"ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ © አለም አቀፍ የድንች ምርምር ማዕከል፣ አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጲያ ፣ እ.ኤ.አ 2020 ዓ.ም ISBN: 978-92-9060-548-5 DOI: 10.4160/9789290605485.v4 የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የህትመት ውጤቶች የተለያዩ የምርምርና የልማት መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች በስፋት ያደርሳሉ፡፡ ተጠቃሚዎች እነዚህን መረጃዎች ለራሳቸው በሚመች ሁኔታ እንዲጠቀሙ ወይም እንዲያራቡ ማዕከሉ ያበረታታል፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ሕትመቶቹ ባለቤት የማዕከሉ መረጃዎች ጥቅም ላይ በዋሉባቸው ሌሎች ሕትመቶች ላይ የማዕከሉ ስም በምስጋና እንዲገለጽና የሕትመቶቹ ግልባጭ እንዲደርሰው ይፈልጋል፡፡ የሕትመቶቹን ግልባጮች ለማዕከሉ ሕዝብ ግንኙነትና ማስታወቂያ መምሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ እንዲላኩልን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ International Potato Center P.O. Box 1558, Lima 12, Peru cip@cgiar.org • www.cipotato.org ጥራዝ 4 የስልጠና መምሪያ በሌሎች ሕትመቶች ላይ ለመጠቀም ትክክለኛው አገላለጽ የሚከተለው ነው፡፡ Stathers, T., Carey, E., Mwanga, R., Njoku, J., Malinga, J., Njoku, A., Gibson, R., Namanda, S. (2013). Everything You Ever Wanted to Know about Sweetpotato: Reaching Agents of Change ToT Manual. 4: Sweetpotato production and management; Sweetpotato pest and disease management. International Potato Center, Nairobi, Kenya. vol.4. የስልጠና መምሪያው የአማርኛ ዝግጅት አስተባባሪዎች የአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል ዋና ሳይንቲስት ዶ/ር ሮላንድ ብሮወር - "የተሻለ አመጋገብ ለተሻለ ጤና" ፕሮጀክት አስተባባሪ አቢዮት አራጋው - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የምርምር ኦፊሰር የመምሪያው የአማርኛ ትርጉም ኤዲተሮች አቢዮት አራጋው - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የምርምር ኦፊሰር አሸብር ክፍሌ - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የምርምር ኦፊሰር ዶ/ር ብርሃኑ ቢያዝን - በአለም አቀፍ ሰብል ምርምር ተቋም በደረቃማ አካባቢ (ኢክሪሳት) ከፍተኛ የምርምር መኮንን ምሕረቱ ቸርነት - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል የምርምር ሥራ አመራር አስተባባሪ የመምሪያው የአማርኛ ንድፍና ሽፋን ዝግጅት ፍሬዘር አስፋው - በአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል ዳታቤዝ ማኔጅሜንት ስፔሻሊስት የመጀመሪያ ህትመት ሰኔ 2012 ዓ.ም. CIP thanks European Union for funding the production of this manual. CIP thanks all donors and organizations that globally supports its work through their contributions to the CGIAR Trust Fund: www.cgiar.org/funders Copyright 2020 © International Potato Center. All rights reserved. This publication is copyrighted by the International Potato Center (CIP). It is licensed for use under the Creative Commons Attribution 4.0 International License መግቢያ ባለፉት አስር አመታት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ዘንድ የስኳር ድንች ሰብል ፍላጎት እየጨመረ፣ ሰብሉ ላይ የሚሰሩ ፐሮጀክቶች ቁጥር እያደገ እንዲሁም ስለሰብሉ የተሻሻለ አመራረት፣ አያያዝና አጠቃቀም ላይ የሚጠየቁ የስልጠና ድጋፎች እየጨመሩ መጥተዋል፡፡ ይህንን እያደገ የመጣ ፍላጎትን ለመመለስ የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከልና በየአገራቱ ያሉ የብሄራዊ ምርምር ተቋማት ተመራማሪዎች ተበታትነው ያሉ የስልጠና ጹሑፎችን በማሰባሰብ ከ1-3 ቀናት የሚፈጁ የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ የሚነሱ ፍላጎቶችን ለመመለስ የዚህ አይነት አቀራረብ ዉስንነት እንደተጠበቀ ሆኖ ምሉዕ የሆኑ የስልጠና መምሪያዎች እስከአሁን ድረስ አልተዘጋጁም፡፡ "የለውጥ ሐዋርያትን መድረስ" የተሰኘው ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም መጀመር ሁኔታዎች በመሰረታዊነት እንዲቀየሩ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ በአለም አቀፍ የድንች ምርምር ማዕከልና በሄለን ኬለር ፋውንዴሽን ትብብር የተተገበረ ሲሆን ስለብርቱካናማ ስኳር ድንች አስፈላጊውን ግንዛቤ ለመፍጠርና ያሉ ሃብቶችን በሰብሉ ላይ በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ለማንቀሳቀስ እንዲቻል አስፈላጊውን አቅም ለመገንባት ያለመ ነበር፡፡ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በቫይታሚን ኤ የበለጸገውን የብርቱካናማ ስኳር ድንች ስርጭትና አጠቃቀም ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ መተግበር እንዲችሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ሰራተኞች አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል፡፡ አጠቃላይ ግቡ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ፣ ደቡብ አፍሪካና ምዕራብ አፍሪካ ክፍለ-አህጉራት በስኳር ድንች አመራረትና አጠቃቀም አዳዲስ ግኝቶች ዙሪያ ለከፍተኛ የስርጸት ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት የሚያስችል አቅም ዘላቂ በሆነ መንገድ መፍጠር ነው፡፡ ስለሆነም "ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" ስልጠናን እንዲሰጡ የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል በሞዛምቢክ፣ ታንዛኒያና ናይጄሪያ አገር በቀል ተቋማትን ለይቷል፡፡ በመጀመሪያው ስልጠና ወቅት የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል ከአገር በቀል ተቋማቱ ጋር በቅርበት ሰርቷል፡፡ በሁለተኛው ዙር ስልጠና አገር በቀል ተቋማቱ ከማዕከሉ ተመራማሪዎች በተሰጣቸው ድጋፍ የስልጠናውን ተግባራት መምራት የቻሉ ሲሆን በሶስተኛ ዙር ስልጠና ወቅት ደግሞ ከማዕከሉ በተደረገላቸው የገንዘብ ድጋፍ አገር በቀል ተቋማቱ ስልጠናውን ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ማከናወን ችለዋል፡፡ በቀጣይ አመታትም ይህ ስልጠና ሳይቋረጥ በአገር በቀል ተቋማቱ እንደሚቀጥልና በወጪም ረገድ ራሱን እንደሚችል ይታመናል፡፡ የዚህን ስልጠና ይዘት በማዘጋጀት ረገድ የግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሃብት ኢንስቲትዩት ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ስታተርስ ያሉትን የስልጠና መምሪያዎች በመከለስ፣ ከተለያዩ የስኳር ድንች ተመራማሪዎች የተገኙ አዳዲስ ዕውቀቶችን በማካተትና ጠንካራ የ"በመስራት- መማር" ተግባራትን በመንደፍ ከፍተኛ ትበብር አድርገዋል፡፡ እኚህ ሳይንቲስት ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ በ2005 ዓ.ም ከኡጋንዳ ብሔራዊ የግብርና ምርምር ድርጅት ተመራማሪዎችና ኬንያ ከሚገኘው የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት የአይ.ፒ.ኤም ማስተባበሪያ ጋር በመሆን ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት የሚሆን ሁሉን አቀፍ የአርሶ አደሮች የመስክ ትምህርት ቤት መምሪያ አዘጋጅተዋል፡፡ በተጨማሪም ይህንን ስልጠና በማዘጋጀት ሂደት ዶ/ር ስታተርስ የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ተመራማሪዎች የሆኑትን ሮበርት ሙዋንጋ፣ ቴድ ካሬይ፣ ጃን ሎው፣ ማሪያ አንድራዴ፣ ማርጋሬት ማክኢዋን፣ ጁዴ ጆኩ፣ ሳም ንማንዳ፣ ሳሚ አጊሊ፣ ጆናታን ኩምቢራ፣ ጆይስ ማሊንጋና ጎድፍሬይ ሙሉንጎን የኤች.ኬ.አይ የስርዓተ ጾታ ስፔሻሊስት የሆኑትን ሶኒ ዴቪድና አብረዋት የሚሰሩትን የኤን.አር.አይ ባልደረቦች ሪቻርድ ጊብሰን፣ ኦሬሊ ቤኮፍና ኬት ቶምሊንስን አማክረዋል፡፡ በዚሁ ሂደትም እኒሁ ሳይንቲስት የስልጠና ዶክመንቶችን ከዶናታ፣ የመጨረሻ ተጠቃሚዎችን መድረስና ሌሎች ፕሮጀክቶች ለዚህ ስልጠና በሚስማማ መልኩ በመውሰድ አዘጋጅተዋል፡፡ ስልጠናው እ.ኤ.አ በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ከተካሄደና የስልጠና መምሪያውም ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ የሰልጣኞችንና አመቻቾችን ፍላጎት ባማከለ ሁኔታ የተከለሰ ሲሆን ለስልጠናው አጋዥ የሆኑ የፓወር ፖይንት ገለጻወችም እንዲታከሉበት ተደርጓል፡፡ ይህ ደረጃውን የጠበቀ የስልጠና መምሪያና አጋዥ ዶክመንቶች እንዲዘጋጁ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ስላደረጉ ዶ/ር ስታተርስን በዚህ አጋጣሚ እናመሰግናለን፡፡ የዚህ ስልጠና ደረጃ የሚመጥነው ሌሎችን በተመሳሳይ ሁኔታ ሊያሰለጥኑ የሚችሉ ከፍተኛ የስርጸት ባለሙያዎችንና የእርሻ ሥራ አስኪያጆችን ነው፡፡ ስልጠናውን በየጊዜው የሚመጡ አዳዲስ ዕውቀቶችና የተሳታፊዎች ግብረ-መልሶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በየአመቱ ለመከለስ ታሳቢ ተደርጓል፡፡ በዚህ ሂደት በመጪው ጊዜያት ንቁና በስኳር ድንች ዕውቀት የበለጸገ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ዕቅድ ተይዟል፡፡ ይህ "ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" ስልጠና ኮርስ ስኳር ድንች ለገቢ ማስገኛና ጤና ማሻሻያ እንቅስቃሴን ዓላማዎች ለማሳካት አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ መተግበር የተጀመረው እ.ኤ.አ በ2009 ዓ.ም ሲሆን ዋና ግቡም እ.ኤ.አ በ2020 ዓ.ም ከሰሃራ በታች በሚገኙ 16 አገራት የሚገኙ 10 ሚሊዮን ቤተሰቦች ኑሮን በዘርፈ-ብዙ የስኳር ድንች ዝርያዎች ጥቅም ማሻሻል ነው፡፡ የአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው፣ በአለም አቀፍ የድንች ምርምር ማዕከል የስኳር ድንች ለገቢ ማስገኛና ጤና ማሻሻያ እንቅስቃሴ መሪ እ.ኤ.አ 2014 ዓ.ም i ምስጋና ይህ የስልጠና መምሪያና ሌሎች አጋዥ ዶክመንቶች የተዘጋጁት በአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው የቅርብ ዕገዛ በዶ/ር ታንያ ሰታተርስ ነው፡፡ ዶ/ር ታንያ የኮርሱ የተለያዩ ርዕሶችን ከዚህ በታች ከተገለጹት ተመራማሪዎች ጋር በመሆን አዘጋጅተዋል፡፡ ርዕስ ሁለትን ከአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው ጋር፣ ርዕስ ሶስትን ከቴድ ካሬይ፣ የአለም ሎሬት ሮበርት ሙዋንጋ፣ ጁዴ ጆኩ፣ ሲልቨር ቱም ዎጋሚሬ፣ ጆይስ ማሪንጋና የአለም ሎሬት ማሪያ አንድራዴ ጋር፣ ርዕስ አራትን ከማርጋሬት ቤንጃሚን፣ ሂዘር ካቸር፣ ጀሲካ ብላከንሺፕና የአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ርዕስ አምስትን ከማርጋሬት ማክኢዋን፣ ሪቻርድ ጊብሰን፣ የአለም ሎሬት ሮበርት ሙዋንጋ፣ ቴድ ካሬይ፣ ሳም ንማንዳ፣ ኢርና አቢዲን፣ የአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ጆይስ ማሊንጋ፣ ሳሚይ አጂሊ፣ የአለም ሎሬት ማሪያ አንድራዴና ጆናታን ኩምቢራ፣ ርዕስ ስድስትን ከቴድ ካሬይ፣ የአለም ሎሬት ሮበርት ሙዋንጋ፣ ጁዴ ጆኩ፣ ጆይስ ማሪንጋና አንቶኒ ጆኩ ጋር፣ ርዕስ ሰባትን ከሪቻርድ ጊብሰንና ሳም ንማንዳ ጋር፣ ርዕስ ስምንትን ከኦሬሊ ቤኮፍና ኪሪሚ ሲንዲ ጋር፣ ርዕስ ዘጠኝን ከኦሬሊ ቤኮፍና ኪሪሚ ሲንዲ ጋር፣ ርዕስ አስርን ከየአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ኪሪሚ ሲንዲና ዳንኤል ዲታቡላ ጋር፣ ርዕስ አስራ አንድን ከሶኒ ዴቪድ ጋር፣ ርዕስ አስራ ሁለትን ከአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ጎድፍሬይ ሙሎንጎና አዲየል ምባቡ፣ ርዕስ አስራ ሶስትን ከአለም ሎሬት ጃን ሎው ጋር፡፡ በተጨማሪም ሂልዳ ሙልዩአ፣ አዲየል ምባቡና ፍራንክ ኦጅዋንግ በሂደቱ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ነበራቸው፡፡ የዝግጅት ቡድኑ አባላት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት በስኳር ድንች አመራረት፣ አጠቃቀምና የአርሶ አደሮች የመማማር ሂደት ዙሪያ ያላቸውን የካበተ ተሞክሮ በመጠቀም ይህንን የስልጠና መምሪያ አዘጋጅተው አቅርበዋል፡፡ በርግጥ እነዚህ ተሞክሮዎች በክፍለ አህጉሩ ካሉ በርካታ የስኳር ድንች አርሶ አደሮችና እንደ የስርጸት ባለሙያዎች፣ ብሔራዊ ተመራማሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ አጓጓዦች፣ መንግስታዊ ካለሆኑ ድርጅቶች፣ የስነ-ምግብ ባለሙያዎች፣ ሚዲያዎችና የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ከመሳሰሉ ባለድርሻ አካላት ትብብር ውጪ የተገኙ ባለመሆናቸው በዚህ አጋጣሚ እያመሰገንን ይህ የስልጠና መምሪያ በስኳር ድንች ላይ ለሚሰሩት ስራ ጥሩ ግብዓት እንደሚሆናቸው እንተማመናለን፡፡ በዚህ መምሪያ ውስጥ የተካተቱት ፎቶግራፎች ከተለያዩ ቦታዎች የተገኙ ሲሆን ማርጋሬት ማክኢዋን፣ የአለም ሎሬት ጃን ሎው፣ ሪቻርድ ጊብሰን፣ ኢርና አቢዲን፣ ኦሬሊ ቤኮፍ፣ ኬት ቶምሊንስ፣ ሳም ንማንዳ፣ ጄ.ኦ ሱሊቫን፣ ጋብሬላ ቡርጎስ፣ ታንያ ስታተርስ፣ ኦላሳንሚ ቡንሚ፣ ቤንሰን ኢጂኦማ፣ ግራንት ሊ ኑርንበርግ፣ ሳሚይ አጂሊ፣ በሞት የተለየው ኮንስታነስ ኦዎሪ፣ ቴድ ካሬይ፣ የአለም ሎሬት ሮበርት ሙዋንጋ፣ አና ፓንታ፣ ኪሪሚ ሲንዲ፣ ፍራንክ ኦጅዋንግ፣ የአለም አቀፍ ድንች ምርምር ማዕከል ዲጅታል ክምችት፣ ጂ. ሆልምስ፣ ቢ. ኤድሙንድስና ኒኮል ስሚት ፎቶግራፎቹን ስላካፈሉን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በመምሪያው ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉት አብዛኞቹ ካርቱኖች የተሳሉት ደግሞ በሙቪን ዌር ነው፡፡ የዚህ መምሪያ የእንግሊዝኛ ጥራዞች የተዘጋጁት በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የሚደገፈው የለውጥ ሐዋርያትን መድረስ ፕሮጀክት አካል ሆነው ሲሆን የአማርኛ ጥራዞቹ ደግሞ በአውሮፓ ኮሚሽን የሚደገፈው የተሻለ አመጋገብ ለተሻለ ጤና ፕሮጀክት አካል ሆነው ነው፡፡ ይህንን መምሪያ በሌሎች ሕትመቶች ላይ ለመጠቀም ትክክለኛው አገላለጽ የሚከተለው ነው፡፡ Stathers, T., Low, J., Mwanga, R., Carey, T., David, S., Gibson, R., Namanda, S., McEwan, M., Bechoff, A., Malinga, J., Benjamin, M., Katcher, H., Blakenship, J., Andrade, M., Agili, S., Njoku, J., Sindi, K., Mulongo, G., Tumwegamire, S., Njoku, A., Abidin, E., Mbabu, A. (2013). Everything You Ever Wanted to Know about Sweetpotato: Reaching Agents of Change ToT Manual. International Potato Center, Nairobi, Kenya. 7 vols. x , 390 p. ii ይህንን የስልጠና መምሪያ እንዴት መጠቀም ይቻላል? ይህ መምሪያ ስለ ስኳር ድንች ማውቅ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ይዟል፡፡ ስለሆነም በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ የስርጸት ባለሙያዎችንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞችን በማሰልጠን ተግባር ለተሰማሩ አካላት ጉልህ ጥቅም እንዳለው ይታመናል፡፡ በእነዚህ አካላት ስልጠና የወሰዱ ባለሙያዎች በበኩላቸው አርሶ አደሮችን ተግባር ተኮር በሆኑ መንገዶች በማሰልጠን ችግሮችን የመፍታትና ውሳኔ የመስጠት ክህሎታቸውን አሳድገው በኑሯቸው የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶችንና መልካም አጋጣሚዎችን በአግባቡ ማስተናገድ እንዲችሉ የመማር፣ የመጠየቅና የመሞከር ልምዳቸውን እንዲቀጥሉ ያበቋቸዋል፡፡ የስልጠናው መምሪያ 14 ርዕሶችን የያዘ ሲሆን ከመጀመሪያዎቹ የጎልማሶች ስልጠናና የሰብሉ መገኛና ጠቀሜታ ርዕሶች በመቀጠል ያሉ ርዕሶች የተዋቀሩት የሰብሉን የዕድገት ዑደት ተከትሎ ነው፡፡ እያንዳንዱ ርዕስ ስለ ርዕሱ ሊታወቁ የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን ከተነተነ በኋላ ለተግባራዊ የመማማር ተግባራት ግብዓት እንዲሆኑ የደረጃ በደረጃ መመሪያዎችን በመዘርዘር በአስሩ ቀን የአሰልጣኞች ስልጠና መርሃ-ግብር ውስጥ እንዴት ሊካተቱ እንሚችሉ ጥቆማን ይሰጣል፡፡ የመጨረሻዎቹ ሁለት ርዕሶች በዋነኝነት የሚያተኩሩት በአሰልጣኞች ስልጠናው መርሃ-ግብር አወቃቀርና ሊደረጉ በሚገቡ ዝግጅቶች ላይ ነው፡፡ በመምሪያው የተካተቱት አስራ አራቱ ርዕሶች ከዚህ በታች በአጭሩ ተገልጸዋል፡፡ ርዕስ 1 ጎልማሶችን እንዲማሩ መርዳት፡ ይህ ርዕስ የጥሩ የስልጠና አመቻች ባሕሪያትን በመተንተን እንዴት የማመቻቸት ክህሎትን ማሻሻል እንደሚቻል ይገልጻል፡፡ የፍላጎት ዳሰሳ በማከናወን፣ የመማማር ውጤቶችን በመቅረጽ፣ ግንዛቤን በመፍጠር፣ ተሳታፊዎችን በመመረጥ፣ የስልጠና መርሃ-ግብርን በማዘጋጀት፣ ግኝት-ተኮር የመማማር ዘዴዎችን በመቅረጽ፣ የረዥም ጊዜ ክትትል ስልቶችን በመቀየስና የማስፋትና ማስፋፋት ተግባራትን በመጠቀም እንዴት ስልጠናን ማቀድ እንደሚቻል ይጠቁማል፡፡ የ"በመስራት-መማር" ተግባራት ሰልጣኞች የተለያዩ ርዕሶችን በሚያመቻቹበት ወቅት ክህሎታቸውን ለማዳበር የሚያስችሉ ልምምዶችን እንዲያደርጉና ሰልጠናውን የመገምገም ጠቀሜታን እንዲረዱ ዕድል ይፈጥሩላቸዋል፡፡ ርዕስ 2 የስኳር ደንች መገኛና ጠቀሜታ፡ ይህ ርዕስ የስኳር ድንችን ታሪካዊ መገኛና ስርጭቱን እንዲሁም ወቅታዊ ጥቅሞቹንና በዓለም ደረጃ ያለውን የምርት መጠን ያብራራል፡፡ ርዕስ 3 የስኳር ድንች ዝርያ መረጣና ባሕሪያት፡ የስኳር ድንች የስር ቆዳና ስጋ ቀለም ከሃምራዊ እስከ ብርቱካንማ፣ ከቢጫ እስከ ነጭ፣ ከክሬም እስከ ወይንጠጅ ባለው ውስጥ ይለያያል፡፡ በተጨማሪም ሰብሉ የተለያየ የቅጠል ቅርጽ፣ የስር መጠንና ቅርጽ፣ ጥፍጥና፣ ልስላሴና የመድረሻ ጊዜ አለው፡፡ እነዚህ ባህሪያት አርሶ አደሮች የትኛውን ዝርያ ማምረት እንዳለባቸው ለመምረጥ ይረዷቸዋል፡፡ የዝርያዎችን የተለያዩ ባህርያት በአርሶ አደር ማሳ ላይ የማወዳደሪያ ዘዴዎች በዚህ ርዕስ ስር ተገልጸዋል፡፡ ርዕስ 4 ብርቱካናማ ስኳር ድንችና ስርዓተ-ምግብ፡ በዚህ ርዕስ ስር የምግብ ክፍሎችና ጥሩ አመጋገብን በተመለከተ ገለጻ የተሰጠ ሲሆን የቫይታሚን ኤ እጥረትን ጨምሮ ደረጃውን ያልጠበቀ አመጋገብ የሚያስከትለውን ጉዳትና ተለምዷዊ የድቀላ ዘዴን በመጠቀም ሰብሎችን በስነ-ሕይወታዊ መንገድ እንዴት ማበልጸግ እንደሚቻል ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ቫይታሚን ኤን የመሳሰሉ በቀላሉ ለመለየት የሚያስቸግሩ የንጥረ-ነገር ፍላጎቶችን ለማርካት ፍላጎትን የመፍጠር ሂደትን ውስብስብነት ጨምሮ ብርቱካናማ ስኳር ድንችን አዘውትሮ የመመገብ ጥቅም በስፋት ተብራርቷል፡፡ ርዕስ 5፡ የስኳር ድንች ዘር ስርዓት፡ በዚህ ርዕስ የተለያዩ የዘር ብዜት ደረጃዎችና የዘር ስርዓት ባለድርሻ አካላት በስርዓቱ ውስጥ ያላቸውን ሚና ጨምሮ የስኳር ድንች የዘር ስርዓቶች በሰፊው ተብራርተዋል፡፡ ብርቱካናማ ስኳር ድንችን ለማስፋፋት ይቻል ዘንድ የአንድ ጊዜ ዘር ስርጭትን ወይም ቀጣይነት ያለው ስርጭት አቀራረብን ለመጠቀም ውሳኔ ላይ መድረስ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፉ ጉዳዮችን በተመለከተ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የዘር ብዜትና ስርጭት ዘዴዎችን ለማቀድ የሚረዱ ምሳሌዎች የተሰጡ ሲሆን ንጹህ ዘር ለመምረጥ፣ ለማቆየትና ለማባዛት የሚጠቅሙ ዘዴዎችም ቀርበዋል፡፡ ርዕስ 6 የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ፡ ይህ ርዕስ በቂ ዘር በተከላ ወቅት ማግኘት እንዲቻል ቀድሞ የማቀድን ጥቅም ጨምሮ ለጥሩ የስርና ሃረግ ምርት የመሬት ዝግጅት፣ የተከላ ዘዴዎች፣ የሰብል ስብጥር፣ የንጥረ-ነገር ፍላጎት፣ የሰብሉ ዋና ዋና የዕድገት ደረጃዎችና በተጓዳኝ የሚያስፈልጉ የአያያዝ ተግባራትን በስፋት ይዳስሳል፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ተባይና በሽታ ቁጥጥር፡ ይህ ርዕስ የስኳር ድንች ቀንደኛ አጥፊ ተባይ የሆነውን ነቀዝና ዋና በሽታ የሆነውን ቫይረስ የህይወት ዑደት በአግባቡ መገንዘብ ተባዩና በሽታው የሚያደርሱትን ጉዳት አርሶ አደሮች ስኬታማ በሆነ መንገድ iii እንዲቆጣጠሩ እንዴት እንደሚያስችላቸው ያብራራል፡፡ በተጨማሪም እንደ ፍልፈል የመሳሰሉ እንስሳቶችን የጉዳት ምልክቶችና የመቆጣጠሪያ መንገዶች ይተነትናል፡፡ ርዕስ 8 ምርት መሰብሰብና ድሕረ-ምርት አያያዝ፡ በምርት መሰብሰብና ማጓጓዝ ወቅት የሚደርሱ ጉዳቶች የስሩን የቆይታ ጊዜና ዋጋን ይቀንሳሉ፡፡ ለድርቆሽ የሚዘጋጅ የስኳር ድንች ስርን ከመጠን በላይ በጸሐይ ማድረቅና ለረዥም ጊዜ ማከማቸት የቤታ ካሮቲን ይዘቱ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ ይህንን ችግር መቅረፍ እንዲቻል ይህ ርዕስ ለድርቆሽ ጥሩ የሆኑ የድሕረ-ምርት አያያዝና አከመቻቸት ተግባራትን የሚተነትን ሲሆን የስር አቅርቦትን፣ ጥራትንና ዋጋን ለመጨመር የሚያስችሉ የማጥገግና የክምችት ዘዴዎችንም ያቀርባል፡፡ ርዕስ 9 ምርት ማቀነባበርና አጠቃቀም፡ ጣፋጭና በንጥረ-ነገር የበለጸጉ በርካታ ምግቦችና ሌሎች አዋጪ የምግብ ምርቶችን ከብርቱካናማ ስኳር ድንች ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ ይህ ርዕስ አነዚህ ምግቦችን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል የሚገልጽ ሲሆን ስኳር ድንች ለእንስሳት መኖነት ያለውንም ጥቅም ይዳስሳል፡፡ ርዕስ 10 ግብይትና ስራ ፈጠራ፡ በዚህ ርዕስ አምስቱ የግብይት ምሶሶዎች (ማለትም ምርት፣ ዋጋ፣ ቦታ፣ ማስተዋወቅና ሰው) ከስኳር ድንች ስርና ሌሎች ምርቶች አኳያ ተተንትነዋል፡፡ ርዕስ 11 የስርዓተ-ጾታና ብዝሃነት ጉዳዮች፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ በግብርና በአጠቃላይና በስኳር ድንች እሴት ሰንሰለት ውስጥ በተለይ የስርዓተ-ጾታና ብዝሐነት ጉዳዮችን ጠቀሜታ መገንዘብ ምን ያክል አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ስኳር ድንች በሴቶች ብቻ የሚመረትበት፣ በወንዶች ብቻ የሚመረትበት ወይም በሁለቱም የሚመረትባቸው ሁኔታዎች የቀረቡ ሲሆን ወንድና ሴት አርሶ አደሮች የሚገጥሟቸው ተግዳሮቶችና ቅድሚያ የሚሰጧቸው ፍላጎቶቻቸውም ተብራርተዋል፡፡ የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች እንዴት በስኳር ድንች ፕሮግራሞች ውስጥ ሊካተቱ እንደሚችሉ የሚያሳዩ ጥሩ ተሞክሮዎችም ቀርበዋል፡፡ ርዕስ 12 የብርቱካናማ ስኳር ድንች ስርጭትና አቀባበልን መከታተል፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ የክትትል አስፈላጊነትና በክትትልና ግምገማ መካከል ያለው ልዩነት ተገልጧል፡፡ አስከትሎም የስኳር ድንች ዘርን ስርጭት፣ የምርት አቅምና ጥቅም ለመከታተል የሚያስችሉ የተለያዩ ዘዴዎች ተብራርተዋል፡፡ የስኳር ድንች ስልጠናዎችን የረዥም ጊዜ ተጽዕኖና ተደራሽነት ለመረዳት ማን እንደሰለጠነ ሙሉ መረጃ መመዝገብ አስፈላጊ መሆኑና ይህም መረጃ ለክትትል ተግባራት ወሳኝ መሆኑ ተገልጧል፡፡ ርዕስ 13 ስለ "ስኳር ደንች ማወቅ የምንፈልገው ሁሉ" የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያ አጠቃቀም፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ የ10 እና 5 ቀናቱ የ"በመስራት-መማር" የአሰልጣኞች ስልጠና መርሃ-ግብር ዝርዝር ቀርቧል፡፡ መርሃ-ግብሩ በየቀኑ የሚሸፈኑ ርዕሶችን፣ ተጠባቂ የመማማር ውጤቶችን፣ የሚከወኑ ተግባራትን ቅደም-ተከተልና ጊዜ እንዲሁም የሚያስፈልጉ ግብዓቶችንና ቅድመ-ዝግጅቶችን በዝርዝር ይገልጻል፡፡ የስልጠና አመቻቾች በአካባቢያቸው ያሉ ተሳታፊዎችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በዚህ ርዕስ ስር የተጠቀሰውን መርሃ-ግብር ሊያሻሽሉት ይችላሉ፡፡ ርዕስ 14 ግብረ-መልሶች፡ የስልጠናው መምሪያ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ የበለጠ እንዲሻሻል ተሳታፊዎች ግብረ-መልስ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ ግብረ-መልሶቹን ለመስጠት የሚያስችሉ ቅጾች ተዘርዝረዋል፡፡የዚህ የስልጠና መምሪያ ተጠቃሚዎች የሚኖራቸውን ማንኛውንም አስተያየት በዚህ ርዕስ ውስጥ በተጠቀሱት ቅጾች ላይ በበሙላት ለዝግጅት አስተባባሪዋ ለአለም ሎሬት ዶ/ር ጃን ሎው በኢሜይል አድራሻቸው j.low@cgiar.org መላክ የሚችሉ ሲሆን አስተያየቶቹም ጠቃሚ ሆነው ከተገኙ በመምሪያው ቀጣይ ህትመቶች ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋል፡፡ iv ማውጫ ርዕስ 6: የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ ........................................................................................................................................... 1 6.1 የስኳር ድንች እርሻን የድርጊት መርሀ ግብር መንደፍ.........................................................................................................................1 6.2 መሬት መረጣና ዝግጅት.................................................................................................................................................................... 2 6.3 የአተካከል ዘዴና የተከላ ወቅት ......................................................................................................................................................... 3 6.4 ለረዥም ጊዜ አቅርቦትና ጥሩ ምርት ለማግኘት አራርቆ/በተለያዩ ቀናት መትከል ......................................................................... 4 6.5 የሰብል ስብጥር................................................................................................................................................................................... 4 6.6 የስኳር ድንች ተክል የዕድገት ፍላጎትና የፊዚዮሎጂ መረበሽ .......................................................................................................... 5 6.6.1 የተለያዩ የስኳር ድንች ሰብል የዕድገት ደረጃዎች ................................................................................................................... 5 6.6.2 አረም ቁጥጥር ........................................................................................................................................................................... 7 6.6.3 ሃረግ ማንሳትና አፈር ማሳቀፍ................................................................................................................................................. 9 6.6.4 የፊዚዮሎጂ መረበሽ................................................................................................................................................................. 9 6.6.5 የስኳር ድንች ሰብልን ውኃ ማጠጣት ................................................................................................................................... 10 6.7 የስኳር ድንች የንጥረ-ነገር ፍላጎት ..................................................................................................................................................... 11 6.8 በስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ የሥርዓተ-ጾታና ብዝሃነት ጉዳዮች ..........................................................................................16 6.9 ስለ ስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ በተግባር መማር ................................................................................................................... 17 6.9.1 የስኳር ድንች ዝርያዎችንና የአያያዝ ተግባራትን ማነጻጸር .................................................................................................... 17 6.9.2 ቅድመ-ዕቅድ ............................................................................................................................................................................19 6.10 ዋቢ ጹሑፎች................................................................................................................................................................................... 21 ርዕስ 7: የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር........................................................................................................................ 23 7.1 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ እንዴት ይከሰታሉ? እንዴትስ ይሰራጫሉ?..........................................................................23 7.1.1 የነፍሳት ተባይ የህይወት ዑደት ...............................................................................................................................................23 7.1.2 የዕጽዋት በሽታዎች የህይወት ዑደት ......................................................................................................................................25 7.1.3 የተቀናጀ የተባይና በሽታ ቁጥጥር ...........................................................................................................................................26 7.2 የስኳር ድንች ነቀዝን መለየትና መቆጣጠር.....................................................................................................................................28 7.2.1 የስኳር ድንች ነቀዝን የህይወት ዑደትና ባሕሪ መለየትና ማወቅ.........................................................................................28 7.2.2 የስኳር ድንች ነቀዝ መቆጣጠሪያ መንገዶች...........................................................................................................................31 7.2.3 ሸካራው የስኳር ድንች ነቀዝ (Blosyrus spp)....................................................................................................................33 7.3 የስኳር ድንች ቫይረስን መለየትና መቆጣጠር .................................................................................................................................33 7.4 የሻጋታ በሽታዎችን መለየትና መቆጣጠር.......................................................................................................................................35 በቅጠል ተሸካሚና በግንድ ላይ ጥቁር ቁስል .................................................................................................................................35 7.5 ፍልፈልን መለየትና መቆጣጠር .......................................................................................................................................................36 7.6 ሸረሪት የመሳሰሉ ነፍሳትን መለየትና መቆጣጠር ...........................................................................................................................37 7.7 የጎተራ ተባዮችን መለየትና መቆጣጠር ...........................................................................................................................................38 7.8 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር የሥርዓተ-ጾታና ብዝሀነት ጉዳዮች ........................................................................40 7.9 የስኳር ድንች ተባዮችንና በሽታዎችን የመቆጣጠሪያ መንገዶችን እየተገበሩ የመማር ሀሳብ ........................................................41 7.9.1 የስኳር ድንች ተባዮችንና በሽታዎችን በመስክ ላይ ማደንና እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል መማር............................42 7.9.2 ድብቅ ጉዳት: የነፍሳት ተባዮችን የህይወት ዑደት የመረዳት አስፈላጊነት .........................................................................43 7.9.3 በቁልፍ የስኳር ድንች ተባዮችና በሽታዎች ላይ ሌሎችን ማሰልጠን................................................................................. 44 7.10 ዋቢ ጹሑፎች..................................................................................................................................................................................45 v ርዕስ 6: የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ ትክክለኛ የዕድገት ሁኔታዎች ከተመቻቹ ስኳር ድንች ከፍተኛ ምርት የመስጠት አቅም አለው፡፡ ሰኳር ድንች ሌሎች ሰብሎች ምርት ሊሰጡ በማይችሉባቸው ቦታዎች ሁሉ ከፍተኛ የሆነ ምርት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ይህም ከሰሀራ በታች በሚገኙ አገሮች በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጠቃሜታው ከፍ ያለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ርዕስ 6 በስኳር ድንች አመራረት ላይ ተጽዕኖ ስለሚፈጥሩ የአካባቢ የአየር ሁኔታዎች፣ አፈርና ንጥረ ነገሮች፣ ውኃ፣ ብርሃንና ሙቀት ከነ አጠቃቀማቸውና ጥሩ የሆነ የስኳር ድንች ሰብል ምርት በዘላቂነት ለማግኘት ከሚያስችሉ የአመራረት ዘዴዎች ጋር ያወሳል፡፡ የልማት ሰራተኞች የተሻሻለ የስኳር ድንች አያያዝ ዕውቀት ከአርሶ አደር አርሶአደር፣ በጾታ እና ከቦታ ቦታ እንደሚለያይ መገንዘብ አለባቸው፡፡ ስኳር ድንች በብዛት በሚመረትባቸው አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች ከፍተኛ የአመራረት እውቀት እንዳላቸውና ሰብሎቻቸውን ያላቸውን ሀብት ተጠቅመው በጥሩ ሁኔታ እንደሚይዙ ይገመታል፡፡ ይህ የስልጠና መምሪያ ስኳር ድንች እንዴት መመረት እንዳለበት አስገዳጅ አንድ ወጥ መመሪያ የማስቀመጥ አላማ የሌለው ሲሆን ይልቁንም ለጥሩ የስኳር ድንች ምርት አስዋጽዖ የሚያደርጉ መርሆዎችንና ተግባራትን አንባቢዎች (ሰልጣኞች) እንዲረዱ ለማድረግ ሞክሯል፡፡ 6.1 የስኳር ድንች እርሻን የድርጊት መርሀ ግብር መንደፍ ለግብርና ስራ ውጤታማነት ድርጊቶችን በጊዜ ወሰን ከፋፍሎ ማከናወኑ ወሳኝ ነው፡፡ በዝናብ መጀመሪያ ወቅት በቂ የተከላ ዘር ማግኘቱ ከሰሀራ በታች ለሚገኙ ስኳር ድንች አምራች አርሶ አደሮች ዋነኛ ተግዳሮት ነው፡፡ በእርግጥ ሌሎችም ተግዳሮቶች ለምሳሌ የስኳር ድንችና የሌሎችን ሰብሎች አያያዝ በማሳና በቤተሰብ ደረጃ አመጣጥኖ ማስኬድ ያለመቻል የመሳሰሉ አሉ፡፡ ይህ ደግሞ በተለይም በዝናብ ጥገኛ በሆኑ፣የአፈር ለምነት በተሟጠጠ መሬት ላይ ለሚሰሩ እና የአየር ሁኔታ መረጃ በአግባቡ ማግኘት በማይችሉ ድሃ አርሶ አደሮች ዘንድ በስፋት የሚታይ ነው፡፡ ብርቱካንማ ስኳር ድንችን ለሚያስተዋውቁ አካላት የህብረተሰቡን የእርሻ ስራ ሰሌዳ ማወቁና ከዚህ ሰሌዳ ጋር የስኳር ድንችን የማምረቻ ወቅት እንዴት ማጣጣም እንደሚቻል መረዳቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የልማት ሰራተኞች ስኳር ድንች ወደ ንግድ የገባበትን ደረጃና በስኳር ድንች እሴት ሰንሰለት ውስጥ የሥርዓተ-ጾታን ሚናና ሀላፊነት መረዳት ያስፈልጋቸዋል፡፡ የወንዶችና የሴቶች የስኳር ድንች ማሳ ባለቤትነት/አያያዝ በአብዛኛው ከሰሀራ ከጌዴኦ ዞን የተገኘ የተጠናቀቀ የስኳር ድንች የእርሻ በታች ባሉ አካባቢዎች ከታች እንደተገለጸው በሶስት ጎራ ይከፈላል፡፡ ስራ ሰሌዳ • በተለምዶ ስኳር ድንች የሴቶች ሰብል ነው፤ ጥቂት ወንዶች ያመርቱታል ወይም አያመርቱትም፤ • በተለምዶ ስኳር ድንች የወንዶች ሰብል ነው፤ ጥቂት ሴቶች ያመርቱታል ወይም አያመርቱትም፤ • በግል በተያዙ፣ በቤተሰብ ወይም የኪራይ መሬቶች ስኳር ድንች የሴቶችና የወንዶች የጋራ ሰብል ነው፤ በርዕስ 11 እንደተተነተነው የሥርዓተ-ጾታ ሚና በስኳር M o n t h W h o i s in v o lv e d ? O th e r a c tiv it ie s / c ro p s J F M A M J n J y A g S O N D M e n , W o m e n , M a le c o m p e tin g f o r w o m e n ’s c hild re n , f e m a le la b o u r a t th is ti m e ድንች አመራረት ላይ ተለዋዋጭ ነው፡፡ በቦታ፣ c hild re n , H ir e d m a le la b o u r , h ire d f e m a le la b o u r እንደየአካባቢው ሁኔታና በጊዜ ይለያያል፡፡ በአብዛኛዎቹ R A I N S Ta sk s La n d p r e p a ra ti o n ከሰሀራ በታች በሚገኙ አገሮች ስኳር ድንች ለቤት ፍጆታ La n d c l e a r i ng M a k i n g m o u nd s / ri d g e s የሚመረት ሲሆን ወንዶቹ የሚያመርቱት በገበያ ላይ አዋጭ O b ta i n in g v in e s T r a n sp o r ti n g v i n e s ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ተገላቢጦሹም ይከሰታል፡፡ Pl a n ti n g W e e d i ng A p p ly i n g f e r ti l ize r በሰሜን ናይጄሪያ የተወሰኑ አካባቢዎች ዋነኛዎቹ የስኳር H a rv e st in g T r a n sp o r t to m a rk e t S e l li n g ድንች አምራቾች ወንዶች ሲሆኑ ሴቶቹ የሚሳተፉት Pr o ce ss in g ro o t s Co n se r v in g v in e s በንግዱ ዓለም አዋጭ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ ከአርሶ አደሮቹ ጋር በመሆን የእርሻ ስራ ሰሌዳ ማዘጋጀት የስኳር ድንች ተግባራት በሚከናወኑበት ጊዜ ሌሎች ተግባራት የሴቶችን ጉልበት የሚሻሙበትን ወቅት ለመረዳትና ነባራዊ ሁኔታዎችን ለማብራራት ይረዳል፡፡ ሌሎቹ የስኳር ድንች ተግባራት ቅድመ ዝግጅት የሚፈልጉ ቢሆንም በታቀደው የተከላ ወቅት ሃረጎችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ እንዲቻል የእርሻ ስራ ሰሌዳ ማዘጋጀት በተለይ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 1 6.2 መሬት መረጣና ዝግጅት ከፍታ : ስኳር ድንች ከዜሮ እስከ 1700 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ባለው ከፍታ ይመረታል፡፡ አንዳንድ ዝርያዎች እስከ 2500 ሜትር ከባህር ወለል በላይ መብቀል ቢችሉም ደካማ ጣዕምና የደራቆት መጠን ይኖራቸዋል፡፡ አፈር : ስኳር ድንች በተለያዩ የአፈር ዓይነቶች ላይ መብቀል ቢችልም ጥልቅ፣ በመካከለኛ ደረጃ ለም፣ አሸዋ ቀመስ የአፈር ዓይነቶች ላይ ከፍተኛ ምርት፣ ማራኪ ቅርጽና ገጽታ ያላቸውን ስሮች ይሰጣል፡፡ በቂ የአየር ዝውውርና የፍሳሽ ማስወገድ ስርዓት በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ሰብሉ በጉብታ ወይም በመደብ ላይ እንዲመረት ይደረጋል፡፡ ስኳር ድንች አነስ ያለ የአሲድነት መጠን ባላቸው