤድስ የተያዘው ሰው በተደራራቢ በሽታዎች ተሰቃይቶ ይሞታል ወይም ትሞታለች። የኤድስ መለያ ምልክቶች ከፍተኛ የክብደት መቀነስ፣ ደረቅ ሳል፣ ከስምንት ቀን በላይ የሚቆይ ተቅማጥ፣ ተመላላ ሽ ትኩሳት፣ የዕጢዎች ማበጥ፣ የቆዳ ሽፍታ፣ ነገሮችን የመርሳት፣ ድብርትና ድካም የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። ማሳሰቢያ፡- እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ከሌሎች በሽታዎች ምልክት ጋር ተመሳሳይነት ስላላቸው በነዚህ ላይ ተመርኩዞ አንድ ሰው ኤድስ አለበት ማለት አይቻልም። ማነው በኤድስ ሊያዝ የሚችለው? በሽታው በማንኛውም ጎሳ፣ በማንኛውም ብሔር ወይም አገር እንዲሁም በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ የሚ ገኝ ስለሆነ ማንም ሰው በበሽታው የመያዝ አቅም አለው። በተለይ ደግሞ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሚያደርጋቸው ባህ ሪ ያላቸው ሰዎችና፣ አደገኛ የአኗኗር ዘይቤ ያላው በተለይም ለልቅ የግብረ ስጋ ግንኙነትና ለተበከለ ደምና የሰው ነት ፈሳሽ ጋር የመነካካት ዕድል ያለው አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ለበሽታው የተጋለጡ ናቸው። በኤችአይቪ መያዝን ልንቆጣጠረው ወይም ኤችአይቪ/ኤድስን መከላከል እንችላለን። መጠነኛ ጥንቃቄዎችን በማድረግ ከፍተኛ ተገላጭ ነት ያላቸው እንኳ የመጋለጥ አደጋውን መቀነስ ይችላሉ። የኤች አይቪ ትርጉም H– HUMAN- በሰው ዘር ላይ ብቻ የሚታይ I– IMMUNO DEFICIENCY በተፈጥሮ በሽታን መከላከል የሚችለውን ኃይል ነጭ የደም ሴሎችን የሚያደክም V- በዓይን የማይታይ ረቂቅ ህዋስ በሰው የደም ሴሎች የሚራባና የሰዎች አካል የሆኑትን ሴሎች የሚበክል የኤድስ ትርጉም A-Acquired- ከሌላ ሰው የተገኘ I- Immune Deficiency- በተፈጥሮ በሽታን የሚከላከል ነጭ የደም ሴልን የሚያዳክም S-Syndrome የበሽታዎች ስብስብ/ምልክቶች 45 ኤች አይ ቪ የማይተላለፍባቸው መንገዶች ኤችአይ ቪ በዓይን የማይታይ ተህዋስ ነው። ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች በህብረተሰቡ ውስ ጥ በሚያደርጉት የዕለት ተዕለት ማህበራዊ ግንኙነቶችና ንክኪዎች ምንም ዓይነት ስጋት ሊፈጥሩበት አይ ገባም። ቫይረሱ ወይም በህዋሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር በምናደርገው ዕለታዊ ግንኙነት ማለት በመጨባበጥ፣ ለሰላምታ በመተቃቀፍ፣ አብሮ በመቀመጥና በመጫወት፣ መፀዳጃ ቤትና መታጠቢያ ቤት አብሮ በመጠቀ ም፣ አብሮ በመመገብ፣ የመመገቢያ እቃዎች አብሮ በመጠቀም፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው መደብር በተገዛ ምግብ፣ በልብስ፣ በማስነጠስ ወይም በማሳል እንዲሁም በተባይ ንክሻ አይተላለፍም ። መድኃኒት ያልተገኘለት ምንም ዓይነት ባህላዊ ይሁን ሳይንሳዊ መድኃኒት ለኤች አይ ቪና ለኤድስ አልተገኘም። ይሁንና በኤች አይ ቪ የተያዙ ሰዎ ች በሽታው ወደ መጨረሻ ደረጃ ወደ ኤድስ ቶሎ እንዳይደርስ ና እንዲዘገይ እንዲሁም ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከኤድስ ተፀ ዕኖ ላለማጋለጥ ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች አሉ። በኤች አይ ቪ/ኤድስ ዘመን ሰዎች ምን ዓይነት ኃላፊነት ሊሰማቸው ይገባል? ለራስ ኃላፊነት መውሰድ፡- በኤች አይ ቪ መያዝ አለመያዝ ምንም ዓይነ ት ምልክት የሌለው ስለሆነ የኤች አይ ቪ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው የ ራሱን ወይም የራሷን ሁኔታ መረዳት የሚቻለው። ፈጥኖ በበሽታው መያ ዝን ማወቅ በሽታውን ለሌላ ሰው ላለማዛመትና ሌሎች ወገኖችን ለመጠበቅ ማስቻል ብቻ ሳይሆን የራሷን ወይም የራሱን የአናኗር ዘዴ ለማሻሻል ያስችላል። ከኤች አይ ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ራሳቸውን ጤናማ አድርገው መቆ የት እንዲችሉ ጭንቀትን ማስወገድ፣ ዕረፍት ማድረግ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መንቀሳቀስ፣ የአመጋገብ ሁኔታን ማሻሻል፣ ሲጋራ አለማጨስ፣ ከአልኮልና ከአደንዛዥ እፅ መራቅና የግል ንጽህናቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ጥ ንቃቄ የጐደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት በማድረግ ራሳቸውን በተደጋጋሚ ለበሽታው ከማጋለጥ መቆጠብ አለባቸው። በኤችአይቪ በተያዙ ሰዎች መሃልም ቢሆን ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል። በተደጋጋሚ ለቫይረሱ መጋለጥ በሽታውን አባብሶ ወደ ኤድስ ሊያደርሰው ስለሚችል። ስለሌሎች ኃላፊነትን መውሰድ፡- በኤች አይ ቪ የተያዙ ሰዎች ሌሎች ሰዎች ከደማቸውና ከሰውነታቸው ከሚወ ጣ ፈሳሽ ጋር ንኪኪ እንዳይኖረውና ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው። በ ኤችአይቪ ከተያዘ ሰው ጋር አብረው የሚኖሩ ወይም አብረው የሚሰሩ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለተለያዩ በሽታ ዎች እንዳይጋለጡ (ለጉንፋን፣ ለተስቦና ሌሎች በሽታ አምጪ ተህዋስያን) ጥንቃቄ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ከኤ ች አይ ቪ/ኤድስ ጋር አብሮ የሚኖሩ ሰዎች ድጋፍን፣ ማበረታታትንና ክብርን ይፈልጋሉ። በህብረተሰቡ ሊገለል ወይም መድሎ ሊፈፀምባቸው አይገባም። ለመከላከል የሚጠቅሙ ሦስቱ የ’’መ’’ ህጎች መ- መታቀብ፡- የግብረ ስጋ ግንኙነት አለማድረግ መ- መወሰን፡- ባንድ ከበሽታው ነፃ በሆነ/ች/ ጓደኛ መወሰንና መተማመን መ- መጠቀም፡- ምንጊዜም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶም መጠቀም 46 በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የምክርና የደም ምርመራ አገልግሎት አንድ ሰው ኤች አይ ቪ እንዳለበትና እንደሌለበት በእርግጠኝነት ሊያውቅ የሚችለው ምርመራ ሲያደርግ ብቻ ነው። ምርመራው በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ምክር አገልግሎት ከመስጠት ጋር መጎዳኘት ይገባዋል። 1ኛ. ስለምርመራው በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ 2ኛ. የምርመራ ውጤታቸው ነፃ ከሆነ ለወደፊቱ እንዴት በጥንቃቄ መኖር እንደሚገባቸው ለማሳወቅ፣ 3ኛ. የምርመራ ውጤታቸው በበሽታው መያዛቸውን የሚያ መለክት ከሆነ በበሽታው የተያዘ ሰው እንዴት ለሌሎች ሰዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት፣ እንዲሁም ለራሳቸው ሊያደርጉ ስለሚገባ ጥንቃቄና የህክምና አማራጮች ለማሳወቅ። የበሽታው የዕድገት በግለሰብና በቤተሰብ ውስጥ ምን ይመስላል? ግለሰብ በበሽታው በመያዝና በመሞት መሃከል ሦስት ደረጃዎችን ያልፋል(የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት በሌለበ ት)። እነዚህ ደረጃዎች ከ8 እስከ 10 ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ሊራዘሙ ይችላሉ። ደረጃዎች ከታች ተዘርዝረዋል። ስ ዕላዊ መግለጫም አለው እነሱም፡- በኤች አይ ቪ መያዝ ግን አለመጠቃት፡-- አንድ ግለሰብ በኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ ከተያዘ በኋላ ምንም ዓይነት የበሽተኛነት ስሜት ሳይታይበት ለረጅም ጊዜ ጤናማና ጠንካራ መስሎ ሊቆይ ይችላል። ይህ ደረጃ ቫይረሱን ከማዛመት አኳያ በጣም አደገኛ ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ ደረጃ ላይ ያሉ ግለሰቦች በቫይረሱ መያ ዛቸውን ስለማያውቁ ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት በማድረግና ስለታማ ነገሮችን በጋራ በመጠ ቀም በቀላሉ በሽታውን ያዛምታሉ። ስለዚህም ይህ ደረጃ ቫይረሱን ከማዛመት አኳያ አደገኛ ጊዜ ነው ማለ ት ነው። ጥሩ አመጋገብና ሕክምና የሚያገኙ ደግሞ ቫይረሱ የሰውነት የመከላከል ኃይልን ቶሎ እንዳያዳ ክም ስለሚያደርገው ምንም ምልክት ሳይታይ ከስድስት እስከ ስምንት ዓመት ድረስ መቆየት ይቻላል። በኤች አይ ቪ መያዝና መጠቃት፡-- በዚህ ደረጃ በኤችአይቪ በተያዘ ሰው ሰውነት የመከላከል አቅም መ ዳከምን ተገን አድርገው ከሚነሱ የተለያዩ በሽታዎች፣ እንደ ሳንባ ነቀርሳ፣ የሳንባ ምችና በተሐዋሲያን በ ሚመጡ በሽታዎች መታመም ይጀምራል፣ ህመሙም እየተመላለሰ በመጣ ቁጥር በሽተኛው ከፍተኛ የድ ካም ስሜት ውስጥ ይወድቃል። ሆኖም ሕክምና በመውሰድ አንዳንድ ከኤድስ ጋር የተዛመዱ በሽታዎችን መከላከል ወይም ማዳን ይቻላል። ከዚህም የተነሳ የቤተሰቡ አባላት ጉልበትና ጊዜ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቡ ጥሪትም በሽተኛውን ለማስታመም ይውላል። ምንም እንኳን እንደሰውነት አቋሙ ቢለያይም በአብዛኛው አንድ ጊዜ በሽተኛው ሙሉ በሙሉ ወደ ኤድስ ደረጃ ከደረሰ የመኖር ተስፋው ከሁለት እስከ ሦስት ዓመ ት ብቻ ነው፤ የፀረ ኤድስ መከላከያ መድሐኒት ካልተወሰደ በስተቀር። በኤድስ ምክንያት መሞትና በቤተሰብ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ፡-- በበሽታው የተያዘ የቤተሰብ አባል ሲሞት የቤተሰቡ አባሎች በቀብርና ሀዘን በመቀመጥ ጊዜ ከማባከኑ ባሻገር የሚያስከትለው ወጪ የቤተሰ ቡን ገቢ ያመነምናል። ከዚህም በላይ ሟች ሚስት/ባል ካላቸው ቀሪው ግለሰብ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ በ በሽታው የመጠቃቱ ጉዳይ አይቀሬ ነው። በሌሎች የቤተሰብ አባላትም ካንዱ ወደ አንዱ እየተላለፈ የኤ ድስ ታማሚና ተጠቂ በመሆን ሴተሰቡ ለረጅም ጊዜ የኤድስ ተጠቂ ይሆናል። ብዙ ቤተሰቦች በተለይ የ ዋና የቤተሰብ አባልን ሞት ለመቋቋም ከፍተኛ ጥረት ይጠብቃቸዋል። የውርሱ ጉዳይም በዘመዶች መሃ ል የመናጠቅ ያህል በሆነበት ማህበረሰብ ውስጥ ደግሞ እንግልቱ ይበዛል። 47 ስዕል 1፡ የግለሰብ የኤችአይ ቪ/ኤድስ የጊዜ ቀመር መገለል ለምን አደገኛና ጎጂ ሊሆን ቻለ? የኤድስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች ብዙ ባልታወቀበትና የተሳሳተ አመለካከትና የተሳሳተ አረዳድ ባለበት በገጠሩ ህብረተሰብ ውስጥ ማግለል በጣም የተለመደ ነው። የየዕለት የተለመዱ እንቅስቃሴዎች የበሽታው መተላለፊያ ዘዴ ዎች ባይሆኑም እንኳን ሰዎች ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር አብሮ ከሚኖሩት ሰዎች ጋር ማንኛውንም አይነት ንኪኪ ማ ድረግ ይፈራሉ። መገለል በበሽታው ለተያዘ ሰው ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቡና በጥቅሉ ደግሞ ለማህበረሰቡ አደገኛ ው ጤት አለው። በበሽታው ተይዘው ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች የኤች አይ ቪ ምርመራ ለማድረግና ያሉበትን ደረጃ ለ ማወቅ ያቅማማሉ። በዚህም ምክንያት በሽታው እየተስፋፋ መሄዱን ይቀጠላል፡፡ ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር አብሮ የ ሚኖሩ ሰዎችም ተገቢውን ህክምና ሳያገኙ ይቀራሉ። ይህን ዝምታና በበሽታው ዙሪያ ያለንን ሚስጥራዊነት በመ ስበር ግልጽነትን በመጨመር፣ ማግለልን በመቀነስና በበሽታው ለተያዙና ለተጠቁ ወንዶችና ሴቶች የተቻለንን ድ ጋፍ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው። በመስክ ሥራ ላይ መድሎና መገለል የማስወገድ ቅምሻ፡- ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር አብሮ ለሚኖር ሰው ወይም ለቤተሰቡ በዘዴ ቅርባቸው/ቅረቢያቸው፣ • ሊያስቀይማቸው ወይም ሊጎዳቸው ከሚችል ቋንቋና ባህሪ ታቀብ/ታቀቢ፣• ከሌሎችም ጋር ከሚያገሉና መድሎአዊ ከሆኑ ድርጊቶች ተቆጠብ/ቢ፣ • በማህበረሰብ ውይይት ወቅት ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩትን ቀላቅላቸው/ቀላቅያቸው፣• የአካባቢ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ባለሞያዎችን በማህበረሰብ ውይይት ጊዜ ድጋፍ እንዲያደርጉልህ• ጠይቅ/ቂ፣ ማህበረሰቡ ስለበሽታው ያለውን መሠረታዊ ግንዛቤ አዳብር፣• ኤድስ ያስከተለው ሞት በኤችአይቪ መያዝ በተለያዩ የኤድስ ተዛማጅ በሽታዎች መጠቃት 6 - 8 ዓመት 2 - 3 ዓመት 48 የተዘጋጀ ጽሑፍ 4፡- በገጠሩ ማኅበረሰብ ውስጥ የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና ይህ ጽሑፍ የኤች አይ ቪ/ኤድስን ትንተና መሠረታዊ ፅንስ ሀሳቦችን ያስተቃውቃል። በግለሰብ ደረጃም ይሁን በ ማኅበረሰብ ደረጃ በኤች አይ ቪ የመያዝ ምንጭ የሆኑትን ይዳስሳል፤ እንዲሁም የኤድስ ተፅዕኖ ተቋሚያችን ይ ለያል። የኤችአይቪ ትንተና ለምን አስፈለገ? ብዙ ሰዎች ስለኤችአይቪ/ኤድስ ወረርሽኝ በስራቸው ላይ አንድ ነገር ማድረግ ይፈልጋሉ? ነገር ግን ምን መሠራት እንዳለባቸው ግልፅ አይሆንላቸውም። በግብርና ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ተገቢውን