የኮምጣጤነት መጠናቸው ከ5.5-6.6 በሆኑ አፈሮች ላይ በጥሩ ሁኔታ ይመረታል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚያም በላይ ሆነ በታች የሆኑ የኮምጣጤነት መጠኖችን ስኳር ድንች መቋቋም ይችላል፡፡ የአፈር አይነት ትንተናና በማሳ ውስጥ ፈጣን የአፈር ዓይነት መለያ ምርመራ በአባሪ 6.1 ላይ ተሰጥቷል፡፡ እንደሌሎቹ ሰብሎች ስኳር ድንች ከአፈር ለምነት ተጠቃሚ ነው፡፡ ስራስር ሰብል እንደ መሆኑ መጠን ስኳር ድንች ከፍተኛ የሆነ የፖታሲየም ንጥረ-ነገር ፍላጎት አለው፡፡ ከፍተኛ የሆነ ናይትሮጅን በተለይም በእርጥብ ስነ-ምህዳራት ቅጠሉን ብቻ አብዝቶ የስሩን እድገትና ውፍረት የተወሰነ ያደርገዋል፡፡ አልፎ አልፎ ካልጨመሩ በስተቀር አርሶ አደሮች በብዛት ለስኳር ድንች ማዳበሪያ አይጠቀሙም፡፡ ይሁን እንጂ ስኳር ድንች ማዳበሪያ ከሚጨመርላቸው እንደ በቆሎ ካሉ ሰብሎች ጋር በፈረቃ ወይም በስብጥር ስርዓት የሚመረት ከሆነ የቅሪተ-ንጥረነገሮች ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ በመሬት ዝግጅት ወቅት የመትከያ ጉብታዎች ወይም መደቦች በባለፈው ዓመት ሰብል ቅሪቶች ወይም በእዳሪ መሬት ላይ በነበሩ የዕጽዋት ብስባሾች ላይ አፈር በመቆለል የሚዘጋጁበት ዋናው ምክንያት የአፈር ለምነትን ለመጨመርና ምናልባት የአፈር መደምደምን ለማስወገድም ጭምር ነው፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ስሮች ዘና ባለ መልኩ እንዲያድጉና እንዲወፍሩ ያደርጋል፡፡ ፍግ፣ ኮምፖስት ወይም አረንጓዴ ብስባሽ መጨመር በጣም ጠቃሚ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የሚጨመረው በጓሮ በሚተከሉ ሰብሎች ላይ ነው፡፡ አመድ በፖታሲየም የበለጸገ ስለሆነ በተከላ ወቅት ከአፈር ጋር መቀላቀል የስኳር ድንች ስርን ፍጥረትና እድገት ከፍ ያደርጋል፡፡ ሰብል ፈረቃና ማምረቻ መሬት መለየት: የበሽታ (ቫይረስ) እና ተባይ (የስኳር ድንች ነቀዝ እና ኔማቶድ) ክስተት እድገት እንዲቀንስ ስለሚያደርግ እንደማንኛውም ሰብል ስኳር ድንችን ከሌሎች ሰብሎች ጋር በማፈራረቅ ወይም መሬት በማሳደር ማምረት ያስፈልጋል፡፡ በርግጥ ኔማቶድ በአብዛኛው ስኳር ድንች አምራች በሆኑ ከሰሀራ በታች በሚገኙ አካባቢዎች ችግር አይደለም፡፡ ስኳር ድንች ጥራጥሬ ሰብሎችን ወይም አዝርዕትን ተከትሎ ቢመረት ጥሩ ምርት መስጠት ቢችልም እንደ ካሳቫ ያሉ የስራስር ሰብሎች ተመሳሳይ የሆነ የአፈር ንጥረ-ነገር ፍላጎት ስላላቸው እነሱን ተከትሎ መመረት የለበትም፡፡ መሬትን ከማሳደር ተከትሎ ለሚከናወን የሰብል ፈረቃ ስርዓት ስኳር ድንችን የመጀመሪያና የመጨረሻ ሰብል ማድረጉ ጠቃሚ መሆኑ ሪፖርት ተደርጓል፡፡ የመጀመሪያ ሲሆን ሰብሉ ከተነሳ በኋላ ለሚቀጥለው ሰብል አፈሩን በቀላሉ ለማዘጋጀት ምቹ የሚያደርግ ቢሆንም በጣም ለም መሬቶች ላይ ሲመረት ከፍተኛ የሆነ ቅጠል በማውጣት አነስተኛ ወይም ምንም ስር ላይሰጥ ይችላል፡፡ ሁሌ የሚቻል ባይሆንም ቫይረስና የስኳር ድንች ነቀዝ ችግር በሆነባቸው አካባቢዎች አዲስ የሚተከሉትን የስኳር ድንች ማሳዎች ከአሮጌዎቹ ማሳዎች ወይም ምርት በቅርቡ ከተሰበሰበባቸው ማሳዎች ማራቅ ያስፈልጋል፡፡ በማሳዎቹ መካከል የመግቻ ሰብሎችን መትከል ወይም በማሳዎች መካከል ቢያንስ 120 ሜትር ርቀት መተው የስኳር ድንች ነቀዝ አዲሱን ማሳ እንዳያገኘው ይከላከላል፡፡ ምንም አይነት ሌላ አማራጭ ከሌለና ማሳውን ደግመን መትከል የግድ ከሆነ ከቀድሞ ሰብል የቀሩትን ስሮችና ሀረጎች ከአፈር ጋር ደጋግሞ በማረስ እንዲዋሃዱ ማድረግ ወይም በተቻለ መጠን ሙሉ በሙሉ ካማሳው ማስወገድ (በማቃጠል ወይም ከብቶችን በመመገብ) የበሽታና ተባይ ስርጭትን በመቀነስ ሊረዳን ይችላል፡፡ ከአንድ የምርት ወቅት ወደ ሌላው የስኳር ድንች በሽታና ተባይ እንዳይተላለፍ ከተቻለ በአንድ ማሳ ላይ ስኳር ድንችን በሶስት ዓመት ልዩነት ማምረት ያስፈልጋል፡፡ በተለይም አዲስ ዝርያ በአካባቢው ለመጀመሪያ ጊዜ የገባ ከሆነ ይህ ስርዓት በጣም ጠቃሚ ይሆናል፡፡ መሬት ማግኘት: በአብዛኛው ከሰሀራ በታች በሚገኙ አካባቢዎች መሬት በባለቤትነት የሚያዘው በወንዶች ስለሆነ በከፍተኛ ደረጃ የስኳር ድንች ሰብል በሴቶች በሚመረትበትና በሚያዝበት ቦታም ቢሆን በመሬቱ ላይ ምን መመረት እንደሚገባው ውሳኔ የሚሰጠው ወንዱ ብቻ ነው፡፡ የልማት ሰራተኞች የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ ትኩረት የሚሻው መሆኑን ተገንዝበው ወንዶች በቀጥታ በማይሳተፉበትም ሁኔታ በስኳር ድንች ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችን ወንዶች ማወቃቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 2 6.3 የአተካከል ዘዴና የተከላ ወቅት ስኳር ድንች በጉብታ፣ በመደብ/ቦይ ወይም ለጥ ባለ መሬት ላይ ሊተከል ይችላል፡፡ ጥሩ የአፈር ውስጥ አየር ዝውውር ለስሮች ማደግና መወፈር በጣም አስፈላጊ ስለሆነ በጉብታዎች ወይም በመደቦች ወይም ከፍ ባሉ ቦታዎች መትከል በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ጉብታዎችና መደቦች በጥሩ ሁኔታ ውኃ እንዲጠፍና ምርት የመሰብሰቡን ሂደት በተለይም ትንሽ በትንሹ ምርት ሲሰበሰብ ሂደቱ በቀላሉ እንዲከናወን ያደርጋሉ፡፡ የመደቦች/ቦዮች እና የጉብታዎች መጠን/ክፍታ እንደየአካባቢው ሁኔታና የአርሶ አደሮች ልማድ ይለያያል፡፡ ማግኘት በሚቻልባቸው ቦታዎች በትራክተር ወይም በሬ ማዘጋጀት ሲቻል አብዛኛውን ጊዜ መደቦች/ቦዮች እና ጉብታዎች በሰው ጉልበት ይሰራሉ፡፡ በስኳር ድንች አመራረት ሂደት የመሬት ዝግጅት እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ጉልበት ከሚጠይቁ ነገሮች የመጀመሪያው ነው፡፡ የጉልበት ችግር በጉብታ ላይ የተተከለ ስኳር ድንች ባለባቸው ቤተሰቦች ስኳር ድንች የሚተከለው ለጥ ባለ መሬት ላይ ነው፡፡ ቢሆንም በዚህ ዓይነት የተመረተው ሰብል በጉብታ ወይም በመደብ ከተተከሉት ጋር ሲወዳደር አነስተኛ ምርት ይሰጣል፡፡ ስዕል 6.1. የመሀል አንጓ ርዝመት እንደየዝርያው ቢያንሰ 3 አንጓ ወይም ከ20-30 ሊለያይ ይችላል፡፡ በአንዳንዶቹ 3 አንጓ 15 ሴሜ ሴ.ሜ ርዝመት ያላቸው የስኳር ርዝመት ሲኖረው በሌሎቹ 30ሴሜ ይሆናል ድንች ቁርጥራጮች ወይም በመደብ ላይ እየተተከለ ያለ ስኳር ድንች ጉንቁሎች ከ20-30ሴ.ሜ በተክሎች መካከልና ከ60-100ሴ.ሜ በመስመሮች መካከል ባለው ርቀት ይተከላሉ፡፡ ይሁን እንጂ አርሶ አደሮች መሬት ለመሬት የሚሳቡትን ዝርያዎች ሰፋ ባለ የተከላ ርቀት ሲተክሉ ቀጥ ብለው የሚበቅሉትን ወይም በከፊል የሚሳቡትን 15 cm ጠበብ ባለ ርቀት በመትከል አንዳንድ ሙከራዎችን ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ በጉብታ ላይ በሚተክሉበት ጊዜ አርሶ አደሮች በአብዛኛው ጊዜ በትንሽ ርቀት ሶስት ቁርጥራጮችን በአንድ ጉብታ ላይ ይተክላሉ፡፡ በአንድ ጉብታ ላይ ሶስት ቁርጥራጮችን ርቀታቸው 1ሜ በ1ሜ በሆኑ ጉብታዎች ላይ የሚተከሉ ከሆነ 30 cm 30000 ቁርጥራጮች ለሄክታር ያስፈልጋሉ፡፡ በመደብ/ቦይ ላይ ደግሞ 30ሴ.ሜ በተክሎች መካከልና 60ሴ.ሜ በመስመሮች መካከል ያለውን ርቀት በመጠቀም የሚተከሉ ከሆነ 55555 ቁርጥራጮች ለሄክታር ይበቃሉ፡፡ የተከላ ርቀቶችን በማስተካከል የስኳር ድንች ስር መጠንን መወሰን ይቻላል፡፡ ጠበብ ያለ ርቀት በብዛት አነስተኛ ስሮች እንዲመረቱ ያደርጋል፡፡ አንዳንድ ገበያዎች ደግሞ እነኝህን አነስተኛ መጠን ያላቸውን ስሮች በይበልጥ ይመርጣሉ፡፡ እንጨት፣ ገጀራ ወይም መቆፈሪያ በመጠቀም 2/3ኛውን የቁርጥራጭ ክፍል በመሬት ውስጥ በማድረግና 1/3ኛውን ብቻ ከመሬት በላይ በማድረግ መትከል ይቻላል፡፡ ሁለት ሶስተኛውን የቁርጥራጭ ክፍል መቅበር ብዙ ስሮች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፡፡ አፈሩና አንጓዎቹ በደንብ እንዲገናኙ በቁርጥራጮች ዙሪያ ያለውን አፈር መጠቅጠቅ ያስፈልጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የታችኛዎቹ ቅጠሎች እንዲወገዱ ይደረጋል፤ ግን አስፈላጊ አይደለም፡፡ አርሶ አደሮች ለአንድ ወይም ለሁለት ቀናት ቁርጥራጮቹን በቀዝቃዛ ጥላ ስር በማድረግ ከተከላ በፊት ስር እንዲያወጡ ያደርጋሉ፡፡ በብዙ ቦታዎች አርሶ አደሮች በተለምዶ በአንድ ጉድጓድ ሁለት ቁርጥራጮችን ይተክላሉ፤ ይህ ደግሞ ለአንድ የተወሰነ መሬት ብዙ ቁርጥራጮችን እንድንጠቀም ያደርጋል፡፡ የልማት ሰራተኞች በአንድ ጉድጓድ/ቦታ አንድ ብቻ ቁርጥራጭ እንዲተክሉና ምናልባትም የሚሞት ካለ መተካት እንደሚገባቸው የስኳር ድንች ቁርጥራጮችን መትከል ለአርሶ አደሮች ይመክራሉ፡፡ በጉብታ ላይ በሚተከልበት ጊዜ ሶስት ቁርጥራጮች በአናቱ ላይ ይተከላሉ፤ ነገር ግን በቁርጥራጮቹ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 3 መካከል ያለው ርቀት ሁል ጊዜ እኩልና በሶስት ማዕዘን አቀማመጥ መሆን አለበት፡፡ በመደብ ላይ ሲሆን ደግሞ ቁርጥራጮቹ ቀጥ ተደርገው ወይም ወደ አንድ ወገን ጋደል ተደርገው በመደቡ አናት ላይ ርቀት ተጠብቆ ሊተከሉ ይችላሉ፡፡ በዋናው የዝናብ ወቅት በቂ የተከላ ሃረግ ከተባዛ በኋላ ስኳር ድንች በአብዛኛው ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የብርዕና አገዳ ሰብሎችና ሌሎች ገቢ ማስገኛ ሰብሎች ቀጥሎ ይተከላል፡፡ ይሁን እንጂ የዝናብ ወቅታቸው አጭር በሆነባቸው አካባቢዎች ይህንን መተግበር ሰብሉን ለድርቅና ለስኳር ድንች ነቅዝ ጥቃት ስለሚያጋልጥ በከፍተኛ ደረጃ ምርት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ 6.4 ለረዥም ጊዜ አቅርቦትና ጥሩ ምርት ለማግኘት አራርቆ/በተለያዩ ቀናት መትከል ስኳር ድንችን በተቻለ መጠን ዝናብ እንደመጣ አስቀድሞ መትከል የዕድገት ወቅቱን ከማራዘም፣ ለቤት ፍጆታና ለገበያ ቀድሞ ስር ከማግኘት አንጻር ጠቃሚ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዝርያዎች መካከል ያለው የመድረሻ ወቅት ልዩነትና የስኳር ድንች ስርን በትንሽ በትንሹ በመቆፈር ለጥቂት ወራት መጠቀም መቻሉ እንደተጠበቀ ሆኖ የስኳር ድንች ማሳን ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ መሸፈን የምርት መትረፍረፍን ስለሚያመጣ ብክነት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ የማምረቻ ወቅት ከፈቀደ በተለያዩ ተከታታይ ሳምንታት ወይም ወራት ልዩነቶች መትከል ከፍተኛ የሆነ ጥቅም አለው፡፡ እነኝህም:-  ያቆጠቆጡትን ቆርጦ በመትከል ሰፋ ያለ ቦታ መሸፈን ይቻላል፤  በተራዘመ ደረቅ ወቅት ወይም ባልተጠበቀ የአየር ሁኔታ የሚከሰተውን የምርት ማጣት አደጋ ለተለያዩ ወራት ማከፋፈል ይቻላል፤  በጉልበት ሠራተኞች ዕጥረት ሊመጣ የሚችለውን ችግር ለተለያዩ ጊዜያት ስለሚያካፍል ችግሩን ሊቀንስ ይችላል፤  በመድረሻ ወቅት ከሚከሰተው ከፍተኛ ከሆነ አቅርቦት በተቃራኒ ወጥ የሆነ የስር አቅርቦት ረዘም ላለ ጊዜ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ በተለይም የየእለት የቫይታሚን ኤ አቅርቦትን ለማሟላት የብርቱካንማ ስኳር ድንች አጅግ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ወጥ የሆነ አቅርቦት በገበያ ስርዓትና በቤት ውስጥ የምግብ አቅርቦት ላይ አዎንታዊ እንድምታ ይኖረዋል፡፡ የተከላ ወቅትን ማራዘም (በተለይም በመጨረሻዎቹ ቀናት ዘግይቶ የተተከለው የማሳ ክፍል) ከዝናብ ወቅት በኋላ ለሚከሰተው ድርቅ ስለሚያጋልጥ ምናልባት የምርት መቀነስ፣ በነቀዝ የመጠቃት፣ በጣም ከፍተኛ ለሆነ በሽታና በሌባ የመወሰድ ዕድልን ሊያሰፋ ይችላል፡፡ ለምግብነትና ለገበያ እንደደረሰ መቆፈር መቻሉና የገበያ ዋጋ ሳቢ ካልሆነና ቤተሰቡ በቂ ምግብ ካለው ለረዥም ጊዜ በማሳ ላይ ሳይቆፈር ማቆየት መቻሉ ስኳር ድንችን ተለማጭ ስብል ያደርገዋል፡፡ በተለያየ ጊዜ አራርቆ መትከሉ ደግሞ የበለጠ ተለማጭ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ 6.5 የሰብል ስብጥር የመሬት ዕጥረትና የሠራተኛ ጉልበት መደብ ለመስራት ውስን በሆነባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ስኳር ድንች ከሌሎች ሰብሎች ጋር በቅንጅት ይመረታል፡፡ የሰብልና የምግብ ብዝሀነትን ከማሻሻሉ በተጨማሪ ሰብል ማሰባጠር የመስራት አቅምን ያሻሽላል፣ ናይትሮጂንን ከሚይዙ ሰብሎች ጋር ከተሰባጠረ የአፈር ለምነት ይጨምራል፣ የአረም ችግርንም ይቀንሳል፡፡ ስኳር ድንች በመደብ ላይ የሚተከል ከሆነ ማሰባጠሩ ቀላል ነው፡፡ እንደማንኛውም የማሰባጠር ሂደት ስኳር ድንችን ከሌሎች ሰብሎች ጋር በምናሰባጥርበት ጊዜ የአተካከል ስርዓቱ ብርሃንና የአፈር ንጥረ-ነገሮችን በሚሻማ መልኩ መሆን የለበትም፡፡ ከቦሎቄ፣ ከአኩሪ አተር ወይም ስኳር ድንች ከእርግብ አተር ጋር ተሰባጥሮ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 4 ከአተር ጋር በስብጥር የሚተከል ከሆነ ስኳር ድንቹ በመደቡ/ቦዩ ላይ ይተከልና ጥራጥሬዎቹ በመደቡ/ቦዩ ግራና ቀኝ እንዲተከሉ ይደረጋል፡፡ ስኳር ድንችን ከሌሎች ሰብሎች ጋር አሰባጥሮ ማምረቱ በስፋት የተለመደ ቢሆንም ተጽዕኖውን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለመገምገም የተደረጉ ጥናቶች ግን ጥቂት ናቸው፡፡ በማላዊ በተደረገው ጥናት ብርቱካንማ ስኳር ድንችን ከበቆሎ ጋር አሰባጥሮ ማምረቱ አትራፊ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ቢሆንም በአካባቢው በቆሎ በሰፊው ስለሚፈለግ አርሶ አደሮቹ ሁለት መስመር በቆሎና አንድ መስመር ስኳር ድንች የተተከለበትን ማሳ መርጠዋል፡፡ ነገር ግን ምርታማና አትራፊ ሆኖ የተገኘው ሁለት መስመር ስኳር ድንች ከአንድ መስመር በቆሎ ጋር አሰባጥሮ ማምረት ነው፡፡ ማዳበሪያን ጥቅም ላይ በማዋል በሚመረት በቆሎ ውስጥ ስኳር ድንችን ማምረት ስኳር ድንቹ ቅሪት ማዳበሪያውን እንዲጠቀም ከማድረጉም ሌላ የስኳር ድንች ነቀዝ ጥቃት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ ስኳር ድንች ከአኩሪ አተር (ከላይ) እና በቆሎ ምስራቅ አፍሪካ የተደረገው ጥናት እንሚያመለክተው የርግብ አተርን ከስኳር (ከታች) ጋር ድንች ጋር ማሰባጠር ከፍተኛ ምርት ይሰጣል፡፡ የእርግብ አተር ናይትሮጂንን ለአፈሩ መጨመር ብቻ ሳይሆን ቀስ እያለ ስለሚያድግ ከስኳር ድንች ጋር ወደ ንጥረ-ነገር ሽሚያ ውስጥ አይገባም፡፡ የእርግብ አተር በጣም ረዥም ስር ስላለው ስኳር ድንቹ ከተነሳም በኋላ ምንም ሌላ ሰብል በማይተከልበት ወቅት ሁሉ ለምልሞ ይቆያል፡፡ በኮስታሪካ በካሳቫ መሀል ሁለት መስመር ስኳር ድንች በተመሳሳይ ጊዜ መትከልና ለተከታታይ አራት አመት ማምረት የሁለቱንም ሰብሎች ምርት ከመጨመሩም ባሻገር ጎላ ያለ የበሽታም ሆነ የተባይ ክስተት እንዳይታይ አድርጓል፡፡ ስኳር ድንችን ከሸንኮራ አገዳ ጋር አሰባጥሮ መትክል ትርፋማ እንደሆነ በደቡብ አፍሪካ የተደረገ ጥናት አረጋግጧል፡፡ በቆሎ ለመሰብሰብ በሚቃረብበት ወቅት አስከትሎ ስኳር ድንች መትከል (ቅብብሎሽ የማሰባጠሪያ ዘዴ) በጋና ማዕከላዊ ክልል ውጤታማ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ስኳር ድንችን በጥምር ግብርና ውስጥ ባሉ ዛፎች ወይም ቁጥቋጦዎች ስር በተለይም ቶሎ በሚደርሱ፣ ክፍት ቅርንጫፎች ባሏቸውና የጸሐይ ብርሃን ስኳር ድንች በተለያዩ ዕጽዋት ውስጥ በማይከለክሉ ዘረ-ጥራጥሬ በሆኑ ዛፎች ስር አሰባጥሮ ማምረት ይቻላል፡፡ እነኝህ ዛፎች ወይም ቁጥቋጦዎች ዘወትር ስለሚመለመሉና የተመለመሉት ቅርንጫፎች ስለሚበሰብሱ አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ-ነገሮች ከመልቀቃቸውም በተጨማሪ የአፈሩን አካላዊ ገጽታ ያሻሽላሉ፡፡ እነዚህ ዛፎች እንደአካባቢው ቢለያዩም በውስጣቸው ሳስባንያ፣ ግራር፣ ካሶድ፣ የእርግብ አተር፣ ካካዎ፣ የዝሆን ጆሮ የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል፡፡ እነዚህ የዛፍ አይነቶች ለስኳር ድንች እንዲመቹ ለማድረግ ከተለመደው የተከላ ርቀታቸው ማለትም በመስመር መካከል 4 - 8ሜ እና በተክሎች መካከል 0.3ሜ በተጨማሪ የተለያዩ ርቀቶችን በመጠቀም ሙከራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 6.6 የስኳር ድንች ተክል የዕድገት ፍላጎትና የፊዚዮሎጂ መረበሽ 6.6.1 የተለያዩ የስኳር ድንች ሰብል የዕድገት ደረጃዎች ተስማሚ የሙቀት መጠኑ ከ20 - 25ዲ.ሴ በሆነበት አካባቢ ስኳር ድንች በአጠቃላይ ለምርት ለመድረስ ከ4 - 5 ወራት ይፈጃል፡፡ በርግጥ ሰፋ ባለ የሙቀት መጠን ከ15 - 35ዲ.ሴ ባሉ ቦታዎች ሁሉ ምርት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ስኳር ድንች የቀን የሙቀት መጠን ከ25 - 30ዲ.ሴ እና የሌሊት የሙቀት መጠን ከ15 - 20ዲ.ሴ በሆነባቸው አካባቢዎች ውስጥ ከተመረተ ከፍተኛ የሆነ የስር ምርት ማግኘት ይቻላል፡፡ ቶሎ የሚደርሱ የስኳር ድንች ዝርያዎች ከ3 - 4.5 ወራት ውስጥ ሊደርሱ ስለሚችሉ በተለይም ከሰሀራ በታች ባሉ አገሮች ዘንድ በረሀብ ወቅት በመድረስ የምግብ ምንጭ ይሆናሉ፡፡ ሙቀትና የብርሃን ቀናት ቁጥር ለስኳር ድንች ምርት ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው፡፡ የአካባቢው የሙቀት መጠን አነስተኛ ሲሆን የመድረሻ ጊዜ ወደ 6-7 ወር ከፍ ሊል ይችላል፡፡ በተጨማሪም በዕድገት ወቅቱ በርካታ ደመናማ ቀናቶች የሚኖሩ ከሆነ የስር ምርቱ አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር ጥራቱም ደካማ ይሆናል፡፡ የመድረሻ ጊዜ መራዘም በስር መጠንም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው፤ አጭር የመድረሻ ወቅት መካከለኛና አነስተኛ የስር መጠን እንዲኖር ሲያደርግ በአንጻሩ አማካይ የስር መጠን ዘግይተው በሚደርሱ ዝርያዎች ላይ ከፍተኛ ነው፡፡ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 5 ስዕል 6.1 የስኳር ድንች ተክል አበባ አንጓ እርሳስ ስሮች መጋቢ ስሮች አኩራች ስሮች ከተከላ በኋላ በአንጓዎች ላይ ቀድሞ በነበሩ ስሮች ላይ ተጨማሪ ስሮች ይወጡና መጋቢ ስሮች ይሆናሉ፡፡ የሙቀት፣ የእርጥበትና፣ የንጥረ-ነገር መጠን የተመቻቸ ከሆነ እነኝህ መጋቢ ስሮች በአፈሩ የላይኛው ክፍል (ከ20 - 25ሴ.ሜ) ላይ ወደ አኩራች ስሮች እየተለወጡ ይሄዳሉ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን መጋቢ ስሮች ወደ አኩራች ስሮች ሳይሆን ቃጫ የበዛበት እርሳስ ስርነት ይለወጣሉ፡፡ አብዛኛዎቹ አኩራች ሰሮች ቀድመው ከወጡ ተጨማሪ (ተቀጥያ) ስሮች የሚፈጠሩ ቢሆንም በአንዳንድ ዝርያዎች በተለይም አፈር ማስታቀፍ ካለ አዳዲስ ተቀጥያዎች ይወጡና ወደ አኩራች ስሮች ይለወጣሉ፡፡ ይህ ደግሞ የስኳር ድንች ስርን በትንሽ በትንሹ እያወጡ ለመጠቀም ምቹ ያደርገዋል፡፡ በአካባቢ ሁኔታና በዝርያዎች ባህሪ ቢለያይም አኩራች ስሮች ፈጠነ ከተባለ መፈጠር የሚጀምሩት ከተከላ በኋላ ባሉት ከ2 - 3 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሲሆን አማካይ የሚጀምሩበት ጊዜ ግን ከ4 - 6 ሳምንት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ ወር ላይ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እጅግ በጣም አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር በመጨረሻ ምርትም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ስዕል 6.2 የስኳር ድንች ስር አፈጣጠር ደረጃዎች ያግ ተስ አስ አስ1 አስ2 አስ3 ቁልፍ፡ ተስ = ተቀጥያ ስር፣ ያግ = ያልተለመደ ግንድ ገበር፣ አስ = አኩራች ስር አጀማመር ምዕራፍ 1 ,2, 3 ምንጭ: Villardon et al., 2009 የአኩራች ስርን መፈጠሪያ አጀማመር በሶስት ምዕራፍ ከፍለን ማየት ይቻላል፤ ጅምር መሰረት (አስ1) እና የተወሰኑ ተቀጥያ ስሮች፣ ካልተለመዱ ግንደ ገበር ጋር የአኩራች ስሮች ጅማሬ(ያግ) (አስ2) እና የአኩራች ስሮች መወፈር (አስ3) ናቸው፡፡ ሙቀት በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት ላይ ተጽዕኖ ስላለው ጥርቅም የሙቀት መጠንን (thermal time growing degree days) መለካቱ እያንዳንዱን ምዕራፍ ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ማወቅ ያስችላል፡፡ ቢዩሬጋርድ በሚባለውና ቶሎ በመድረስ በሚታወቀው የአሜሪካ ስኳር ድንች ዝርያ ላይ በተደረገው የመስክ ሙከራ የዕድገት ደረጃ አሰ1 በተተከለ በ3 ቀናት፣ የዕድገት ደረጃ አስ2 በ13 ቀናት እና የዕድገት ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 6 ደረጃ አስ3 በ26 ቀናት እንደሚደርስ ታይቷል፡፡ በእነኝህ ወሳኝ በሆኑ የዕድገት ደረጃዎች ውስጥ ከፍተኛ ሙቀት፣ ድርቅ ወይም ጎርፍ ከገጠመው ቃጫማ የሆነ እርሳስ ስር ስለሚፈጠር የሰብሉ ምርት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡ ከተተከለ ከ8 - 12 ሳምንታት ባሉ ጊዜያት ተክሉ ያለውን አቅም ሁሉ ስር ለማኩረት/ለማወፈር ያውላል፡፡ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው አኩራች ስሮች በአንድ ተክል ላይ ከተፈጠሩ የእያንዳንዱ ስር ክብደትና መጠን አነስተኛ ይሆናል፡፡ በተቃራኒው በቁጥር ትንሽ አኩራች ስሮች ካሉ የእያንዳንዱ ስር ክብደትና መጠን ትልቅ ይሆናል፡፡ ለእድገት የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ ተሟልተው የሚመረት ስኳር ድንች እንደየዝርያው ቢለያይም የሀረጉ እድገት የተትረፈረፈ ይሆናል፣ ከጉዳት ላይ የማይጥል የበሽታና የተባይ ክስተት ይኖራል እንዲሁም ሰብሉ በንጥረ ነገር እጥረት አይጎዳም፡፡ አንዳንድ ቅጠል በሊታ ተባዮች የተወሰነ የሀረጉን ክፍሎች ቢበሉ እንኳ ጤናማ ሰብል ጉዳቱን ማካካስ ይችላል፡፡ የስኳር ድንች ሀረግ ከፍተኛውን ርዝመት የሚይዘው በመጨረሻው የዕድገት ምዕራፍ አጋማሽ ላይ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ የሰብሉ ቅጠሎች ለምልመው ይታያሉ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ ግን ቅጠሉን ጠብቆ ከማቆየትና አዳዲስ ቅጠሎችን ከማውጣት ይልቅ ያለው ኃይል በሙሉ ስር ለማኮረት ስለሚውል የሀረጉ መጠን እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ስኳር ድንች ሶስት ዋና ዋና የእድገት ምዕራፎች አሉት፡፡ በእያንዳንዱ ምዕራፍ መከናወን አዲስ ተቆፍሮ የወጣ የስኳር ድንች ስር የሚገባቸው ተግባራት በሠንጠረዥ 6.1 ላይ ተተንትነዋል፡፡ ሠንጠረዥ 6.1 የተለያዩ የስኳር ድንች ሰብል ዕድገት ደረጃዎችና አስፈላጊ ተግባራት ሳምንት ምስል የዕድገት ምዕራፍ ባህሪያት ተግባራት 0 1. መመስረቻ ወይም  ተከላ  ተከላ 1 መጽደቂያ ምዕራፍ  ፈጣን የጨቅላ ስሮች ዕድገት  ክፍተት መሙላት 2  አኩራች ስሮች መለየት ይጀምራሉ  ለዕድገቱ ማነቆ የሆኑ ነገሮችን 3  ዘገምተኛ ሀረግ ዕድገት (ድርቅን ወዘተ.) ማስወገድ  አኩራች ስሮች ጅማሬ 4 2. ማዕከላዊ ምዕራፍ  ፈጣን የሀረግ ዕድገት  አረም 5 (የአኩራች ስሮች ጅማሬ)  የቅጠል ስፋት መጨመር 6 7 8 9 3. የመጨረሻው ምዕራፍ  የሀረግ ዕድገት ይቆማል  ሀረግ ማንሳት 10 (የአኩራች ስሮች  ፈጣን የአኩራች ስሮች ውፍረት 11 መወፈሪያ) 12  በቢጫነትና ወደ መሬት በመውደቅ  መኮትኮትና ማሳቀፍ 13 ምክንያት የቅጠል ስፋት መቀነስ 14 15  ምርት መሰብሰብ  ምርት መሰብሰብ 16 17 18  52 6.6.2 አረም ቁጥጥር አረሞችን በመጀመሪያዎቹ መጽደቂያ ቀናትና ከተከላ በኋላ ባሉ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ ካልተቆጣጠርናቸው የስኳር ድንች ተክሎችን ንጥረ-ነገሮች ይሻማሉ፣ ተባይና በሽታም ይሸከማሉ፡፡ የተወሰኑ የሳር አረም ስሮች የስኳር ድንች ስሮችን ሊበሱና ሊጎዱ ሁሉ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በታች የተጠቀሱት ሶስት ዋና ዋና የአረም ቡድኖች ናቸው፡፡ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 7 ሠንጠረዥ 6.2 ዋና ዋና የአረም ቡድኖች ምሳሌ ሳሮች ቄጠማ ባለ ሰፋፊ ቅጠሎች ሠርዶ (ኢምፔራታ እንግጫ (ሳይፕረስ የወፍ ቆሎ (ላንታና የውሻ እምቧይ (ሶላነም ሲይሊንደሪካ) ኤስኪዩለንተስ) ካማራ) ኢንካነም) Spear grassEng Nut grassEng Sleeper weed, wild Nightshade, Sodom’s sageEng appleEng አረሞች አንዳንዴ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ አንዳንዶቹ ታጭደው ለእንስሳት ምግብነት ይውላሉ፤ አንዳንዶቹ ታጭደው በአፈር ላይ እንደ ጉዝጓዝ ያገለግላሉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ኮምፖስት እንዲሆኑ ተደርገው ከአፈር ጋር በማቀላቀል የአፈር ለምነት እንዲጨምርና የአፈር ገጽታ እንዲሻሻል ያደርጋሉ፡፡ ከስኳር ድንች ማሳ ውስጥ አረሞች በአብዛኛው ጊዜ በሰው ጉልበት ይወገዳሉ፡፡ የስኳር ድንች ሀረጎች አንዴ አድገው መሬቱን ከሸፈኑ ተጨማሪ የአረም ቁጥጥር አያስፈልግም፡፡ ቢሆንም አንዳንድ እርጥብ አካባቢዎች የሚበቅሉ ጠንካራና መንቻካ አረሞችን መርጦ ማስወገድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ እነኝህ አረሞች አልፈው አልፈው በማሳ ውስጥ የሚገኙ ከሆነ በእጅ መንቀል ይቻላል፡፡ ካልሆነ ግን መቆፈሪያ በመጠቀም አኩራች ስሮች በሙሉ በአፈር መሸፈናቸውን በማረጋገጥ ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ሰብል በሌለበት አረም ማስወገዱ በጣም ቀላል ነው፡፡ እንደ ሰርዶ (spear grass (Imperata spp.))፣ ሰርዶ ሳር (star grass (Cynodon spp.))፣ እንግጫ (nut grass (Cyperus spp.)) እና መከዳ ሳር (couch grass (Digitaria spp.)) ያሉ ቋሚ የሆኑ አረሞችን የማስወገድና ዓመታዊ አረሞችን የመቅበሩ ስርዓት በመሬት ዝግጅቱ ወቅት መከናወን አለበት፡፡ በመደብና ጉብታ መስሪያ ወቅት የትኛውም አዲስ አረም ከአፈር ስር መቀበር አለበት፡፡ ከዚያም ሌላ የማረሙ ሂደት ሰብሉ ከተተከለ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ሳምንታት ውስጥ ሀረጉ አፈሩን ከመሸፈኑ በፊት መከናወን አለበት፡፡ አረሞችን ጠንካራ ስርና ቅጠል ከማውጣታቸው በፊት ማስወገድ ቀላል ሲሆን እንዲሁም ሌላኛውን ትውልድ ለመተካት ዘር ከማሰራጨታቸው በፊት መወገድ እንደሚገባቸው ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ጉዝጓዝ የአረምን ብቅለት በእጅጉ ሊቀንስ ይችላል፡፡ ሰብል ፈረቃም የአረም ዘር ባንክ እንዳይጎለብት ያደርጋል፡፡ የሰብል ስብጥርም ቢሆን አረሙ የጸሐይ ብርሃን እንዳያገኝ በማድረግና በሁለቱ ተጣማሪ ሰብሎች መካከል ባለው ጠባብ ቦታ አረሙ ሊያደርስ የሚችለውን የንጥረ-ነገር ሽሚያ በመቀነስ ጉዳቱ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ ሰፊ እርሻ ያላቸው አምራቾች አረምን ለመቆጣጠር እንደ ግላይፎስፌት የመሳሰሉትን ጸረ-አረም መድኃኒቶች ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ይህ በጥሩ ሁኔታ ሊከናወን የሚችለው ከተከላ ሁለት ሳምንታት በፊት ሲደረግ ነው፡፡ በናይጄሪያ ፕሪምኤክስትራ ጎልድን (ብርቱ ቅመም፡ አትራዚን እና ኤስ-ምቶላክህሎር) የተሰኘ ጸረ-አረም መድኃኒት 1.5 ኪ.ግ በሄክታር ስኳር ድንቹ በተተከለ ከ1 - 2 ቀናት ውስጥ መርጨት በጣም ውጤታማ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ሰርዶ (spear grass weed (Imperata cylindrica)) በጣም በብዛት የሚከሰት ከሆነ የግላይፎስፌትና ፕሮሜትሪይን/ኤስ-ሜቶላክለር ውህድ 3.2 እና 2 ኪ.ግ በሄክታር በአቀማመጥ ቅደም ተከተላቸው መሰረት በ4፣ 8 እና 12 ሳምንታት ከተከላ በኋላ ማድረግ ፍቱን የመቆጣጠሪያ ዘዴ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ጸረ-አረም መድኃኒቶች በሚረጩበት ጊዜ መሰረታዊ የሆኑ ጥንቃቄዎች መደረግ አለባቸው፡፡ በመያዣ ዕቃው ላይ ያለውን ትዕዛዝ መከተል፣ የተጠቀሰውን መጠን ብቻ መጠቀም፣ መከላከያ ልብሶችን መጠቀም፣ ነፍሰጡር ወይም የሚያጠቡ ሴቶች ጸረ-አረም ወይም ጸረ-ተባይ መድኃኒቶችን መርጨት እንደሌለባቸው ማወቅ፣ በንፋስ ምክንያት በአቅራቢያ ወደሚገኘው ሰብል ሊረጭ ስለሚችል በነፋሻማ ቀን ያለመርጨት፣ ርጭቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መርጫውን ማጠብና ዕጣቢውን ከውሃ አካል በማራቅ ቀድሞ በተዘጋጀ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 8 ጉድጓድ ውስጥ መጨመር ዋና ዋና የጥንቃቄ እርምጃዎች ናቸው፡፡ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ጸረ-አረም መድኃኒቱ ውድ ሊሆንባቸውና የአረጫጨቱ ስርዓትና ጊዜ ልክ እንደተጠበቀው ላይሆንላቸው ይችላል፡፡ 6.6.3 ሃረግ ማንሳትና አፈር ማሳቀፍ የስኳር ድንች ሃረግ ከእርጥብ አፈር ጋር ሲገናኝ በአንጓዎቹ ላይ ስር ማውጣት ይጀምራል፡፡ አንዳንድ አምራቾች ይህ እንዳይከሰትና በስሮቹ ላይ አነስ ያሉ ለገበያ የማይቀርቡ ስሮች እንዳይፈጠሩ ሀረጎችን ቀና አድርገው ከአፈሩ ያላቅቃሉ፡፡ ይህ ተግባር የሚከናወን ከሆነ ሀረጎቹ እንዳይገለበጡ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሀረጎቹ ከተገለበጡ በላያቸው ያሉት ቅጠሎች ሊበሰብሱ ይችላሉ፡፡ አፈር ማሳቀፍ የሚከናወነው አኩራች ስሮች ለጸሐይና ለነቀዞች እንዳይጋለጡ ለማድረግ ነው፡፡ በተክሉ ዙሪያ ያለውን አፈር በመቆፈር በጎርፍ ወይም በስሮቹ መወፈር/መዘረጋጋት ምክንያት የተፈጠረው ስንጥቅ እንዲሸፈን ይደረጋል፡፡ 6.6.4 የፊዚዮሎጂ መረበሽ ብዙ ነገሮች በስኳር ድንች ምርት ላይ ተጽዕኖ ያደርጋሉ፡፡ የተከላ ሃረጎች ጥራት፣ የአፈር ዓይነት፣ የመሬት ዝግጅትና የአፈር ለምነት አያያዝ፣ ዝርያ፣ የአየር ሁኔታ፣ የተከላ ርቀት፣ የተከላና የምርት መሰብሰቢያ ወቅት፣ የቫይረስና የተባይ ጥቃት መጠን፣ መስኖና የዝናብ ስርጭት ወዘተ ከእነዚህ መካከል ይገኙበታል፡፡ ፊዚዮሎጂያዊ ረብሻ በተለያዩ ነገሮች ለምሳሌ በአካባቢያዊ፣ በፊዚዮሎጂያዊና በዝርያ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የበሽታ ጥቃት መስሎ ስህተት ውስጥ ይጥላል፡፡ የአንዳንድ ፊዚዮሎጂያዊ ረብሻዎች ምክንያቶቻቸውና መከላከያ ስልቶቻቸው በሠንጠረዥ 6.3 ላይ በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 9 ሠንጠረዥ 6.3 የሰኳር ድንች ፊዚዮሎጂያዊ ረብሻዎች፣ ምክንያቶችና መከላከያ ስልቶች ፊዚዮሎጂያዊ ረብሻ ምልክቶች ምክንያቶች መከላከያ ስልቶች ሚዩቴሽን ያልተለመደ መልክ በቆዳ ስኳር ድንች ከፍተኛ የሆነ ፖዘቲቭ አመራረጥ ስልትን ወይም በስጋ ላይ መታየት የተፈጥሮ ሚዩቴሽን አለው መጠቀምና እንደዚህ አይነት ባሕሪ የያዙ ተክሎችን የተከላ ሃረግ በሚዘጋጅበት ወቅት ማስወገድ ውኃ አዘል ገላ በስሩ ውጨኛው ክፍል ለረዥም ጊዜ ስሮችን ስኳር ድንችን ውኃ ላይ አነስ ያለ እብጠት ለእርጥብ አፈር ማጋለጥ በማይተኛበት አፈር ላይ ወደ ኦክሲጂን እጥረት መትከል፣ መደቦች ወይም ያመራል ጉብታዎች እርጥበት ባለባቸው አካባቢዎች በበቂ ሁኔታ ከፍ ማለታቸውን ማረጋገጥ በጸሐይ መንፈር በፀሐይ የነፈረው የስር ከፍተኛ ሙቀት ባለበት ከምርት ስብሰባ በኋላ ክፍል ወይንጠጅ-ቡኒ ጊዜ ስሮቹን ለጸሐይ ስሮችን ወዲያውኑ በጥላ ስር መልክ ሲኖረው ለበሽታ ማጋለጥ ማስቀመጥ የተጋለጠ ነው መሰንጠቅ በስር ቆዳ በተለይ በትላልቅ ባልተስተካከለ ሁኔታ ዝርያዎች በመጠቃት ስሮች ላይ ስንጥቅ በተለይም ያልተስተካከለ አቅማቸው ይለያያሉ፡፡ የተለመደ ነው፣ በኔማቶድ ውኃ ባለበት ሁኔታ ላይ በደረቅ ወቅት መስኖ በተጠቁ ስሮች ላይ ይብሳል ሲያድግ ስንጥቅ ይፈጠራል መስጠት ጠፍጣፋ ግንድ ጠፍጣፋ ግንድ ከበርካታ አልተረጋገጠም ጠፍጣፋ ግንዶች አብዛኛውን ቅጠሎች ጋር ጊዜ ይነቀሳሉ/ይጣላሉ፡ እንደተከላ ሃረግም ጥቅም ላይ መዋል የለባቸውም 6.6.5 የስኳር ድንች ሰብልን ውኃ ማጠጣት ከደቡብ አፍሪካ ውጪ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ለስኳር ድንች ሰብል የመስኖ ውኃ አይሰጥም፡፡ ምንም እንኳን ስኳር ድንች ድርቅ ይቋቋማል ቢባልም ውኃ ለስኳር ድንች ምርት ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ሰብሉ ዘለግ ላለ ጊዜ ለድርቅ የሚጋለጥ ከሆነ ምርት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡ የድርቅ ጉዳት የሚወሰነው የውኃ እጥረት ባጋጠመበት የተክሉ የዕድገት ደረጃ ነው፡፡ ስኳር ድንች ጥልቅ (0.75 - 0.9 ሜ) እና ቅርንጫፍማ የስር ስርዓት ስላለው ከሌሎች ተክሎች በተቃራኒው ከጥልቅ አፈር ውስጥ ውሃ እንዲያገኝ ያስችለዋል፡፡ የተስተካከለ 500 ሚ.ሜ ዝናብ በዕድገቱ ወቅት ማግኘት ከቻለ ከፍተኛ ምርት ሊሰጥ ይቻላል፡፡ አስፈላጊና የሚገኝ ከሆነ ስኳር ድንችን በዕርጥብ አፈር ላይ እንዲያድግና በዕድገት ጊዜውም ሁሉ በቂ ዕርጥበት እንዲያገኝ ለማድረግ የመስኖ ውኃ መጠቀም ይቻላል፡፡ መስኖ የአፈር ሙቀትንም ለመቀነስ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 10 አብዛኞቹ የመስኖ አጠቃቀም ስልቶች (በቦይ፣ በጠብታ፣ በጎርፍ፣ እና በርጭት) ለስኳር ድንች ይስማማሉ፡፡ ሰብሉ በመደብ ከተተከለ አንድ ቦይ እያለፉ በቦይ የማጠጣት ዘዴን መጠቀም ይቻላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ጠብታ መስኖ በአንዳንድ የምርምር አያያዝ ስርዓቶች ዘንድ እየተተገበረ ያለ ሲሆን ውጤታማ የውኃ አጠቃቀም ዘዴ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የጠብታ መስኖ ውጤታማ የሆነው ከ10 - 15 በመቶ የሸክላማ አፈር ባሕሪ ባላቸውና በደንብ ውኃ የሚጠፍበት መሬት ላይ እና ከፍተኛ ከባቢያዊ ሙቀት ባለባቸው ቦታዎች እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ምንም እንኳ በስኳር ድንች የውሃ ፍላጎት ላይ ያለው መረጃ ውሱን ቢሆንም በተተከለ አንድ ወር ውስጥ በቂ ውሃ እንደሚያስፈልገውና በተስተካከለ ስርጭት ከ450 - 650ሚሜ መጠን ውኃ በዕድገት ዘመኑ እንደሚያስፈልግ ከስምምነት ተደርሷል፡፡ አንዴ ስሮቹ ከጸደቁ የአፈር ዕርጥበት መጠን እየቀነሰ ቢመጣም ዝናብ ሲከሰት እንደገና በማቆጥቆጥ በህይወት ይቆያሉ፡፡ የመስኖ ፍላጎት በአፈር ዓይነት፣ በዝናብ፣ በውኃ ጥራትና መኖር፣ በዝርያና በዕድገት ደረጃ ይወሰናል፡፡ በአጠቃላይ ከተከላ አንስቶ እስከ ሃያ ቀናት በሳምንት ሁለቴ፣ ከ20 - 40 ቀናት በሳምንት አንዴና ከ40 ቀን እስከ ምርት መሰብሰቢያ በየሁለት ሳምንታት ልዩነት አንድ ግዜ የመስኖ ውኃ ይሰጣል፡፡ የመስኖ ውሃ በሚሰጥበት ጊዜ አፈሩ እርጥብ መሆን ያለበት እስከ ሰብሉ ስር ክልል ብቻ ነው፤ ከዚያ ማለፍ የለበትም፡፡ ስኳር ድንች ከፍተኛ የሆነ የእርጥበት መጠን ስለማይፈልግ ከመጠን በላይ ውሃ ማጠጣት ወይም ረዘም ላለ ጊዜ የሚዘንብ ከባድ ዝናብ የአኩራች ስር ዕደገትን በመቀነስ፣ ውኃ የቋጠረና የበሰበሰ ስር እንዲኖር በማድረግ ችግር ይፈጥራል፡፡ በፔሩ የውኃ ዳርቻ አካባቢዎች ስኳር ድንች በተደጋጋሚ መስኖ ይሰጠዋል፡፡ የለሰለሰ አፈር እንዲኖር መስኖ የሚጀምረው ከተከላ በፊት ነው፡፡ ከዚያም ቀለል ያለ መስኖ ሰብሉ እንዲጸድቅ ይሰጣል፣ ከተከላ በኋላ ባሉት በመጀመሪያዎቹ 5 - 6 ሳምንታት፣ ከማሳቀፊያ ጊዜ በኋላና ልክ ምርት ከመሰብሰቡ በፊት ዘወትር እንዲጠጣ ይደረጋል (ርዕስ 7ን ይመልከቱ) ፡፡ በዝርያና በአፈር ዓይነት ቢለያይም ባጠቃላይ ከ2000 - 3000 ሜትር ኩብ ውሃ በሄክታር በምርት ወቅት እንዲሰጥ ይመከራል፡፡ 6.7 የስኳር ድንች የንጥረ-ነገር ፍላጎት ሁሉም ሰብሎች ከአፈር ውስጥ ንጥረ-ነገሮችን ይወስዳሉ ማለትም ምርት በሚሰበሰብበት ጊዜ እነኝህ ንጥረ ነገሮች ከአፈሩ ይወገዳሉ፡፡ የአፈሩን የንጥረ-ነገር ይዘት ጠብቆ ለማቆየት በሰብል የተወሰዱት ንጥረ-ነገሮች ወደ አፈሩ መመለስ አለባቸው፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችለው የሰብሎችን ቅሪተ አካሎች በእርሻ አፈር ውስጥ እንዲደባለቁ በማድረግና እንዲበሰብሱ በመተው ወይም ማዳበሪያዎችን (የተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ) በመጨመር ነው፡፡ በኤስያ የስኳር ድንች ሀረጎች እንደ አረንጓዴ ብስባሽ ያገለግላሉ፡፡ ዕጽዋት ንጥረ- ነገሮችን ለዕድገታቸው ብቻ ሳይሆን የበሽታ መከላከያቸውንም ለማጎልበት ጭምር ይጠቀማሉ፡፡ ስኳር ድንች እንደ ሌሎቹ ስራስር ስብሎች ከፍተኛ ፖታሲየም እና አነስተኛ ናይትሮጂንና ፎስፈረስ ከአፈር ይወስዳል፡፡ ፖታሲየም ለአኩራች ስር ዕድገት በጣም ጠቃሚ በመሆኑ የዚህ ንጥረ-ነገር በብዛት መገኘት ስኳር ድንችን ተጠቃሚ ያደርገዋል፡፡ አመድ ብዙ የፖታሲየም ንጥረ-ነገር ይዘት ስላለው በማሳ ውስጥ በመጨመር ንጥረ-ነገሩን ማግኘት ይቻላል፡፡ ቢሆንም የፖታሲየም መጠን ብቻ በቂ አይደለም፤ የፖታሲየምና የናይትሮጅን ምጥጥኖሽ ጭምር እንጂ፡፡ የተሻለ የስር ወፍረት ሊገኝ የሚችለው ናይትሮጂንና ፖታሲየም አንድ ለሶስት (1፡3) በሆነ ምጥጥኖሽ ሲጨመር ነው፡፡ በሰብሉ አጋማሽ የዕድገት ደረጃ ወቅት ፖታሲየም መጨመር ስሩ ጠንካራ ቆዳ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ናይትሮጂን ከመጠን በላይ ከሆነ ብዛት ያለው ሀረግና ደካማ የስር ዕድገት እንዲኖር ያደርጋል፡፡. በተለይ ናይትሮጂን ከሰብሉ አጋማሽ ዕድሜ በኋላ የሚጨመር ከሆነ ጎጂ ነው፡፡ ስኳር ድንች የአፈር ለምነት አነስተኛ በሆነባቸው ሁኔታዎች ሁሉ ምርት ይሰጣል ቢባልም በጣም አነስተኛ የሆነ የናይትሮጂን መጠን የሰብሉ ሀረግ ዕድገት ውስን እንዲሆን ያደርጋል፤ ምርቱም አነስተኛ ይሆናል፡፡ በአፈር ውስጥ በተለያዩ መንገዶች ንጥረ-ነገሮች ሊጨመሩ ይችላሉ፡፡ ፍግ ከሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ይልቅ በቀላሉ ሊገኝ ስለሚችል መጠቀም ይቻላል፡፡ በዚህን ያክል መጠን ማድረግ የተለመደ ባይሆንም በሄክታር 5 ቶን ፍግ እንዲጨመር ይመከራል፡፡ የንጥረ-ነገር ይዘቱ እንደየፍጉ አይነት ስለሚለያይ አንደ ወጥ የሆነ መጠን መጨመር አስቸጋሪ ነው፡፡ አርሶ አደሮችም በተለያየ የፍግ መጠን ላይ ሙከራ በማድረግ የትኛው የተሻለ ሰብል እንደሚሰጥ ማየቱ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ፍግን ከተከላ ከተወሰኑ ሳምንታት በፊት መጨመር ያስፈልጋል፡፡ ይህ ስልት ከተከላው በፊት ፍጉ ከአፈሩ ጋር ተዋህዶ ተገቢውን ንጥረ-ነገር መልቀቅ መጀመሩን ያረጋግጥልናል፡፡ በደንብ ያልተብላላ ፍግ አረምን ወደ ማሳ ስለሚጋብዝ መወገድ አለበት፡፡ እንደ ናይትሮጂን - ፎስፈረስ - ፖታሲየም (ኤን.ፒ.ኬ) ያሉ ቅልቅል ማዳበሪያዎች በተለያየ ምጥጥኖሽ ገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ በጣም ጠቅለል ያለው የስኳር ድንች ማዳበሪያ መጠን ናይትሮጂን (34-45ኪ.ግ/ሄ)፣ ፎስፈረስ (55-101ኪ.ግ/ሄ) እና ፖታሲየም (84-169 ኪ.ግ/ሄ) ወይም ኤን.ፒ.ኬ 6፡9፡15 ምጥጥኖሽ ነው፡፡ በናይጄሪያ 15፡15፡15 (400ኪ.ግ/ሄ) ኤን.ፒ.ኬ ማዳበሪያ ይጠቀማሉ፡፡ ቢሆንም የንጥረ-ነገር ፍላጎት ከአፈር አፈር ስለሚለያይ ለእያንዳንዱ ቦታ የአፈር ናሙና ተወስዶ መጠናትና በየአካባቢው የማዳበሪያ ሙከራ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 11 ተፈጥሯዊም ይሁኑ ሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎች ከተከላ በፊት በእኩል ደረጃ በተፈለገው መጠን በማሳው ልክ ይበተኑና ከአፈሩ ጋር እንዲደባለቁ ይደረጋል፡፡ ውጤታማ የሆነ የማዳበሪያ አደራረግ ግን ከሰብሉ ጎን በመስመሩ አንጻር መጨመርና በእያንዳንዱ ተክል ስር ካለው አፈር ጋር እንዲዋሃድ ማድረግ ነው፡፡ አርሶ አደሮች በፈረቃ ለማምረት ሰፊ መሬት ካላቸው በተወሰነው መሬት ላይ ናይትሮጂን ከአየር ላይ የሚስቡና የሚያቆዩ ዘረ- ጥራጥሬ የሆኑትን ዛፎች በመትከል ስኳር ድንች ከመትከላቸው አስቀድሞ በእዳሪ መልክ ለሁለት ዓመታት ቢያቆዩና ስኳር ድንች ቢተክሉበት የስር ምርትን በከፍተኛ ደረጃ መጨመር እንደሚቻል ምርምሮች አረጋግጠዋል፡፡ በሙከራ እንደታየው ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ከመጨመር ይልቅ ዘረ-ጥራጥሬ የሆኑትን ዛፎች በእዳሪ መሬት ላይ መትከልና ስኳር ድንችን ማስከተል የስር ምርትን ይጨምራል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው የሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎች ሊይዙ የማይችሏቸውን በብዛት የሚፈለጉና በአነስተኛ መጠን የሚፈለጉ ንጥረ-ነገሮችን በውስጣቸው ስለሚይዙ ነው፡፡ የአፈር ኮምጣጤነት መጠን ለሰብሉ የሚያስፈልገው ንጥረ-ነገር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ስላለው በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ስኳር ድንች ኮምጣጤነቱ ከፊል አሲድና ከፊል ጨዋማ (5 - 7.5) በሆነ አፈር ላይ በጥሩ ሀኔታ ይበቅላል፡፡ አፈሩ በጣም አሲዳማ ከሆነ (ለምሳሌ ከ5 በታች ከሆነ) ከተከላ በፊት ኖራ መጨመር ያስፈልጋል፡፡ የአፈር የንጥረ-ነገር ይዘት ምርመራ የሚያስፈልገውን የኖራ መጠን ለማወቅ ይረዳል፡፡ ስኳር ድንች የሚመረትበትን አፈር የንጥረ-ነገር መጠን ማለትም የትኛው በአነስተኛ ደረጃ የትኛው ደግሞ በብዛት እንዳለ በአፈር ምርመራ ማወቁ በጣም ጠቃሚ ቢሆንም ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገሮች በአርሶ አደሮች ዘንድ የተለመደ አይደለም፡፡ የስኳር ድንች ተክል የንጥረ-ነገር ዕጥረት ምልክቶች ለአርሶ አደሮችም ሆነ የልማት ሰራተኞች የንጥረ-ነገር ዕጥረትን ለመለየት ያስችሏቸዋል፡፡ አንድ ዕጽዋት የንጥረ-ነገር ዕጥረት ከገጠመው የተወሰኑ ምልክቶችን በተለይ በቅጠሎቹ ላይ ያሳያል፤ ይሁን እንጂ አጠቃላይ የዕድገት ስርዓቱም ይጠቃል፡፡ ዋና ዋና የዕጽዋት ንጥረ-ነገር ዕጥረት ምልክቶች: -  በዕጽዋቱ አካላት ላይ ያልተለመዱ መልኮች መታየት፤ o መገርጣት፡ ቅጠሎች ወደ ደብዛዛ አረንጓዴና ቢጫ መልክ ይቀየራሉ o የተቃጠለ ነቁጥ: በቅጠሉ ላይ ህዋሳት በሞቱባቸው አካባቢዎች ደረቅ ፈዛዛ ቡኒ መልከ መታየት o የቅጠሎች ወይንጠጅ መልክ መያዝ o ቡኒ መሆን  ቅጠሎች ባልተጠበቀ ሁኔታ ይራገፋሉ፤  ተክሎቹ ከጤናማዎቹ በተቃራኒ ይጫጫሉ፤  የዕጽዋቶቹ አካል ቅርጸ-ቢስ መሆን ለምሳሌ ቀጭን ወይም ሹል ግንድ እና የቅጠሎች መሸብለል፤  የስርና የግንድ ጫፎች ወደኋላ መሞት፤  ባረጁና በታዳጊ ቅጠሎች ላይ ተመሳሳይ የሆነ ምልክት ለተለያዩ ንጥረ-ነገሮች ዕጥረት ሊታይ ይችላል፤  ይሁን እንጂ የዕጥረት ምልክቶች ከቫይረስ ምልክቶችና የተክሉ ባሕሪያት ጋር መምታታት የለባቸውም፤ የፖታሲየም፣ የናይትሮጂንና የፎስፈረስ ዕጥረት ምልክቶች ከሠንጠረዥ 6.4 እስከ 6.6 ድረስ ተዘርዝረዋል፡፡ የሌሎች ንጥረ-ነገሮች መረጃና ፎቶግራፍ ከስኳር ድንች ድረ-ገጽ ማግኘት ይቻላል http://keys.lucidcentral.org/keys/sweetpotato. የፖታሲየም ዕጥረት ለስኳር ድንች ስር ምርት ማነስ የተለመደ ምክንያት ነው፡፡ የስራስር ሰብሎች ከፍተኛ የሆነ የፖታሲየም ፍላጎት ስላላቸው በአንድ ማሳ ላይ በተከታታይ የስራስር ሰብሎችን መትከል የፖታሲየምን መጠን ከአፈር ውስጥ እንዲሟጠጥ ያደርጋል፡፡ የናይትሮጂን ዕጥረት አነስተኛ የተፈጥሮ ብስባሾች ባለባቸው አፈሮች ወይም ማዳበሪያ ወይም ፍግ ለተወሰኑ ጊዜያት ሳይጨመር ሰብል በተመረቱባቸው መሬቶች ላይ የተለመደ ነው፡፡ የናይትሮጂን ዕጥረት ይኖራል ተብሎ በሚታሰብበት ቦታ አንድ መስመር ተክል ላይ ዩሪያ ማዳበሪያ በመጨመር በትክክል የናይትሮጂን እጥረት መኖር ያለመኖሩን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ቦታዎች ዩሪያ የተጨመረበት ቦታ ከሌሎች መስመሮች ይልቅ ደማቅ አረንጓዴ ሆኖ ይታያል፡፡ የእሳተ ገሞራና ገሀ አፈሮች ፎስፈረስን ለተክሉ እንዳይደርስ አምቀው ይይዛሉ፤ በአሲዳማ አፈሮች ደግሞ የአሉሚኒየም መርዛማነት ይህን ያስከትላል፡፡ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 12 ሠንጠረዥ 6.4 በስኳር ድንች ላይ የፖታሲየም ንጥረ-ነገር ዕጥረት ምልክቶች የፖታሲየም ንጥረ-ነገር ዕጥረት ምልክቶች  አጫጭር ሀረጎች ከአጫጭር ውስጠ አንጓዎችና ትናንሽ ቅጠሎች ጋር የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች ናቸው፤  ቅጠሎች በተለይም በዳርቻዎቻቸው ላይ ጠቆር ያለ (ጥቁር አረንጓዴ) መልክ ይኖራቸዋል፤  አጭርና ደብዛዛ መልክ ያላቸው የቅጠል ደጋፊዎች፤  አንጸባራቂ ነጠብጣቦች በቅጠል ላይ መታየት፣ መጀመሪያ በታችኛው ቅጠል ስር ይጀምራል፤  ያረጁ ቅጠሎች ላይ መጀመሪያ ከቅጠሉ ዳርቻ ይጀምርና ከዚያም ወደ ቅጠሉ መሰረት የሚዘልቅ ቢጫ ወይም ቀላ ያለ መልክ ማሳየት፤  ተክሎች በቀላሉ ይጠወልጋሉ፣ ቅጠሎቻቸውም በቀላሉ ይረግፋሉ፤  ከፍተኛ የሆነ ዕጥረት ሲያጋጥም ጥቁር ባረጁ ቅጠሎች ላይ ቢጫ መልክ መታየት አረንጓዴ ከሚሆኑት የቅጠሉ መሰረትና ከቅጠሉ ደም ስሮች አጠገብ ካለው ህብረ ህዋስ በስተቀር ጠቅላላው ቅጠል ቢጫ ይሆናል፤  አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አኩራች ስሮች፤  አኩራች ስሮች ረዥምና ቀጭን ይሆናሉ፤  አኩራች ስሮች በቀላሉ በስር አብስብስና ኔማቶድ ይጠቃሉ፤ 100, 14 እና 1.7 በመቶ ፖታሲየም በደረሰ ቅጠል ላይ የውስጠ-ደም ስሮች የመወየብና የድርቀት ስርጭት ባረጁ የተጨመረባቸው ተክሎች መወየብን ተከትለው የተፈጠሩ ትናንሽ ቅጠሎች ላይ ቁስሎች ምንጭ: O’Sullivan et al., 1997 ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 13 ሠንጠረዥ 6.5 በስኳር ድንች ላይ የናይትሮጂን ንጥረ-ነገር ዕጥረት የናይትሮጂን ንጥረ-ነገር ዕጥረት ምልክቶች  ቅጠሎች ከደብዛዛ አረንጓዴ እስከ ቢጫ እንዲሁም ደብዛዛ ዕይታ ይኖራቸዋል፤  አነስተኛ የሀረግ እድገት፤  ያረጁ ቅጠሎች በጠርዝ አካባቢ ቀላ ማለት፣ በመሀል ቢጫ መሆንና ከዚያም በሙሉ የቀይ ቡኒ መልክ መያዝ፤  ያረጁ ተክሎች ግንድ ቀላ ማለት፤  አጭር ደጋፊ ቅጠል፤  ምልክቶቹ ከተክሉ የታችኛው ክፍል ጀምረው ወደ ላይ እየሰፉ ይሄዳሉ፤ የናትሮጂን ዕጥረት ያለበት መሬት (ፊትለፊት) እና ናይትሮጂን የተጨመረበት መሬት (ከበስተኋላ) ጤናማ ተክል (ግራ) እና የናይትሮጂን ባረጁ ቅጠሎች ላይ ፈዛዛ ቢጫ በለጋ ቅጠሎቹ ጀርባ ላይ ባሉ የደም ዕጥረት ያለበት ተክል (ቀኝ) ምልክትና በለጋ ቅጠሎች ጀርባ ላይ ስሮች ላይ ቀላ ያለ መልክ መታየት ባሉ የደም ስሮች አካባቢ ቀይ መልክ ምንጭ: O’Sullivan et al, 1997 ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 14 ሠንጠረዥ 6.6 በስኳር ድንች ላይ የፎስፈረስ ንጥረ-ነገር ዕጥረት ምልክቶች የፎስፈረስ ንጥረ-ነገር ዕጥረት ምልክቶች  ቅጠሎች ከጥቁር አረንጓዴ እስከ ሰማያዊ መልክ ከወይንጠጅ የቅጠል ደም ስሮች ጋር ይኖራቸዋል፤  አነስተኛ የሀረግ ዕድገት፤  የቅጠሎች ያለግዜ ማርጀትና ወደ ወይንጠጅ ከዚያም ወደ ቢጫነት መቀየር፤  በቅጠል ደም ስሮች መካከል መወየብ/መገርጣት ከዚያም ባረጁ ቅጠሎች ላይ ወደ ቁስል መቀየር፤  ቅርጽ አልባ የሆኑ ትናንሽ አኩራች ስሮች፤  በአኩራች ስሮች ላይ ወይንጠጅ መልክ በግልጽ መታየት፤ የፎስፈረስ ዕጥረት ባለባቸውና እያረጁ ባሉ ቅጠሎች ላይ የሚታዩ ቀለሞች፤ አበቦቹ በዕድገት ወቅት የተከሰቱ ጫናዎች ውጤት ናቸው ጤናማ ተክል (ግራ) እና ፎስፈረስ ያጠረው በታዳጊ ቅጠሎች ላይ የወይንጠጅ መልክ በጣም በፎስፈረስ ዕጥረት የተጠቃ ተክል (ቀኝ) መታየት ቀጫጫ የስድስት ወር ተክል፣ ያረጁ ቅጠሎች ወይንጠጅ መልክ መያዝና ማርጀት እንዲሁም የለጋ ቅጠሎች ጥቁር አረንጓዴ መሆን ምንጭ: O’Sullivan et al., 1997 ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 15 ከንጥረ-ነገር ዕጥረት በተጨማሪ ስኳር ድንች የውሃ ዕጥረት፣ የንጥረ-ነገር መመረዝና የበሽታ ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡ የውሃ ዕጥረት፡ ስኳር ድንች ከሌሎች ሰብሎች ጋር ሲነጻጸር ድርቅን ይቋቋማል፡፡ ቢሆንም ረዘም ላለ ጊዜ በተለይም አኩራች ስሮች መፈጠር በሚጀምሩበት ወቅት የውሃ ዕጥረት ከገጠመው የአኩራች ስሮች ቁጥር ይቀንሳል፣ ስሮቹ አብዛኛውን ጊዜ ትናንሽ ይሆናሉ እንዲሁም ምርት የመስጠት አቅሙ ይቀንሳል ፡፡ ቀጥተኛ የሆነ የውሃ ዕጥረት ምልክቶች የቅጠሎች መጠውለግና የዕድገት መቀነስ ናቸው፡፡ የውሃ ዕጥረት የስኳር ድንች ተክሎችን ለቫይረስና ለተባይ ጥቃት እንዲጋለጡ ከማድረጉም ባሻገር አኩራች ስሮች እንዲሰነጣጠቁ ያደርጋል፡፡ የንጥረ-ነገር መርዛማነት: አብዛኛዎቹ ንጥረ-ነገሮች ከሚፈለገው በላይ ከተጨመሩ መርዛማ ይሆናሉ፡፡ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ናይትሮጂን ሁለቱ የታችኛዎቹ ተክሎች በቫይረስ የተጠቁ ናቸው ማዳበሪያ የስኳር ድንች ሀረግ ተቀማጥሎ እንዲያድግ ቢያደርግም የአኩራች ስር ጅማሬንም ይሁን ዕድገትን ያሰናክላል፡፡ ሁሉም ስኳር ድንች እንደማያብብ ቢታወቅም ከፍተኛ ናይትሮጂን ስኳር ድንች እንዳያብብ ያደርጋል፡፡ የፖታሲየም መመረዝ በስፋት አይታይም፡፡ ስኳር ድንች በጥሩ ሁኔታ የአፈር አሲዳማነትን ይቋቋማል፡፡ የቫይረስ ጥቃት ምልክቶች: ዕጽዋት የቀነጨረ ዕድገት፣ የቅጠሎች መሸብለል፣ እና/ወይም የቅጠሎች ወይም የቅጠል ደም ስሮች መልክ የመቀየር ምልክት የሚያሳዩ ከሆነ በቫይረስ በሽታ የተጠቁ መሆናቸውን መገመት ይቻላል፡፡ ቫይረሶች ሁሉጊዜ እንደ ክሽክሽና ነጫጭ ዝንቦች በመሳሰሉ መጣጭ ተባዮች ይተላለፋሉ (ለተሟላ ትንተና ርዕስ 7ን ይመልከቱ)፡፡ አንዳንድ ጊዜ የበሽታና የንጥረ-ነገር ዕጥረት ልዩነቶችን መለየት በጣም ያዳግታል፡፡ የቫይረስና የንጥረ ነገር-ዕጥረት መሰረታዊ ልዩነት ቢኖር የበሽታ ምልክት አልፎ አልፎ አንድ ወጥ ባልሆነ መልኩ የሚታይና የተወሰኑ ዝርያዎችን ብቻ የሚያጠቃ መሆኑ ነው፡፡ በአንድ ማሳ ውስጥ ተቀላቀለው ጤናማና በሽተኛ ሰብሎች ይገኛሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የበሽታ ምልክት በድንገት ይከሰታል፡፡ በተቃራኒው የንጥረ-ነገር ዕጥረት ከእድገቱ መጀመሪያ አንስቶ የማሳውን ግማሽ ወይም ሙሉ ያጠቃል፡፡ 6.8 በስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ የሥርዓተ-ጾታና ብዝሃነት ጉዳዮች በርዕስ 11 ላይ ስኳር ድንችን በተመለከተ የሥርዓተ-ጾታና ብዝሃነት ጉዳዮች ጠለቅ ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ ውስጥ ቁልፍ የሥርዓተ-ጾታና ብዝሃነት ጉዳዮች ከዚህ እንደሚከተለው ተገልጸዋል፡፡ የተለያዩ ሰዎች ስለስኳር ድንች አያያዝ የተለያዩ ግንዛቤዎች አሏቸው፡፡ ይህ ምናልባት ስኳር ድንች በማምረት ባካበቱት ልምድ፣ ስኳር ድንችን በማምረት ሂደት ባላቸው ሚና፣ ሊያገኙ በሚችሉት የሀብት መጠን፣ የመረጃ መረብንና ስልጠናን የማግኘት ዕድል እና ስኳር ድንች በህይወታቸው ውስጥ ባለው አስፈላጊነት የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ የልማት ሰራተኞች ማን የትኛውን የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ ተግባራትን እንደሚፈጽም፣ መቼ እነኝህ ተግባራት እንደሚከናወኑ፣ እንዴት እንደሚከናወኑ፣ እነኝህን ተግባራት የሚፈጽሙ ሰዎች ምን ዓይነት ችግር እንደሚገጥማቸው እና ሌሎች ምን ዓይነት ተግባራት ጉልበትና መሬት ከስኳር ድንች ጋር እንደሚሻሙ መረዳት ይገባቸዋል፡፡ ይህንን ግንዛቤ ለማጎልበት አባሪ 11ለ ጠቃሚ መሳሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማን ምን እንደሚያደርግ (ይህ እንደቤተሰቡ ሁኔታ ወይም ሰብሉ ለምን ጉዳይ እንደሚመረት (ለገበያ ወይም ለቤት ፍጆታ) ከግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት) ከመገንዘብ ባሻገር ስኳር ድንች ለማምረት የሚያስፈልገውን ሀብት ማን እንደሚቆጣጠር፣ ውሳኔ ማን እንደሚሰጥና የሚገኘውን ጥቅም ማን እንደሚገለገልበት መገንዘቡ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም የትኛው ቦታ ስኳር ድንች እንደሚመረት፣ የትኛው ሰብል ቅድሚያ እንዲሚመረትና እንክብካቤ እንደሚደረግለት፣ ስኳር ድንች በስብጥር መተከል እንዳለበትና እንደሌለበት፣ እንደ መሬት ዝግጅት፣ ቦይ ማውጣት፣ ጉብታ መስራት፣ተከላ፣ ምርት መሰብሰብ፣ ማጓጓዝና ማቀነባበር ለመሳሰሉ ተግባራት ጉልበት ስለማግኘት፣ የመስኖ ውኃ የተከላ ሃረጎችን ለማቆየት ማግኘት፣ ፍግና ማዳባሪያ ማግኘት እና ከስኳር ድንች ሽያጭ የተገኘው ገቢ ማን ጋ እንደሚቀመጥ ወይም ውሳኔ ማን እንደሚሰጥበት የመሳሰሉትን ማወቅን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 16 እነኝህ ምን ዓይነት መረጃ መለዋወጥ እንደሚገባን፣ ለማን ማካፈል እንዳለብን፣ ለየትኛዎቹ ሰዎች መቼ ትኩረት መስጠት እንደሚገባን እንድናውቅ የሚያስችሉ ጠቃሚ ነገሮች ናቸው፡፡ ከግንዛቤ ውስጥ የገባው የስኳር ድንች በአርሶ አደሮች ኑሮ ላይ የሚያመጣው ለውጥ (ይህ ምናልባት በቤተሰብ ሁኔታና ወንድ ወይም ሴት በመሆን ሊለያይ ይችላል) አርሶ አደሮቹ ስኳር ድንችን ለማምረት የሚያስፈልጋቸው ወጪ፣ ጊዜና ሀብት ደረጃ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል፡፡ በአብዛኛዎቹ ከሰሀራ በታች በሚገኙ አገሮች ሴቶች በስፋት ስኳር ድንች በሚያመርቱባቸውም ቦታዎችም ጭምር ወንዶች የመሬት ባለቤቶችና የትኛው ሰብል በየትኛው መሬት ላይ መተከል እንደሚገባው ውሳኔ ሰጭዎች እንደሆኑ ይወሰዳል፡፡ ስለዚህ የልማት ሠራተኞች ወንዶች የመሬቱ ባለቤት ባይሆኑም በፕሮጀክቱ ተግባራት ወቅት እንዲሳተፉ ማድረግ (ቀጥተኛ ተዋናይ ባይሆኑም) ወሳኝ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡ 6.9 ስለ ስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ በተግባር መማር እነኝህ በመስራት የመማር ተግባራት የተነደፉት በተግባር እያዩ የመማርን ዕድል ለመፍጠር ነው፡፡ ሙሉ የ10 ቀን የአሰልጣኞች ስልጠና ትምህርት መርሀ-ግብር በርዕስ 13 ላይ ተተንትኗል፡፡ የሚከተሉት ተግባራት በስልጠናው 6ኛ ቀን ላይ የሚከናወኑ ሲሆኑ ለግንዛቤ ያክል መርሃ ግብሩ በሚከተለው ሰንጠረዥ እንደተመለከተው ይሆናል፡፡ ቀን ርዕስ የሚጠበቅ የስልጠና ውጤት ተግባራት 6 የስኳር ድንች ተሳታፊዎች: - ተግባር 6.9.1: የስኳር ድንች ዝርያዎችንና አያያዝ አመራረትና ሰብል ተግባራትን ማነጻጸር፡ የስኳር ድንች መስክ ሙከራ አያያዝ - አርሶአደሮቹ የተለያዩ ዝርያዎችን ማቋቋም (ለዝርዝሩ 6.9.1ን ተመልከቱ) [3 ሠዓት] ለማነጻጸር እንዲችሉ ወይም የተለያዩ የሰብል አያያዝ - ተግባር 6.9.2: ቅድመ ዕቅድ፡ ዘዴዎችን የመስክ ሙከራ እንዲጀምሩ ሊረዱ ይችላሉ፤ - የስኳር ድንች የእርሻ ስራ ቀን መቁጠሪያ ማዘጋጀት፤ - የተለያዩ የስኳር ድንች የዕድገት - ተያያዥ የሆኑ የሰብል አያያዝ ተግባራትንና ቅድመ ደረጃዎችና ደረጃዎቹ በስብል ዕቅዶችን መለየት አያያዝ ላይ ያላቸውን እንድምታ - ከተግባራቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ የሥርዓተ-ጾታ ይረዳሉ፤ ሚናዎችንና ምን ለውጦች እየታዩ እንደሆነ መወያየት (6.9.2ን ይመልከቱ) [75 ደቂቃ]፤ - ገለጻ 6. የስኳር ድንች የዕድገት ደረጃዎችን ለመሸፈን (የድህረ-ምርት ደረጃዎችን ጨምሮ) ተሳታፊዎች በማስታዎሻ ደብተሮቻቸው ላይ ሙሉ የዕድገት ደረጃዎችን ይስላሉ፡፡ ከውይይቱ በኋላ ተሳታፊዎች በየዕድገት ደረጃው ለየትኛው ተግባር ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ በዝርዝር ያስቀምጣሉ [45 ደቂቃ]፤ 6.9.1 የስኳር ድንች ዝርያዎችንና የአያያዝ ተግባራትን ማነጻጸር ከስልጠናው የሚጠበቅ ውጤት: ተሳታፊዎች አርሶአደሮች የተለያዩ ዝርያዎችን ወይም የተለያዩ የሰብል አያያዝ ዘዴዎችን ለማነጻጸር የመስክ ሙከራ እንዲያከናውኑ ያግዛሉ፤ ጊዜ: 3 ሠዓት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች: ተገላላጭ ቻርት፣ እስክሪብቶዎች፣ ገመድ፣ ሜትር፣ አካፋ፣ መለያ፣ እንጨት፣ በቅርብ ቦታ የሚገኝ ሙከራው የሚመሰረትበት ማሳ፣ የዚህ መምሪያ ርዕስ 3፣ 6 እና 7፣ “ስኳር ድንቼን ምን እያጠፋብኝ ነው?” በሚለው መጽሃፍ ውስጥ ከገጽ 20 - 22 ላይ የተጠቀሰው፤ ቅድመ ዝግጅት፡ ተሳታፊዎች የሙከራውን ንድፍ የሚያስቀምጡበትንና ሙከራውን የሚያካሂዱበትን በአቅራቢያ የሚገኝ 30 በ 30 ሜትር የሆነ ባዶ ማሳ ማግኘት፤ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 17 የድርጊት ቅደም ተከተል: 1. ተሳታፊዎችን አምስት ሰዎች ባሉበት ቡድን እንዲከፋፈሉ መጠየቅ፡፡ አገልግሎት ለሚሰጧቸው አርሶ አደሮች ይጠቅማሉ የሚሏቸውን የሙከራ ዕቅዶችና ንድፎች እንደሚያወጡ ለተሳታፊዎቹ ማብራራት፡፡ ሙከራዎቹ እጅግ በጣም የተወሳሰቡ እንዳይሆኑና አንድ ሙከራ አንድን ርዕስ ብቻ የሚመለከት መሆን እንዳለበት፣ ነገር ግን ከዚያ ካለፈ ለመረዳት እጅግ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ተሳታፊዎችን ማስገንዘብ ያሰፈልጋል፤ 2. በሙከራው ዓላማና በሚወዳደሩ ነገሮች ላይ በደንብ መወያየትና ከስምምነት መድረስ እንዳለባቸው ማስገንዘብ (የምናወዳድራቸው ነገሮች በጣም ብዙ ወይም በጣም አነስተኛ ከሆኑ ጥሩ መረጃ ልናገኝባቸው አንችልም፣ በአንድ ሙከራ ከ3 - 5 ተወዳዳሪዎች ካሉ ጥሩ ነው)፣ የአርሶ አደሩ አያያዝ ወይም ቴክኖሎጂ ከአዳዲሶቹ ጋር ለማወዳደሪያነት እንደሚገቡ መርሳት እንደሌለባቸው ማስገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ቀጥሎም ስለሚከተሉት ነገሮች እንዲያስቡባቸው ማስታወስ:-  ምን ሊያገኙ ሙከራ እያደረጉ እንደሆነ፤  ምን ዓይነት ነገሮችን እንደሚያወዳድሩ፤  በሙከራው ዕቅድ፣ አያያዝና ግምገማ የትኞቹ አርሶ አደሮች መሳተፍ እንዳለባቸው እንዲለዩ (በዚህ ልምምድ ላይ አርሶ አደሮችን በገሃዳዊው ስራ ላይ በሚሳተፉበት መጠን እንደማያሳትፏቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል)፤  ምን ያህል ጊዜ ማሳቸውን እንደሚጎበኙና ሲጎበኙም ምን ምን ነገሮችን እንደሚመለከቱ ወይም እንደሚለኩ/እንደሚመዘግቡ፤  የሙከራቸው ውጤት ምን ያህል ተዓማኒነት እንዳለው እንዴት እርግጠኛ እንደሆኑ? (ለምሳሌ የድግግሞሽ ጽንሰ ሀሳብ አስፈላጊነትና በሙከራው የሚያዩትን ነገር ቢያንስ ሶስት ጊዜ መደጋገም በሙከራው የሚወዳድሩት ነገሮች ልዩነት በአፈሩ ልዩነት ሳይሆን ሙከራ በምናደርገው ነገር ልዩነት የመጣ እንደሆነ እንዲያውቁ ማድረግ በራስ መተማመናቸውን ያሳድግላቸዋል) [ማስታወሻ: በአርሶአደሮች ማሳ ላይ የሚወዳደሩ ነገሮችን የተለያዩ አርሶአደሮችን በመጠቀም መደጋገም ይቻላል፡፡ ይህ በአርሶ አደር ማሳ ላይ ዝርያዎችን የምንፈትሽበትን ሙከራ የምናስቀምጥበት መንገድ ነው፡፡]፤  ማሳቸው ምን ያህል ሰፊ እንደሆነ፤  እንዴት ያገኙትን ነገሮች ለስርጸት ሠራተኞችና ለሌሎች ለማካፈል መጋበዝ እንዳለባቸውና ግኝታቸውን ለጎብኝዎቻቸው እንዴት እንደሚያቀርቡ (ለምሳሌ አርሶ አደር ለአርሶ አደር ገለጻ፣ በግልጽ የሚታይ መለያ፣ ከጉብኝዎች ጋር በመሆን አሳታፊ ግምገማ?)፤ የሙከራቸውን ንድፍ አስቀምጠው ለተቀሩት ተሳታፊዎች እንዲያቀርቡ ለቡድኖቹ ባዶ የሚገላለጥ ቻርት መስጠት [45 ደቂቃ]፤ 3. እያንዳንዱ ቡድን የየራሱን ሙከራ ዓላማ፣ የሚወዳደሩ ነገሮችን እና የሙከራውን ንድፍ እንዲያቀርብ መጠየቅ፡፡ ከዚያም ጠቅላላው ቡድን ሙከራ ስለመስራት በ“ስኳር ድንቼን ምን እያጠፋብኝ ነው?” መጽሃፍ ከገጽ 20-22 ያለውን እንዲያነቡ መጠየቅ፣ ቡድኖቹ በሙከራ ንድፋቸው ላይ መቀየር የሚገባቸው ነገር መኖር ያለመኖሩን እንዲወያዩ መፍቀድ [30 ደቂቃ]፤ 4. በአቅራቢያ ወደሚገኘው ማሳ በመሄድ እያንዳንዱ ቡድን የየራሱን ሙከራ መለያውን ጨምሮ እንዲያስቀምጥ መጠየቅ፡፡ ማሳው አራት ማዕዘን ቅርጽ እንዲይዝ ዘጠና ዲግሪ እንዴት እንደሚሰራ ለተሳታፊዎች ማብራራት/ማሳየት፡፡ [ማስታወሻ፡ የተከላ ሃረግ በበቂ ሁኔታ እንደማይኖራቸው ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የተለያዩ ቁራጭ መሬቶችን ንድፍ ማውጣት፣ ስዕልን ጨምሮ በእያንዳንዱ ቁራጭ መሬት ላይ ምን እንዳለ ግልጽ መለያ ማድረግ ይችላሉ] ይህንን ለማድረግ አንድ ሰዓት እንዳላቸውና ሁሉም ቡድን ዞሮ የሙከራ መስኩን ማየት እንዳለበት ማብራራት፡፡ አመቻቹ ተሳታፊዎች ስለ ሙከራው ንድፍ በደንብ እንዳሰቡበት እየተዟዟረ ይመለከታል (ለምሳሌ የመሬት ተዳፋትነት መኖሩን፣ የመሬቶቹን መጠን፣ የሚወዳደሩ ነገሮች (ዝርያዎች) በዘፈቀደ ስለመቀመጣቸው እና ግልጽ መለያ መደረጉን)፡፡ አመቻቹ በመስክ የሚወዳደሩ ነገሮች እንዴት በዘፈቀደ እንደሚቀመጡ ቀለል ባለ ምሳሌ ሊያሳይ ይችላል [60 ደቂቃ]፤ 5. ከተከላ ከሶስት ወራት በኋላ እንደመጣ እንደ አንድ ጎብኚ እንግዳ በመሆን ጠቅላላውን ማሳ ዞሮ ማየት፡፡  ማንኛውንም ስለ ሙከራ ንድፉ የታዩ ግድፈቶችንና እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል? ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 18  መችና እንዴት ማሳዎችን ከአርሶ አደሩ ጋር በመሆን መገምገም እንዳለብን?  ለምን በተግባር ሙከራ አርሶ አደሮቹ ራሳቸው እየሰሩ ማየታቸው ስለሙከራው ውጤት ከመስማት ይልቅ እንደረዳቸው?  ለሚወዳደሩ ነገሮች ግልጽ መለያ ማድረግ ለምን እንዳስፈለገ?  ለምን ወንድና ሴት እንዲሁም የተለያየ የሀብት ደረጃ ያላቸውን አርሶ አደሮች ማሳተፍ ጠቃሚ እንደሆነ? [30 ደቂቃ] ውይይት ማድረግ፤ 6. ተሳታፊዎች የራሳቸውን ሙከራ ዓላማና የሙከራ ንድፍ እንዲሁም ይጠቅሙኛል የሚሏቸውን የሌሎች ቡድኖች ዓላማና የሙከራ ንድፍ በማስታወሻ ድብተራቸው እንዲገለብጡና ሙከራቸውን በሚያስቀምጡበት ወቅት እንዳይረሷቸው አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን ማቅለም እንዳለባቸው ማስታወስ [15 ደቂቃ]፤ 6.9.2 ቅድመ-ዕቅድ ከስልጠናው የሚጠበቅ ውጤት፡ ተሳታፊዎች የተለያዩ የስኳር ድንች የዕድገት ደረጃዎችንና ደረጃዎቹ በስብል አያያዝ ላይ ያላቸውን እንድምታ ይረዳሉ፤ ጊዜ: 75 ደቂቃ፤ የሚያስፈልጉ ነገሮች: ተገላላጭ ቻርት፣ ሉኮች፣ የማርከር እስክሪብቶ፣ እርሳሶች፣ ፕላስቲክ ማጣበቂያ፤ የድርጊት ቅደም ተከተል: 1. ተሳታፊዎች 10 ሰዎች ባሉባቸው ቡድኖች ራሳቸውን እንዲያካፍሉ መጠየቅ (በተቻለ መጠን ሁሉም የሚኖሩት/የሚሰሩት በተመሳሳይ ስነ-ምህዳር ውስጥ ቢሆን ይመረጣል፤ ምክንያቱም የዝናብ መምጫ ወቅት ተመሳሳይ ስለሚሆን) ፡፡ ከተሳታፊዎች ሁለቱ እንደአመቻች ራሳቸውን እንዲቆጥሩና በተቻለ መጠን የተሟላ የስኳር ድንች እርሻ ስራ ቀን መቁጠሪያ እንዲያዘጋጁ መጠየቅ፡፡ እነሱንም ስለሚከተሉት ጉዳዮች ማሳሰብ፡-  በመቁጠሪያው ላይ ዝናብ የሚዘንብባቸው ወቅቶችና ወራቶች ላይ ምልክት ማድረግ፤  ከስኳር ድንች አመራረትና ደህረ-ምርት አያያዝ ጋር ተያይዞ የሚተገብሯቸውን ስራዎች በጥንቃቄ በማሰብ እንዲጀምሩ፤  በቤተሰብ መሀል ማን በተለይ ስራውን እንደሚተገብር የሚያሳዩበትን ሂደት እንዲያካትቱ፤ ምናልባት ሚስትና ባል በቅንጅት የሚሰሩ ከሆነ በእያንዳንዳቸው ምን ያህል እንደሚተገበር በመቶኛ እንዲያስቀምጡ (በአባሪ 11ለ ያለው የስኳር ድንች ሰብል እርሻ ተግባር ቀን መቁጠሪያ የበለጠ ሊረዳ ይችላል)፤  በመቁጠሪያቸው ውስጥ ቃላትን፣ ስዕሎችንና ምልክቶችን መጠቀም አንደሚችሉ፤  ለተቀሩት ተሳታፊዎች መቁጠሪያቸውን ማቅረብ እንደሚገባቸው እና  በመቁጠሪያቸው ስር አምስት የሚጠጉ ባዶ መስመሮችን መተው እንዳለባቸው [30 ደቂቃ]፤ 2. አሁን ተሳታፊዎቹ የተከላ ሃረጎቻቸውን በደረቅ ወቅት በጥንቃቄ የሚጠብቁ ከሆነ መቼ የተከላ ሃረጋቸውን መምረጥ እንዳለባቸውና እንዴት በደረቅ ወቅት ጠብቀው እንደሚያቆዩ መጠየቅ፡፡ ዝናቡ ከመጀመሩ በፊት ልክ ዝናቡ እንደዘነበ ለመትከል እንዲያስችላቸው አስቀድመው በቂ የተከላ ሃረጎቻቸውን ስለሚያመርቱበት ሂደት ተሳታፊዎችን መጠየቅ (ያላቸውን የመሬት መጠን በትክክል መግለጽ አለባቸው) ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ መወያየትና በመቁጠሪያቸው ውስጥ ማካተት አለባቸው (በመቁጠሪያው ስር ባሉ ባዶ መስመሮች):  ከባለፈው የሰብል ወቅት መቼ ንጹህ የተከላ ሃረጎችን እንሚመርጡ፤  እነኛን የተከላ ሃረጎች በደረቅ ወቅት ውሃ ማጠጣትን ጨምሮ እንዴት ጠብቀው እንደሚያቆዩ፤  የችግኝ ማባዣ መደብ አዘገጃጀት፣  ጠብቀው ካቆዩዋቸው የተከላ ሃረጎች ውስጥ ንጹህ የተከላ ቁርጥራጮችን እንዴት እንደሚወስዱና እንደሚተክሉ፤  የማባዣ ቦታቸውን እንዴት ጠብቀው እንደሚያቆዩ፣  ቁርጥራጮችን እንዴት እንደሚሰብስቡ (ማስታወሻ፡ ይህ ዳግም ያቆጠቁትን መሰብሰብን ያጠቃልላል (ተከታታይ ለብዙ ጊዜ ቁርጥራጮችን መውሰድን)) [20 ደቂቃ]፤ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 19 3. ሁሉም ቡድኖች እያንዳንዱ ቡድን ጋር በመሄድ ስላዘጋጀው የእርሻ ተግባር ቀን መቁጠሪያ አጠር ያለ መግለጫ እንዲሰጣቸው መጠየቅ፤ ስለሚከተሉት ጉዳዮች ጥያቄዎችና የውይይት ሀሳቦች እንዲነሱ ማበረታታት፡-  ስለ ቅድመ ዕቅድና የተከላ ሃረጎችን ስለመጠበቅ ጠቀሜታና ተሳታፊዎች ስለሚታያቸው ተግዳሮቶች፤  የስኳር ድንች ምርት የጉልበትና የገቢ የሥርዓተ-ጾታ ጉዳዮች፤ ማንን በስኳር ድንች አመራረት ማሰልጠን እንዳለባቸው በተመለከተ የሥርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ሚና፤  ሌሎች አንገብጋቢ አስቀድመው መታቀድ ስለሚገባቸው ጉዳዮች፤  እንደ ነባራዊ ዕውነታ ማመሳከሪያ የእርሻና የቤተሰብ እንቅስቃሴዎች ሌሎች ገጽታዎችና የጉልበት በበቂ መልኩ የመገኘት ጉዳዮች [25 ደቂቃ]፤ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 20 6.10 ዋቢ ጹሑፎች Abidin, P.E., Chipungu, F.C., Kazembe, J., (2011). Initial observation: Intercropping maize and sweetpotato at Bvumbe Research Station in the 2010/2011 rainy season. 