ምላሽ ለኤችአይቪ/ኤድስ ለመ ስጠት በማኅበረሰቡ ውስጥ የወረርሽኙ ደረጃ ጋር የተዛመደ መሆን ይኖርበታል። ስለኤችአይቪ/ኤድስ የሚገልፅ ም ንም መረጃ በሌለበት ሁኔታ በገጠሩ ባብዛኛው ክፍል አሁን ባለበት ደረጃ የሚከተሉትን መለየት ያስፈልጋል፡- የገጠሩ ህብረተሰብ ለኤችአይቪ የመጋለጥ አደጋው ምን ያህል እንደሆነ፣ • ማህበረሰቡ ቀድሞውኑ በኤድስ ተፅዕኖ ሥር የወደቀ መሆኑን መለየት፣• የግለሰብ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ማለፊያ በሮች የማኅበረሰብ የስጋት ምንጭ ከማየታችን በፊት ኤች አይ ቪ/ኤድስ በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚመስል መመርመር ጠቃሚ ነው። ይህ የኤችአይቪ ማለፊያ በሮች በሚለው የስዕል መግለጫ (ስዕል1) ሊወክል ይችላል። ማለፊያ በሮ ቹ የግለሰብ የመያዝ አደጋን ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ የሚያደርጉት ምን ምን እንደሆኑ ወይም ለኤድስ ተፅዕኖ ተ ጋላጭነትን ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ የሚያደርጉ ምን ምን እንደሆኑ እንድናውቅ ይረዳናል። ማለፊያ መንገዱ ሦስት በሮች አሉት፡- በር 1፡ - በኤችአይቪ መያዝ (“የኤችአይቪ መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳብ መረዳት” የሚለውን ጽሑፍ ተመልከ• ት/ቺ/ – ዋነኛ የመያዝ ምንጭ የሆኑትን ተመልከት/ቺ)፣ በር 2፡ - ከኤድስ ጋር የተዛመዱ በሽታዎች (የኤችአይቪ መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች የሚለውን ጽሑፍ ተመል• ከት/ቺ/ – ለአይነተኛ ምልክቶች፣ ስር የሰደዱ በሽታዎች፣ ክብደት መቀነስ ተመልክት/ቺ)፣ በር 3፡- ከኤድስ ጋር የተዛመደ ሞት፣• 49 ስዕል 1፡ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ማለፊያ መንገድ የፀረ-ኤች አይ ቪ/ኤድስ መድኃኒትን ጨምሮ ምንም ዓይነት እንክብካቤና ህክምና በሌለበት በበሮቹ መሃል ለማለ ፍ የሚከተለውን ጊዜ ይወስዳል። ከበር 1 እስከ በር2 በአማካይ ከ6 እስከ 8 ዓመት • ከበር 2 እስከ በር3 በአማካይ ከ1 እስከ 2 ዓመት• የማዘግያ እድሎች የጊዜ መስጫአንቀሳቃሾች በኤችአይቪ ኤድስ የመያዝ አደጋን የመቀነስ በኤች አይ ቪ የመያዝ ምንጭ በር 1፡ በኤች አይ ቪ መያዝ ከ6-8 ዓመት በበሽታው መጠቃትን ለማዘግየት ከኤድስ ጋር የተዛመዱ በሽታዎችና ሞትን የሚያፋጥኑ ምክንያቶች በር 3፡ ከኤድስ ጋር የተዛመደ ሞት በር 2፡ ከኤድስ ጋር የተዛመዱ በሽ ታዎች ከ1-2 ዓመትየቀሩትን የቤተሰብ አባላት ኤ ድስ ባስከተለው ሞት በተዕፅኖ የሚያጋልጡ ምክንያቶች ጥቃቱን ለመቋቋም የተቀሩት ማለፍ ይቀጥላሉ 50 በበር 1 መግባት ሊቀለብሱት ወይም ሊመልሱት አይቻልም። የግድ ወደፊት አንድ ቀን ወደ በር 2 እና 3 ያደር ሳል ምንም እንኳን ጉዞው ከ6-10 ዓመት የሚወስድ ቢሆንም (ፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት ከተወሰደ ሊበልጥ ይ ችላል) ግለሰቦች በተላላፊ መንገዱ የሚያልፉበት እንዲሁም ጉዞውን የሚጨርሱበት ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች ላ ይ ተመረኮዘ ነው። የበሽታው አንቀሳቀሽ እነማን ናቸው? ሦስት ዓይነት አንቀሳቃሽ ቡድኖች አሉ፡- ሰዎችን በኤችአይቪ መያዝ አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ምክንያቶች (በአብዛኛው በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ጥ• ንቃቄ የጎደለው ግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ) እንደ ድህነት፣ ከቦታ ቦታ መዘዋወር፣ ከቤተሰብ መፈናቀ ል፣ ብቸኝነት፣ ከመጠን በላይ አልኮል መውሰድና ባህላዊ ድርጊቶች የመሳሰሉት፣ በሽታውን ወደ ኤድስ ደረጃ እንዲደርስ ማለትም በኤድስ ተዛማጅ በሽታዎች ወደ መታመም ወይም ወደ • ሞት የሚያፋጥኑ ምክንያቶች – መላልሶ በቫይረሱ መያዝ፣ የቤተሰቡ ስብጥር ዓይነት፣ አነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለ ቤተሰብ፣ ውስን የአኗኗር ዘዴ፣ መድሎዎና መገለል የመሳሰሉት፣ ኤድስ በሚያስከትለው ሞት የቀሩት ቤተሰቦችን ለኤድስ ተፅዕኖ ጥቃት መጋለጥን የሚያባብሱ ምክንያቶ• ች – እንደ ቤተሰቡን ለመምራት የቀረው ሰው ፆታና እድሜ፣ የቤተሰብ ስብጥር ዓይነት፣ የቤተሰቡን የ ንብረት/የሀብት ደረጃ፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ውስን ያኗኗር ዘዴ፣ ወረርሽኞችን ለመከላከል ምን ዓይነት ጥሩ አጋጣሚዎች አሉ? ኤችአይቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገው እንቅስቃሴ ዋናው ምክንያት ከሚከተሉት አንዱን ለመ ፈፀም ነው። ስለኤችአይቪ/ኤድስ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግና በማሳወቅ ሰዎች የአኗኗር ዘዴዎችን በማሻሻል በበር 1 • እንዳይገቡና በበሽታው እንዳይያዙ ለማድረግ፤ የባህሪ ለውጥ ማምጣት፣ የሕክምና አገልግሎቶችን ማሻሻ ል፤ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን በመታከም፣ ኮንዶም መጠቀም፣ በበሽታው የተያዘ ሰው ወደ በር 2 የሚያደርገውን ጉዞ ለማዘግየት ከኤድስ ጋር የተያያዙ በሽታዎችና • ሞት እንዳያገኘው የባህሪ ለውጥ እንዲያመጣ ማድረግ፣ የአመጋገብ ስርዓቱን ማሻሻል፣ ጉልበት ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ማሳየት፣ ደህንነት አጠባበቅ ዘዴ ማስተማር፣ የጤና አገልግሎት መስጠት፣ ፀረ- ኤችአ ይቪ መድኃኒት የሚያገኝበትን መንገድ ማመቻቸትና በማህበረሰቡ ሴፍቲ ኔት እንዲታቀፍ ማድረግ፣ ቁልፍ የቤተሰብ አባል በሞት ከተለየ በኋላ (ከበር 3 በኋላ) ቀሪው የቤተሰብ አባላት ኑሮአቸውን እንዲያ• ስተካክሉ ንብረታቸውን መጠቀም እንዲችሉና እንዲቆጣጠሩ ማድረግ፣ የአኗኗር ዘዴያቸውን ማሻሻል እነ ዲችሉ ማድረግ የማህበረሰቡን ሴፍቲ ኔት ማጠናከር፣ የኤችአይቪ ማለፊያ መንገዱን በመጠቀም ኤችአይቪ/ኤድስን እንዴት በሥርዓተ ፆታ ለመተንተን መጠቀም እን ችላለን? የሴቶችና የወንዶችን የመጋለጥ ልዩነት ለመረዳት የኤችአይቪ ማለፊያ መንገዱን መጠቀም እንችላለን፡- ሴቶች በተፈጥሯዊ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በባህላዊ በሆኑ ምክንያቶች የበለጠ በበሽታው የመያዝ • አደጋ ውስጥ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ የመያዝ አደጋውን ሊቀንሱላቸው የሚችሉ ነገሮችን የማግኘት እድላቸውም ጠባብ ነው (የመረጃ ምንጮችን፣ የኢኮኖሚ አቅማቸው፣ጥንቃቄ ላለው ግንኙነት የመደራደ ር አቅም፣ ኮንዶም የመጠቀም) ሴቶች ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ለተዛመዱና ለሚያባብሱ በሽታዎች የበለጠ የመጋለጥ አዝማሚያ አላቸ• ው። ምክንያቱም ሕክምና የማግኘት እድላቸው በጣም የተወሰነ ስለሆነ በተለይ ጥሬ ገንዘብ የሚያስፈል ግ ከሆነ እንዲሁም ደግሞ ከኤድስ ጋር የሚኖሩትን የመንከባከብ ሥራ ስለሚሠሩ ሴቶች የበለጠ አደጋ ውስጥ ናቸው። በተለይ ደግሞ ጥንቃቄ የተሞላበት የእንክብካቤ ተግባሮችን ጠንቅቀው ካላወቁ፣ ሴቶች ለትዳር አጋራቸው ሞት ተፅዕኖ በጣም የተጋለጡ ናቸው። በተለይ ደግሞ ንብረቱ በበሽታው ዘመ• ን ከተሟጠጠ ወይም በዘመዶች ከተዘረፈ፡፡ ሴቶች ተገቢው ስልጠና ካልተሰጣቸውና የገቢ ምንጭ እንዲ ያገኙ የማድረግ እድል ካላገኙ የቤተሰቡ ኑሮ ከፍተኛ አደጋ ላይ ይወድቃል። 51 የኤችአይቪ ማለፊያ መንገዱ የሴቶችን የመያዝ አደጋና ለበሽታው ተፅዕኖ የመጋለጥ እድሎችን የሚቀንሱ ሁኔታዎ ችን ለማወቅም ልንጠቀምበት እንችላለን። ህብረተሰቡ የሚያልፍባቸው የበሽታው ደረጃዎች ምን ምን ናቸው? ኤድስ ሲጀምር፡-• የኤችአይቪ/ኤድስ መኖር በጣም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ነገር ግን በቅርቡእያደገ እንደ ሚሄድ ይጠበቃል። ምክንያቱም ከፍተኛ የስጋት አካባቢዎች የሆኑ በመኖራቸውና አሽጋጋሪ ድልድይ የሆኑ የ ማህበረሰብ ክፍሎች ስላሉ፣ ኤድስ ሲያጠቃ፡-• የኤችአይቪ/ኤድስ መኖር በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል(መረጃዎች እንደሚያመለክቱትና በግል ፅም የሚታይ ነው) ነገር ግን ማህበረሰቡ ገና ከኤድስ ጋር ተዛማጅነት ባላቸው በሽታዎችና ሞት ሲጠቃ አይ ታይም፣ የኤድስ ተፅዕኖ፡-• የኤችአይቪ መኖር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡ ማህበረሰቦችና ቤተሰቦች ከኤድስ ጋር ተያያ ዥነት ባላቸው በሽታዎችና ሞት ይጠቃል፡፡ በኤድስ ተፅዕኖ ስርም ይወድቃል፡፡ እነዚህ ደረጃዎች ከኤችአይቪ/ኤድስ ማለፊያ መንገዶች ጋር ማነፃፀር ይቻላል። ማህበረሰቡ ኤድስ ሲጀምር የሚለ ው ደረጃ ላይ የሚገኝ ከሆነ ብዙ አባላቱ ከበር 1 ፊት ለፊት ናቸው ማለት ነው። ኤድስ ሲያጠቃ የሚለው ደረጃ ላ ይ ከሆኑ የተወሰነው ህብረተሰብ ክፍል በበሽታው ተይዟል ስለዚህ ወደ በር 2 እያዘገመ ነው። ከኤድስ ጋር በተያያ ዘ ብዙ ሰዎች የሚሞቱ ከሆነ ማህበረሰቡ በር3 ተሻግሮ ከኋላው ይገኛል ማለት ነው። ማህበረሰቡ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እንዴት ልናውቅ እንችላለን? በኤችአይቪ/ኤድስ የመያዝ ስጋትና የተጋላጭነት ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉትን በመለየት ህብረተሰቡ1. የሚገኝበትን ሁኔታ በመረዳት፣ የኤድስ ተፅዕኖ ጠቋሚዎችን በመለየት ማህበረሰቡ በኤድስ ተፅዕኖ ስር መውደቅ አለመውደቁን2. በመረዳት፣ በገጠሩ ማህበረሰብ ውስጥ የኤችአይቪ መያዝ አደጋ ምንጮች ምንድናቸው? በገጠሩ ማህበረሰብ ሦስት የመያዝ አደጋ ምንጮች አሉ በያንዳንዱ ወረዳ ዙሪያ የኤችአይቪ/ኤድስ አደገኛ አካባቢ የመሆን አቅም ያላቸው ቦታዎች ወይም• ሰዎች በብዛት የሚዘዋወሩበትና ለኤድሰ ተጋላጭ የሚያደርጉ ቦታዎች መኖር፣ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው አስተላላፊ ድልድይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ዝቅተኛ ደረጃ• ተጋላጭነት ካላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የሚያደርጉት ተደጋጋሚ ግንኙነትና አንዴ በሽታው በገጠሩ ማህበረሰብ ውስጥ ከገባ የበሽታውን ስርጭት የሚያፋጥኑ ባህላዊ ልማዶች• ድርጊቶች ናቸው። የነዚህ ሦስት ነጥቦች የርስበርስና ከገጠሩ ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ተያያዥነት በስዕል 2 ተመልክቷል። በግብርና ም ርትና ገበያ ሥራ ውስጥም ያለውን የተጋላጭነት አደጋ ግንዛቤ መውሰድም አስፈላጊ መሆኑን አለመዘንጋት ነው። 52 የገጠሩ ማህበረሰብ ስዕል 2. በገጠሩ ማህበረሰብ የርስ በርስና ከከተማው ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች የኤች አይ ቪ የስጋት አካባቢዎች ምንድን ናቸው? የኤች አይ ቪ የስጋት አካባቢዎች በከተሞች ብቻ የተወሰነ ጉዳይ አይደለም፡፡ በገጠሩ ማህበረሰብ ውስጥም ይገኛ ል። ከተለያዩ ቦታዎች የተሰባሰቡና የተወሰነ ጊዜ ያለተጓዳኝ ብቻቸውን ከቤታቸው ውጭ የሚያሳልፉ ሰዎች የሚ ገኙበት ቦታ አንዱ ሲሆን አንዳንድ ለኤድስ ተጋላጭ የሚየደርጉ ቦታዎች በሁሉም ወረዳዎች ይገኛሉ፤ለምሳሌ የ አስተዳደር ተቋማት የሚገኙበት ማዕከሎች፣ የንግድ ቦታዎችና የገበያ ስፍራዎች፣ ኮሌጆችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህ ርት ቤቶች፣ የቅጥር ማዕከሎች የመሳሰሉትም የስጋት አካባቢዎች ናቸው፡፡ ሌሎች የስጋት ቦታዎች ደግሞ አካባ ቢያቸው ባሉት ሁኔታዎች የተመረኮዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ዋናው መንገድ ላይና ባቡር ጣቢያዎች፣ የተወሰነ የግንባ ታ ስፍራና፣ ሰፋፊ እርሻዎች፣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ አስተላላፊ ድልድዮች የህብረተሰብ ክፍሎች እነማን ናቸው? ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ያለውን የገጠር አካባቢን ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ካለው ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኙ ሦስት አ ይነት አስተላላፊ ድልድዮች አሉ። (ስዕል 2 ይመልከቱ) በሥራ ምክንያት፣ በትምህርት ወይም ሌላ ማህበራዊ ጉዳይ የገጠሩን ማህበረሰብ ከፍተኛ የስጋት አካባቢ • ከሆኑ ከከተማው ጋር የሚያገናኙ ጎልማሶችና ወጣቶች ናቸው። እነዚህ ተግባሮች ከቤትና ከማህበረሰቡ ደ ንቦች ርቆ ሄዶ ማከናወን ስላለበትና ብቸኝነትና ከማህበረሰቡ ዕይታ ውጭ በመሆናቸው አንዳንድ ያልተለ መዱ ተግባሮችን ለመፈፀም ይገፋፋሉ፣ ቫይረሱን ሊሸከሙ የሚችሉ ከውጭ ወደገጠሩ የሚገቡ ሰዎች– እነዚህ ለሥራ ወደገጠሩ የሚመጡ ባለ• ሙያዎችና አብዛኛውን ጊዜ ብቻቸውን የሚኖሩ፣ ወቅታዊ ሥራ ለመስራት የሚመጡ የቀን ሠራተኞች፣ የፖለቲካ ሰዎች፣ ወታደሮች፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ የግንባታ ሠራተኞች፣ አጓጓዦች፣ ነጋዴዎች፣ ከብት አ ርቢዎች፣ ዘመዶች፣ ጎብኚዎች፣ ስደተኞች፣ ተፈናቃዮችና ሰፋሪዎች ናቸው፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥና ጎረቤት ማህበረሰቦች መሃል ለዕለት ተዕለት ሥራ፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ወይ• ም ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች፣ የኤችአይቪ መስፋፋትን የሚያግዙ ምን ምን ባህሎች፣ ደንቦችና ባህላዊ ድርጊቶች ናቸው? አንዴ ቫይረሱ በገጠሩ ማህበረሰብ ውስጥ ከገባ ባህላዊ ድርጊቶችና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች የበሽታውን በሰዎች መሃል መስፋፋት ሊያ በየጎረቤት ማህበረሰቡ መሃል የሚመላለሱ ሰዎች ከፍተኛ ተጋላጭነት ካላቸው አካባቢዎች ወደ ገጠሩ ማህበረሰብ የሚገቡ ሰዎች ከገጠሩ ወደ ከፍተኛ ተጋላጭነት ወዳለው ወደ ከተማ የሚመላለሱና ከገጠሩ ማህበረተሰብ ጋር የሚገናኙ ሰዎች በወረዳው ለኤድስ ተጋላጭ የማያደርጉ ቦታዎች በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ ባሕላዊና ማህበራዊ ድርጊቶች 53 ግዙ ይችላሉ። እነዚህ ባህላዊ ልማዶች ሰዎች በኤችአይቪ የመጠቃታቸው አደጋ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ከቦታ ቦታ ና ከባህል ባህልና በየማህበረሰቡ መሃል ይለያያሉ። እንደሚከተለው ሊመደቡ ይችላሉ፡- ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም፤ የጋብቻ ሁኔታዎች፣ ብዙ • ወዳጅ ማበጀት፣ ብዙ ማግባት፣ ጠለፋ፣ የኮንዶም አጠቃቀም፣ ጫት መቃምና አልኮል መውሰድ፣ ፈት ማግባት ወይም መውረስ፣ የግንዛቤ እጥረት፣ ኮንዶምን በብቃት አለመጠቀም፣ ከተያዘ ሰው የሚወጡ የሰውነት ፈሳሾች ጋር መነካካት፤ ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶች፣ ስለበሽታው የግንዛቤ እ• ጥረት መኖርና ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍ፣ የግንዛቤ እጥረት፣ ተገቢ ህክምና ወይም የመድሃኒት አገልግሎት አለማግ• ኘት፣ ማህበረሰቡ በኤድስ ጥቃት ተፅዕኖ ስር መሆኑን ጠቋሚዎች ምን ምን ናቸው? በብዙ የገጠሩ ማህበረሰብ ውስጥ መስራትን አስቸጋሪ ከሚያደርጉ ጉዳዮች አንዱ የኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ አናሳ መሆን ነው። በማህበረሰቡ ውስጥ ከኤድስ ጋር የተዛመዱ በሽታዎችና ሞትን በተመለከተ የተፃፈ መረጃ በሌለበ ት ሁኔታ ማህበረሰቡ ምን ያህል በኤድስ እንደተጠቃና በተፅዕኖ ሥር እንዳለ ለማወቅ ጉዳቱ እንደደረሰባቸው ሊ ያሳውቁ የሚችሉ ሌሎች ወኪል አማራጮችንና ምልክቶችን መፈለግ ይኖርብናል። እነዚህ ለውጦች ደግሞ ከኤድ ስ ሌላ ምክንያቶችንም ሊያሳዩ እንደሚችሉ ማስታወስ ያስፈልጋል። የባህሪ ለውጥ፡- የግብረ ስጋ ግንኙነት ወዳጆችን ቁጥር በመቀነስ ማለትም ከጋብቻ ውጭ ያሉ ግንኙነቶ• ች በመቀነስ፣ ሴተኛ አዳሪዎችን ያለመጠቀምና ከአንድ በላይ ጋብቻን በመተው፣ ፈቶችን ማግባት መተ ው፣ አላስፈላጊ የሆኑ ከቤት ውጭ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች በመተው፣ ምላጮችን አለመጋራት፣ ከጋብቻ በፊት ግብረ ሥጋ ግንኙነት አለማድረግ፣ አንድ ለአንድ መወሰን፣ ቅድመ ጋብቻ የኤችአይቪ/ኤድስ ምር መራ ማድረግ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የቤተሰብ ስብጥር ለውጥ፡- በእማወራ የሚመራ ቤተሰብ ቁጥር መጨመር፣ ወንድ • በብቸኝነት የሚያስተዳድረው ቤተሰብ መብዛት፣ የወላጅ አልባ ሕፃናት ቁጥር ማደግና የአያት ልጅ አሳዳ ጊዎች ቁጥር ማደግ፣ የእርሻ ሥራና የአናኗር ለውጥ፡- የያንዳንዱ ቤተሰብ የታረሰ የመሬት መጠን መቀነስ፣የእዳሪ መሬት መ• ብዛት፣ አነስተኛ የሰው ኃይል ወደሚፈልግ ሥራ ማዘንበል (ለምሳሌ ብዙ ጉልበት በማይጠይቁ የሰብል ወይም የዕርባታ ዘዴዎች)። በቤተሰብ ያለው የሥራ ክፍፍል መለወጥና፣ የሥራ መተጋገዝ ልምዶች መ ለወጥ ከበሽታው ጋር አብሮ ለመራመድ በማህበረሰቡ ምላሽ ላይ ያለ ለውጥ፡- ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር አብሮ ለ• ሚኖር ሰው የሚደረግ እንክብካቤ፣ የሀዘንና የቀብር ባህላዊ ሥነስርዓት ለውጥ በቀረው ቤተሰብ ላይ የ ሚተወውን ሸክም ለመቀነስ፣ ለኤድስ ተፅዕኖ የበለጠ የተጋለጠው ቤተሰብ የትኛው ነው? የበሽታው ተፅዕኖ ከቫይረሱ ጋር አብሮ እንደሚኖረው ሰው ፆታ፣ እድሜ የአኗኗር ዘዴ የቤተሰብ ሀብት መጠን ሊለያይ ይችላል። የቤተሰብ ሀብት መጠን የተባለው የቤተሰቡን አስፈላጊ የሰው ጉልበት፣ የህክምና አገልግሎትና ለምግብ በቂ ገንዘብ ማግኘትን በሚመለከት ነው። ፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒት የማግኘትን ዕድል ማሳደግ፣ የቤት ለ ቤት እንክብካቤና የሲዲ4 ምርመራ ለማድረግ መቻልን ያካትታል። በሴት ወይም በእማወራ የሚመራ ቤተሰብ ለ በሽታው የበለጠ የተጋለጠ ነው። 54 የኤችአይቪ ፒራሚድ አንዴ ማህበረሰቡ ከኤድስ ጋር ተያያዥነት ያለውን ሞትና /ሀ/ መታመም ሲጀምር /ለ/ ይህ የችግሩ ጫፍ ብቻ ነ ው(ስዕል 3) ። በጣም ብዙ የህብረተሰቡ አባል በኤችአይቪ ተይዞ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ገና ምንም ምልክት አያሳይም /ሐ/። ብዙ ቤተሰቦች በተለያ መንገድ ህመምተኞችን ለመንከባከብ፣ ወላጅ አልባ ህፃናትን ለመደገፍ በ ሚባክን ገንዘብ ብዙ የቤተሰብ አባሎች ተጎድተዋል /መ/። በጥቅሉ መላው ማህበረሰብ በጥቃት አደጋ ውስጥ ነ ው/ሠ/ ። ስለዚህም በበሽታው የመያዝ ዕድሉ ዝቅተኛ ቢሆንም እንኳ የችግሩ ስፋት ለመስክ ሥራ ከፍተኛ ፈተ ና እንደሚሆን መገመት አያዳግትም። ስዕል ሦስት፡- የኤችአይቪ/ኤድስ ፒራሚድ ከኤድስ ጋር ተዛማጅ የሆነ ሞት/ሀ/ በኤድስ ተፅዕኖ ስር ያለ ቤተሰብ ከአድስ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ህመሞች/ለ/ በHIV የተያዘ /ሐ/ በHIV/AIDS የተጠቃ/መ/ ከፍተኛ የስጋት ደረጃ /ሠ/ ኤድስ ያነዣበበበት ቤተሰብ ኤድስ የተከሰተበት ኤድስ የተከሰተበት ኤድስ የተከሰተበት 55 የተዘጋጀ ጽሑፍ 5፡- ሴቶች በኤት አይ ቪ/ኤድስ ተጠቂ እንዲሆኑ ይሚያደርጉ ምክንያ ቶችና ተዛማጅነታቸው በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፈው የኤችአይቪ ቫይረስ ከሴት ወደ ወንድ ይልቅ ከወንድ ወደ ሴት የመተላለፍ ዕድሉ በጣም በብዙ እጅ ያመዝናል። ወጣት ሴቶች የማራቢያ አካላቸው ሙሉ ለሙሉ አድጎ ያልዳበረ በመሆኑ ለበሽታው የበለጠ የተጋለጡ ና• ቸው። የውስጥ አካላቸው ስስ ክፍሎች እንደጎለመሱት ሴቶች ጠንካራ ባለመሆኑ የመከላከል አቅሙ ደካ ማ ነው። ወጣት ሴቶችና ልጃገረዶች በባህል ምክንያትም ለኤችአይቪ የተጋለጡ ናቸው። ምክንያቱም ወንዶች ልጅ • እግር ሴቶችን የመምረጥና የማግባት ተለምዶ በመኖሩ፣ ሴቶች በኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና እንዲሁም በስሜታዊ ጉዳዮች ጥምር በወንዶች ላይ ጥገኛ በመሆናቸው • የተነሳ ጥንቃቄ የጎደለው ግብረ ሥጋ ግንኙነትን ላለማድረግ ወይም በጥንቃቄ ለማድረግ መደራደር ይቸ ግራቸዋል። ስለዚህ ሁሉም ሴቶች ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ይርቃሉ ወይም ጥንቃቄ የጎደለውን ግንኙነት እምቢ ይላሉ ማለት አይቻልም፣ ወንዶች ብዙ ሴት ወዳጆችን ማፍራታቸው የተለመደ ነው። ስለዚህ በአንድ ላንድ ጋብቻ የተወሰኑትን ጨ• ምሮ ብዙ ሴቶች ለኤችአይቪ የመጋለጥ አደጋ ላይ ይወድቃሉ ማለት ነው፣ በወንዶችና በሴቶች መካከል ስነ ወሊድን፣ ግብረ ሥጋ ግንኙነትንና ጤና አጠባበቅ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገ• ር ደካማ ግንኙነት በመኖሩ በስነወሊድና ወሲብ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለመስጠት እኩል ኃላፊነት የመሸከም ሁኔታ አለመታየት፣ የሴቶችን የገንዘብ አቅም ያገናዘበ፣ በስፋት የሚገኝ፣ በሴቶች ቁጥጥር ሥር የሆነ የመከላከያ ዘዴ• አለመኖር፣ ሴቶች ለጤና፣ ለትምህርትና ለሥልጠና፣ ለገቢ ምንጭ፣ ንብረት ለማፍራትና ለሕጋዊ መብቶች• ውስን ተደራሽነት ስላላቸው ስለኤችአይቪና ስለኤድስ ሊያገኙት የሚገባቸው ዕውቀት ላይ ተፅዕኖ አለው። ስለዚህም ራሳቸውን ከበሽታው ለመከላከል ያላቸው አቅምም ደካማ ይሆናል፣ እያደጉ የመጡ ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት አዳዲስ የኤችአይቪ ጉዳዮች መነሻዎች ፆታዊ ትንኮሳ መ• ሆኑን ነው። በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታና በሌሎች ማህበራዊ ስፍራዎች በሚደረጉ አ ስገድዶ መድፈርና ፆታዊ ትንኮሳና ያለፈቃድ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር የሚደረግ ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ለበሽታው የመጋለጥ አደጋ ላይ ይቻላል። (በተለይ ለሴቶች በቡጭራና መተሻሸት ምክንያት)፣ ለኤችአይቪ/ኤድስ የመጋለጥ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ወረርሽኙን ለመቋቋም እንክብካቤ ከሚያደርጉት 95% ሴ• ቶች ናቸው፣ ከላይ የተገለፁት ጉዳዮች ፆታን ማዕከል ባየረገ የሥራ ክፍፍል፣ ንብረት መቆጣጠር፣ ማህ በራዊና ባህላዊ ጉዳዮች ተደምሮ ከወጣት ወንዶችና ጎልማሶች ይልቅ ሴቶችና ልጃገረዶች ምን ያህል አስ ቀድው ለበሽታው የተጋለጡ እንደሆኑ ያስረዳሉ። ስለዚህ፡- ኤችአይቪ/ኤድስን በአግባቡ ለመከላከል የሥርዓተ ፆታ ድርሻን የስልጣን ተዛማጅነትንና ሴቶች ማብቃት • የተመለከቱትን ጉዳዮች መታገል ይኖርብናል፡፡ ሴቶች ለዕውቀት ያላቸውን መብት መቀበል ወሳኝ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ከኤችአይቪ መከላከልና ራስ• ዋን ከመጠበቅ አኳያ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫ እንድታደርግና አስፈላጊ እርምጃ እንድትወስድ ስለሚያስችላት፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የግብረ ሥጋ ግንኙነት መተግበር የወንዶች ጉዳዩን መረዳት፣ ተሳታፊነትና መተባበ• ር ይጠይቃል፣ የኤክስቴንሽን ሠራተኞችም ሴቶችን ከወንዶች ተጓዳኞቻቸው ወደ ጤና አገልግሎቶች አብረዋቸው እንዲ• ሄዱና ስለ ሥነ ተራክቦ ጤንነትና ስለስነ ተዋልዶ ጤንነት ጉዳዮች እንዲወያዩ እንዲጠይቁ መገፋፋት አ ለባቸው። 56 የተዘጋጀ ጽሑፍ 6፡- የችግር ምክንያትና ውጤት ትስስር መግለጫ ዛፍ መርሆች የችግር ምክንያትና ውጤት መግለጫ ዛፍ የችግር መተንተኛ መሳሪያ ሆኖ ለመስክ የልማት ሠራተኞችና ለማህ በረሰቡ የሚጠቅም ሲሆን የአንድን ችግር ምክንያቱንና ውጤቱን ለመለየትና ለመመርመር እንዲሁም ተዛማጅነቱ ን ለማወቅ የሚረዳ ነው። ዋና ዋና ምክንያቶችን ለመለየትና ለመተንተን የሚረዳ መሳሪያ ነው። ይህ ደግሞ ችግሩን ለመፍታት ለምንነድፈ ው ስትራቴጂ ወይም ስልት መሠረት ይሆናል። በችግሩ ምክንያት ላይ የሚደረግ ውይይት ከማህበረሰቡ ውስጥ በጣም በችግሩ የተጠቃውን ክፍል ለመለየትና የችግሩን ምክንያቶች ለመቅረፍ በምናደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ለ መካፈል ፍላጎት ያላቸውን ወገኖች ለማግኘት ይረዳል። (የያንዳንዱ ችግር ምክንያት በራሱ ችግር መሆኑንም መ ረዳት ይጠቅማል) ውጤት ችግር ምክንያት ‘ስሙ እንደሚያመለክተው ይህ መሳሪያ ዛፍን ይመስላል። ዛፍ ስሮች በስዕሉ ላይ ከታች በኩል የሚታዩት የዋና ው ችግር ምክንያት ይወክላሉ። በስዕሉ መሃል ላይ ሚገነው የዛፍ ግንድ ዋናው ችግር ነው። ቅርንጫፎቹ በስዕሉ ላይ ከላይ በኩል ያሉት የዋና ችግር ውጤትን ይወክላሉ።’ በጥቅሉ የችግር ምክንያትና ውጤት መግለጫ ዛፍ ዋ ና ዓላማ በህብረተሰብ ውስጥ የሚገኘውን ዋና ችግር በአግባቡ ለመረዳትና ምክንያቶቹን ለይቶ እንደ ችግሩ ክብደ ትና ቅለት ቅደም ተከተል አውጥቶ ውጤታማና ቋሚ መፍትሄ ለማበጀት እንዲረዳን ነው። ምናልባት ይህን ተግ ባር ለመፈፀም እንደ ብቸኛ መሳሪያ የምንጠቀምበትና ማስታወስ የሚገባን አንድ ቃል “ለምን?” የሚለው ነው። ይ ህ አጭር ቃል ምን ዓይነት የሚገርሙ መልሶችን እንደሚያስገኝልንና ችግሩን ለመፍታት ለምንነድፈው የጣልቃ ገብነት ስትራቴጂ እንደሚረዳን ማወቅ ያስፈልጋል። ስለዚህ ምንጊዜም ግልፅ ጉዳይ እንኳ ቢሆን ለምን? ብሎ ከ መጠየቅ ወደኋላ አትበሉ። 