7pp. Allemann, J., (2004). Chapter 4: Fertilisation, irrigation and weed control. In: Guide to Sweet Potato production in South Africa. Niederswieser, J.G. (Ed.). pp 27-38. ARC, Pretoria, Republic of South Africa. ISBN 86849-292-3. Anikwe, M.A.N., Ubochi, J.N., (2007). Short term changes in soil physical properties under tillage systems and their effect on sweetpotato (Ipomoea batatas L.) growth and yield in tropical ultisol in Southeast Nigeria. Australian Journal of Soil Research, 45(5): 351-358. Ennin, S.A., Dapaah H.K., Asafu- Agyei, J.N., (2007). Land preparation for increased sweetpotato production in Ghana. Proceedings of the 13th ISTRC symposium, 227-232. Faber, M., Laurie, S., Ball, A., Andrade, M., (2010). A crop-based approach to address vitamin A deficiency in southern Africa: a regional manual for SADC. ARC, Pretoria, South Africa. 109pp. Fuentes, S., Chujoy, E., (2009). Chapter 18: Sweetpotato in South America. In: The Sweetpotato. G. Loebenstein, G. Thottappily, (Eds.) Springer. p429. Huaman, Z., (1992). Systematic Botany and Morphology of the Sweetpotato Plant. CIP Technical Information Bullet 25, 22pp. Leventis Foundation and Pro – Natura International, (2005). Agroforestry Guide Series No. 1: An Introductory Field Manual on Agroforestry Practices in Nigeria and Ghana. Moreno, R.A., (1982). Intercropping with sweetpotato (Ipomoea batatas) in Central America. In: Sweet Potato: Proceedings of the First International Symposium,(AVRDC Publication No. 82-172) R.L. Villarreal and T.D. Griggs, (Eds.) Tainan, Taiwan: Asian Vegetable Research and Development Centre (AVRDC). pp 243-254. Nelson, S.C., Elevitch, C.R., (2011). Farm and forestry production and marketing profile for sweetpotato (Ipomoea batatas). In: Elevitch, C.R., (Ed.) Specialty Crops for Pacific Island Agroforestry. Permananent Agriculture Resources (PAR), Holualoa, Hawaii http://agroforestry.net/scps 20pp. Njoku, J.C., Okpara, D.A., Ikeorgu, J.E.G. (2003). Responses of sweetpotato to duration of mucuna fallow. Tropical Science, 42: 44-47. Onwueme, I.C. (1978). The tropical tuber crops, yams, cassava, sweet potato, cocoyams. John Wiley and Sons Ltd. 234 pp. O’Sullivan, J.N., Asher, C.J., Blamey, B.C., (1997). Nutrient disorders of sweetpotato. 25pp. ACIAR, Australia. Smith, T.P., Stoddard, S., Shankle, M., Schultheis, J., (2009). Chapter 14: Sweetpotato production in the United States. In: The Sweetpotato. G. Loebenstein, G. Thottappily, (Eds.) Springer. pp287-323. Stathers, T., Namanda, S., Mwanga, R.O.M., Khisa, G., Kapinga, R., (2005). Manual for sweetpotato integrated production and pest management farmer field school in sub-Saharan Africa. CIP, Uganda. pp168+xxxi ISBN 9970-895-01-X Susan-John, K., Suja, G., Edison, S., Ravindran, C.S., (2006). Nutritional disorders in tropical tuber crops. Central Tuber Crops Research Institute, India. pp74. van de Fliert, E., Braun, A.R., (1999). Farmer Field School for Integrated Crop Management of Sweetpotato: Field Guides and Technical Manual. CIP. 265pp. van den Berg, A.A., Laurie, S.M., (2004). Chapter 3 Cultivation. In: Guide to Sweet Potato production in South Africa. Niederwieser, J.G. (Ed.). pp 15-26. ARC, Pretoria, Republic of South Africa. ISBN 86849-292-3. Villordon, A., Labonte, D., Firon, N. (2009). Development of a simple thermal time method for describing the onset of morpho-anatomical features related to sweetpotato storage root formation. Scientia Horticulturae, 121: 374-277. ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 21 ማስታወሻ የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ ርዕስ 6 - የስኳር ድንች አመራረትና አያያዝ - 22 ርዕስ 7: የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር 7.1 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ እንዴት ይከሰታሉ? እንዴትስ ይሰራጫሉ? የስኳር ድንችን ነፍሳት ተባይና በሽታ ለመከላከልም ሆነ ለመቆጣጠር ከየት እንደ መጡ፣ እንዴት እንደሚሰራጩ፣ መቼ እንደሚከሰቱ፣ በእርግጥም እንዴት እነሱን መረዳትና መከላከል እንደሚቻል ማወቁ ጠቃሚ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የህይወት ዑደታቸውንና የመሰራጫ መንገዳቸውን ለማቋረጥ፣ የህይወት ዑደታቸውን በተለያየ ደረጃ ለማወቅ፣ ቁጥራቸውን እንዴት እንደሚገነቡና አደገኛ ደረጃ ላይ እንደሚደርሱ ለመረዳት የህይወት ዑደታቸውን፣ ባህሪያቸውንና ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱባቸውን መንገዶች ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ 7.1.1 የነፍሳት ተባይ የህይወት ዑደት በህይወት ዑደት ጊዜ ነፍሳት ተባዮች የተለያዩ የዕድገት ደረጃዎችን ያልፋሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እኛ የምንረዳው ካሉት የዕድገት ደረጃዎች ውስጥ አንዱን ማለትም የጉልምስ ዕድገት ደረጃን ብቻ ነው፡፡ የጉልምስ ዕድገት ደረጃ የሚጫወተው ሚና ቢኖር ዘር ለመቀጠል ወይም ለመራባት ሲሆን ሰብሉን ግን ሊመገብ ወይም ላይመገብ ይችላል፡፡ ከግንኙነት በኋላ ሴቷ ነፍሳት ተባይ እንቁላሎቿን በተመረጡ ቦታዎች ላይ ትጥላለች (ለምሳሌ ከቅጠል ስር፣ በአፈር ላይ ወዘተ)፡፡ እንቁላሎቹ ይፈለፈሉና ጨቅላዎቹ ነፍሳት ተክሉን እየተመገቡ አድገው በመጨረሻም ጉልምስ ይሆናሉ፡፡ ቢሆንም በብዙዎቹ ነፍሳት ተባዮች የእድገት ደረጃ ውስጥ ጨቅላዎቹ ከጉልምሶቹ በጣም የተለዩ ሲሆን አንድ ናቸው ብሎ ለማሰብም ራሱ አዳጋች ነው፡፡ ከአንድ የዕድገት ደረጃ ወደ ሌላው ደረጃ የሚቀየሩበት ሂደት ልውጠተ-ቅርጽ/ሜታሞርፎሲስ/ ይባላል፡፡ የአንዳንድ ነፍሳት ልውጠተ-ቅርጽ ሂደት የተሟላ ሲሆን በዚህን ጊዜ የትልና ድህረ-ትል/ዕጭ የእድገት ደረጃዎች ከጉልምስ ጋር በፍጹም አይመሳሰሉም፡፡ አንዳንድ የተባይ ዝርያዎች ደግሞ ከፊል (ያልተሟላ) ልውጠተ-ቅርጽ ሂደት አላቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ከእንቁላል የሚፈለፈለው ኩብኩባ ሲባል ቀስ በቀስ እያደገ ጉልምስ ይሆናል፡፡ ሁለቱም ሂደቶች ከዚህ በታች ተገልጸዋል፡፡ የተሟላ ልውጠተ-ቅርጽ (ጉልምስ እንቁላልትል ዕጭ ጉልምስ): በዚህ ልውጠተ- ጉልምስ እንቁላል ቅርጽ ሂደት የሚያልፉ ተባዮች የትል ደረጃቸው (ለምሳሌ አባጨጓሬ) ከእንቁላል ይፈለፈልና በአካባቢው የሚገኘውን ተክል አካል ክፍል እየተመገበ አድጎና ቆዳውን ገፎ እንቅስቃሴ በማቆም ወደ ዕጭ/ፑፓ ደረጃ ይሸጋገራል፡፡ ምንም እንኳን ዕጭ/ፑፓ ባይንቀሳቀስም በውስጡ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ በማድረግ በፍጹም ልዩ ወደ ሆነው ጉልምስ ደረጃ ይቀየራል፡፡ ለምሳሌ እጭ ትል ጥንዚዛ፣ የእሳት ራት ወይም ቢራቢሮ ፍጹም የተለየ ባህሪ ያሳያሉ፡፡ ይህ ፍጹም የሆነ የቅርጽና ባህሪይ ለውጥ አርሶ አደሩ ለምሳሌ በስኳር ድንች ስብል ላይ ሲንቀሳቀስ ያየውን ጥቁር ትንሽ ነቀዝ ከሳምንታት በኋላ ደግሞ ከስኳር ድንች ስር ላይ ከሚታየው ቀዳዳና የስኳር ድንች ስር ውስጥ የሚርመሰመሱ ነጫጭ ትሎች ጋር ለማገናኘት በጣም አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥርበታል፡፡ ስዕል 7.1 የስኳር ድንች ነቀዝና ቢራቢሮ የህይወት ዑደት የተሟላ ልውጠተ-ቅርጽ ሂደት (ከዕንቁላል ወደ ትል ወደ ዕጭ/ፑፓ ወደ ጉልምስ) ጉልምስ ጉልምስ የስኳር ድንች የስኳር ድንች ነቀዝ እንቁላል ቢራቢሮ እንቁላል ዕጭ ዕጭ ትል ትል ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 23 የነፍሳት ተባዮችን የተለያዩ የዕድገት ደረጃዎችና በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ለአርሶአደሩ ማሳወቅ ተባይ መኖሩን እንዲለይና አደገኛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ነው፡፡ የስኳር ድንች ተባዮች ከፍተኛ ጉዳት ካደረሱ በኋላ ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ ጉልምስ/ እናት ነፍሳቶች በማሳው እንዳያርፉ ወይም እንቁላላቸውን እንዳይጥሉ ማድረግ እጅግ በጣም የተሻለ ነው፡፡ የስኳር ድንች ነቀዝ በሳይንሳዊ ስሙ ካይላስ (Cylas spp) ተብሎ የሚጠራው፤ እንዲሁም ሸካራ ቆዳ ያላቸው ብሎሳይረስ (Blosyrus sp.) ዝርያዎች፣ የጠራ ክንፍ ያላቸው የእሳት እራት፣ የስኳር ድንች ቢራቢሮ፣ ተምች እንደ ምሳሌ የቀረቡ ጉልምሱ ከትሉና ከዕጩ/ፑፓው ጋር በፍጹም የማይመሳሰልባቸውና የተሟላ ልውጠተ-ቅርጽ ሂደት የሚያካሂዱ ተባዮች ናቸው፡፡ ያልተሟላ ልውጠተ-ቅርጽ ሂደት (ጉልምስ  እንቁላል  ኩብኩባ  ጉልምስ): አንዳንድ ጉልምስ አንቁላል ተባዮች ያልተሟላ ልውጠተ-ቅርጽ ሂደት ሲያካሂዱ ኩብኩባው (ከትል በተቃራኒ) በቀጥታ ከእንቁላል ይፈለፈላል፡፡ ኩብኩባው ክንፍና የመራቢያ አካል ከማጣቱና በመጠን ከማነሱ በስተቀር ከጉልምስ ተባይ ጋር አንድ ዓይነት ነው፤ በተመሳሳይ አኳኋንም ይመገባሉ፡፡ ኩብኩባ ኩብኩባዎች በተደጋጋሚ ቆዳ በመግፈፍ ያድጉና በመጨረሻም ጉልምስ ይሆናሉ፡፡ ክሽክሽ፣ ነጫጭ ዝንቦች፣ አንበጣ፣ እና መጣጭ የትኋን ዝርያዎች ያልተሟላ ልውጠተ-ቅርጽ ሂደት ከሚያካሂዱ ተባዮች ውስጥ እንደምሳሌ ልንወስዳቸው እንችላለን፡፡ ክሽክሽና ነጫጭ ዝንቦች የስኳር ድንች ቫይረስ በሽታን ያሰራጫሉ፡፡ አንበጣ የስኳር ድንችን ቅጠል ቢመገብም እንደ አናሳ ተባይ ይታያል፡፡ መጣጭ ትኋኖች እንቡጦችንና ቅጠሎችን ሲመገቡ በቅጠል ላይ ጥቁር ጠባሳ እንዲኖርና እንዲጨማደድ ያደርጋሉ፤ ይህም ከፍተኛ ጉዳት ደረጃ ደርሶ የተክሉ እድገት እንዲቀጭጭ ያደርጋል፡፡ ስዕል 7.2 ያልተሟላ ልውጠተ-ቅርጽ ሂደት የሚያሳይ የክሽክሽ፣ አንበጣና መጣጭ ትኋን የህይወት ዑደት (ከእንቁላል ወደ ኩብኩባ ወደ ጉልምስ) ኩብኩባ የጉልምስ ህይወት ከ2-3 ሳምንት ዕንቁላል ከ6-9 ቀናት ይፈለፈላል ጉልምስ ዕንቁላል 5 ዕንቁላሎች ኛ ጉልምስ 1ኛ የአንበጣ ህይወት ዑደት 5 የኩብኩባ ዕድገት ደረጃዎች ከ16-18 4ኛ ቀናት 2ኛ የክሽክሽ ህይወት ጉልምስ ኩብኩባ ዕንቁላል ዑደት የመጣጭ ትኋን 3 ህይወት ዑደት ኛ የነፍሳት ተባዮች ዕድገት ጊዜያትና መራቢያ ወቅቶች፡ አንድ ተባይ ከእንቁላል አንስቶ እስከ ጉልምስ የሚደርስበት የዕድገት ደረጃ በአካባቢ ሁኔታ ይወሰናል፡፡ የአካባቢ ሙቀት ከፍ ያለ ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ የተባዮች ዕድገት ይፋጠናል፤ ይሁን እንጂ የሙቀት መጠኑ እየጨመረ ሄዶ ከፍተኛ ደረጃ ሲደርስ የተባዮችን ዕድገት ከመግታቱም ባሻገር እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡ ጨቅላ ተባዮች የሚመገቡት የምግብ ዓይነትም የእድገት መጠናቸውን ይወስናል፡፡ አንዳንድ ተባዮች የተለያዩ የዕፅዋት ዝርያዎችንና የዕፅዋት አካል ክፍሎችን ይመገባሉ፡፡ እነኝህም ዕጽዋት አማራጭ-አስጠጊ ዕፅዋት ይባላሉ፡፡ ለምሳሌ የስኳር ድንች ነቀዝ የውሃ ጎመን/ስፒናች በሳይንሳዊ አጠራሩ አይፖሚያ አኩቲክ (Ipomoea aquatic) ይመገባል፤ ስኳር ድንች የሚተከልበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስም ይጠለልና አዲስ ስኳር ድንች ሲተከል መልሶ ያጠቃል፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 24 ፈጣን የተባዮች ቁጥር መጨመር: ነፍሳት በጣም ስዕል 7.3 ፈጣን የስኳር ድንች ነቀዝ ቁጥር መጨመር አጭር የሆነ ዕድሜ ስላላቸው ብዙ እንቁላሎችን በአንድ ጊዜ በመጣል ቁጥራቸው በፍጥነት እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ አንድ የስኳር ድንች ነቀዝ የወንድ ነቀዞች 100 እንቁላሎችን ብትጥልና ሁሉም ወደ ጉልምስ ቁጥር አድገው 50ዎቹ ሴቶች ቢሆኑ በሚቀጥለው ጊዜ እያንዳንዳቸው 100 እንቁላል ቢጥሉና ሁሉም አድገው የሴት ነቀዞች ቁጥር ግማሾቹ ሴት ቢሆኑ ከሁለት ወር በኋላ 2500 እናቶች ይኖራሉ፡፡ እነኝህ በተራቸው 100 እንቁላል ቢጥሉ ከሶስት ወር በኋላ የስኳር ድንች ተክል የሚመገቡና መነሻ ላይ ከ1 ወር ከ2 ወር በኋለ ከ3 ወር በኋለ (1ሴ +1ወ) በኋለ 50ሴ 25001ሴ (12 5000ሴ ለእርባታ ዝግጁ የሆኑ 125000 ወንድና 125000 ሴት (ሴ 100 +50ወ) +2500ወ) +125000ወ) ነቀዞችን እናገኛለን፡፡ እንቁላሎችን ትጥላለች እንደዚህ ዓይነት አስገራሚ የሆነ የተባይ ወረርሽኝ ቢከሰትም አብዛኛዎቹ ተባዮችን በሚያጠቁ በሽታ አምጭ ተህዋሲያን/አቸንፍር ተጠቅተው ይወገዳሉ፣ ከፊሎቹ በአዳኞች ወይም በጥገኞች ይገደላሉ ወይም በቀላሉ በምግብ ዕጥረት ይሞታሉ፡፡ በሽታ አምጭ ተህዋሲያን/አቸንፍር፡ በአይን የማይታዩ ረቂቃን ተህዋሲያን እንደ ባክቴሪያ፣ ሻጋታና ቫይረስ የመሳሰሉ በነፍሳት ተባዮች ላይ በሽታ የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ ወደ ተባይ አካል ውስጥ በመግባት፣ በመኖርና በመባዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባዩን በማዳከም እንዲሞት ያደርጋሉ፡፡ በበሽታ የተጠቁ ነፍሳት ተባዮች ያብጣሉ፣ ልዩ መልክ ያሳያሉ፣ ከተለመደው በጣም ዝቅተኛ እንቅስቃሴ ያሳያሉ እና መብላት ያቆማሉ፡፡ በስነ-ህይዎታዊ መንገድ ተባዮችን ለመቆጣጠር አንዳንድ ጊዜ እነኝህ ተህዋሲያን ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ለምሳሌ በሳይንሳዊ ስያሜው ባሲለስ ቱሪንጄንሲስ (ቢቲ) በመባል የሚታወቀው ባክቴሪያ የስነ-ህይዎታዊ ጸረ-ተባይ ምሳሌ ነው፡፡ ገዳይ አዳኞች: እነዚህ ሌሎች ፍጥረታትን የሚያድኑ፣ የሚገሉና የሚመገቡ እንስሳት ወይም ሌሎች ነፍሳት ናቸው፡፡ ሸረሪቶች፣ ጉንዳኖች፣ በመሬት ውስጥ ያሉ ጥንዚዛዎች፣ ፌንጣ ወዘተ ሁል ጊዜ በስኳር ድንች ማሳ የሚገኙና የሰብሉን ተባዮች በመብላት ለአርሶ አደሩ እገዛ የሚያደርጉ ነፍሳት ናቸው፡፡ ስለዚህ በጸረ-ነፍሳት መድኃኒቶች መገደል የለባቸውም፡፡ ተህዋሲያን: በተጠቂያቸው አካል ውስጥ በመግባት አስጠጊያቸውን ከመሞቱ በፊት የሚመገቡ ህይወት ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡ እነኝህ አብዛኛውን ጊዜ የተርብ ወይም የዝንብ ዝርያዎች ናቸው፡፡ እንቁላላቸውን በተጠቂያቸው አካል ላይ ይጥሉና እንቁላሉ ተፈልፍሎ የተጠቂውን አካል ሰርስሮ በመግባት ይመገበዋል፡፡ የተባዮች ስርጭት: ሁላችንም ነፍሳት ተባዮች ሲሳቡና ሲበሩ አይተን እናውቃለን፡፡ የተባይ ጥቃት ችግር ተከሰተ የሚባለው ተባዮች በመራመድ ወይም በመብረር በአዲስ ዕጽዋት ላይ ሲያርፉ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ ተባዮች በጣም ረዥም ርቀት በንፋስ፣ በአፈር፣ በዘር/ቁርጥራጭ (የሰውን ምግብ ጨምሮ)፣ በእርሻ ቁሳቁሶች፣ በእግር/ጫማ፣ በእንስሳትና በተሽከርካሪዎች እንደሚጓዙ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ ነው፡፡ ለዚህም ነው የእጽዋት ጥበቃ ባለሙያዎች ተባዮች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ አዲስ ቦታ በሀገር ውስጥም ይሁን ከአንድ አገር ወደ ሌላው አገር እንዳይሰራጩ የዕጽዋትን አካል ክፍሎች/ዘር/ቁርጥራጭ ናሙና ወስደው የሚመረምሩት፡፡ 7.1.2 የዕጽዋት በሽታዎች የህይወት ዑደት የዕጽዋት በሽታዎች የተለየና ውስብስብ የህይወት ዑደት አላቸው፡፡ ነፍሳት ተባዮች ህይወታቸውን የሚጀምሩትና የሚባዙት ከጉልምስ እንደሆነ ሁሉ በሽታዎችም የህይወት ዑደት የሚጀምሩት ቀድሞ ከነበረው ጥቃት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ በበሽታ የተጠቃን ዘር አለመጠቀም ወይም ከቦታ ቦታ አለማንቀሳቀስ ጠቃሚ ነው፡፡ የሻጋታና የባክቴሪያ በሽታዎች የተለየ የማንቀላፊያ የዕድገት ደረጃ አላቸው፡፡ በዚህም የእነዚህ በሽታ አምጭ ዘአካላት ለብዙ ጊዜ በሞተ ቅጠል ላይ ይቆዩና በንፋስ ከዚህ በፊት ወዳልተጠቃ አዲስ ሰብል ይሄዳሉ፡፡ ይህ የማረፊያ/የእንቅልፍ የዕድገት ደረጃ አዲስ አስጠጊ ላይ ሲያርፍ ስር ይሰዳል፡፡ ሻጋታን በተመለከተ የማረፊያ አካላቶቻቸው/ስፖሮች/ በተጠቃው ቅጠል ላይ ተገማምደው በሚታዩ ቀጫጭን ጸጉሮች ላይ እንደ ጥቁር ነጥብ ይታያሉ፡፡ አልፎ አልፎ በአረማሞ ላይ እንደሚታየው ይህ አካል ብዙ ይሆንና ስፖሮቹ (የሻጋታው ዘሮች) በጣም በግልጽ ይበናሉ፡፡ ዕጽዋት በሻጋታ ወይም በባክቴሪያ የሚጠቁበት የተለመዱ መንገዶች ስፖሮች (የሻጋታ ዘሮች) በንፋስ አማካይነት ከአሮጌ/ከበፊት ማሳ ሲበኑ፣ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 25 ስፖሮች (የሻጋታ ዘሮች) ከወዳደቁ ቅጠሎች ላይ በዝናብ አማካይነት ሲረጩና በተበከሉ ቁርጥራጮች፣ በተለይም ስብሉ እንደ ስኳር ድንች ተቆርጦ በመትክል ዘዴ የሚባዛ ከሆነ ናቸው፡፡ ቫይረሶች የተጠቂያቸው አካል ውስጥ በራሳቸው ጊዜ ሰርስረው በመግባት በሽታ የሚያስከትሉበት ሂደት የተለመደ አይደለም፡፡ በዚህ ፋንታ በሌሎች ፍጥረታት፣ አብዛኛውን ጊዜ ሰብል መጣጭ በሆኑ እንደ ነጭ ዝንብ፣ ክሽክሽ፣ ወይም አንበጣ ላይ ጥገኛ ይሆናሉ፡፡ እንዲህ አይነቶቹን በሽታዎች ከአንድ ሰብል ወደ ሌላው የሚያስተላልፉትን ህይወት ያላቸው ፍጥረታትን ተሸካሚዎች/አስተላላፊዎች/ቬክተር እንላቸዋለን፡፡ የወባ ትንኝ ከበሽተኛው ሰው ደም መጥጣ ወባን ወደ ጤነኛው እንደምታስተላልፍ ሁሉ ክሽክሽ ወይም ነጫጭ ዝንቦችም ከበሽተኛው ተክል ወደ ጤነኛው ቫይረስን ያስተላልፋሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ እነዚህ ተባዮች ወባን ወደ ሰው ከሚያስተላልፉት ትንኞች ጋር ተመሳሳይ የሆነ ድርጊት ይፈጽማሉ፡፡ ስለዚህ ነፍሳቱን ከአሮጌው ማሳ ወደ አዲሱ ማሳ እንዳይሄዱ ከገታን በሽታው ወደ አዲሱ ማሳ እንዳይገባ ተከላከልን ማለት ነው፡፡ ሴቷ ትንኝ ወባን እንደምታስተላልፈው ሁሉ አንድን ቫይረስ አንድ ተባይ ብቻ ያስተላልፋል፡፡ እናም ነጫጭ ዝንቦች የካሳቫ አወያቢ ቫይረስ በሽታን ወይም የስኳር ድንች ቅጠል አግርጥ/አቀጭጭ ቫይረስን፤ ክሽክሽ ደግሞ የስኳር ድንች ቅጠል አዥጎርጉር ቫይረስን ያስተላልፋሉ፡፡ አንዴ ዕጽዋቱ በቫይረሱ ከተጠቁ ቫይረሱ ተባዝቶ በሁሉም የሰውነት ክፍል ውስጥ ስለሚሰራጭ ሁሉም የተክሉ ክፍሎች ይበከላሉ (ቫይረሶች ከኤልክትሮኒክ ማይክሮስኮፕ በስተቀር በአይን ሊታዩ አይችሉም)፡፡ በመሆኑም ክሽክሽና ነጫጭ ዝንቦች ከየትኛውም የተክሉ አካል ክፍል ቫይረሱን ሊያገኙና ሊያሰራጩ ይችላሉ፣ ከየትኛውም አካል ክፍል የሚወሰደው የተከላ ቁርጥራጭ የተበከለ ይሆናል እንዲሁም ጤናማ መስለው ከሚታዩ ተክሎች ጭምር የሚወሰዱ የተክሉ ክፍሎች የተበከሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስዕል 7.4 የቫይረስ የህይወት ዑደት ነጫጭ ዝንቦችና ክሽክሾች ነጫጭ ዝንቦችና ክሽክሾች ከተበከለው ከበሽተኛው ወደ ጤናማው ሰብል ቅጠል ያስተላልፋሉ ሲመገቡ ቫይረሱን ይወስዳሉ የቫይረስ የህይወት ዑደት በቫይረስ የተጠቃ ሰብል ጤናማ ሰብል ቫይረሱ በተክሉ ውስጥ ተባዝቶና ተሰራጭቶ የበሽታ ምልክት ማሳየት ይጀምራል፡፡ 7.1.3 የተቀናጀ የተባይና በሽታ ቁጥጥር ይህ የአካባቢ ጥበቃን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ተባዮችን/በሽታን የማስወገድ፣ የመቀነስ ወይም የመከላከል ስርዓት ወይም ውጥን ነው፡፡ ይህ ዘዴ ክትትልን፣ ሰብል ፈረቃን፣ ማሳ ጽዳትን፣ የተሻሻሉ የሰብል አያያዝ ተግባራትን፣ አካላዊ/መሳሪያን እና ስነ-ህይወታዊ መንገዶችን አቀናጅቶ በመጠቀም ተባዮች/በሽታዎች አደጋ ከሚያስከትሉበት ብዛት እንዲቀንሱና የኬሚካል መቆጣጠሪያ መንገዶችን መጠቀም እንዲቀንስ በማድረግ በሰው ልጅ ጤንነትና በአካባቢ ደህንነት ላይ ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ የሚያደርግ የተባይና በሽታ መቆጣጠሪያ ዘዴ ነው፡፡ የተቀናጀ የተባይና በሽታ መቆጣጠሪያ ዘዴ ትኩረት የሚያደርገው አደገኛ ተባዮችንና በሽታዎችን በመቆጣጠር ጤናማ ሰብል እንዲኖርና በአካባቢ ላይ ሊከሰት የሚችለውን ብክለት በመቀነስ በተፈጥሮ ያሉትን ስነ-ህይወታዊ የመቆጣጠሪያ መንገዶችን በማበረታታት ላይ ነው፡፡ በሰብሉ ዓይነት፣ በአካባቢ ሁኔታ፣ በአፈርና በመሬት አቀማመጥ ወዘተ የተቀናጀ ተባይና በሽታ መቆጣጠሪያ ዘዴ ከአርሶ አደር ወደ አርሶ አደር የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ በአጠቃላይ ይህ ዘዴ ብዝሃ-ሕይወት እንዲሻሻል በማድረግ (በጊዜና በቦታ የተለያዩ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 26 የዕጽዋት አይነቶችንና ጠቃሚ ዘአካላት ቁጥር ይጨምራል) የተባይና በሽታ ወረርሽኝ አናሳ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ የተለያዩ የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችን በአንድ ላይ አጣምሮ መጠቀም የሚቻል ሲሆን በዚህን ጊዜ ኬሚካል መጠቀም ግድ ከሆነ ኬሚካሉን መጠቀም ያለብን፡-  ተባዩና በሽታው ከተወሰነው መጠን አልፎ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ከሆነ፣  ኬሚካሉ ለሰውም ሆነ ለእንስሳት አደጋ የማያስከትል ከሆነ፣  ኬሚካሉን በሚረጨው ሰው ላይ ጉዳት የማያስከትል ከሆነ፣  በአካባቢ፣ በሌሎች እንስሳት እና ጠቃሚ ዘአካላት ላይ ጉዳት የማያደርስ ሆኖ ሲገኝና  ከርሰ ምድር ውኃ የማይበክል መሆኑ ሲረጋገጥ መሆን አለበት፡፡ ክትትል ማካሄድ የስኳር ድንች ተባይ ወይም በሽታ ጥቃት ምልክቶችን በመደበኛነት ማየትን፣ የታዩትን ምልክቶችም ተባዮቹና በሽታዎቹ በተለያዩ የአየር ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት እንደሚያድጉና ባህሪያቸውን እንደሚቀያይሩ ካለው ግንዛቤ ጋር ማዛመድንና የመቆጣጠሪያ መንገዶችን ውጤታማነት መፈተሽን ያጠቃልላል፡፡ የማሳ ጽዳት ማካሄድ ዋና ዓላማው በሽታ/ተባይ አምጭ/አስተላላፊዎችን/ተሸካሚዎችን መከላከል ወይም ማጥፋት ነው፡፡ የተከላ ቁርጥራጮች ጤናማና ከበሸታና ከተባይ ነጻ መሆን አለባቸው፡፡ ለአዲሱ ሰብል የብክለት ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ አሮጌ የተከላ ቁርጥራጮችና አስጠጊ ዕጽዋት/አረሞች በማቃጠል፣ በመቅበር ወይም ለእንስሳት መኖነት በመጠቀም ማስወገድ ይገባል፡፡ በቁስሉ/ጉዳቱ በኩል በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ሊገቡ ስለሚችሉ ጤናማ ሰብሎችን ላለማቁሰል/ላለመጉዳት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በሽታና ተባይ እንዳይዛመት ለመከላከል ማሳ ውስጥ ሲሰራ በጣም ጤናማ ከሆነበት የማሳው ክፍል ወደ የበሽታ ምልክት ወደታየበት በኩል እንዲሆን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የመስክ ላይ ጉልበት ሠራተኞች በሽታዎች በጫማቸው፣ በእግራቸው፣ በልብሳቸው፣ በከብቶችና በመስኖ ውኃ እንደሚሰራጩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሰብሉን ብቻ የሚያጠቁ በሽታዎችና ተባዮች መጠናቸው እየጨመረ እንዳይሄድ የሰብል ፈረቃ አመራረት ስርዓትን መከተል ጠቃሚ ነው፡፡ የተሻሻሉ የሰብል አያያዝ ተግባራት የመከላከያ መንገድን መጠቀም በበሽታ ያልተጠቁ የተከላ ቁርጥራጮችን መጠቀምን፣ ሰብሉ በበሽታው በቀላሉ እንዳይጠቃ የሚረዱ ነገሮችን ለምሳሌ ሰብሉ በአፈር ለምነት ዕጥረትና በውሃ ዕጥረት እንዳይጎዳ ማድረግና ሰብሉን በሚስማማው ቦታ ማምረትን ያጠቃልላል፡፡ ጤናማ ተክል በሽታንና ተባይን በተሻለ መልኩ ይቋቋማል፡፡ የበሽታ ወይም የተባይ ጥቃት የማይቀር መሆኑ የሚታወቅ/በጣም የሚጠረጠር ከሆነ የሚቋቋሙ ዝርያዎችን መትከል ያስፈልጋል፡፡ ከዋና ዋና በሽታዎች እና የተባይ ጥቃት ወቅቶች ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ የተከላ ወቅትን ማስተካከል ይቻላል፡፡ በጣም ደካማ ሰብል እንዲበቅል ስለሚያደርግ ጥቅጥቅ ያለ አተካከልን ማስወገድ አለብን፡፡ ምክንያቱም እነኝህ ደካማ ተክሎች ይበልጥ በበሽታና በተባይ ይጠቃሉ፡፡ የሰብል ስብጥር ስርዓት መከተል ብዝሃነትን ስለሚጨምር የበሽታና ተባይ ጥቃትን ይቀንሳል ፡፡ የሰብል ፈረቃ ትግበራን መጀመር ሰብሉን ብቻ የሚያጠቁ ተባዮችና በሽታዎች መጠን እየጎለበተ እንዳይሄድ ያደርጋል፡፡ ሜካኒካል ቁጥጥር ማካሄድ አካላዊ እርምጃዎችን በውስጡ ያጠቃልላል፡፡ በራሪ ነፍሳት ከተክሉና ከችግኝ አካባቢ እንዳይደርሱ የመረብ ዋሻ/መጠለያ መጠቀም ይቻላል (አባሪ 5.2ን ተመልከቱ)፡፡ አፈሩን በላስቲክ መሸፈን የተባይ ትል የስኳር ድንቹን ስር የሚያጠቃበትን ደረጃ ይቀንሳል፡፡ አጣብቂኝ ወጥመድ፣ የወንድ ነፍሳትን መሳቢያ ሆርሞን እና የብርሀን ወጥመድ ነፍሳት ተባዮችን ለማጥመድ ያገለግላሉ፡፡ ዘሮችን፣ ስሮችን ወይም ቁርጥራጮችን በሞቀ ውኃ ወይም በሞቃት አየር ማከም ተባዮችን ይገድላል፤ አፈርን ብርሃን በማያስተላልፍ ፕላስቲክ ለሁለት ሳምንታት መሸፈን በአፈር ውስጥ ያሉ ተባዮችን ይገድላል፡፡ ማሳን ለተወሰነ ጊዜ በውኃ ማጥለቅለቅ የተወሰኑ አደገኛ ተባዮችን ሊገድል ይችላል፡፡ የተበከሉ ቁርጥራጮችን ማስወገድና ማጥፋት የተባዮችንና በሽታዎችን ስርጭት ይቀንሳል፡፡ በስነ-ህይወታዊ መንገድ ተባዮችንና በሽታዎችን የመቆጣጠር ሂደት ተፈጥሯዊ ጠቃሚ ጠላቶችን ይጠቀማል፡፡ ተፈጥሯዊ ጠላቶች አዳኞችን፣ ጥገኞችን እና በአይን የማይታዩ ጥቃቅን ዘአካላትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ አዳኞች ሌሎች ፍጥረታትን የሚያድኑ፣ የሚገሉና የሚመገቡ እንስሳት ሲሆኑ ባጠቃላይ ጠንካራ የአፍ አካባቢ፣ ዕይታና እግር አሏቸው፡፡ ጥገኛዎችም ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 27 ሌሎች እንስሳትን ይመገባሉ ነገር ግን ይህን የሚያደርጉት በሰውነት አካል ውስጥ ገብተው የሚፈልጉትን ነገር ከተጠቂያቸው የአካል ፈሳሽ ወይም ህዋሳት በማግኘት ነው፡፡ ከዚያም ተጠቂያቸውን ያደክማሉ ወይም ለሞት ይዳርጋሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ነፍሳትን የሚያጠቁ ጥገኞች ተርብ ወይም የዝንብ ዝርያዎች ሲሆኑ ጉልምስ ነፍሳቶቹ ተጠቂውን ያፈላልጉና ሲያገኙት እንቁላላቸውን በአካሉ ላይ/ውስጥ ይጥላሉ (አንዳንድ ጥገኞች እንቁላላቸውን በተጠቂያቸው እንቁላል ላይ፣ አንዳንዶቹ በትል፣ አንዳንዶቹ በዕጭ/ፑፓ፣ አንዳንዶች ደግሞ በኩብኩባ፣ ሌሎቹ በጉልምስ አካል ላይ ይጥላሉ)፡፡ የእነኝህ ጥገኞች እንቁላሎች ተፈልፍለው የተጠቂውን አካል ሰርስረው በመግባት ወደ ትል ያድጋሉ፤ ትሉም የአስጠጊውን/ተጠቂውን አካል ይመገባል፤ ቀስ በቀስ አስጠጊውን ያዳክማል እድገቱንም ያግዳል፤ በተጠቂው አካል ውስጥ ወይም በአካባቢው ወደ ዕጭ/ፑፓ ይቀየራል፤ ዕጩ/ፑፓው ወደ ጉልምስ ይቀየራል፡፡ በሽታ አምጭ ተህዋሲያን/አቸንፍር በአይን የማይታዩ ረቂቃን ተህዋሲያን እንደ ባክቴሪያ፣ ሻጋታና ቫይረስ የመሳሰሉ በነፍሳት ተባዮች ላይ በሽታ የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ ወደ ተባይ አካል ውስጥ በመግባት፣ በመኖርና በመባዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባዩን አዳክመው እንዲሞት ያደርጋሉ፡፡ በበሽታው የተጠቁ ነፍሳት ተባዮች ያብጣሉ፣ ልዩ መልክ ያሳያሉ፣ ከተለመደው በጣም ዝቅተኛ እንቅስቃሴ ያሳያሉ፣ መብላት ያቆማሉ እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ ዱቄት በሚመስል ነገር ይሸፈናሉ፡፡ በስነ-ህይወታዊ መንገድ ተባዮችን ለመቆጣጠር አንዳንድ ጊዜ እነኝህ ተህዋሲያን ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ በሳይንሳዊ ስያሜው ባሲለስ ቱሪንጄንሲስ ( በአጭሩ ቢቲ) በመባል የሚታወቀው ባክቴሪያ በሰፊው እየተመረተ ለገበያ በመቅረብ ላይ ያለ ስነ-ህይዎታዊ ጸረ-ተባይ ነው፡፡ የተፈጥሮ ጠላቶችን ስንጠቀም በተቻለ መጠን በጊዜ/ሳይዘገይ ቢሆን ጠቃሚ ነው፤ በተጨማሪም ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር ያስፈልጋል ለምሳሌ እነሱን የሚስቡ ተክሎችን መጠቀም፣ እርጥበት አዘል አየር እንዲጨምር ማድረግ ወዘተ፡፡ የተፈጥሮ ጠላቶችን ስነ-ህይወታዊ ዑደት ማወቁ ጠቃሚ ነው፤ ከተቻለም በምርት ስብሰባ ወቅት የጠቃሚ ነፍሳት ብዛት እንዳይጎዳ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ስነ- ህይወታዊ ዑደታቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ የተፈጥሮ ጠላቶች የተወሰነ ምግብ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ ማለት በእርሻ መሬት ላይ አነስተኛ መጠን ያላቸው ተባዮች ሊኖሩ እንደሚገባ መቀበል አለብን ማለት ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እነኝህ የተፈጥሮ ጠላቶች በተለይም አንድ ዓይነት ምግብ ብቻ የሚመገቡት በፍጹም ሊቆዩ አይችሉም፡፡ ከተራቡ ይጠፉና የተባይ ነፍሳት በፍጥነት እንዲባዙ ዕድሉን ያገኛሉ፡፡ በተቀናጀ የተባይ/በሽታ ቁጥጥር ዘዴ ውስጥ የኬሚካል ቁጥጥር ማለት በጣም መርጠው የሚገሉና ጠቃሚ ነፍሳት ላይ ጉዳት የማያደርሱ ጸረ-ተባዮችን/በሽታዎችን መጠቀም፣ መርጦ የመተግበር/የመርጨት ስርዓትን መተግበር ለምሳሌ በአዳዲስ/ጨቅላ ሰብሎች ላይ አለማድረግ ወይም ዘርን በጸረ ተባዮች መለወስን እና የመሳሰሉትን ማለት ነው፡፡ ለተባይና በሽታ ቁጥጥር ኬሚካሎች ጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ የሚረጨውን ሰራተኛ፣ ከጎረቤት ያሉትን ሰዎችና እንስሳትን እንዲሁም አካባቢን በማይነካ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ይህም በርጭት ወቅት መከላከያ ቁሳቁሶችን መልበስ፣ ነፍሰ ጡሮች፣ አጥቢዎች፣ ህጻናት ወይም ምግብ የሚያዘጋጁ ሰዎች እንዳይረጩ ማድረግን ያጠቃልላል፡፡ እንጥብጣቢዎች ወደ አካባቢው እንዲበኑ ስለሚያደርጋቸው ርጭት በንፋስ ወቅት መካሄድ የለበትም፡፡ የመርጫ ቁሳቁሶች በየጊዜው መታጠብ ያለባቸው ሲሆን እጣቢው በውሃ አካላት አካባቢ እንዳይደፋ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ኬሚካሎች በግልጽ የሚታይ መለያ ተደርጎባቸው ከምግብ ርቀው በትክክል መቀመጥ አለባቸው፡፡ የጸረ-ተባይ/በሽታ ኬሚካል መያዣዎች ደግሞ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ተደርገው መበሳት አለባቸው፡፡ ጸረ-ተባዮች/በሽታዎች መርዝ እንጂ መድኃኒት እንዳልሆኑ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ጸረ-ተባይ/በሽታ ኬሚካሎች መረጨት የሚገባቸው በተባይና በሽታ ዳሰሳ ጊዜ በሚደረገው ምልከታ እንጂ በርጭት መርሀ ግብር መሆን የለበትም፡፡ ስለሆነም መከናወን የሚገባው የልኬት ገደቡ (የተባዩ ክስተት ጉዳት ሊያስከትል የሚችልበት መጠን) የደረሰ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ (ለምሳሌ ጸረ-ተባይ/በሽታ ለመርጨት የሚወጣው ወጭ ተባዩ/በሽታው ያደርሳል ተብሎ ከሚታሰበው ኪሳራ በላይ ከሆነ ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ አያስፈልግም)፡፡ አብዛኞቹ አርሶ አደሮች ሁሉንም አይነት የመቆጣጠሪያ መንገዶችን በማዋሀድ ለመጠቀምና የትኛው መንገድ ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝ ለመሞከር ይፈልጋሉ፡፡ 7.2 የስኳር ድንች ነቀዝን መለየትና መቆጣጠር 7.2.1 የስኳር ድንች ነቀዝን የህይወት ዑደትና ባሕሪ መለየትና ማወቅ የስኳር ድንች ነቀዝ ዋነኛው የስኳር ድንች ተባይ ሲሆን ሰብሉ በሚበቅልባቸው በየትኛውም የዓለም ክፍሎች ይገኛል፡፡ ጉልምሱ ትልቅ ጉንዳን የሚመስል ሞላላ፣ ትንሽ ጥቁር ወይም ብረት መልክ ያለው (ከ5-6 ሚሜ ርዝመት) ነው፡፡ ወንድና ሴት ነቀዞች በአንቴናቸው/ቀንድ ቅርጽ እንደሚለዩ መናገር ይቻላል፤ የወንዱ ቀጥ ያለ ሲሆን የሴቷ ደግሞ ከጫፉ አበጥ ያለ ነው፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 28 ከግንኙነት በኋላ ሴቷ ነቀዝ ራሷ አኝካ በፈጠረቻቸው ሀረጎች ላይ ባሉ ቀዳዳዎች ወይም በቀላሉ ሊገኙ በሚችሉ ስሮች ላይ እንቁላሎቿን አንድ በአንድ ትጥላቸዋለች፡፡ ሴቷ ነቀዝ በህይወት መቆየት የምትችለው ለአራት ወራት ብቻ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት መጣል የሚገባትን (ከ50-250) እንቁላሎች ጥላ ትጨርሳለች፡፡ ሰብሉ ስር ከማኮረቱ በፊት በማሳው ከደረሰች እንቁላሎቿን በሀረግ ወይም በቅጠል ላይ ትጥላለች፡፡ ስሩ ማኮረት ከጀመረ ግን ከመሬት በላይ የወጣ/የተጋለጠ ስር መፈለግ ትጀምራለች፡፡ ነቀዞች አፈርን መቆፈር ስለማይችሉ ወደ ስኳር ድንች ስር የሚደርሱት ደርቆ በተሰነጠቀ አፈር የስኳር ድንች ነቀዝ ትል ውስጥ ወይም ሀረግ ውስጥ በመግባት ውስጥ ለውስጥ ያኮረተውን ስር እስኪያገኙ በመጓዝ ነው፡፡ ሴቶቹ ነቀዞች የመመገቢያና የእንቁላል መጣያ ቀዳዳዎችን በሀረግና በስር ላይ ያበጃሉ፡፡ እንቁላል የያዙ ቀዳዳዎች ከነቀዞቹ በሚመነጨው ነገር ስለሚሸፈኑ ጠቆር ባለ መልካቸው ይታወቃሉ፡፡ የእንቁላሎቹ የዕድገት ወቅት በአካባቢው ሙቀት መጠን ቢወሰንም ለመፈልፈል ከ3-7 ቀናትን ይፈጃሉ፡፡ የሚፈጠረው ትል እግር አልባ፣ ጎበጥ ያለና ነጭ መልክ ሲኖረው ጠቆር ያለ ቡኒ ራስ አለው፡፡ የስኳር ድንች ነቀዝ እንቁላል መመገብ ሲጀምር በሀረግ ወይም በስሩ ላይ ቀዳዳ ይፈጥራል፤ የሚኖረውም እንደእንቁላሉ እዚያው ውስጥ ነው፡፡ ጥቃቱን ሲቀጥል በስሩ ላይ የተለያዩ ጥቋቋር ቀዳዳዎችና ቦዮች በተደጋጋሚ የሚታዩ ሲሆን እነዚህም የስኳር ድንች ሰብል አጥፊ ናቸው፡፡ ትሉ የሚፈጥረው የመመገቢያ ቀዳዳዎችና ቦዮች የስሩን የገበያ እሴት ከመቀነሳቸው ባሻገር በነቀዝ ከተበላው ስር አጠገብ ላለው ስር የተባዩ ምንጭ ይሆናሉ፡፡ የተባዩ ወረራ በአነስተኛ መጠን ቢሆን እንኳን ተርፕኖይድ የተሰኘ መራራ ኬሚካል በማመንጨት የስሩን ጥራት በማበላሸት ለገበያ የሚሆነውን ምርት ይቀንሳል፡፡ ይህ ጉዳት ስሩ ከተሰበሰበ በኋላም እንኳን ሊቀጥል ይችላል፡፡ ትሉ ወደ ዕጭ/ፑፓ ከመቀየሩ በፊት ከ11 እስከ 33 ቀናት ይቆያል፡፡ የስኳር ድንች ነቀዝ ፑፓ ዕጩ/ፑፓው በትሉ ዋሻ ውስጥ ከ3-28 ቀናት ይቆያል፤ ከዚያም ጉልምሱ ይፈጠራል፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ጉልምሱ ነጣ ያለ ቡኒ መልክ ቢኖረውም ከአንድ ሳምንት ግድም በኋላ ጠቆር ያለ ቡኒ መልክና ጠንካራ ሽፋን ይኖረዋል፡፡ ከዚያም ጉልምሱ ከስሩ ይወጣና ለጾታዊ ግኑኝነት መንቀሳቀስ ይጀምራል፡፡ ሴቷ ነቀዝ ወንድን የሚስብ ሽታ ታመነጭና ወንድ መፈለግ ትጀምራለች፡፡ ወንዱ ነቀዝ በማታ ሴቷን ፍለጋ መዞር የሚጀምር ሲሆን በቀን ግን ራሱን ቅጠል ስር ያለበለዚያም በአፈር ስንጥቅ ውስጥ ደብቆ ያቆያል፡፡ ማታ ጾታዊ ግንኙነት ያደርጉና ሴቷ ቀን ቀን መመገብና ዕንቁላል መጣል ትጀምራለች፡፡ ጠቅላላ ከእንቁላል እስከ ጉልምስ ድረስ ያለው የህይወት ዑደት 32 ቀናትን ይፈጃል፡፡ እጅግ በጣም ብዙ ጉልምሶች ጉልምስ የስኳር ድንች ነቀዝ በቅጠል ላይ መኖር ስሩ በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጠቃ ያሳያል፡፡ ስዕል 7.5 የስኳር ድንች ነቀዝ የህይወት ዑደት የወንዱ ነቀዝ አንቴና ቀጥ ያለ ነው የሴቷ አንቴና እንደዱላ ጫፍ አበጥ ያለ ነው ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 29 ጉልምሱ የስኳር ድንች ቅጠል እየተመገበ ይቆያል ዕጭ/ፑፓ (3-28 ቀናት) በትሉ ዋሻ በስርና ሃረግ ውስጥ ይቀመጣል እንቁላሎች (ከ3-7 ቀናት) በተጋለጡ ስሮች እና ሃረጎች ላይ ይጣላሉ ትል (ከ11-33 ቀናት) በመመገቢያ ዋሻ ወይም ቀዳዳ ውስጥ እየተመገበ ያድጋል ምንጭ: Stathers et al., 2005 በስኳር ድንች ነቀዝ የተጠቃ ስር በስኳር ድንች ነቀዝ የተጠቃ ሀረግ/ግንድ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 30 7.2.2 የስኳር ድንች ነቀዝ መቆጣጠሪያ መንገዶች አርሶ አደሮች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ተባይ መቆጣጠሪያ መንገዶች በተቀናጀ መልኩ በመጠቀም በስኳር ድንች ነቀዝ ሊመጡ የሚችሉ የምርት ቅነሳዎችን መከላከል ይችላሉ፡፡ አፈር ማስታቀፍ: የአካባቢው የአየር ሁኔታ ደረቅ ከሆነና አፈሩ የሚሰነጣጠቅ ከሆነ ነቀዙ በቀላሉ ወደ ስሩ በመድረስ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡ አፈሩ ሲደርቅ ከስሩ አካባቢ በመሸሽ ስሩ በቀላሉ ለነቀዝ እንዲጋለጥ የሚያደርግ ሲሆን በመትከያ መደቦችና ጉብታዎች ላይ ያለው አፈርም ተሰነጣጥቆ ተባዩ ስሩን በቀላሉ እንዲያገኘው ያደርጋል፡፡ ለዚህም ነው የስኳር ድንች ስሮች ከካሳቫ ስሮች በተቃራኒው በአፈር ውስጥ ለረዥም ጊዜ ያለ አፈር ማሳቀፍ መቆየት የማይችሉት፡፡ አፈር ማሳቀፍ በተወሰነ መልኩ በሰብሉ ዙሪያ ወይም በመትከያ መደብ ላይ ያለውን አፈር ስንጥቁን በመሙላትና የተጋለጡ ስሮችን በመሸፈን ተክሉ በተባይ እንዳይጎዳ ያደርጋል፡፡ ማሳቀፍ በተለይም ስሩን ትንሽ በትንሽ እየቆፈሩ ጥቅም ላይ ለማዋል በሚደረገው ሂደት ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሴቶች በማሳቸው ውስጥ ተዟዙረው ተለቅ ያለውን ስር በመፈተሽ ለምግብነት ወይም ለገበያ ሊጠቀሙ ካወጡ በኋላ አፈሩን ማንኛውም ስንጥቅ ካለ ለመድፈን ወደ ቦታው ይመልሱታል፡፡ ይህ ድርጊት የነቀዞችን ጥፋት ከመቀነሱም ባሻገር ምርትን ይጨምራል፡፡ የማሳ ጽዳት: ያረጁ ሀረጎችንና የስር ቅሪቶችን ከማሳ ውስጥ ጠርጎ ማውጣትና ማስወገድ (ማቃጠል ወይም ለከብት መኖነት መጠቀም) የስኳር ድንች ነቀዞችና ሌሎች ተባዮች የህይወት ዑደታቸው እንዳይቀጥልና ወደ አዳዲስ ማሳዎች እንዳይገቡ ይከላከላል፡፡ ስኳር ድንች በዓመት ከሁለትና ከዚያ በላይ በሚመረትባቸው አካባቢዎች የስኳር ድንች ነቀዞች በቀላሉ እንዲቆዩና አዳዲሶቹን ማሳዎች እንዲያገኙ ስለሚያደርግ ለእንደዚህ ላሉ አካባቢዎች ይህኛው መንገድ ቀላል የመቆጣጠሪያ ዘዴ ነው፡፡ ስኳር ድንችን በተደጋጋሚ በአንድ ማሳ ላይ ያለመትከል (ሰብል ፈረቃ) እና አዳዲሶቹን ማሳዎች ከአሮጌዎቹ በተቻለ መጠን ማራቅ (ማሳዎችን ማግለል) የተባዩ ተጨማሪ የመቆጣጠሪያ መንገዶች ናቸው፡፡ የስኳር ድንችን ሀረግ የአፈር ለምነትን ለማስጠበቅ ከማሳው ላይ የምንተው ከሆነ ለጸሀይ ማጋለጥና ከአፈሩ ጋር ከመቀላቀላችን በፊት መድረቁንና መብቀል ያለመጀመሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ወዶ አደግ ሰብሎች (ከባለፈው ወቅት ቅሪት በድንገት ባልተፈለገ ጊዜ በቅለው የሚታዩ የስኳር ድንች ተክሎች) እና አስጠጊ ተክሎች የስኳር ድንች ነቀዝ ቁጥርን ለመቀነስና ከአንደኛው ወቅት ወደ ሌላኛው ወቅት እንዳይሻገሩ መወገድ አለባቸው፡፡ ንጹህ የተከላ ቁርጥራጭ መጠቀም፡ በተባይ ያለተበከለ ወይም ንጹህ የተከላ ቁርጥራጭ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ነቀዞች በሀረጉና ደርቀው ወደ እንጨትነት በተቀየሩ የስኳር ድንች ሀረጎች ላይ እንቁላላቸውን ይጥላሉ፡፡ በሀረጉ ላይ የተባዩን የመመገቢያና የእንቁላል መጣያ ቀዳዳዎችን መለየቱም አዳጋች ነው፡፡ ስለዚህ ለተከላ የምንጠቀመው የሀረግ ክፍል ከጫፍ መሆን አለበት፡፡ በምንም ሁኔታ እስከ 10ሴ.