57 የተዘጋጀ ጽሑፍ 7፡- በፆታ የተሰበጣጠሩ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚረዱ አሳታፊ መ ሳሪያዎች/ዘዴዎች ይህ መረጃ የቀረበው በሥርዓተ ፆታ ትንተና መረጃ ሰነድ ውስጥ የተገለፀውን የመረጃ መሰብሰቢያ ሰነድ ለመደገፍ ነው። የሀብት ደረጃ ማውጣትና በመጠን ማስቀመጥ (ከሰነድ 1 ጋር ለመጠቀም) የውጭ ሰዎችና የማህበረሰቡ አ ባላት በሀብትና በእኩልነት ጉዳዮች ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። የማህበረሰቡን አመለካከት ጠልቆ መረዳት ወሳኝ ነው። በማህበረሰቡ ውስጥ የተለያዩ ሰዎች (ወንዶች፣ ሴቶች፣ ነጋዴዎች ሠራተኞች) ለሀብት የተለያየ መ ስፈርት ሊያወጡለት ይችላሉ። የሀብት ደረጃ ግን የተመሠረተው የማህበረሰቡ አባላት በመሃከላቸው ውስጥ በሀብ ት ማን ትንሽ የተሻለ ማን በጣም የተሻለና ማን ደሃ እንደሆነ ያውቃሉ የሚለው ግምት ላይ ነው። ይህንን በሌላ ዘዴ ማመሳከርና ውጤቱን ማረጋገጥ ጥሩ ነገር ነው። (ለምሳሌ ቀጥታ በቦታው ተገኝቶ መመልከት)። የዚህ ዓይነቱ የማህበረሰቡ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ዝርዝር መግለጫዎች ለቃለ መጠይቅ፣ የሚመረቡትን ቤተሰቦ ች ትኩረት የሚሰጣቸው ተሳታፊዎችን ለመለየት፣ (ለምሳሌ ድሃ የስልጠና ተወዳዳሪ) የፕሮጀክት ተሳታፊ የሆኑ ቤተሰቦች ተሳታፊ ካልሆኑት በተወሰነ ጊዜ ምን ዓይነት መሻሻል እንዳመጡ ለማወቅ ይረዳል። ከዚህም ሌላ ችግ ሮችን ለመፍታት በሚደረጉ ስትራቴጂዎች ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች፣ የችግር፣ ወይም ሊደረግ ስለሚገባው መፍትሄ እንደየሀብት ደረጃው ለመወያየት ይጠቅማል። በመጠን ማደራጀት፡- አብዘኛውን ጊዜ በሀብት ላይ የተመሠረተ ማህበራዊ ልዩነቶችን ለማወቅ ይጠቅማል። በመጠ ን ማደራጀት የተለያዩ የሀብት ደረጃ ላይ ያሉ ቡድኖችን በመቶኛ ስሌት ለማስቀመጥና የማህበረሰቡ አባላት የየቡ ድኑን ደረጃ ለመለየት ተጠቀሙበትን መስፈርት ለማወቅ ይጠቅማል። በመጠን ለማደራጀት በቅርብ በምናገኛቸው ቁሳቁሶች መጠቀም እንችላለን። ለምሳሌ፡- ባቄላ፣ ጠጠር፣ የዛፍ ፍሬ፣ የመሳሰሉት በኋላ ወደ መቶኛ ማስላት ይ ገባል። ለምሳሌ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉትን የቤተሰቦች ብዛት ለመወከል ሃያ ጠጠር ውሰዱ፡፡ አንድ ፈቃደኛ ተሳ ታፊ ጥራና ሃያውን ጠጠር እንደየቤተሰቡ ሀብት ደረጃ እንዲያከፋፍላቸው አድርግ። ለሌሎች ተሳታፊዎችም በድ ልድሉ ላይ ማስተካከያ ካላቸው ዕድል ይስጣቸው፡፡ ሁሉም ተሳታፊ ወደስምምነት እስከሚመጡ። ወቅታዊ የጊዜ መቁጠሪያ (ከመረጃ ሰነድ 1 ጋር የሚሄድ) የወቅታዊ የጊዜ መቁጠሪያ ዋና ዓላማው የገጠሩ ማህበረሰብ ወንዶችን፣ ሴቶችን ወንዶች ልጆችንና ልጃገረዶችን ጨምሮ በዓመቱ ውስጥ ምን ዓይነት ሥራዎች መቼ እንደሚሰሩ ለማወቅና ችግሮችንም ማለት መቼ መቼ የሥ ራ ጫና እንደሚበዛ ወይም አዳዲስ አሠራሮችን ለማስተዋወቅ የትኛው ጊዜ ተስማሚና ምቹ እንደሆነ ለመለየት ይጠቅማል። ወቅታዊ የጊዜ መቁጠሪያ ለማዘጋጀት የዝናብ ወራት የሚጀምርበትን የመጀመሪያ ወር በካላንደሩ መጀመሪያ ላይ መዝግብ (እንደተለመደው የጊዜ መቁጠሪያ ላይሆን ይችላል) ዋና ዋና የሚመረቱ የሰብልና የእንስሳት ዓይነቶችን መዝግባቸው። መቼ መሬት እንደሚያዘጋጁ፣ እንደሚዘሩ፣ እንደሚያርሙ፣ እንደሚያጭዱ ወራቱን ፃፋቸው። በ እንስሳት ዕርባታ በኩል ሥራው ዓመቱን በሙሉ የሚሠራ ነው ወይስ በየወቅቱ ልዩነቶች ይኖሩታል። በየወቅቱ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ወይም መልካም አጋጣሚዎችን በዓመቱ ውስጥ በየወሩ ያለውን ለውጥ ጭም ር መመዝገብና ማጥናት ያስፈልጋል። ወቅታዊ የጊዜ መቁጠሪያ ሌሎች ተግባራትን እንደ የሰው ጉልበት ፍላጎቶ ች፣ የጤና ችግሮች፣ መኖ አቅርቦት፣ የገቢና የወጪ ሁኔታ፣ የገበያ ዋጋ፣ የፍልሰት ሁኔታዎች ፣ የምግብ አቅ ርቦት፣ የተባይና በሽታ መገኘት የመሳሰሉትን ለማወቅ ሊዘጋጅ ይችላል። ፆታዊ የሥራ ክፍፍልን ወይም በዓመ ቱ ውስጥ የትኛው የህብረተሰብ ክፍል በምን ወራት ሥራ እንደሚበዛበት ወይም እንደሚቦዝንም ለማወቅ ይጠቅ ማል። 58 ወቅቶች/ ተግባራት ወራት ሚያዝያ ግንቦት ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ መስከረም ጥቅምት ህዳር ታህሳስ ጥር የካቲት መጋቢት ዝናብ መሬት ዝግጅት ወ፣ል ወ፣ል ጉልጓሎ ሴ፣ልገ ሴ፣ልገ መዝራት ወ፣ሴል ወ፣ሴል ማረም ሴ፣ልገ ል፣ወ ሴ፣ልገ ል፣ወ ማጨድ/ ማምረት ወ፣ሴ ወ፣ሴ መውቃት መውቂያ አውድማ ማዘጋጀት ል፣ወ ሴ፣ልገ ማስታወሻ፡- ወ= ወንድ፣ ል= ወንድ ልጅ፣ ሴ= ሴት፣ ል= ልጃገረድ 59 የተዘጋጀ ጽሑፍ 8፡- በማህበረሰቡ የሚሰራ ካርታ ዝገጅት ማህበረሰቡ የሚያዘጋጀው ካርታ አሳታፊ የገጠር ግምገማ መረጃ ለማሰባሰብ ከሚረዱት መሳሪያዎች አንዱ ነው። ወደ ሰባት ዓይነት የሚጠጉ ካርታ ዝግጅቶች አሉ። እነሱም መልክአ ምድራዊ፣ የሀብት ምንጭ ማሳያ ካርታ፣ የእርሻ/ይዞታ ንድፍ፣ ታሪካዊ፣ የተፅዕኖ መከታተያ ካርታ፣ ማህበራዊ ካርታ፣ የእንቅስቃሴና ሞዴል ካርታዎች ናቸው። እንደ ምክን ያቱና እንደ ፍላጎቱ አንዱን የካርታ አሠራር መውሰድ ይቻላል። የኤችአይቪ አደጋ አካባቢ ለመለየትና አስተላላፊ ድልድዮች የሆኑ ሰዎችን እንቅስቃሴ ለማሳየት የአካባቢው ሰዎች የራ ሳቸውን አካባቢ፣ ገበሬ ማህበር ወይም ወረዳ ካርታ ማዘጋጀት ይችላሉ። ለማዘጋጀት የሚጠቅሙ መሠረታዊ ነጥቦች፡- የኤችአይቪ አደጋ አካባቢ ካርታ ለማዘጋጀት የሚቀጥሉት ነጥቦች ያስፈልጉ ይሆናል። ዝርዝር ተግባራትን ቀላል በሆነ ዘዴ መንደፍ፣• የሚፈለገው ውጤት እንዲገኝ ትክክለኛውን የሰዎች ስብጥር ተጠቀም፣ • በውይይት ወቅት የሀሳብ መጫን አስወግድ፣ ብዙ ሀሳቦችን እንዲያፈልቁ ጊዜና ዕድል በመስጠት የሚስማሙ• በት ነጥብ ላይ እስኪደርሱ ጠብቅ፣ ተሳታፊነትን እንጂ ትክክለኛነትን ብቻ አጉልተህ አታቅርብ፣ • በአካባቢ ከሚገኙ አንደ አበባ፣ የዘር ፍሬ፣ ቅጠል፣ የተለያየ ቀለም ያለው አፈርና የመሳሰሉትን• በመጠቀም ካርታውን እንዲሰሩ ሰዎችን አበረታታ። የአስተባባሪው/ዋ ድርሻ፡- “ተሳትፎህን ቀንስ/ሺ፣ ተከታተል/ይ፣ ጣልቃ አትግባ/ቢ፣ ወይም አትሞክር/ሪ” አስተባባሪው እዚህ የተገኘው አቅጣጫ ለማስያዝና ስለገጠሩ አካባቢ ለመማር እንጂ ሊያስተምር አይደለም። ምሳሌ፡- “ይህንን አካባቢ ብዙ አላውቀውም። በመንደሩ ውስጥ የሚያልፈውን መንገድ ነው የማውቀው። የመንደሩን ሌ ሎች ቦታዎች ታሳየናለህ? ለምሳሌ ስብሰባ የሚደረገው የትነው ቦታው? እንደነዚህ ዓይነት ትክክለኛውን ለማወቅ የሚጠየቁ ጥያቄዎች የማህበረሰቡን ተሳትፎ ይጨምራሉ ያደፋፍራሉ። በመ ጨረሻም የማህበረሰቡን ካርታ አሁን በሰሩት መንገድ ለምን እንደሰሩት ጠይቃቸው። ከራሳቸው እይታ አንፃር ጉድለት ካለው አስተያየታቸውን እንዲሰጡ አድርግና በተገቢው መንገድ መዝግበው። ሦስትዮሽ፡- የሚቻል ከሆነ የተለያዩ የማህበረሰቡ አባላት (ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አረጋዊያን፣ ህፃናት...) በካርታው ላይ አስተያየታቸው ን እንዲሰጡ አድርግ። የካርታ ሥራ ውሱንነት፡- ጊዜ መውሰዱ፡-• በአብዛኛው የማህበረሰብ ካርታ ሥራ ከታሰበው ጊዜ በላይ ይወስዳል። ነገር ግን ከቡድን ቡድ ን ይለያያል። (የቡሬ ማህበረሰብ አባላት በገበሬ የማህበራቸውን የካርታ ሥራ የኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑት ን ቦታዎች ውይይትና የተለያዩ ተቋማት ማሳየትን በ2 ሰዓት ውስጥ ነው ያጠናቀቁት።) የተማረውን ማሳተፍ፡-• ብዙ ጊዜ በማህበረሰብ ውስጥ ጥቂት ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች መኖራቸው አይቀር ም። እነዚህ ሰዎች ውይይቱን በመቆጣጠር ከሌሎች ተራ ሰዎች (ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ልጆች፣ ግለሰቦች) ሊ ገኝ የሚችለውን ሰፊ ተሳትፎ ጥላ ሊያጠሉበት ይችላሉ። ወደ ትክክለኛነት ማድላት፡- • ካርታው ትክክለኛውን የጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ ዝርዝር ነገሮች፣ ጉብታዎች ለ ማሳየት ሳይሆን አሳታፊ የሆነ ውይይት ለመጫር ነው። ስለዚህ ትክክለኛ የሆነ ውጤት ለማምጣት ሲባል ተ ገቢ ያልሆነ መራቀቅን ማስወገድ ያስፈልጋል። የእውነታው ግልባጭ አለመሆን፡-• ካርታው በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙትን ነገሮች ሁሉ የሚወክል ባለመሆ ኑ መሬት ላይ የሚገኙት እውነታዎች ግልባጭ አይደለም። 60 የተዘጋጀ ጽሑፍ 9፡- ሥርዓተ ፆታንና ኤችአይቪ/ኤድስን እንደዋና ተግባር እንዲወሰድ የማስተባበር/የማሳለጫ ክህሎት የሥርዓተ ፆታና ለኤች አይ ቪ/ኤድስ መረጃ አሰባሰብና አተናተን ውጤታማነት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች ዋ ናው በመስክ ሠራተኛውና በማህበረሰቡ መሃል ሊኖር ሚገባው የመተማመንና የእርግጠኝነት ደረጃ ነው። ይህ ደ ግሞ ውጤታማ የማስተባበር/የማሳለጫ ሙያን ይጠይቃል። የመስክ ሠራተኞች ውጤታማ ተግባር ለማከናወን ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸውን የመተማመን ደረጃ ከፍ ማድረግ አለባቸው። የመተማመን ደረጃን ከፍ ማድረግ ያስፈለገው መልካም የሥራ ሁኔታና ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር ስለ ሚያደርግ ነው። ይህ በራሱ ጥርጣሬን አስወግዶ የወደፊት ሥራን ያቀላል። መተማመንን ለማሳደግ በተለየ ሁኔ ታ አስቸጋሪ ሊያደርግ የሚችለው በመስክ ሠራተኛውና በማህበረሰቡ መካከል የቋንቋ፣ ሃይማኖት ወይም የባህል ልዩነት ሲኖር ነው። በተለይ ደግሞ ከገጠር ሴቶች ጋር መተማመንን ማሳደግ በጣም አስፈላጊ ነው። ሴቶች የወንዶች የበላይነት በሚን ፀባረቅበት ህብረተሰብ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ የተረሱ ናቸው። ሴቶችም ሆኑ ወንዶች መስክ ሠራተኞች ውጤታ ማና ቀረቤታን የፈጠረ መተማመንን በገጠር ሴቶች ውስጥ ለመገንባት ትዕግስተኛ፣ ብልሃተኛና ዘዴኛ መሆን ይ ኖርባቸዋል። የዚህ ዓይነቱን የጋራ መግባባት ለመፍጠር በመስክ ሠራተኞችና በማህበረሰቡ መሃከል ፊት ለፊት ሲገናኙ በመና ገር ወይም በምልክት መልዕክት በሚተላለፍበት ሁኔታ ውስጥ ማህበረሰበራዊ ግንኙነቶችን ማድረግ ያስፈልጋል። የመስክ ሰራተኛው እነዚህን የመግባቢያ ምልክቶች በጥሩ ሁኔታ መረዳት መቻል ተገቢውን ምላሽ መስጠት የመ ስክ ሥራውን ውጤታማ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ የመስክ ሠራተኞች የተሳካ ግንኙነት ከማህበረሰቡ ጋር ለማድረግ እ ንዲችሉ መለማመድና ብቃታቸውን ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል። ሌላው ቀርቶ የማህበረሰቡ አባላት የውጭ እንግዳ በመሃከላቸው በተደጋጋሚ መገኘትን የተላመዱ ቢሆንም የመጀመሪያው የአቀባበል ሁኔታ ለመስክ ስራው መቃና ት አስተዋፅኦ ያደርጋል። መተማመንና የእርግጠኝነት ግንኙነቶች አመሰራረትን ቀላል ወይም ከባድ ማድረጉ ላይ የመጀመሪያው አቀባበል፣ የማህበረሰቡ የርስ በርስ የመወያያ ዘዴና ጥያቄና መልስ አስጣጥ የሚያሳድረውን ተጽኖ መረዳት በጣም አስፈላ ጊ ነው። ለውጤታማነት ቁልፍ ታሳቢዎች፡- ቀላልና ግልፅ የሆነ ቋንቋ ተጠቀም (የቋንቋው ችግር ካለብህ አስተርጓሚ ተጠቀም፡፡ ነገር ግን በአመራረጥ ላይ ጥ ንቃቄ ያስፈልጋል) ስብሰባዎችን ለሴቶች በሚመች ቦታና ሰዓት ማድረግ ያስፈልጋል፣ • ሴቶች የራሳቸውን ችግሮችና ፍላጎቶች እንዲናገሩ ለማበረታታት የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቀም/ሚ• ከሴቶች ጋር በሥራ ቦታቸው ላይ መደበኛ ያልሆነ ውይይት ማድረግ፣ የሚሠሩትን ሥራ ማገዝ፣ የመ• ሳሰሉት ተሳትፎአቸውን እንዲያጠናክሩ ያበረታታቸዋል፣ ለቤተሰብ አባላት በሙሉ በዘዴ የቀረብክና አሳቢ ሁን፣• በማህበረሰብ ውይይት ላይ በኤችኤይቪ/ኤድስ የተያዙ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸውን አሳትፍ/ፊ፣• የማግለልና መድሎ ድርጊቶችንና ቋንቋዎችን አስወግድ፣ • ባህላዊም ይሁኑ ሳይንሳዊ ዕውቀቶች ሊከበሩና ሊበረታቱ ይገባል፣ • የገጠር ሰዎች ድርጊቶችና የአኗኗር ዘዴያቸው በጥቅሉ በእንግዶች ሊከበርና ሊበረታታ ይገባል፣• የገጠር ሰዎች ስለሚደረገው ስብሰባ ምንነት እንዲያውቁት ይገባል። ስለዚህ ጥያቄ የመጠየቅ፣• ማብራሪያና ማረጋገጫ የማግኘት መብት አላቸው፣ 61 የውጭ ሰዎች ሁሌም ከገጠሩ ህዝብ ለመማር ጉጉት አላቸው። ስለዚህ ያስተምራሉም እንዲሁ• ደግሞ ይማራሉም፣ የገጠሩ ህዝብ የመስክ ሥራውን ለሚያሰናክል ወይም ውጤታማ ለሚያደርግ ውሳኔዎች ሁሉ• ኃላፊነቱን ይወስዳል ወይም ተጠያቂ ነው፣ ከአይናፋር ሰዎች ጋር መስራት፡- መጠነኛ ቁጥር ያለው ቡድን መስርት፣ • ለአስተያየታቸው ዋጋ ስጥ፣ • በግል አስተዋፅኦ የሚያደርጉትን አበረታታ፣ • ስማቸውን እወቅ፣ እንዲናገሩ ስትፈልግ በስማቸው ጥራቸው፣• ግብረ መልስ ማምጣት ወይም ማስታወሻ መያዝ የመሳሰሉትን ኃላፊነቶች ለቡድኑ አባላት • ስጥ፣ በራስ መተማመንን እንዲያዳብሩ አስመስሎ መጫወትን አብዝተህ ተጠቀም፣• ተሰሚነት ካላቸው ሰዎች ጋር መስራት፡- የስብሰባውን አላማ ግልፅ አድርግ፣ • ባሉ ሕጎች ላይ ተስማማ፣ • በቡድኑ ውስጥ ኃላፊነት ስጣቸው፣• አማራጭ ባህሪያትን አጠናክር፣• ቡድኑን ወደ አናሳ ቡድን ክፈል። (በአንድ በኩል ቁልፍ ተሳታፊዎችን በሌላው በኩል ደግሞ• ተሰሚነት ያላቸውን በአንድ ላይ) ከስብሰባ በኋላ መደበኛ ያልሆነ ውይይት አድርግ፣• በማህበረሰብ ውይይት ላይ ማደረግና አለመደረግ ያሉባቸው ነገሮች አድርግ የተዘጋጀህና የተደራጀህ ሁን፣• በሰዓቱ ድረስ፣ • አስተያየቶች በመነሳት ሊስተናገዱ የሚችሉ • ጥያቄዎችን ጠይቅ/ቂ ከመልሳቹ ዕውነቱን ለማግኘት ሞክር/ሪ• አድምጥ• ሰዎች እንዲያወሩ ቃላትና ቃላት አልባ • በእንቅስቃሴ ዘዴዎች አነቃቃቸው፣ • ንቁ ሁን፣ ድርቅ አትበል፣• ጥበበኛ ሁን፣ • ቀረቤታን ፍጠር• በአካባቢ የሚገኙትን ቁሳቁስ • ተጠቀም/ሚ አታድርግ አታስተምር• አትጫን• አትመሞክር፣ • መሪ ጥያቄ አትጠይቅ፣ • አታስገድድ፣• አታንሾካሹክ፣ • አታቋርጥ፣ • መልሶቹን አታቃልል፣ • ጣትህን አትቀስር፣ • መደበኛ አትሁን፣ • ከማህበረሰቡ ወይም ከቡድኑ ርቀህ • አትቀመጥ፣ 62 የተዘጋጀ ጽሑፍ 10፡- የመስክ ሥራ ሂደት ዝግጅት፡- ቦታዎችን መምረጥ፣• በመስክ ሥራው ወቅታዊነት ላይ መስማማት፣• ባለስልጣኖችንና ማህበረሰቡን መገናኘት፣ • ቡድን መመስረትና ኃላፊነትን መከፋፈል፣ • የሚጠየቁ ጥያቄዎች ዝርዝር ማዘጋጀት• ፣ የመስክ ሥራውን ማካሄድ፡- ከማህበረሰቡ ጋር መገናኘት፣• ራስህን ማስተዋወቅና የመስክ ሥራውን ዓላማ ማስረዳት፣ • በየቡድን ክፈላቸው (የሴትና የወንድ ቅልቅል መሆን ይችላል)፣ • ከያንዳንዱ ቡድን እንደገና ለሚያስረዱ ለሁለት ሰዎች ኃላፊነት መስጠት (አንድ ወንድ አንድ ሴት• ከየቡድኑ) አሳታፊ መረጃ ሰነዶችን በመጠቀም መረጃህን መሰብሰብ፣• መረጃ መሰብሰብ፡- የሴቶች ቡድን መረጃ መሰብሰብ፡- የወንዶች ቡድን የድርጊት መርሃ ግብር ለማህበረሰቡ ስለተገኘው መረጃ ማስረዳት መረጃ መተንተንና መተርጎም ማካፈል 63 የተዘጋጀ ጽሑፍ 11፡- በከፊል የተዘጋጀ ቃለ መጠይቅ እንዴት እንደምናቀርብ ሙሉ በሙሉ ከተዘጋጀ ቃለ መጠይቅ በተቃራኒ በከፊል የተዘጋጀ ቃለ መጠይቅ ማለት ጥቂት ጥያቄዎች አስቀ ድመው ከታወቁ ነገሮች የተዘጋጀ ቃለ መጠይቁን የሚመራ ማለት ነው። የስርዓተ ፆታን የኤች አይ ቪ/ኤድስ ት ንተና መደበኛ ጥያቄዎችን አዘውትሮ አይጠቀምም። ነገር ግን እንደ አስፈላጊነቱ የሚስተካከሉ መሪ የመቆጣጠሪ ያ ዝርዝር ጥያቄዎችን በብዛት እንደሚጠቀም ይታወቃል። በከፊል የተዘጋጀ ቃለ መጠይቆች ከግለሰብ ጋር፣ ከቡ ድን ጋር፣ ከቁልፍ መረጃ አቀባዮች ጋርና ከትኩረት ቡድን ጋር መጠቀም ይቻላል። በዋናነት ሦስት ዓይነት ጥያቄዎች አሉ። እነሱም፡- መሪ ጥያቄ፡-• የሚጠበቀውን ምላሽ እንዲሰጥ ማድረግ ነው። ጠያቂው ተጠያቂውን አውቆም ይሁን ሳያ ውቅ ከሚያነሳው ጉዳይ ጋር እንዲስማማ ወይም እንዲደግፍ ማድረግ ነው፣ ቀጥተኛ ጥያቄ፡-• የዚህ ዓይነቱ ጥያቄ ዓላማው የተወሰነ የመረጃ ነጥብ ለማግኘት ነው። በአብዛኛው ጥ ያቄዎቹ –– ስንት ናቸው፣ ምን ያህል፣ ምን ያህል ይደጋገማል፣ ማን፣ መቼ፣ የት፣ ለምን፣ የሚሉ ቃሎችን ይጠቀማሉ፣ ነፃ ጥያቄ፡-• የዚህ ዓይነቱ ጥያቄ በክርክር ውስጥ ቁልፍ ጥያቄዎች ናቸው። ለተጠያቂው እንደፈለገው እ ንዲመልስ ነፃነት የሚሰጡ እንጂ መልሱ ወደተፈለገው ነጥብ እንዲመጣ የሚያደርጉ አይደሉም። የግል ቃለ መጠየቅ፡- በምክንያት ለተመረጡ የግል መላሾች የሚደረግ ቃለ መጠየቅ ነው። በዚህም መሠረት መሪዎችን፣ ፈጠራ ሰዎችን፣ ሴት የቤተሰብ መሪን፣ ደሀ ገበሬንና የመሳሰሉትን ያካትታል። የተለያዩ ገበሬዎችን በተመሳሳይ አርእስት ላይ ቃለ መጠይቅ ማድረግ የተለያዩ አስተያየቶችን፣ ስሜቶችን፣ ስልቶችን ለማግኘት ይረዳል። ግለሰብ መላሾችን ስለዕውቀት ደረጃቸውና ስለባህሪያቸው ራሳቸውን መጠየቅ ይመከራል። የቁልፍ መረጃ አቀባዮች ቃለ መጠየቅ፡- ይህ ዓይነቱ ቃለመጠይቅ የሚደረገው በአንድ አርዕስት ላይ ልዩ ዕውቀት ካለው ሰው ጋር ነው። መረጃ አቀባዮቹ ስለሌሎች ሰዎች የዕውቀት ደረጃና ባህሪ ለሚጠየቁት ጥያቄ ይመልሳሉ ተብሎ ይጠበቃል በተለይ ደግሞ ሰፋ ስላሉ የአሠራር ዘዴዎች የመረጃ አቀባዮች መልስ ሊያሳስት እንደሚችል አደጋው ቢኖርም ማመሳከሩ እንዳለ ሆኖ መረጃ አቀባዮች የመረጃ ዋና ምንጭ ናቸው። በማህበረሰቡ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሰዎች ዋጋ ያላቸው መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ። የቡድን ቃለ መጠየቅ፡- የዚህ ዓይነቱ ቃለ መጠይቅ ሰፋ ያለ መረጃ ወይም ዕውቀት ያስገኛል (በማህበረሰብ ደረጃ ያለ መረጃ)። በተጨማሪ ወዲያው በሌሎች የቡድን አባላት ስለሚረጋገጥ ማመሳከሪያ ማግኘት ይቻላል። የቡድን አባላቱ ቁጥር (እንደ ደንብ የተወሰደ ከ20-25 ከበለጠ) ለመምራት ያስቸግራል። የትኩረት ቡድን ቃለ መጠይቅ፡- ይህ ዘዴ የተለዩ አርእስቶችን ከአነስተኛ የቡድን አባላት (6-12) በጥልቀት ስለሚወያዩበት በርዕሱ ላይ በቂ ዕውቀት ያላቸው ጋር በዝርዝር መነጋገር ነው። አብዛኛውን ጊዜ ውይይቱ ከዋናው ጉዳይ እንዳይ ወጣ ወይም ማንም ተሳታፊ ስብሰባውን በራሱ ተደማጭነት ሥር እንዳያደርግ አስተባባሪ ይሰየማል። 64 በከፊል የተዘጋጀ ቃለመጠይቅ የማድረግ መመሪያ ዝግጅት 1. ተገቢ የሆነ ቃለመጠይቅ አድራጊ ቡድን • መምረጥ፣ በየኃላፊነት ቦታዎች መሰየም፣ ማለትም ማስታወሻ ያዥ፣ ታዛቢ፣ አወያይ፣ አስተባባሪ፣ ጥያቄዎችን በግልፅ ማዘጋጀት፣ቃለ መጠይቅ • እንዴት እንደሚደረግ ተስማማ/ሚ። ለምሳሌ ከትኩረት ቡድን ጋር፣ ከቁልፍ መረጃ ሰጪዎች ጋር፣ ከግለሰቦች ጋር ራስህን ለቃለ መጠይቁ አዘጋጅ/ጂ። • የቃለ መጠይቁን መሪ ጥያቄ ዝርዝር • ማዘጋጀት፣ 3.በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ ጠይቅ/ቂ፣ አብዛኛው ቃለ መጠየቅ ግልፅና ሰፋ ያሉ• ለመልስ ሰጪው በራሱ መንገድ ውይይት እንዲያደርግ ዕድል የሚሰጡ እንጂ በጠያቂው የሚመሩ መሆን የለባቸውም፣ ለምን፣ ምን የት፣ መቼ፣ ምን፣ እንዴት • የመሳሰሉትን ቃላትና ሐረጎች ተጠቀም/ ሚ፣ ከመልሶቹ እውነትን ለማግኘት ሞክር/ሪ፣• መልስ የሚሆን አስተያየት አታቅርብ/ቢ፣• መላሾችን አትቃወም/ሚ፣• ማስተማርና መምከር ተው/ይ፣• በጥንቃቄ ወደ ቁምነገሩ አምራ/ሪ• ጊዜ ውሰድ። ወደሌላ ጥያቄ ከመሄድህ/ሽ• በፊት መላሾች መልሳቸውን ሰጥተው እስኪጨርሱ ታገስ/ሽ፣ ቃለ መጠየቅ ማድረግ መጀመር 2. ባህላዊ ሰላምታ በመስጠት ጀምር/ሪ፣ • ማንነትህን ግለፅ ሰምህን፣ሥራህን ለምን • እንደመጣህ/ሽ፣ ልትቀመጥበት የምትችል ትክክለኛ ቦታ ምረጥ/ጭ፣• ቃለመጠይቅ ከሚጠየቁት ጋር ተመሳሳይ ቦታ፣ ከፍ ያለ ቦታ እንዳትመርጥ፣ ቀረቤታ አሳይ እንዲሁም አክብር/ሪ፣ • ባህሉ በተቀበለው ትህትና በተሞላበት አነጋገር • ጀምር/ሪ፣ በመሃከላቸው ያለውን ገደብ ለመቀነስ የተጠቂዎች• ን ቋንቋ ተጠቀም/ ሚ፣ ቃለመጠይቁ ክርክር ወይም ሂደት ሆኖ ቁም ነገር አ• ዘል መረጃዎች ከውስጡ እያደጉ የሚወጡ ቀላል ው ይይት ሊሆኑ ይገባል። የመረጃው ጥራት በአብዛኛው የሚወሰነው በቃለመጠይቁ አድራጊውና በተጠያቂው መሃል በተመሠረተ ቅርበት ላይ ነው። ተከታታል፣ ላልተለመዱ ሁኔታዎች፣ ባህሪዎች፣ • ልዩነቶች፣ ድምጽ አልባ ምልክቶች አይንህን ገልጠ• ህ ጠብቅ፣ 4. ቃለመጠይቁን መመዝገብ የማስታወሻ ገጾችህን ለሁለት ክፈላቸው • አንዱ ለሚሰጠው መልስ ሌላው ለተገነዘብካቸው ጉዳዮች አድርግ/ጊ፣ መፃፍ ከመጀመርህ በፊት ተጠያቂዎችን • ይቅርታ ጠይቅ/ቂ ወይም አስፈቅድ/ጂ፣ እየተባለ ያለውን መዝግብ/ቢ• የቃለ መጠይቁን ዝርዝር፣ • አስፈላጊ ነጥቦችን፣ • ማነው ቃለመጠይቅ የጠየቀው፣ • ማነው በቡድኑ ውስጥ ያለው• የትነው ቃለመጠይቁ የተካሄደው፣• 5.ቃለ መጠይቁን መዝጋት የውይይቱን ማጠቃለያ አቅርብ/ቢ፣• ውሃ ወይም የአካባቢውን መጠጥ• ቢሰጡህ እምቢ ላለማለት ሞክር/ሪ፣ ፎቶግራፍ አታንሳ/ሺ። አስቀድመህ• ፈቃደኝነታቸውን ጠይቀህ/ሽ ካላገኘህ/ሽ በስተቀር ካሜራው ዘመናዊ ከሆነ ያነሳኸውን አሳያቸው፣ ቃለመጠይቁን በትህትና ጨርስ/ሺ፣• ለተጠያቂዎች ምስጋና አቅርብ/ቢ፣• 65 የተዘጋጀ ጽሁፍ 12፡ ከግብርና ጋር ተዛማጅነት ባላቸው ተግባሮች ውስጥ ሥርዓተ ፆታንና ኤችአይቪ/ኤድስን እንደዋና ተግባር እንዲወሰድ ጥልቅ ሀሳቦችን በውይይት ማፍለቅ ሥርዓተ ፆታዊ ጉዳዮች፡- እንደ ኤክስቴንሽን ሠራተኛና የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኛ፣ የወረዳ አስተዳደር ሠራተኛ ምን ማድረግ እችላለሁ? የሴቶችን የኤኮኖሚ ደረጃ ከፍ ለማድረግ? በስልጠና ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ፤ የሴቶች ተሳትፎ መጠን ምን ያህል መሆን እንዳለበት ኢላማ • ወይም እቅድ ማድረግና በስብሰባ ላይ ሴቶች ቢያንስ ከ40% በታች ከሆኑ ስብሰባ አለማድረግ። ስብሰባዎ ችን በገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከላት ወይም ለሴቶች ተሳትፎ ምቹ ሊሆኑ የሚችሉበት ቦታዎችን መም ረጥና ማድረግ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ወደቤታቸው ተመልሰው ምግብ ማብሰል፣ ልጆቻቸውንና ከብቶ ቻቸውን መንከባከብ ስላለባቸው፡፡ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከላት በአካባቢያቸው ለሴቶች አስፈላጊ በሆኑ ንብረቶች፣ የባልና ሚስት የጋራ ስልጠናዎች፣ የስልጠና ጊዜያቶችን የማመቻቸት (ለምሳሌ ወቅታዊ የጊ ዜ መቁጠሪያ ወይም ዕለታዊ የቀን መቁጠሪያ በመጠቀም) የትኛው ወራት ለሴቶች የበለጠ ለስልጠና ም ቹ ምንደሆነ በመምረጥ፣ በመስክ ሥራ ላይ ሴቶች እንዲበረታቱ በማድረግ የመሳሰሉትን ለመስራትና ት ኩረት ለመስጠት ያስችላሉ። የስልጠና ፍላጎቶችን ጥናት በማድረግ የሚሰጡ ስልጠናዎች የሴቶችን ሞ ራል ከፍ ለማድረግና የገበሬ ሴቶችን ፍላጎቶች ያሟሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳል። ሴቶች የግብርና ግብዓቶችንና እንዲሁም የቁጠባና የብድር ማህበራትን አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን ዘ• ዴ ማጠናከር፣ ለሴቶች የሚመቹ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ። የሰርቶ ማሳያ ጣቢያዎችን በብዛት ማዘጋጀትና • የየጣቢያዎችን ሥራዎች ሴቶች እንዲመሩ በአሳታፊ የቴክኖሎጂ ማሳደጊያ ዘዴዎች እንዲካፈሉ፣ በመስ ክ ሥራና በአውደ ራዕዮች እንዲሳተፉ ማበረታታት፣ ሴቶች መረጃዎችን የሚያገኙበትን ዘዴ ማጠናከር፤ መረጃዎች ሴቶች በቀላሉ ሊያዩት የሚችሉበት ሥፍ• ራ ላይ እንዲሆን ማድረግ፤ ከተግባራዊ የጎልማሶች የመሰረተ ትምህርት አሰጣጥ ጋር ማያያዝ፤ የግብር ና ሴቶችን ለማግኘትና የጤና ኤክስቴንሽን መልዕክቶችን ለማስተላለፍ የቤት ለቤት መገናኛ ዘዴ መጠቀ ም፣ ለገበያ የሚሆኑ ምርቶችን በመሸጥ ሂደት የሴቶችን ተሳትፎ ማጎልበት። የሴቶች ምርት ተብሎ በሚታሰ• ብ ምርቶች ላይ የሴቶችን አቅም በስልጠና ማጠናከር ። ገበያዎችን በማሳደግ እድገታቸውን መደገፍ፣ ግ ብአቶችንና ብድር አገልግሎት በቅርበት የሚያገኙበትን ማመቻቸት፣ የቴክኒክ ስልጠናዎችን መስጠት መ ሠረታዊ የአሠራርና የገበያ ሥርዓት ሙያን ማሻሻል፤ በወንዶች በሚዘወተሩ ሙያዎች ላይ ሴቶችን ማሰልጠን፣ ለምሳሌ ማረስ ውጤታማ የሆኑ ሴቶች ብዙ ም ውጤታማ ካልሆኑት ጋር የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ማድረግ፤ በባህል በወንዶች በሚዘወተሩ የምርት ሂደት ላይ የሴቶችን ብቃት ማሳደግ ለምሳሌ የንብ ዕርባታ፡፡ ሴቶች የግብይት ቡድን ፈጥረው የ መከራከርና የመደራደር አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ማበረታታት፣ ባህላዊ ገደቦችን ለማሸነፍ መሞከር፤ ሴቶች በማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መሳተፍ እንደሚችሉ ማ• ህበረሰቡ በተለይም ወንዶች እንዲያምኑና እንዲቀበሉ ጥረት ማድረግ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የሴቶችን ተቀባይነት ለማጉላት፡- በማህበራዊ ጉዳዮች ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ማጎልበት ለሴቶች የአመራር ስልጠና• መስጠት፤ ለገበሬ ሴቶች ሽልማት ማበርከት፣ ተምሳሌት ሴቶችን ማቅረብ፤ ሴቶች የልማት ሠራተኞች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሴት ሠራተኞች• በአካባቢው እንደ ተምሳሌት ሊወሰዱ ይችላሉ፣ 66 በሬድዮ የሴቶች ፕሮግራሞችን ማሠራጨት፣• በአካባቢው የሚገኙ በማህበራዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያቸው ምርታማ የሆኑ ሴቶችን• እንዲሁም በአመራር ላይ የሚገኙትን ሴቶች ፎቶዎች/ፓስተሮች በገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከሉ አካባቢና ሌሎች መገናኛ ስፍራዎች መለጠፍ፣ በመስክ የሥራ ቀን ወይም አውደ ርዕይ ላይ ለሴቶች መረጃ የመስጠት ኃላፊነትን መስጠት፣• በማህበረሰቡ ስብሰባ ላይ ሴቶች አቅራቢ እንዲሆኑ ማደፋፈር፣• የሴቶችን የሥራ ጫና ለመቀነስ፡- ጉልበትና ጊዜ የሚቆጥቡ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም - ለምሳሌ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ፣• በሴቶች የሚዘወተረውን ሙያ ለወንዶች ማስተማር - ለምሳሌ ልጆችን ሐኪም ቤት መውሰድ፣ ምግብ ማ• ብሰል፣ ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ማንሳት፡- የሥርዓተ ፆታ ትንተና በየሰብሉና በየእንስሳት ዕርባታው ዓይነት ከገበያው አቅም ጋር እያገናዘቡ• መስራት፣ በፆታ የተሰበጣጠሩ መረጃዎችን መሰብሰብ መተንተንና ማሳወቅ፣ • የግብርና አመራረትና የቴክኖሎጂ ምርጫን ለመወሰን ስርዓተ ፆታ መረጃንና ትንተና መጠቀም፣ • የቤተሰብን ሀብትና ገቢን አጠቃቀም ለሴቶችም ለወንዶችም በአንድ ላይ ማሰልጠን። (የቤት ለቤት• የኤክስቴንሽን ዘዴ በመጠቀም ጥንዶችን ማሰልጠን)፣ በመንደሩ ሴቶች ነክ ማህበራትን ማጠናከር፣• ሴቶችን እንዳይሳተፉ የሚከለክሉ ባህሎችና ወጎችን ለመከላከል በማህበረሰብ ደረጃ ግንዛቤ እንዲፈጠር ማ• ድረግ፣ በሴቶች የሚመሩ ቤተሰቦች የሚያጋሟቸውን ችግሮች መለየትና እንዲቋቋሙ መርዳት (ብዙዎቹ ወደ ድህ• ነት ያዘነበሉ ናቸው)፣ የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮችን ከወረዳው የገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከል የድርጊት መርሃ ግብር ጋር ማዋሃድ፣• ተግባራት ወደ ሥራ ከመተርጎማቸው በፊት፤ ለሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች ይህ ምን ይረባል? መስራትስ ይች• ላል ወይ? የሚለውን ማየትና መገንዘብ (አባሪ 1 ተመልከት/ቺ) ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ ወይም በትብብር መስራት፤ ለምሳሌ በሴቶች የሚመሩ ቤተሰቦችንና • ያገቡ ሴቶችን በመለየትና እንደዋነኛ ተጠቃሚ ትኩረት በመስጠት፣ በኢኮኖሚያዊ ተግባራት እንዲሳተፉ ለ ማበረታት ከሴቶች ጉዳይ ጋር አብሮ መሥራት፣ 67 በተጨባጭና በትስትራቴጂክ ፆታዊ ፍላጎቶች መሟላት መሃል ያለ ልዩነት፡- አንድ ፕሮጀክት የትኛው ዓይነት የፆታ ፍላጎት ላይ መስራት እንደፈለገ አስቀድሞ ማወቅ ይገባዋል። ተጨባጭ ፆታዊ ፍላጎቶች ሰዎች ለየዕለት ኑሯቸው የሚያስፈልጋቸው መሠረታዊና ቁሳዊ ፍላጎቶች ጋር በእጅ• ጉ የተቆራኘ ነው። ይህንን ተጨባጭ ፍላጎት ለማሟላት አሁን ያለው በፆታ ላይ የተመሰረተ የሥራ ክፍፍልና የስራ ድርሻ ችግር አይኖርበትም። በዚህ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች የወንዶችንና የሴቶችን ሁኔታዎች ለማሻሻል ከሥልጣንና ከዕኩልነት ይልቅ ውጤታማ የሀብት አጠቃቀምን ማሳወቅ ላይ ያተኩራል፡፡ (ከግርጌ ይመልከቱ) ስትራቴጂካዊ ፆታዊ ፍላጎት አሁን ያለውን የፆታ መለያዎችን በወንድና ሴት መሐል ያለውን ግንኙነት• በመቃወም የሁሉም እኩል ባለመብትነትን ይደግፋል። ስለዚህ የሥራ ክፍፍል ከዚህ በኋላ በሰፊው በፆታ ላይ የተመሠረተ አይሆንም። ከዚሁ ጋር አብሮ ንብረትን የማግኘት፣ የመቆጣጠርና የመጠቀም ክልከላ ከፆታ ልዩነት ጋር ሊያያዝ አይችልም። ስትራቴጂክ ሥርዓተ ፆታን ፍላጎት ለማሟላት አንድ ፕሮጀክት ሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ተነፃፃሪ ደረጃ በመለወጥ ጎልተው እንዲወጡና እኩል እንዲስተናገዱ ለማድረግ ይጥራል። አራቱ ቁልፍ ነጥቦች ውጤታማነት፡- ሀብትንና ጉልበትን በአግባቡ በሥራ ላይ ማዋል፣ • ማብቃት፡- ሰዎች ስለህይወታቸው በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲሰጡ፣ እውቀት ሙያና • እርግጠኝነትን እንዲያዳብሩ የማድረግ ሂደት ሲሆን የበለጠ በራሳቸው እየተማመኑም ይሄዳሉ፣ እኩልነት፡- ለሁሉም የማህበረሰቡ አባል እኩል መብትና ዕድል መስጠት ነው ።• እኩልነት፡- ለሁሉም የማህበረሰቡ አባል ተመሳሳይ አቀባበልና አገልገሎተ መስጠት።• በስትራቴጄካዊ የፆታ ፍላጎትና በተጨባጭ ፆታዊ ፍላጐት መሃል ፍፁማዊ የሆነ ድንበር የለም፡፡ አንድ ኘሮጀ• ክት የተጨባጭ ፍላጎቶችን የማሟላት ሥራ እየሰራ እግረመንገዱን የስትራቴጂክ ፍላጎትንም ሊያሟላ ይችላ ል። 68 ሥርዓተ ፆታዊ ፍላጎቶች፡- ሴቶች ከወንዶች የተለየ ልዩ ፍላጎት አላቸው፤ሴቶች ካለባቸው የሦስትዮሽ የሥራ ድርሻ ብቻ የተነሳ ሳይሆን በ ማህበረሰቡ ውስጥ ካላቸው በወንዶች ተፅዕኖ ቁጥጥር ሥር ከመሆናቸው የተነሳ ከወንዶች የተለየ ልዩ ፍላጎት አላቸው። ይህም ተጨባጭ የፆታ ፍላጎትንና ስትራቴጂክ የፆታ ፍላጎትን ለመለየት ይጠቅማል። ተጨባጭ ፆታዊ ፍላጎቶች ስትራቴጂካዊ ፆታዊ ፍላጎቶች አሁን መሆን ያለበት፣ አጭር ጊዜ ረጅም ጊዜ የሚፈጅ ለያንዳንዷ ሴት ልዩ የሆነ ለሁሉም ሴቶች የጋራ የሆነ ከዕለት ፍላጎት ጋር የተዛመደ ምግብ፣ ከዝቅተኛ ደረጃዎች ጋር የተዛመደ፤የበታችነት መጠለያ፣ ገቢ፣ ጤናማ ልጆች ወዘተ. የንብረትና የዕውቀት ዕጦት፣ ለድህነትና ለትንኮሳመጋለጥ በቀላሉ በሴቶች ሊለዩ የሚችሉ የመጥፎ ጐንነት ወይም የመለወጥ አቅም መሠረት አያስፈልግም፡፡ በቀላሉ በሴቶች ሊለዩ የሚችሉ አንዳንድ ግብአቶችን በማቅረብ ሊቃለል የሚችለው የንቃት ደረጃን ከፍ በማድረግ፣ ሊቃለሉ የሚችሉ፤ የምግብ፣ በራስ መተማመንን በመጨመር፣ በማስተማር፣ የውሃ፣ የእጅ ፓምፕ፣ ክሊኒክ ወዘተ. የሴቶች ድርጅቶችን በማጠናከር፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ወዘተ. ተጨባጭ ፆታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት ስትራቴጂክ ፆታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት ሴቶችን እንደተጠቃሚ ወይም እንደ - ሴቶችን እንደ ለውጥ ሠራተኛ የመጠቀም- ተሳታፊ የማሳተፍ ዝንባሌ፣ ወይም የለውጥ ሠራተኛ እንደሆኑ ማድረግ፣ የሴቶችን ህይወት ማሻሻል ይችላል፣ - በማህበረሰቡ ውስጥ ሴቶች ያላቸውን ደረጃ- በጥቅሉ ልማዳዊ ሃላፊነታቸውንና ማሻሻል፣- ማህበራዊ ግንኙነታቸውን - ሴቶችን በማብቃት ግንኙነታቸውን ከፍ አይለውጥም ሊያደርግ ይችላል፣ 69 ከታች የተመለከተው ምሳሌ እንደሚያሳየው ተጨባጭም ይሁን ስትራቴጂክ ፆታዊ ፍላጎቶች ዕቅድ ነዳፊዎች በ ገቢ መጠን ብቻ ሳይሆን በሥርዓተ ፆታ መሠረት የትኩረት ቡድን መለየት ከቻሉ ሊሟላ የሚችል መሆኑን ነ ው። የጣልቃ ገብነት ዓይነቶች የሴቶች ድርሻ ተብሎ የ ሚታወቅ የፆታዊ ፍላጎቶች ይሟ ላሉ ወ ማ ማአ ተፆፍ ስፆፍ 1 የቅጥር ፖሊሲ ሀ. የሙያ ስልጠና ምግብ ዝግጅት × × ልብስ ስፌት × × ግንብ ሥራ × ×/ሀ/ ለ. ብድር ማግኘት ለቤተሰብ የተመደበ × × ለሴቶች የተመደበ × ×/ለ/ 2 የሰዎች የአሰፋፈር ፖሊሲ ሀ. የቤት ባለቤትነት በወንድ ስም × × በሴት ስም × × ×/ሐ/ 3 መሠረታዊ አገልግሎቶች ሀ. የልጆች ማቆያ ስፍራ ያለው በማህበረሰቡ ውስጥ ነው × × × × × እናት በምትሰራበት አካባቢ × × × አባት በሚሰራበት አካባቢ × × ×/መ/ ለ. የጤና ክሊኒክ በማህበረሰቡ ውስጥ ሴቶች ቀን ቀን ሥራ በሚሰሩበት ጊዜ ጠዋት ጠዋት ክፍት ነው × × ከሠዓት/ምሽት ክፍት ነው × × × × × ሐ. የገጠር የኤክስቴንሽን የስብሰባ ሰዓት ጠዋት ጠዋት ክፍት ነው × ከሠዓት/ምሽት ክፍት ነው × × × × × ወ = የመውለድ ማ= ማምረት ማአ= የማህበረሰባዊ አመራር ተፆፎ=ተጨባጭ ፆታዊ ፍላጎት ስፆፍ= ስትራቴጂክ ፆታዊ ፍላጎት (ሀ) ፆታን መሠረት ያደረገ የሥራ ክፍፍልን መለወጥ በሴቶች የመሬት ባለቤትነት በህግ ወይም በባህል መለወጥ፣ (ለ) የገንዘብ አገልግሎቶችን መቆጣጠር፣ (ሐ) መድልዎን ማሸነፍ፣ (መ) የቤት ውስጥ የሥራ ጫናን መቀነስ፣ እንደ ልማት ሠራተኛ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኛ ወይም ወረዳው አስተዳደር አባል ምን ላድርግ ...ስለኤችአይ ቪ/ኤድስ የበለጠ ለማሳወቅና ግንዛቤ ለማዳበር፡- 70 ገበሬዎች ስለኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ የሚያገኙበትን መንገድ ማጠናከር፤ በስልጠና ላይ ስለኤች አይቪ ኤድ- ስ ድራማ ማዘጋጀት፣ በአውደ ራዕዮች፣ በማህበረሰብ ግልፅ ስብሰባዎች ላይ፣ የመቆጣጠሪያ ዝርዝር በመ ጠቀም የኤችአይቪ/ኤድስ ግንዛቤ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መጠነኛ ጥናት በተለዩና በተመረጡ ቡድኖች መሃ ል ማድረግ፤ ለምሳሌ፡- ከብት አርቢዎች፤ በሁሉም ሥፍራ ምንጊዜም የኤችአይቪ/ኤድስ መልዕክት ቀጣይ ነት ባለው መንገድ ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። ነጋዴዎች፣ ደላሎች፣ ተጓጓዦች፣ የእለት ተእለት ሠራተኞች ስለኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ የሚያገኙበትን - መንገድ ማጠናከር፤ (እነዚህ ሰዎች በቡድን ተሰባስበው ስለማይገኙ የቡድን አባል አይደሉም። አብዛኛውን ጊዜ አስተላላፊ ድልድዮችን ይወክላሉ) በገበያ ቀናት ስለኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ ለማስተላለፍ የመገናኛ ብዙ ሀን ዘዴን መጠቀም። ፖስተሮችንና ጽሑፎችን አዘጋጅቶ ማደል። ለምሳሌ በገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ በ ወረዳ የትምህርት ማዕከላት። በመስክ ሥራ ቀናት፣ የእንስሳት ግብይት አወደ ራዕይ በሚቀርቡበት ቀናት በገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከላ- ት በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የምርመራና የምክር አገልግሎት እንዲኖር ማድረግ፣ ለአካባቢ ሲኒማ ቤቶች ስለኤችአይቪ/ኤድስ የሚገልፁ አጫጭር ፊልሞችን ማቅረብ፣ - ከኤች አይቪ/ኤድስ ጋር አብሮ የሚኖሩ ሰዎች የምስክርነት ቃላቸውን የሚሰጡበት በስልጠና ወቅቶች በገበ- ያ ቦታዎች ማዘጋጀት፣ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ስለኤችአይቪ/ኤድስ መረጃ ማስራጨት፣- ከአርሶ አደሩ ማህበረሰብ ጋር ስለኤችአይቪ/ኤድስ ግልፅ ውይይት ማድረግ፤ (ለምሳሌ በማህበረሰብ- ውይይት ላይ ወይም በኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና ላይ)፣ ...በኤች አይ ቪ የመያዝ አደጋን ለመቀነስ፡- የግብርና ግብአቶችን ለመግዛት ወይም ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት ገበሬዎች የሚያደርጉትን- ዝውውር መቀነስ። የገበሬዎች የኅብረት ሥራ ማህበራትን በየአካባቢው ማቋቋም፤ በዘር ማባዣ ሥራ ላይ ድጋፍ መስጠት፣ በወረዳው የግብርና ግብአት መሸጫ ሱቆች እንዲበራከቱ ማበረታ- ታት፣ የጥገና አገልግሎቶች በየሥራው አካባቢ እንዲሆኑ መደገፍ፣ የገበያ ምርት ፍለጋ የሚደረገውን ጉዞ መቀነስ፣ ለገጠሩ ማህበረሰብ የገበያ መረጃ ማቅረብ፤ በአምራቹና በ- ነጋዴው መሃል የስልክ ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ፤ በወረዳው ገበሬዎች ምርታቸውን የሚያስቀምጡ በት፣ ነጋዴው መጥቶ የሚረከብበት ጊዜያዊ ጣቢያ ማቋቋም፤ ለገበያ አቅርቦት ሁለገብ ህብረት ሥራ ማህ በራትን መቋቋም፣ ከስልጠና ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ዝውውሮችን መቀነስ፤ ስልጠናዎች በአካባቢው በገበሬዎች ማሰልጠኛ - ማዕከል እንዲሰጡ ማድረግ በተጨማሪ ስልጠናዎች ለጥንዶች እንዲሆን ማመቻቸት፣ የገበያ ውጤታማነትን ማሻሻል፤ በማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች የአያያዝ ሥርዓት ማሻሻል እንዲኖር ማድረግ፣ - የዋጋ ወይም ተመን ዝግጅቶች ከጊዜ መስመር ጋር እንዲጣጣሙ ማድረግ ገበሬዎች፣ ሠራተኞች፣ ነጋዴዎች ገበያቸውን ጠቃሚ በሆነ መንገድ እንዲገለገሉበት ማበረታታት፣ አስተ- ሳሰባቸው እንዲሰፋና ቁጠባ እንዲማሩ፣ ወደፊት ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ቤተሰብ አብሮ እንዲያቅ ድና አብሮ ወጪውን እንዲተምን ስልጠና መስጠት፣ በስልጠና ያገኙትን ሙያ እንዴት እንደሚጠቀሙበት መከታተልና መቆጣጠር፣ የሠራተኞችን ዝውውር መቀነስ፤ በየወቅቱ የሚፈለገውን ወቅታዊ የጉልበት ሥራ መቀነስ ( ለምሳሌ አፈ- ርና ውሃ ጥበቃ) የእርሻ ሥራ የተራዘመና ሙሉ ዓመቱን የሚሰራ ሥራ በማድረግ ለምሳሌ በመስኖ ማል ማት፤ ከብቶችን ማድለብ፣ የዶሮ ዕርባታ ማቋቋምና የገጠሩን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል የመሄድ ወይም የ መፍለስ ጉጉትን መቀነስ ይቻላል፣ የሴቶችን የኢኮኖሚ ደረጃ ከፍ ማድረግ (የሥርዓተ ፆታ ክፍሉን ይመልከቱ) - በገጠሩ ማህበረሰብ የሚያገለግሉ ሙያተኞች መሃል ያለውን የመያዝ አደጋ መቀነስ፣- ለኤድስ ተጽዕኖ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ከኤችአይቪ /ኤድስ ጋር አብሮ የሚኖሩትን ሰዎችና ቤተሰባቸውን መርዳት፤ ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ለሚኖሩ - 71 ሰዎችና ቤተሰባቸው ሀብትና አቅም የሚመች ሁኔታን የሚፈጥሩ ምርቶችን ማስተዋወቅ፤ (ለምሳሌ ለመኖሪ ያ ቤት ቅርብ የሆነ፤ ብዙ ጉልበት የማይፈልግ፣ ብዙ ገንዘብ የማይጠይቅ፣ አነስተኛ አደጋ ያለው ሥራ የበ ግና የፍየል ዕርባታ የመሳሰሉት፤ ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ለሚኖሩ ሰዎችና ለቤተሰባቸው ለሚሆኑ የገበያ እ ድሎችን ማሳደግ -- የግብርናም ይሁኑ ወይም ከከግብርና ውጭ -- ከቫይረሱ ጋር አብሮ የሚኖሩ ሰዎችና ቤ ተሰባቸው ምርታቸውን ወደገበያ ሊያጓጉዙ የሚችሉበትን የትራንስፖርት ቡድን መመስረት፤ ሰፋ ያለ ሙያ እንዲያገኙ ለጥንዶች ስልጠና መስጠት፤ ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ለሚኖሩ በተለይ የፀረ-ኤችአይቪ መድሐኒት ተጠቃሚ ለሆኑት የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት እንዲችሉ የሰብልና የእንስሳ እርባታ ሥራን ማስተዋወቅ፣ ሌሎችን መረዳት፤ በአነስተኛ ነጋዴዎች መሃል የሽያጭ ቡድኖችን ማቋቋም፤ ሲታመሙ ቦታቸው እንዳይጎ- ድል ደህንነትን በተቻለ መጠን መጠበቅ፤ ብዙ ጉልበት የማይጠይቁ ቴክኖሎጂዎችንና አሠራሮችን በማሳየት፤ ህ- ብረት ሥራ ማህበራትን፣ የቡድን አባላትን የቤት አያያዝና የደህንነት አጠባበቅ ስልጠና መስጠት፣ Cross cutting/ ሁለገብ ጉዳዮችን መፈፀም፡- በማህበረሰቡ የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና አድርግ፣ - የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮችን ከወረዳው ገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከል እቅድ ጋር ማዋሃድ፣ - የተለያዩ ተግባሮች በሥራ ከመተርጎማቸው በፊት፣ ለኤችአይቪ ይኸ ምን ማለት ነው? ከዚህ የተሻለ መስ- ራት እችላለሁ ወይ? ብሎ መፈተሽ (አባሪ 1 ተመልከት) ከአጋር ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት፤ ለምሳሌ የኤችአይቪ/ኤድስ መቆጣጠሪያና መከላከያ ጽ/ቤቶች ጋር - ምከንያቱም ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር አብሮ የሚኖሩትን ሰዎችና ቤተሰባቸውን ለማወቅ ስለሚረዳ፣ የምርታማነትና ገበያ ስኬት ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ፕሮጀክቶች የመቆጣጠሪያ ዝርዝር፡- ተግባራት አዎ የለም እባካችሁ የተለዩ የግብርና ምርት /ቴክኖሎጂዎችን/ ተግባሮችን በዚህ ሥ ር ግለጹ 1 የሥርዓተ ፆታ መረጃዎች ለሰብል/ለቴክኖሎጂ ለእንስሳት ዕርባታ/ ቅድሚያ ወጥቶለት ተሰብስቦ ተተንትኗል። 2 በተለያየ ደረጃ የስርዓተ ፆታ ግንዛቤን ለማዳበር እርምጃዎች ተወስደዋል? 3 ከላይ ያለውን የሥርዓተ ፆታ ትንተና ተንተርሶ ከታች ለተዘረዘሩት ጉዳዮች መልካም አጋጣሚዎ ች መለየት ተችሏል? 72 የሴቶችን ንብረት መቆጣጠር የሚችሉበትን • መንገድ መጨመር - ግብዓትን፣ ብድር ማ ግኘትን፣ ቴክኖሎጂን፣ ሴቶች ሙያና ዕውቀት ሚያገኙበትን መንገ• ድ መጨመር፣ በገበያ መር የግብርና ልማት ውስጥ የሴቶ• ችን ተሳትፎ ማሳደግ፣ በቤተሰብ ውስጥ ወይም በገበሬ ቡድኖች ወ• ይም በሴቶች ማህበራትና ድርጅቶች ውስጥ የሴቶችን የመወሰን ድርሻ ማጠናከር፣ ጉልበት ቆጣቢ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች የሚገ• ኙበትን መንገድ በማስተባበር የሴቶችን ደህ ንነትና የሥራ ጫና ማሻሻል፣ 4 በዕቅድ በተያዙ ድርጊቶች ውስጥ ፆታዊ እኩልነ ት በተሳታፊነትና በተጠቃሚነት መልኩ የሚያረ ጋግጡ ተግባራዊ እርምጃዎች ተለይተው ተቀም ጠዋል? በተለይ ሴቶች በተለያዩ ተግባራትና አስፈላጊ ውሳኔ • ሰጪ አካላት ውስጥ በተመጣጠነ ደረጃ እን ዲሳተፉ ልዩ ግቦችን ማስቀመጥ በዚህ ሁኔታ ሴቶች ጋር መድረስ እንዲችሉ• ና ሥራቸውንም በዚሁ አቅጣጫ እንዲተል ሙ በተለየ ሁኔታ የመስክ ሠራተኞችን ችሎ ታ ማሻሻል፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ /መያድ/ ተግባባሪ ድ• ርጅቶችን ለመምረጥ ከሴቶች ጋር የመስራት ልምድና ፈቃደኝነት እንደ መስፈርት እንዲወ ሰዱ ማድረግ፣ ለተግባራዊነት አዳዲስ ተባባሪዎችንና ግንኙነ• ቶችን መፍጠር፣ ፆታዊ የተበታተኑ ድርጊቶችንና ተፅዕኖ ጠቋ• ሚዎችን መለየት፣ 5 ኤችአይቪ/ኤድስን እንደ ዋና ተግባር እንዲወሰድ ማድረግን በተመለከተ መልካም አጋጣሚዎችን ከ ታች ለተመለከቱት ጉዳዮች መለየት፣ የኤችአይቪ/ኤድስን ግንዛቤና መረዳትን ለማ• ዳበር፣ ለኤችአይቪ/ኤድስ የመጋለጥ አደጋን ለመቀ• ነስ፣ ለኤድስ ተፅዕኖ ተጋላጭነትን ለመቀነስ፣• ለተግባራዊነት አዳዲስ ተባባሪዎችና ግንኙነቶ• ችን መፍጠር፣ 73 የተዘጋጀ ጽሁፍ 13፡ የድርጊት መርሃ ግብር የድርጊት መርሃ ግብር አንድን እቅድ ከግብ ለማድረስ፣ የተወሰኑ አስፈላጊ ዝርዝር ተግባራትን በተወሰነ የጊዜ ገ ደብ ውስጥ፣ በአግባቡ በተበጀ የገንዘብ አቅምና አስፈላጊ ቁሳቁሶች፣ እንዲሁም ተገቢውን የሰው ሀብት ተጠቅመን ለመስራት እንድንችል የሚረዳን መሳሪያ ነው። ከተባባሪ ድርጅቶችም ሆነ ከልዩ ልዩ ምንጮች የምናገኛቸው ድጋ ፎች ከግምት ይካተታሉ። ለሚከተሉት ጥቂት ቁልፍ ነጠቦች የድርጊት መርሃ ግብር ሲዘጋጅ ሊታወሱ የሚገባቸው ናቸው። የግብ ግልጽነት፡-• የታቀዱት ተግባራት ሲከናወኑ የሚጠበቀው ውጤት ከወዲሁ ግልጽ ሆኖ እንዲታይህ አ ድርግ። ሊለኩ የሚችሉ ጠቋሚዎችን አስቀምጥ፤ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን እንደ የጊዜ እጥረት፣ የገ ንዘብና የቁሳቁስ ወይም የሰው ሀብት እጥረት የመሳሰሉትንና የተጠበቀው ግብ ለመድረስ ወይም የታሰበው ን ተግባር ለመፈፀም የሚያግዱህን በሙሉ መለየት፣ የድርጊት ዝርዝር፡-• አእምሮ ውስጥ የመጡልህን ሀሳቦች፣ ድርጊቶችንና አማራጮች በዝርዝር መፃፍ፤ ቅ ደም ተከተላቸውን ወይም ምክንያታቸውን ለማስቀመጥ አለመሞከር፤ እንደአመጣጣቸው በወረቀት ላይ ማ ስፈር፣ ዝርዝሩን መተንተን፣• ቅደም ተከተሉን ማስተካከልና የማያስፈልጉትን ማስወገድ፡- እንደአመጣጡ የተፃፈውን ዝርዝር ሀሳቦችን ከልብ መመልከት፣ ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉትን ሀሳቦች መለየትና አላስፈላ ጊና ግልጽ ያልሆኑትን ሀሳቦች ማስወገድ። በመጨረሻም ሊተገበሩ የሚችሉ ዝርዝር ሀሳቦችን መለየት፣ የተገኘውን ዝርዝር ወደ ዕቅድ መለወጥ፡-• የመጨረሻውን የድርጊት መርሃ ግብር ለማዘጋጀት በሚረዳ መ ልኩ ሊሟሉ በሚገባቸው በየደረጃው በሚገኙ አካሄዶችና ድርጊቶች ላይ መወሰን። በመጨረሻም ዕቅዱን በ ጥንቃቄ መመርመርና ለአጠቃቀም ምቹና ቀላል እንዲሆን ማመቻቸት፣ መከታተልና መከለስ፡-• አዳዲስ በሚገኙ መረጃዎች፣ በሚያጋጥሙ ጋሬጣዎችና በትግበራ ላይ ለሚመጡ አ ዳዲስ ክስተቶች ዙሪያ እቅዳችንን ለመከታተልና ለመከለስ ጊዜ መስጠት፣ የድርጊት መርሃ ግብሩን የት ላስቀምጠው? የድርጊት መርሃ ግብሩ በሥራ ቦታ በመደበኛነት በቀላሉ ሊታይ የሚችልበት ሥፍራ ላይ ሊቀመጥ ይገባዋል። በ ልማት ሠራተኞች፣ በወረዳ ባለሙያዎች ወይም በአጋሮቻቸው የተዘጋጀ የድርጊት መርሃ ግብር በገበሬዎች ማሰ ልጠኛ ማዕከሎች ወይም በገጠር ልማት ቢሮዎች ሊቀመጥ ይችላል። የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች በዋናው ዕቅድ ውስጥ እንዴት ይካተታሉ? በተግባር መርሃ ግብር ዝግጅት ወቅት የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ ማስገባት የፕሮጀክት ግብረ ኃይ ሉን፣ ተበዳሪዎችንና ተባባሪዎች የገጠር ልማት ፕሮጀክቶች ሲዘጋጅ የሥርዓተ ፆታ አሳሳቢ ሁኔታዎችን እንዲለ ዩና የገጠሩን ድሃ ሕብረተሰብ የኢኮኖሚ አቅምን ለማሻሻል ማለት ሴቶችን በእጅጉ ተጠቃሚ በማድረግ የራሳቸው ንና የቤተሰባቸውን የኑሮ ደረጃ እንዲያሻሽሉ ይረዳል። ከመርሃ ግብር ዝግጅት አስቀድሞ የሥርዓተ ፆታ የሥራ ድርሻና ኃላፊነት፣ ሴቶችና ወንዶች በማህበረሰቡ ውስ ጥ ያላቸው ቦታ፣ አስፈላጊ ንብረቶች ላይ ያላቸው የመጠቀምና የመቆጣጠር አቅም መረጃዎች ተሰብስበው ሊተ ነተኑ ይገባል። ከሁሉም በላይ በግብርና ልማት እንቅስቃሴ በጥቅሉና በተለይም በገበያ ተኮር ግብርና ውስጥ የሴ ቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚረዱ መልካም አጋጣሚዎችንና አሳሳቢ ችግሮችን መለየትና ለመርሃ ግብር ዝግጅቱ መጠቀም ያስፈልጋል። 74 እነዚህ ትንተናዎች ሴቶችን በፕሮጀክቱ አፈፃፀም ውስጥ እንዴት እንደምናልማቸው፣ የቀረበው የፕሮጀክት ዓላማ ና ዘዴ የውጤታማነት ዕድሎቹ የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ላይ እንዲሆን መሻሻል ያለበት ከሆነና እንዲሁም ደ ግሞ የሴቶችን ተጠቃሚነትን የሚሸረሽሩ ሁኔታዎችን በተቻለ አቅም ለማሳነስ የሚረዱ ጠቋሚዎች ናቸው። በት ንተናው ውስጥ ሊታሰቡ የሚገባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ይገኙበታል። ማምረት የፕሮጀክቱ ተግባራት የሴቶችን ምግብ የማምረት ጥረት ይቀይረው ይሆን? • የሰብል ዓይነት ላይ ለውጥ ማድረግ የሴቶችን ልማዳዊ ገበያ ይጎዳ ይሆን? • አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የሴቶችን ልማዳዊ የገቢ ማግኛ ሥራ ያስቀሩ ይሆን? • የፕሮጀክቱ ተግባራት ወይም ውጤቱ የሴቶችን የሥራ ጫና ይጨምር ይሆን? • በማምረት ሂደት ውስጥ የሴቶችን የሥራ ድርሻና እኩል ተጠቃሚነት የሚጎዱ ለውጦችን ለማከካስ ፕሮጀ• ክቱ ምን በማካካሻ ጠቀሜታዎችን አስተዋውቋል? ስልጠና የሴቶችን የሥራ ድርሻ የሚጎዱ የማምረት ሂደት ለውጦችን ለማቅለል ወይም የሴቶችን እኩል• ተጠቃሚነት ለማሻሻልና ከማምረት ሂደቱ ወይም ሙያው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ምን አይነት ስልጠና ሊካተት ይገባዋል? ፕሮጀክቱ የተጠቃሚውን ህብረተሰብ የአኗኗር ዘይቤ በፍጥነት መለወጥ ይችላል? ለምሳሌ፡- ከእጅ• ወደ አፍ ከማምረት አልፎ ለገበያ ማምረት ማስቻል፣ ምን ዓይነት ስልጠና ሴቶችን ከለውጡ ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው ይችላል?• ሌሎች ተጨማሪና ደጋፊ ፕሮግራሞችን እንደ ጤና፣ ትምህርት፣ የማህበራዊ ኑሮ ዕድገት• ለማካተት አቅሙ አለ ወይ? ሴቶችን የስልጠናው ተጠቃሚ ለማድረግ ከወንዶች ተነጥለው ብቻቸውን መሰልጠን ይኖርባቸው ይሆን?• ስልጠናዎች ሴቶችን ሌሎች ሃላፊነቶችን የሚወጡበትን ሰዓት ከግምት ያስገቡና ለዚሁ የተመቻቹ መሆን • ይኖርባቸዋል? የሴቶችን ስትራቴጂካዊ የሥርዓተ ፆታ ፍላጎት ለማሟላትና በውሳኔ አሰጣጥ ላይ የራሳቸውን ተፅዕኖ ማሳ• ደርና መቆጣጠር እንዲችሉ ለማድረግ ምን አይነት ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል? (ለምሳሌ የእርሻ መሳሪያዎ ች ጥገናና እድሳት ስልጠና)? ሴቶችም ወንዶችም ፕሮጀክቶች የሚሰጧቸውን ጥቅሞች ተረድተውና ተከፋይ እንዲሆኑ የገጠር ሠርቶ ማ• ሳያ እርሻዎች ጠቀሜታ አላቸው ወይ? ፕሮጀክቱ ላልተማሩ ወንዶችና ሴቶች የተለየ የማስተማሪያ ዘዴና የመገናኛ መንገድ ያስፈልገው ይሆን?• የገጠር ሴቶችን የገቢ ማስገኛተግባራት ከመደገፍ አንፃር ፕሮጀክቱ ሥራ አመራረጥ፣ ሂሳብ አያያዝንና የሥ• ራ ፈጣሪነት ሙያን፣ እንዲሁም ገበያ ጥናትን የመሳሰሉ ስልጠናዎችን ማካተት ይችላል? መረጃ መረጃዎችና የኤክስቴንሽን አገልግሎቶች ሴቶች ዘንድ ይደርሳሉ? • የፕሮጀክቱን ተግባራት በተመለከተ መረጃዎች በቀጥታ ለሴቶችና ለወንዶች ይሰጣሉ? የፕሮጀክቱን• መልዕክት ለሴቶች ለማድረስ የተለየ የመገናኛ ዘዴ ያስፈልግ ይሆን? (ሴቶች ለሴቶች የመገናኛ አገልግሎት ወይም የገጠር የሴቶች ቡድኖችን መጠቀም)? ፕሮጀክቶች የሴቶችን እኩል ተጠቃሚነት ለማራመድ መልእክቶቹ ከባህሉ ጋር በተጣጣመ መንገድ የተዘ• ጋጁ ናቸው ወይ? ተሳትፎ የፕሮጀክቱ ዓላማ ሲዘጋጅ ሴቶችን አማክረዋል? ተሳትፎስ አድርገዋል? • በፕሮጀክቱ ቀረፃና እቅድ ውስጥ ሴቶች ተሳትፎ አድርገዋል? • 75 ሴቶች በአካባቢ ውሳኔ አሰጣጥ የማይከፈሉ ከሆነ፣ ፕሮጀክቱ ውስጥ ባሉ የውክልና ዘዴዎች• አማካይነት ሊከፈሉ ይችላሉ? (ለምሳሌ እንደ ማህበራዊ ዕድገት ቡድኖች፤የዚህ ዓይነቱ ቡድን የሚችል ከሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ዕድል ይኖራል? ሴቶችን በፕሮጀክቱ እንዲሳተፉ ለማድረግ የሴቶች መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅቶች ሊቀጠሩ• ይችላሉ? የመጓጓዣ ችግር የሴቶችን ተሳትፎ የሚገድብ ከሆነ ፕሮጀክቱ በዚህ በኩል ራሱን ማደራጀት ይችላል?• ሴቶች እንዲሳተፉ ለማበረታታት ፕሮጀክቱ የማነቃቂያ ቡድን ያስፈልገው ይሆን? • አቅርቦትና ተደራሽነት የፕሮጀክቱ ደንቦችና ሁኔታዎች ሴቶች መሬት እንዳይኖራቸው ወይም እንዳያገኙ፣ ብድር እንዳይቀበሉ፣ የ• ህብረት ሥራ ማህበራት አባል እንዳይሆኑ፣ ምርት እንዳይሸጡ፣ ክፍያ እንዳይቀበሉ የሚከለክለውን ሕጋዊ ገደብ ማሸነፍ የሚችሉ ናቸው? የሴቶች የንብረት ማፍራት መብት በአሁኑ ጊዜ ከወንዶች እኩል ባይሆን ፕሮጀክቱ የሴቶችን እኩል ተጠቃ• ሚነት ሊያሳድግ ይችላል? (ለምሳሌ አዲስ የመሬት ስሪት ቢዘረጋ ፕሮጀክቱ የባለቤትነት ማረጋገጫው በቤ ተሰብ ደረጃ በጋራ በሴትና በወንድ ስም እንዲሆን እንዲሁም በሴት በሚመራ ቤተሰብ ውስጥ በሴቷ ብቻ እ ንዲሆን ማድረግ ይችላል) በፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ ውስጥ በቀጥታ ተሳትፎ ላላቸው ሴቶች ሌሎች ሰፋ ያሉ ሊቆጠሩ የሚችሉ የቁሳዊ • ግብአቶች አቅርቦትና አገልግሎት መስጠት የመሳሰሉ እቅዶች ሊታሰቡ ይችላሉ ወይ? ለተጨማሪ ንባብ ጥቂት የኢንተርኔት ምንጮች Time Management-guide.com 2002.http://www.time-management-guide.com/plan.html Mind Tool Ltd. 1995-2008. http://www.mindtools.com/pages/artcle/new HTE_4.htm Action planning: http//www.careers.ed.ac.uk?CCPP/Making_Plans/action_plan.htm 76 የተዘጋጀ ጽሁፍ 14፡ ሥርዓተ ፆታንና ኤችአይቪ/ኤድስን ከክትትልና ግምገማ ዘዴዎች ጋር ማቀናጀት ሥርዓተ ፆታንና ኤችአይቪ/ኤድስን ከክትትልና ግምገማ ዘዴዎች ጋር ማቀናጀት የሥራ አመራሩን ቁልፍ መሳሪያ ና የልማድ ባለሙያዎች፣ ኤክስፐርትቶች፣ ሠራተኞችና ተባባሪዎች የገጠር ልማትን በጥቅሉና የገበያ መር ልማ ት ፕሮጀክቶችን ሲቀረፁ የሥርዓተ ፆታና የኤችአይቪ ጉዳዮችን ማየት እንዲችሉ እገዛ ያደርጋል። ከሁሉም በላይ ጤናማ አሠራር ለማምጣት ውጤትን፤ ግኝትንና ተፅኖን ለመከታተልና ለመገምገም ያስችላል። ሥርዓተ ፆታንና ኤችአይቪ/ኤድስን ከክትትልና ግምገማ ዘዴዎች ጋር እንዴት ማቀናጀት ይቻላል። በገጠር ልማ ት ፕሮጀክት ውስጥ ውጤታማና ሥርዓተ ፆታና ኤችአይቪ ላይ ያተኮረ የክትትልና የግምገማ ሥርዓት ለመዘር ጋት የሚከተሉት አበይት ተግባራት በፕሮጀክቱ ውህደት ውስጥ ሊጤኑ ይገባል። ሥርዓተ ፆታ ኤችአይቪ/ኤድስ ደረጃ 1- መለየትና መዘጋጀት ደረጃ 1- መለየትና መዘጋጀት የምርጥ ተሞክሮ ዳሰሳው ወይም መሠረታዊ ለአካባቢው የኤችአይቪ አደጋና ለኤድስ • ጥናቱ ሥርዓተ ፆታ ላይ ያተኮረ መሆኑን ተጋላጭነት የምርጥ ተሞክሮዎች ጥናት ማረጋገጥ፣ መኖሩን ማረጋገጥ፣ የልማት ፕሮጀክቶች ጣልቃ ገብነት (intervention) የገበያ መር የግብርና ልማት የሚያሳድረውን• በወንዶችና በሴቶች ላይ ያለውን መልካም መልካም አጋጣሚ ወይም አሉታዊ ተፅዕኖ አጋጣሚ ወይም የአሉታዊ ተፅዕኖ አቅም ለመረዳት በቅድሚያ የኤችአይቪ አደጋና ለመረዳት ቅድሚያ የሥርዓተ ፆታ ጥናት ተጋላጭነት ትንተና ማድረግ፣ ወይም ትንተና ማድረግ፣ ባሉት መረጃዎች ላይ ተሞርክዞና ጉዳዩ ባሉት መረጃዎች ላይ ተሞርክዞና ጉዳዩ • የሚመለከታቸውን በማማከር ከሥርዓተ ፆታ ጋር የሚመለከታቸውን በማማከር ከኤችአይቪ ተዛማጅነት ያላቸውን ግቦችና ቅደም ተከተሎች /ኤድስጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ግቦችና መለየት፣ ቅደም ተከተሎች መለየት፣ ሥርዓተ ፆታን ከገበያ መር የግብርና ልማት ጋር ኤችአይቪ/ኤድስን ከገበያ መር የግብርና • ለማቀናጀት ተቋሟዊ አቅም ወይም ብቃት ላይ ልማትጋር ለማቀናጀት ተቋሟዊ አቅም ዳሰሳ ማድረግ፣ ወይም ብቃት ላይ ዳሰሳ ማድረግ፣ 77 ደረጃ 2- ማለምና መዳሰስ ደረጃ 2- ማለምና መዳሰስ ሥርዓተ ፆታ በግቦችና ዓላማዎች ውስጥ ኤችአይቪ/ኤድስ በግቦችና በዓላማዎች ውስጥ• የተካተተ መሆኑን ማረጋገጥ፣ መካተቱን ማረጋገጥ የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮችን ለማንቀሳቀስ እንዲሁም የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮችን ለማንቀሳቀስ• መሻሻሎችንና ግኝቱን ለመከታተልና ለመገምገም እንዲሁም መሻሻሎችንና ግኝቱን ለመከታተል የሚያስ ችል አቅም ለመገንባት ማቀድ፣ለመገምገም የሚያስች ል እቅድም ለመገንባት ማቀድ፣ • የክትትልና ግምገማ ዘዴ ማዘጋጀት፡- • የክትትልና ግምገማ ዘዴ ማዘጋጀት፡- ለውጤትና ለተፅዕኖ የሚረዱ ቁልፍ የሥርዓተ • ለውጤትና ለተፅዕኖ የሚረዱ ቁልፍ• ፆታ ጠቋሚዎችን መለየትና መምረጥ ጠቋሚዎችን መለየትና መምረጥ. የተሻለ ወይም ብቁ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ • የተሻለ ወይም ብቁ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ• መምረጥና ጊዜውን መወሰን መምረጥና ጊዜውን መወሰን. ደረጃ 3- መተግበር ደረጃ 3- መተግበር በተመረጡት ጠቋሚዎች ላይ ተሞርክዞ ሥርዓተ በተመረጡ ጠቋሚዎች ላይ ተመርዞ • ፆታ ነክ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ የኤችአይቪ/ኤድስ ነክ መረጃዎችን መሰብሰብ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ግምገማው ያሳየውን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ግምገማ• መሻሻል ከተቀመጠለት ዓላማ አንፃር መከታተል ያሳየውን መሻሻል ከተቀመጠለት ዓላማ በግኝቱ መሠረት እርማት እንዲደረግ ግብረ አንፃር መከታተል በግኝቱ መሠረት መልስ መስጠት፣ እርማት እንዲደረግ ግብረ መልስ መስጠት መሻሻሎች መኖራቸውን አሰሳና ከሥርዓተ ፆታ መሻሻሎች መኖራቸውን አሰሳና ከ • ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ውጤቶች ለማምጣት ሥርዓተ ፆታ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው እርማት ካስፈለገ እርማት ማድረግ፣ ውጤቶች ለማምጣት እርማት ካሰፈለገ እርማ ት ማድረግ የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮችን ጠቋሚዎች የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች ጠቋሚ ማለት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ከሥርዓተ ፆታ ጋር ተ ያያዥነት ያላቸውን ለውጦች አመላካች ማለት ይችላል። ስለዚህ የሥርዓተ ፆታ ስታቲስቲክስ ስለሴቶች አሀዛዊ መረጃዎችን ሲያቀርብ የሥርዓተ ፆታ ጠቋሚዎች ግን ባለው ማህበራዊ ደረጃ መሠረት ሴቶች ያሉበትን ደረጃ ቀ ጥተኛ መረጃ ያቀርባል(Johonson, 1985) የሥርዓተ ፆታ ጠቋሚዎች ምሳሌ በ”ሐ” አገር ከ82% ወንዶች እንዲ ሁም ከዛሬ አምስት ዓመቱ 30% እና 52% ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ 60% ሴቶች ከመኃይምነት ተላቀዋል። ስንት ወንዶችና ሴቶች፣ ከተለያዩ ጎሳዎች የመጡ ሰዎች፣ ከተለያዩ ዝርያዎች እና ከተለያዩ የሀብት ደረጃ • የተገኙ ሰዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ይሳተፋሉ? በተለያየ የፕሮጀክቱ ደረጃዎች ውስጥ የሴቶችና የወንዶች አስተዋጽኦ ደረጃ ምን ያህል ነው? (በመንግስታ• 78 ዊ፣ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፣ አገር ውስጥ ባለጉዳዮች)፣ በቁልፍ ተግባራት ውስጥ የአካባቢ ባለጉዳዮች፣ ሴቶችና ወንዶች ተሳትፎ ደረጃ ምን ያህል ነው? (ለምሳሌ • የፕሮጀክቱ ወርክ ሾፖቹ ላይ የሚሳተፉ ወንዶችና ሴቶች ቁጥር፣ በሥልጠናዎች ላይ የሚሳተፉ ወንዶችና ሴቶች ብዛት፣ በሰብል ፍተሻ ላይ የሚሳተፉ ወንዶች ሴት ገበሬዎች ቁጥር)፣ የኤክስቴንሽን አገልግሎቶች አሰጣጥ እንዲያድግ የሚጣጣሩ ሴት የልማት ሠራተኞች ቁጥር፣• ገጠር ሴቶችን ማለትም በሴቶች የሚመራ ቤተሰብን ወይም በወንዶች የሚመራ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ሴት • አርሶ አደሮችን አቅም ለማሳደግና ሌሎች አገልግሎት ለመስጠት የተነደፈ ስትራቴጂ አለ ወይ? በሴቶች የሚመራ ቤተሰብና ያገቡ ሴቶች መረጃ በመስጠት፣ በስልጠና ወይም በሥራ ፈጣሪነት የታሰቡ አ• ሉ? በገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ደረጃ የሴት ሰልጣኞች ቁጥር መጨመር፣ የካሪኩለም እንደገና መታየትና • መሻሻል እንዲሁም የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮችን ለገበሬዎች በሚሰጥ ስልጠና እንዲካተት ማድረግ፣ በችግሮች መለየት ተግባራት ውስጥ ወይም በቅደም ተከተል አወሳሰን ውስጥ፣ በማቀድና በትግበራ• በመሳሰሉት ጥናቶች ውስጥ የሚሳተፉ ሴት አርሶ አደሮች ቁጥር፣ የሴቶችን ተሳትፎ ለማጎልበት የተወሰዱ እርምጃዎችና የሴት ተመራማሪዎችን ቁጥር ለማሳደግ የተነደፈ • ስትራቴጂ መኖር፣ የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮችን ጠቋሚዎች የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮችን ጠቋሚዎች ማለት በማህበረሰብ ውስጥ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ከኤች አይቪ/ኤድስ ጋ ር ተያያዥነት ያላቸው ለውጦችን አመላካች ማለት ይቻላል። ስለዚህ የኤች አይቪ/ኤድስ እስታትስቲክስ በማህበ ረሰቡ ውስጥ ስለኤችአይቪ/ኤድስ አሀዛዊ መረጃዎችን ለምሳሌ በምን ያህል መጠን እንደሚገኝ ሲያመለክት፤የኤች አይቪ/ኤድስ ጠቋሚዎች ግን በማህበረሰቡ ውስጥ. ኤች አይቪ/ኤድስ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ቀጥተኛ መረጃ ይሰጣል። የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳዮች ጠቋሚ ምሳሌ ሊሆን የሚችል ለማቅረብ 1.3 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን በኤ ች አይ ቪ ተይዘዋል፣ በኢትዮጵያ የገጠሩ ማህበረሰብ ውስጥ የኤች አይ ቪ የመገኘት ደረጃ 1.8% ነው፤ ከወጣ ቶችና ጎልማሶች (15-49 ዕድሜ ክልል) ሞት ውስጥ 35% በኤድስ ምክንያት ነው። ስንት በኤችአይቪ/ኤድስ የተያዙና የተጎዱ ቤተሰቦች ከተለያዩ ጎሳዎች፣ ዝርያዎችና የተለያየ የሀብት ደረ• ጃ ላይ ያሉ ከባለጉዳዩ ጋር ይሳተፋሉ፣ የአካባቢ ባለድርሻ አካላት በቁልፍ ተግባራት ላይ ያላቸው የተሳትፎ ደረጃ ምን ያህል ነው? ለምሳሌ ከ• ኤችአይቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ማህበራት፣ የኤችአይቪ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮዎች የልማት ሠራተኞችና የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች (ለምሳሌ ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ከሚኖሩ ማህበራት ውስጥ በወርክሾፕ ፕሮጀክቶችና በስልጠናዎች ላይ የሚሳተፉ ወንድና ሴት ቁጥር ምን ያህል ነው?) የኤክስቴንሽን አገልግሎት ውስጥ የሚሳተፉ ወይም የሚደገፉ በወላጅ አልባ የሚመሩ፣ በሴቶች የሚመ• ሩ፣ በአያቶች የሚመሩ ቤተሰቦች በቁጥር ምን ያህል ናቸው? ኑሯቸውን መምራት እንዲችሉ በኤችአይቪ/ኤድስ የተያዙና የተጎዱ ቤተሰቦችን ወይም ግለሰቦችን አቅም • ለመገንባት የተነደፈ ስትራቴጂ አለ? በኤችአይቪ/ኤድስ ዙሪያ ግንዛቤ ለማዳበርና የኤችአይቪ ስርጭትን ለመቀነስ የሚያስችል ስትራቴጂ መኖ• ር፣ በኤችአይቪ የመያዝ አደጋን ለመቀነስ የተነደፈ ስትራቴጂ መኖር፣• 79 አባሪ 1፡- የሥልጠና ቅምሻዎች፡- ቅድመ ሥልጠና ለዕረፍት ለሚወጡ ቡድኖች በቂ ቦታ ያለው፣ የወንበር አቀማመጥ እንደልብ ማስተካከል የሚያስችል ለም• ሳ ቅርበት ኖሮት ሰዓት ለመቆጠብ የሚረዳ የመሰብሰቢያ ቦታ መፈለግ፣ ንጽህናውንና አቀማመጡን ለማየት ከስልጠናው አንድ ቀን በፊት ቦታውን መጎብኘት፣ • ስልጠናው ሲሰጥ፡- የስልጠናውን ዓላማ በማስረዳት ጀምር፣ • በተለያዩ ክፍለ ጊዜዎች መሃል የቀደመውንና የሚቀጥለውን በማገናኘት ላይ ትኩረት አድርግ• ለአጠቃላይ ፕሮግራሙ የሚረዱ ተጨማሪ ንባቦችን ማጣቀስ፣ አስፈላጊ በሆነበት ቦታ የዕይታ ዘዴ ወይም በማየት እንዲረዱ ማድረግ፣ • ሁሉንም ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን እንዲያቀርቡ አትጠይቅ ከዛም ከዚህም ምላሽ ማግኘት• ይጠቅማል፣ በሰዓት መጠቀም የትምህርቱን ይዘት ካለው ሰዓት ጋር እንዲጣጣም ማድረግ፣• ተሳታፊው ንቁ እንዲሆን የስልጠናውን ትኩረት ጉዳዮች በክፍሉ ዙሪያ ማዞር፤ የክፍሉን የተለያዩ• ቦታዎች ለተለያየ ተግባራት መጠቀም፣ ዝምታ የሚያጠቃቸውን ተሳታፊዎች በተለይ ሴቶችን በሁሉም ፊት ትምህርት እንዲያቀርቡ• ማደፋፈር፣ የተሳታፊዎችን ንቃት ለማግኘት አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ላይ ድምጽን ከፍ ማድረግ፣• የቡድኑ ደንቦች መከበራቸውን መከታተል፣ • ለየክፍለ ጊዜው ዋና ዋና ነጥቦችን የሚያነሳ አጫጭር ማጠቃለያ መደረጉን ማረጋገጥ፣• የመስክ ሥራ በጉዞ ላይ የሚጠይቀውን ጊዜ ለመቀነስ ለመሰብሰቢያ ቦታ ቅርብ የሆነ ማህበረሰብ ምረጥ፣• ለመንደርደሪያነት የቀረበው ሰዓት ለሁሉም ማህበረሰብ አባላት ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ካልሆነ• ማስተካከል፣ ማህበረሰቡ ከመስክ ሥራው የማይሆን ውጤት እንዳይጠብቅ ጥንቃቄ ማድረግ፣ • ተሳታፊዎች አስፈላጊውን መረጃ ሁሉ ማሰባሰባቸውን ለማረጋገጥ አስቀድመው በትንተና ደረጃ• እንዲያስቡ በመስክ ሥራው ላይ ማበራታት፣ ከመስክ ሥራው ሲመለሱ ራሳቸውን እንዴት እንደሚያቀርቡ ማለት የጉብኝቱን ዓላማ ማን• እንደሚያስረዳ፣ የመስክ ሥራው ፕሮግራም አደረጃጀት (በትናንሽ ቡድን ወይም በጥቅል) ማህበረሰቡን እንዴት በቡድን እንደሚከፋፈሉ አስቀድመው እንዲያስቡ ማድረግ፣ ሁሉም ተሳታፊ ባለበት ግብረ መልስ ሲሰጥ ሴቶች እንዲሳተፉ ማበረታታት፣• ተሳታፊዎች የመረጃ ትንተናቸውን ሲጨርሱ ተገላጭ ቻርቶችን፣ ካርታዎችንና የመሳሰሉትን• ለማህበረሰቡ ቅርብ ወደሆነው የገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከል መመለስ፡፡ ማስተባበር/ የሥልጠና ቡድን በቡድን አባላት መሀል ግትርነት መኖር የለበትም፣ • ለእያንዳንዳችን አስተያየት ወይም ሀሳብ ከበሬታ መስጠት፣• 80 የእይታ ድጋፎችን መጠቀም የትምህርቱን አወራረድ በቀላሉ ያመላክታል የኤችአይቪ/ኤድስ ትንተና ምን ያደርግልናል? ማህበረሰቡ በኤችአይቪ/ኤድሰ ተፅዕኖ ሥር ነው? ስዕል 1. የኤች አይ ቪ/ኤድስ ትንተና አስፈላጊነት Use of visuals aids facilities the flow of topics Figure 1: Why HIV/AIDS analysis is important አንድ ነገር ማድረግ እፈልጋለሁ? ነገር ግን ምን ላድርግ? የኤችአይቪ/ኤድስ አፈጣጠር ምን ይመስላል? ማህበረሰቡ በመጠቃት አደጋ ላይ ነው? ተገቢውን ምላሽ መለየት 81 የኤችአይቪ/ኤድስ መተላለፊያ መንገድ በኤችአይቪ መያዝ ከኤድስ ጋር የተዛመደ በሽታ ከኤድስ ጋር የተዛመደ ሞት ስዕል 2. የኤችአይቪ/ኤድስ መተላለፊያ መንገድ Figure 2: HIV/AIDS pathway የመያዝ አደጋን ለመከላከል ምን ማድረግ እንችላለን? 2 ጥንቃቄ የጐደለው የግብረ - ስጋ ግንኙነት ከእናት ወደ ልጅ- የተበከለ የሰውነት ፈሳሽ- ሰዎች በቫይረሱ የመያዝ አደጋ ላይ ምን ይጥላቸዋል? 1 በሽታው ተባብሶ ወደ ኤ ድስ ደረጃ እንዳይደርስ ም ን ማድረግ እንችላለን? 4 በሽታውን ምን ያባብሰዋል? ወደ ሞት ያደርሳልን? 3 ፈጣን የሰውነት ክብደት - መቀነስ፣ ትኩሳት፣ ደረቅ ሳል፣ ተቅማጥ የዕጢዎ ች ዕብጠት፣ ማሳከክ፣ መ ርሳት በኤድስ ምክንያት ቁልፍ የ ቤተሰብ አባል ሲሞት ቀሪ ውን ቤተሰብ ለመርዳት ም ን ማድረግ እንችላለን? ለኤድስ ተፅዕኖ ቤተሰብን የ ሚያጋልጡት ምንድን ናቸ ው? 5 * ኤችአይቪ ምርመራ 82 የገጠሩ ማህበረሰብ የቡሬ ገጠር ኤችአይቪ 2.1% ስዕል 3. በገጠሩ ማህበረሰብ ኤች አይ ቪ የሚያስይዙ ምንጮች ለኤችአይቪ የሚያጋልጡ ቦታዎች 10-20% አስተላላፊ ድልድይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ወጐች ልማዶችና ባህሎች ጥንቃቄ የጐደለው የግብረሥጋ ግንኙነት- ከእናት ወደ ልጅ- የተበከሉ የሰውነት ፈሳሾች- 83 Figure 3: Sources of risk of HIV infection in rural communities 84