ሜ ለመሬቱ የተጠጋ ሀረግ ለተከላ መጠቀም አያስፈልግም፡፡ በቫይረስ የተበከለ የተከላ ቁርጥራጭ የምንጠቀም ከሆነ የቫይረስ በሽታዎች ወደ አዳዲስ ማሳዎች ሊተላለፉ ስለሚችሉ ለተከላ የምንጠቀመውን ቁርጥራጭ መውሰድ የሚገባን ቢያንስ በእይታ ጤናማ ከሆነው ተክል መሆን አለበት፡፡ በደረቅ ወቅት አፈሩ ከመሰንጠቁ በፊት ጊዜ ጠብቆ ምርት መሰብሰብ፡ ስኳር ድንችን በዝናብ ወቅት መጀመሪያ ላይ መትከል የደረቅ ወቅት ሳይመጣ፣ አፈሩ ሳይሰነጠቅና የነቀዝ ጥቃት ሳይከሰት ምርቱን የመሰብሰብን ዕድል ያሰፋል፡፡ በቪየትናም የደረቅ ወቅት ከመምጣቱ ከሁለት ሳምንታት አስቀድሞ ምርት መሰብሰብ በነቀዝ ጥቃት ምክንያት ይመጣ የነበረውን የምርት ቅነሳ ከ30 በመቶ ወደ 5 በመቶ ማውረድ እንደሚያስችል ታይቷል፡፡ ሰብል ፈረቃ: ስኳር ድንችን ከሌሎች ሰብሎች ጋር አፈራርቆ መትከል አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም በማሳችን አንድ ወገን ላይ በተከታታይ ስኳር ድንች ያለመኖሩ ከአንድ የምርት ወቅት ወደ ሌላው የምርት ወቅት የሚሸጋገረውን የነቀዝ ቁጥር በጣም ይቀንሳል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በሰብሉ ቅሪተ አካላት አማካይነት የመተላለፊያው ዕድል የሰፋ ይሆናል፡፡ የምርት ወቅት/ዓመት 1 የምርት ወቅት/ዓመት 2 የምርት ወቅት/ዓመት 3 ስኳር ድንች ስኳር ድንች ስኳር ድንች ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 31 ማሳ መለየት: የስኳር ድንች ነቀዝ አብዛኛውን ጊዜ ስለማይበር ከበረረም በጣም አጭር ርቀት (ከ500-1000 ሜ) የስኳር ድንች ተክል ለማግኘት ስለሆነ አዲስ የሚተከሉ ማሳዎችን በተቻለ መጠን ከሌሎች ነባር ማሳዎች ወይም ስኳር ድንች ተተክሎ ከነበረበት ማሳ ማራቅ የነቀዝ ጥቃትን ለመከላከል ያስችላል፡፡ የተፈጥሮ ጠላቶች/ጠቃሚዎች: በተፈጥሮ የሚገኙ አዳኝ እንስሳትን እንደ ጉንዳን፣ ፌንጣ፣ ሸረሪትና የምድር ጥንዚዛዎችን በስኳር ድንች ማሳ ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ነቀዞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ይረዳል፡፡ የጉንዳኖቹን መጠለያ ወደ ስኳር ድንች ማሳ ማንቀሳቀስ አደኑን ያፋጥናል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች የሻጋታ ዝርያዎች (ቢዩቨሪያ ባሲያና) አፈርን ወይም የተከላ ቁርጥራጮችን ለማከምና የስኳር ድንችን ነቀዝ ለመቀነስ ይጠቅማሉ፡፡ ጸረ-ተባይ ኬሚካሎችን በማሳ ውስጥ ያለመርጨት በተፈጥሮ የሚገኙ ጠቃሚ ተባዮች እንዳይጠፉና ቁጥራቸውም እንደተጠበቀ እንዲቆይ ይረዳል፡፡ የተባይ ችግር ለመቀነስ በተፈጥሮ የሚገኙ ጠላቶችን መደገፍ ማገጃ ሰብሎች: አዲስ በተተከለውና በአሮጌው ማሳ መካከል ከ3 - 5ሜ ስፋት ባለው ቦታ ላይ ካሳቫ፣ በቆሎ፣ ማሽላ ወይም ሙዝ መትከል ተባዩ ወደ አዲሱ ማሳ የሚያደርገውን ጉዞ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡ ይህንን ለማድረግ በቂ ርዝመት ያላቸው መግቻ ሰብሎች አስቀድሞ በበቂ መጠን መትከል ያስፈልጋል፡፡ በሌላ በኩልም እነዚህ ሰብሎች ከስኳር ድንች ሰብል የሚመነጨውን ሳቢ ሽታ ነቀዙ እንዳያስተውል ጭምር የሚገቱ መሆን አለባቸው፡፡ ጉዝጓዝ: ከተከላ በኋላ አፈሩን በጉዝጓዝ መሸፈንና ጉዝጓዙም እንደ ተጠበቀ እንዲቆይ ማድረግ የአፈርን እርጥበት ከመጠበቁም ባሻገር የአፈር መሰንጠቅን በመከላከል የነቀዝ ጥቃት እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ በጎርፍ/ውኃ ማጥለቅለቅ፡ የስኳር ደንች ምርት ከተሰበሰበ በኋላ ማሳውን ቢያንስ ለ48 ሰዓታት በውኃ ማጥለቅለቅ ያሉት የስኳር ድንች ነቀዞች ታፍነው እንዲሞቱ ያደርጋል፡፡ በጸረ-ተባይ ኬሚካል መቆጣጠር: የስኳር ድንች ነቀዝ ሁሉንም የእድገት ደረጃውን (እንቁላል፣ ትል፣ ዕጭ/ፑፓ እና ጉልምስ) የሚያከናውነው በስር ወይም በሀረግ ውስጥ ተደብቆ በመሆኑ በጸረ-ተባይ ኬሚካል መቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በአንዳንድ አገሮች ከተከላ በፊት የተከላ ቁርጥራጮች በመድኃኒት ውስጥ በመንከር የነቀዝ ወረራ ጊዜ በብዙ ወራት እንዲዘገይ ያደርጋሉ፡፡ ነቀዝ የሚቋቋሙ የስኳር ድንች ዝርያዎች፡ እስከአሁን ድረስ የስኳር ድንች ነቀዝን የሚቋቋም አንድም ዝርያ በተመራማሪዎች አልተፈጠረም፡፡ ቢሆንም ረዘም ያለ ስር/ጥልቅ ስር ያላቸው አጫጭር ስር ካላቸው የስኳር ድንች ዝርያዎች በቀላሉ ለነቀዙ ስለማይገኙ በአንጻራዊ መልኩ በአነስተኛ ደረጃ ይጠቃሉ፡፡ ቶሎ የሚደርሱ ዝርያዎች የነቀዝን ጥቃት በቀላሉ ያመልጣሉ፡፡ ምክንያቱም የአፈር ድርቀት ሳይመጣና አፈሩ ሳይሰነጣጠቅ ለምርት ስለሚደርሱ ነቀዞቹ ሊያገኟቸው አይችሉም፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 32 የጾታ ሽታ ወጥመድ፡ በአንዳንድ አገሮች ይህ ወጥመድ በፋብሪካ ደረጃ ይመረትና ወጥመዱን የያዘ ማባበያ በስኳር ድንች ማሳ ውስጥ ውኃና ሳሙና ብጥብጥ ባለበት ዕቃ አናት ላይ ይሰቀላል፡፡ ወንዴ ነቀዞች በጠረኑ ተታለው ይመጡና ከስር ባለው ውኃና ሳሙና ብጥብጥ ውስጥ ወድቀው ይሞታሉ፡፡ ይሁን እንጂ በኡጋንዳ በተደረገው ጥናት ማባበያው በስኳር ድንች ስር ላይ የሚደርሰውን የነቀዝ ጥቃት በሚታይ ሁኔታ ሲቀንስ አልታየም፡፡ 7.2.3 ሸካራው የስኳር ድንች ነቀዝ (Blosyrus spp) ሸካራው የስኳር ድንች ነቀዝ (ብሎሳይረስ ዝርያ) እንደ ስኳር ደንች ነቀዝ (ካይለስ ዝርያ) አደገኛ ተባይ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ በአንዳንድ የአፍሪካ አካባቢዎች ትልቅ ጥቃት ያደርሳል፡፡ ጉልምሱ ሸካራ የስኳር ድንች ነቀዝ ከተለመደው የስኳር ድንች ነቀዝ (ካይለስ ዝርያ) የሚበልጥና ከ8 - 9ሚ.ሜ የሚረዝም ተባይ ነው፡፡ ሸካራና ጠቆር ያለ አካሉ ከአፈር ጋር በደንብ ተመሳስሎ እንዲኖር አስችሎታል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ቢጫ መልክ ያላቸው እንቁላሎችን በስኳር ድንች ቅጠል ጠርዝ አካባቢ ይጥሉና ቅጠሉን ወደ እንቁላሎቹ እንዲታጠፍ ያደርጋሉ፡፡ ሴቷ አፈር ላይ ከወዳደቁ ቅጠሎችም ስር እንቁላሏን ልትጥል ትችላለች፡፡ በቅጠሉ ላይ የተጣሉት እንቁላሎች ከተፈለፈሉ በኋላ ትሎቹ ከቅጠሉ ጋር ተጠቅልለው ወደ መሬት ይወርዱና መሬት ውስጥ ሰርስረው በመግባት ምግብ ይፈልጋሉ፡፡ የስኳር ድንች ስር ሲያገኙ ቆዳውን ይመገቡታል፣ በቆዳውም ላይ ጥልቅ ጉድጓድ ይፈጥራሉ፡፡ ጉዳቱ ከመቶ እግርና ከቁምቡርስ ጥቃት ጋር ይመሳሰልና የገበያን እሴት በጣም እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ የተበላሸውንም ለማስወገድ ጠለቅ አድርጎ መላጥን ስለሚጠይቅ የምርት ቅነሳንም ያስከትላል፡፡ ይሁን እንጂ እነኝህ ነቀዞች ከስኳር ድንች ነቀዝ በተቃራኒው የስሩ ጣዕም እንዲመር የሚያደርግ ኬሚካል አያመነጩም፡፡ ትሉ ወደ 30 ቀናት ያህል ከተመገበ በኋላ ለተከታታይ 20 ቀናት ዕጭ/ፑፓ ሆኖ ይቆያል፡፡ ጉልምሶቹ ቀን ቀን በወዳደቁ ቅጠሎች ስር ተደብቀው ይቆያሉ፡፡ ከወይንጠጅ ወደ ጥቁር የሚያደላው ኩሳቸው (በግምት 7ሚሜ የሚጠጋ ርዝመት ያለው) ከመሬት በላይ መገኘቱ በዋናነት የሸካራ ነቀዝ መኖርን ያመለክታል፡፡ በክፍል 7.2.2 ላይ የተጠቀሱት የተባይ መቆጣጠሪያ መንገዶች አብዘኛዎቹ የሸካራ ስኳር ድንች ነቀዝን ለመቆጣጠርም ያገለግላሉ፡፡ ተጨማሪ ስለ ስኳር ድንች ተባዮች መረጃና ፎቶግራፍ ከሰሀራ በታች ለሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከስኳር ድንች የተቀናጀ የተባይ ቁጥጥር የአርሶ አደሮች የመስክ ትምህርት ቤት መምሪያ/ማኑዋል እና ከስኳር ድንች ዳሰሳ ድረ ገጽ https://keys.lucidcentral.org/keys/sweetpotato/ ማግኘት ይቻላል፡፡ 7.3 የስኳር ድንች ቫይረስን መለየትና መቆጣጠር ቫይረሶች እጅግ በጣም ትንንሽ ስለሆኑ በዓይናችን ማየት አንችልም፡፡ ይሁን እንጅ የሚያስከትሉትን ችግር ማየት ይቻላል፡፡ በአፍሪካ ከየትኛውም ይልቅ በስኳር ድንች ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ፍጡራን ናቸው፡፡ ቫይረሶች በአስጠጊዎቻቸው አካል ውስጥ ብቻ ሊኖሩ፣ ሊራቡና ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ሁሉም ዕፅዋትን የሚያጠቁት ቫይረሶች ከአንድ ተክል ወደ ሌላኛው ለመተላለፍ የዕፅዋቱን ፈሳሽ የሚመገቡ ነፍሳትን ይፈልጋሉ፡፡ እንደ ክሽክሽ ወይም ነጫጭ ዝንቦችን የመሳሰሉ ነፍሳት ተክሉን በሚመገቡበት/ፈሳሽ ከተክሉ በሚመጡበት በተመሳሳይ ጊዜ በሽታውንም ያስተላልፋሉ፡፡ አንድ ቫይረስ ወደ አስጠጊው አካል ህዋስ ውስጥ ከገባ የህዋሱን የመባዛትና የዕድገት ስርዓቶችን በመቆጣጠርና በማስገደድ ህዋሱ በሰብሉ ቦታ ራሱን የሚመስሉ ቫይረሶችን በከፍተኛ ደረጃ እንዲያመርት ያደርጋል፡፡ ከዚያም እነዚህ አዳዲስ የቫይረስ ቅንጣቶች በተክሉ አካል ውስጥ ይሰራጩና ብዙ ህዋሳትን ይወራሉ፡፡ ስኳር ድንችን ጨምሮ በተክሎች ላይ የሚታዩ የቫይረስ ምልክቶች፡-  የዕድገት መቀነስ/መቀንጨር፡ ተክሎቹና ቅጠሎቹ ትናንሽ ሆነው እንዲቀሩ ያደርጋል  የቅጠሎች ህብረ-ህዋሳት መወየብ (መደብዘዝ) በመሆኑም በበሽታው የተጠቁ ተክሎች ከሌሎቹ ተለይተው ይታያሉ፡፡ ይህም በጥቅል ወይም በአብዛኛው ጊዜ በዋና የቅጠሉ ደም ስሮች መካከል በማዥጎርጎር ወይም ደግሞ የቅጠል መጋቢ ደም ስሮችን ተከትሎ በማገርጣት ሊሆን ይችላል  ቅርጽ አልባ ቅጠሎች ከወጣ ገባ ወይም ከጥቅል ገጽታ ጋር ይታያሉ  ከወትሮ በተለየ ሁኔታ የተቀለሙ ቅጠሎች፣ አብዛኛውን ጊዜ ወይንጠጅ ወይም ቢጫ ጠቅላይ ወይም ነጠብጣብ ወይም ቀለበት ያላቸው ቅጠሎችና  አነስተኛ የስኳር ድንች ስር ምርት ናቸው፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 33 በአፍሪካ ስኳር ድንችን የሚያጠቁ ሁለት ዓይነት ቫይረሶች አሉ፡፡ እነዚህም ላባ መሰል አዥጎርጉር የስኳር ድንች ቫይረስ (Sweet potato feathery mottle virus (SPFMV) እና የስኳር ድንች አቀርጣጭ አቀጭጭ ቫይረስ Sweet potato chlorotic stunt virus (SPCSV) ሲሆኑ እንደቅደም ተከተላቸው በክሽክሽና በነጫጭ ዝንቦች አማካይነት ይተላለፋሉ፡፡ እያንዳንዱ ቫይረስ ለብቻው በጣም አነስተኛ የበሽታ ምልክት የሚያሳይ ቢሆንም ሁለቱ በአንድ ላይ በአንድ ተክል ላይ ካሉ ግን ከፍተኛና ኃይለኛ በሽታ ያስከትላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ በሽታው የስኳር ድንች ቫይረስ በሽታ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ነፍሳት የስኳር ድንችን ቫይረስ ረዥም ርቀት ወስደው አያሰራጩም፡፡ ነገር ግን የተከላ ቁርጥራጮች ወይም የስኳር ድንች ስሮች ረዥም ርቀት የሚሄዱ ከሆነ ቫይረስን በሰፊው ያሰራጫሉ፡፡ ስለዚህ የሰብሎቻችንን በቫይረስ የመጠቃት ዕድል ለመቀነስ፡- 1) ቢያንስ በአይን ሲታዩ ጤናማ ከሆኑ ተክሎች የተከላ ቁርጥራጮችን መውሰድ፡፡ በተጨማሪ:-  በተቻለ መጠን የተከላ ቁርጥራጭ የምንወስድበት ማሳ ጤናማ መሆኑን ለማረጋገጥ መሞከር፡፡ ይህ በበሽታ ተይዘው ግን ምልክት ያላሳዩትን ተክሎች የመውሰዱን ዕድል በጣም ይቀንሳል፡፡  የስኳር ድንች ቫይረሶችን ካረጁ ተክሎች ላይ ማየቱ አዳጋች ስለሆነ ቁርጥራጮቹን ከለጋ ወይም ከደረሱ ሰብሎች ብቻ መሰብሰብ፡፡ 2) በጨቅላ ስብሎች ላይ ወዲያው እንደታዩ ተክሎቹን ከቦታው ማንሳትና ማቃጠል ወይም ለእንስሳት መመገብ፡፡ የታመሙትን ለይቶ የማንሳቱ ተግባር ነቀሳ ሲባል በአንድ ማሳ ውስጥ የቫይረስን በሽታ ከተክል ወደ ተክል ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡ የተበከለ ተክል በማንኛውም ሁኔታ ጥሩ ምርት ሊሰጥ እንደማይችል ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጊዜ የታመሙትን ተክሎች በመንቀስ ከማሳው ጥሩ ምርት የማግኘት እድልን ማሻሻል ይቻላል፡፡ ካልሆነ ግን ነፍሳት የታመሙትን ሰብሎች ተጠቅመው በማሳው ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ቫይረሱን በማሰራጨት ምርት እንዲቀንስ ያደርጋሉ፡፡ በተነቀሰበት አካባቢ የሚገኙ ተክሎች ክፍተቱን በመሙላት ወፋፍራም ስሮችን ያኮርታሉ ወይም አርሶ አደሩ ራሱ ክፍተቱን በአዳዲስ የተከላ ቁርጥራጮች መሙላት ይችላል፡፡ 3) በሽታውን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን መትከል፡ አንዳንድ ዝርያዎች በቫይረስ በሽታዎች ላይጠቁ ይችላሉ፡፡ ሰለዚህ የተለያዩ ዝርያዎችን በመውሰድና ተደጋጋሚ ሙከራ በማድረግ የትኛዎቹ ዝርያዎች እንደሚጠቁ ማየት ይቻላል፡፡ 4) ባለፈው ዓመት/ወቅት ስኳር ድንች በተመረተበት ማሳ ላይ አዲስ ስኳር ድንች ያለማምረት፡ ከባለፈው ዓመት የቀሩ ስሮች ወይም ሀረጎች በመሬት ውስጥ ካሉና የሚያቆጠቁጡ ከሆነ በሽታውን ይዘው የሚበቅሉ ስለሆነ አዲስ ወደ ተተከለው ሰብል በሽታውን ያሰራጫሉ/ያጋባሉ፡፡ ይህ አሰራር የስኳር ድንች ነቀዝንም ለመቆጣጠር ይጠቅማል፡፡ 5) አዳዲሶቹን የስኳር ድንች ሰብሎች በፊት ከነበረው ማሳ አርቆ መትከል፡ ይህን ዘዴ በተግባር ላይ ማዋል ለክሽክሽና ነጫጭ ዝንቦች ከአሮጌዎቹ ሰብሎች ወደ አዳዲሶቹ ሰብሎች የቫይረስ በሽታን ማስተላለፍን በጣም አዳጋች ያደርግባቸዋል፡፡ ይህ አሰራር የስኳር ድንች ነቀዝንም ለመቆጣጠር ይጠቅማል፡፡ በቫይረስ የተያዙትን ተክሎች ምልክቱ እንደታየ ወዲያውኑ ማስወገድ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ ይረዳል ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 34 7.4 የሻጋታ በሽታዎችን መለየትና መቆጣጠር ከቫይረስ በሽታዎች በተጨማሪ የስኳር ድንች ተክሎች በሻጋታና በባክቴሪያ በሽታዎች ይጠቃሉ፡፡ የሻጋታ በሽታዎች በስኳር ድንች ቅጠልና ግንድ ክብ ቡናማ ወይም ጠቆር ያለ ቁስለት ያስከትላሉ፡፡ ሌሎች ምልክቶች ብናኝ ስፍራዎችን/ክልሎችን ወይም የሻጋታ ዘር መሸከሚያ ቃጫ ክምሮችን ያጠቃልላሉ፡፡ ብናኝ ክልሎች የሻጋታውን ዘር የያዙ ሲሆኑ በሽታውን ከአንድ ተክል ወደ ሌላው እንዲሰራጭ ሲያደርጉ ቃጫዎቹ ደግሞ ሻጋታው አዳዲስ የተክሎችን አካል ክፍል የሚወርበት መሳሪያ ነው፡፡ አልተርናሪያ፣ ፎሞፕሲስ እና ብላክ ሮት የተባሉት ዋና ዋና የስኳር ድንች የሻጋታ በሽታዎች ናቸው (ሠንጠረዥ 7.1ን ይመልከቱ)፡፡ ሠንጠረዥ 7.1 የሶስቱ የሻጋታ በሽታዎች ምልክት፣ መሰራጫ መንገድና መቆጣጠሪያ መንገዶች አልተርናሪያ ፎሞፕሲስ ብላክ ሮት (ሴራቶሲይስት ዝርያ) ምልክቶች: በቅጠል፣ በግንድ ወይም በቅጠል ደጋፊ ምልክቶች: ያረጁ ቅጠሎች ቅርጸ ቢስ (ከ5- ምልክቶች: በወፋፍራም ስሮች ላይ ጎድጎድ ያለ ቡኒ ላይ ቡኒ ቀለም ያለው ቁስለት፣ የበሬ ዓይንን 10ሚሜ ስፋት)፣ ጠቆር ባለ ወይን ጠጅ እስከ ነጥብ (0.5ሴሜ የክበብ አጋማሽ መስመር) ይከሰትና የሚመስሉ የተደራረቡ ክብ ቅርጽ ገጽታና ቡኒ ጠርዝ የተከበበ፣ ነጣ ካለ አስከ ፈዛዛ ቡኒ ጠንካራ፣ ደረቅና ጥቁር ይሆናል፡፡ ምናልባት ነጥቦቹ በትክክል የሚታይ ጠርዝ ይፈጥራል፡፡ ነጠብጣቦቹ የሆነ ቁስል ከጥቁር ስፒል ጭንቅላት ይገናኙና ሙሉ በሙሉ ስሩን ሊሸፍኑት ይችላሉ፡፡ ሁልጊዜ በገረጣ አክሊል የተከበቡ ናቸው፡፡ ብዙ የሚመስል መዋቅር ጋር አላቸው፡፡ በስሩ ላይ ጥቁር ነጠብጣብ ያለባቸው ቦታዎች ቁስለቶች አንድ ላይ ተገናኝተው የቅጠሉን ገጽ ሲበሉ ጣዕማቸው ልክ እንደ መራራ ፍራፍሬ ስርጭት: ሻጋታው በሰብሎች ቅሪተ-አካል ይሸፍናሉ፣ ቀጥሎም ቅጠሉ ይራገፋል፡፡ በተጠቁ ይሆናል፡፡ ተክሉ በስሩ ላይ ባለው ቁስል የተነሳ በአፈር ውስጥ ይቆይና ዘሮቹ ማሳው እርጥበት ተክሎች ስር የሚገኘው መሬት በጥቁር ርጋፊ ቀጫጫ ቁመናና ውይብ መልክ ይኖረዋል፡፡ ይህ ሲያገኝ ይበተናሉ፡፡ ቅጠሎች ምንጣፍ የተሸፈነ ነው፡፡ በሽታ በስር፣ በተክሎችና የተከላ ቁርጥራጮች ላይ በመስክና በማስቀመጫ ቦታ ጉዳት ሊያስከትል ስርጭት: ሻጋታው በአፈር፣ በተክሎች ቅሪተ- ይችላል፡፡ አካላት ውስጥ እና በአካለ-ሻጋታ (mycelium and conidia) ይቆይና በዝናብ፣ በመስኖ ውሀ፣ በንፋስ፣ ስርጭት: ሻጋታው በአፈርና በሰብሎች ቅሪተ-አካላት በነፍሳት አማካይነት ይሰራጫል፡፡ ከፍተኛ የሆነ ውስጥ ይቆያል፡፡ መቁሰል የመበከል እድልን አንጻራዊ ወበቅ/እርጥበት አዘል የአየር ጸባይ ያሰፋል፣ የተበከሉ ስሮች የተበከለ ችግኝ ይሰጣሉ፡፡ ለወረራና ዘር ለመፍጠር ያግዛቸዋል፡፡ የአልተርናሪያ ቅጠል አንጥብ ምልክቶች ባረጁ ቅጠሎች የፎሞፕሲስ ምልክት ብላክ ሮት (ሴራቶሲይስት ዝርያ) ምልክቶች በስር ላይ በቅጠል ተሸካሚና በግንድ ላይ ጥቁር ቁስል የፎሞፕሲስ አዳዲስ ምልክቶች የብላክ ሮት ምልክት በስር ላይ ቁጥጥር: ሰብል ፈረቃ፣ ምርት ከተሰበሰበ በኋላ ቁጥጥር: ሰብል ፈረቃ፣ የማሳ ንጽህናን ቁጥጥር: ሰብልን ማፈራረቅ፣ ንጹህ ዘር መጠቀም፣ የቀረውን የሰብል ቅሪት ማስወገድና ማቃጠል፣ መጠበቅ ውጤታማ መሆን አለበት ምከንያቱም ብዙ ጊዜ ለማስቀመጥ ካሰብን በጥንቃቄ ስሮቹን ንጹህ ዘር መጠቀም፣ የርጭት የመስኖ ዘዴ ሻጋታው በማሳ ውስጥ በሚተዉ ዕጽዋት መምረጥ፣ በማስቀመጫው ውስጥ አይጦችና ነፍሳት ያለመጠቀም፣ በሽታ የሚቋቋሙ ዝርያዎችን ቅሪተ-አካል ውስጥ ስለሚቆይ ነው፡፡ እንዳይገቡ መቆጣጠር፣ በሽታ የሚቋቋሙ መትከል፣ ጸረ-ተባይ መድኃኒቶችን እንደ ዝርያዎችን መትከል፣ ቁርጥራጮችን እንደ ቤኖሚል ማንኮዜብ፣ ክሎሮታሎኒለ እና ዳይሪን መጠቀም ወይም ቲቤንዳዞል በመሳሰሉ ጸረ-ሻጋታ መድኃኒቶች ውጤታማ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ መዘፍዘፍ ወይም ስሮቹን ከማከማቸት በፊት በጸረ- አስቀድመን ማጥናት ያስፈጋል፡፡ ነፍሳት መድሓኒት መርጨት ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 35 7.5 ፍልፈልን መለየትና መቆጣጠር ከነፍሳት ተባይና በሽታ በተጨማሪ አንዳንድ የጀርባ አጥንት ያላቸው እንደ ፍልፈል፣ አይጥ፣ ጃርት፣ ፍየል፣ ጅግራ፣ ዝንጀሮ፣ ጦጣ፣ ከብቶች፣ ዝሆን ያሉ አደገኛ ስኳር ድንችን የሚያጠቁ እንስሳት አሉ፡፡ የቁጥቋጦ ወይም የእሾህ አጥር የስኳር ድንች ማሳን ከአሳማ፣ ከጃርት፣ ከከብቶች፣ ከፍየሎች ሊከላከል ይችላል፡፡ የቤት እንስሳት በደረቅ ወቅት ነባር ማሳዎችን፣ የስኳር ድንች ዘር ማቆያዎችን እና ማባዣዎችን እንዳይረግጡ መታሰር አለባቸው፡፡ ፍልፈሎች ስኳር ድንች የተተከለበትን መደብ ወይም ጉብታ ሰርስረው በመግባት የስኳር ድንችን ስሮች ይመገባሉ፡፡ ከሚበሉት ይልቅ ብዙዎችን በመነካካት ያበላሻሉ፡፡ በስኳር ድንች ማሳ ውስጥ አዲስ ተቆፍሮ የተቆለለ አፈር ሲገኝ፣ የስኳር ድንች ሀረጎች ተጎትተው ወደ አፈር ውስጥ ሲገቡ ሲታይ፣ በስኳር ድንች መደብ ወይም ጉብታ አጠገብ ጉድጓዶች ሲታዩ የፍልፈሎች መኖርንና ያስከተሉትን ጉዳት ያሳያል፡፡ አርሶ አደሮች ከጎረቤቶቻቸው ጋር ተባብረው ከሰሩ እንደ ፍልፈል ያሉ ዘረ- አይጥ ተባዮችን የመቆጣጠሩ ሂደት የተሻለ ይሆናል፡፡ ያንን ፍልፈል እንዲቆም አድርግ! አርሶ አደሮች ከዚህ የሚከተሉትን ተግባራት በመፈጸም ዘረ-አይጥ ተባዮች በስኳር ድንች ሰብል ላይ የሚያስከትሉትን ጉዳት መቀነስ ይችላሉ: -  የዘረ-አይጥ ዋሻዎችን ማጥፋት፤  በማሳ ዙሪያ ያሉትን ዕጽዋቶችንና ቆሻሻዎችን ማጽዳት የዘረ-አይጥ ቁጥር እንዲቀንስ ይረዳል፤  በማሳ ዙሪያ ጠለቅ ያለ ቦይ መቆፈር ዘረ-አይጥ ተባዮች ወደ ማሳ የሚያስገባ የውስጥ ለውስጥ መንገድ በቀጥታ እንዳይቆፍሩ ያግዳቸዋል፤  አንዳንድ የማባረሪያ ቁሳቁሶች በዘረ-አይጥ መተላለፊያ ጉድጓዶች ውስጥ ማድረግ፤ የአንዳንድ ዕጽዋት ቅጠሎች አባራሪ ባሕሪ አላቸው፣ የበርበሬ ቃሪያና የከብት ኩበት ወይም የሰው እዳሪ አንድ ላይ አድርጎ ዘረ-አይጥ ጉድጓድ ውስጥ ማቃጠል፤  አንዳንድ መርዛማነትና ጠለቅ ያለ ስር ያላቸውን እንደ ድግጣ (Tephrosia vogelli ) ያሉ ቁጥቋጦዎችን መትከል እንደ አባራሪ ተክል ሊጠቅም ይችላል፤ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 36  የሰሊጥ ስሮች ለዘረ-አይጥ መርዝ ናቸው ተብሎ ስለሚታሰብና ዘረ-አይጦች ስሮቹን አልፈው ስለማይቆፍሩ በስኳር ድንች ማሳ ዙሪያ ሰሊጥ መዝራት፤  የፈላ ውኃ ጉድጓዳቸው ውስጥ በመጨመር ዘረ-አይጦችን ማቃጠል ወይም የሚያቃጥል ሚጥሚጣ ዱቄትና የፈላ ውሃ ቀላቅሎ በጉድጓዳቸው ውስጥ መጨመር፤  ህጻናት በማይደርሱባቸው ቦታዎች ወጥመድ ማስቀመጥ፤  መመረዝ፤ መርዞች አንዳንድ ጊዜ በዘረ-አይጥ ጉድጓዶች ውስጥ ይጨመራሉ ያለበለዚያም የስኳር ድንች ስርን መርዞ እንደመሳቢያ መጠቀም ይቻላል፡፡ ቢሆንም ዘረ-አይጥ አጥቢዎች ስለሆኑ እነሱን የሚጎዳ መርዝ ሁሉ ሰዉንና ሌሎች እንስሳትን ሊጎዳ ስለሚችል አብዛኛውን ጊዜ ህጻናትና እንስሳት መሳቢያውን እንዳይበሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ካልተደረገበት በስተቀር ጥቅም ላይ እንዲውሉ አይመከሩም፡፡ 7.6 ሸረሪት የመሳሰሉ ነፍሳትን መለየትና መቆጣጠር የነጭ ጨርቅ ንብርብር በመሳሰሉ ድሮች የስኳር ድንች ቅጠሎችና ግንዶች የሚሸፈኑት በሸረሪት መሰል ነፍሳት ተባዮች የመጠቃት ምልክት ነው፡፡ እነኝህ ነገሮች አልፎ አልፎ ጉዳት ያስከትላሉ፡፡ በአጠቃላይ በእነዚህ ተባዮች ጥቃት ምክንያት ቅጠሎችና ተክሎች ቀለል ያለ የመቀጨጭ ወይም ቅጠሎችና ሀረጎች የመወፈር ምልክት የሚያሳዩ ሲሆን ሰብሉም ደካማ ምርት ይሰጣል፡፡ አልፎ አልፎ ጠቅላላው ሰብል ቢጎዳም የጥቃቱ ምልክት በአንድ ወይም በተወሰኑ ተክሎች በተለይም በተወሰኑ ዝርያዎች ላይ ይታያል፡፡ ሸረሪት መሰል ተባዮች እንቡጥና ጨቅላ ቅጠሎችን ሲመገቡ የዕድገት ሆርሞኖችን በተክሉ ሰውነት ውስጥ ይረጫሉ፡፡ ተክሉም ጥቅጥቅ ያለ የጸጉር ንጣፍ በማብቀል ለተባዮቹ መከላከያ ይሆናል፡፡ ጉልምሱ የአቧራ ነቁጥ ይመስላል፡፡ ሰብሉንም የሚወሩት እንደ በቀኝ በኩል ያለው ስዕል የሸረሪት መሰል ተባይ ዋነኛ አቧራ በንፋስ ኃይል በመብነን ነው፡፡ ስለእነዚህ ተባዮችና ምልክት(ነጫጭ ጸጉሮችና ወፈር ያለ ሀረግ) በስተግራ ያለው ቅጠል ያለተጠቃና ከተመሳሳይ ዝርያ የተወሰደ የመቆጣጠሪያ መንገዳቸው ብዙም አይታወቅም፡፡ ይሁን እንጂ የ‹‹ፓትሪክ ማኮካ የስዎንጎ›› ማቀነባበሪያ ካምፓኒ በኬኒያ የሚከተሉትን የመቆጣጠሪያ መንገዶች አፍልቆ ስራ ላይ እንዲውሉ አድርጓል፡- 1. ማሳን አዘውትሮ መጎብኘት፣ ጸጉራማ እንቡጦችን መፈለግ፣ የመጀመሪያው የጥቃት ምልክት የሚታይበትን መለየት፡፡ ምልክት የታየበትን ሀረግ ጫፍ መቁረጥና ማቃጠል ያልተጠቁ ቅርንጫፎች እንዲወጡ ያግዛል፡፡ 2. የምልክቱ መታየት የሚደጋገም ከሆነ መከርከምን ከጸረ-ሸረሪት መድሀኒት ጋር አቀናጅቶ መጠቀም አዳዲስ ያልተጠቁ ቅርንጫፎች እንዲወጡ ያደርጋል፡፡ በሰብሎች ላይ ጸጉራማነትን የሚያስከትል ሸረሪት መሰል ተባይ በአጉሊ መነጽር ሲታይ 3. የተጠቁ የሀረግ ጫፎችን እስከ 30 ሳ.ሜ ጥልቀት ድረስ በአፈር ውስጥ ከ4-5 ቀናት መቅበር ተባዩ ሙሉ በሙሉ እንዲሞት ያደርጋል፡፡ ከዚያም ቁርጥራጮቹ ይተከሉና ጤናማ ሆነው ያድጋሉ፡፡ 4. ሌላው አርሶ አደር በምዕራብ ኬንያ እንዳሳወቀው የተጠቃውን ሀረግ መቁረጥና ቅጠሎቹ ሙሉ በሙሉ እስኪረግፉ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ በጥላ ስር አቆይቶ መትከል ተባዩን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 37 7.7 የጎተራ ተባዮችን መለየትና መቆጣጠር ተባዮችና በሽታዎች ከመስክ አልፈው በድህረ-ምርትም ጊዜ ስኳር ድንችን ያጠቃሉ፡፡ የደረቀውንም ሆነ አዲስ የተሰበሰበውን የስኳር ድንች ምርት በማከማቻ ውስጥ እንዳያጠቁና ምርት ቅነሳ እንዳያስከትሉ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ የሚወሰዱት እርምጃዎችም የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ:-  ለጎተራ ያዘጋጀነው ምርት በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘቱን ማረጋገጥ (ለምሳሌ ለደረቁ ምርቶች በትክክል መድረቃቸውን፣ አዲስ ለተሰበሰቡ ወይም ለደረቁ ምርቶች በተባይና በበሽታ ያለመጠቃታቸውን ማረጋገጥ)፤  ማከማቻ ቁሳቁሱ በጥሩ ደረጃ ላይ መገኘቱን ማረጋገጥ (ለማከማቻ የምንጠቀመው ቁሳቁስ ምርቱን በአግባቡ ማስቀመጥ መቻል አለበት፡፡ በአንጻራዊ መልኩ ቀዝቃዛ፣ ከዘረ-አይጥ ተባዮች ነጻ የሆነ[ዘረ-አይጦች እንዳይገቡ ለመከላከል ከመሬት 1ሜ ከፍ ማለት አለበት፣ የአይጥ መከላከያ በእግሩ ላይ የተደረገ መሆን አለበት፣ ምንም አይነት የተንጠለጠለ ቅርንጫፍ የሌለው መሆን አለበት]፣ ወፎች፣ የቤት እንስሳት እና ሌቦች የማይደርሱበት፤ ከውሃ ጉዳት ነጻ የሆነ (ቢቻል ከጣራ ስር እንዲሆንና ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ያልሆነበት ቦታ መሆን ይገባዋል)፤  የማከማቻ ስፍራውን ማጽዳት (በማከማቻ አካባቢ ባሉ ቦታዎች በሚገኙ የወዳደቁ ነገሮች ውስጥ ተባዮች ሊራቡ ስለሚችሉ ንጽህናው በደንብ መጠበቅ አለበት)፤ ከባለፈው ዓመት ሊተላለፉ የሚችሉ ተባዮችን ለማስወገድ ማንኛውም የሰብል ቅሪት መወገድ አለበት፤ የማከማቻ ቁሳቁሱም በደንብ መጽዳት ይገባዋል [ጆኒያዎችን ከውስጥ ወደ ውጭ መገልበጥ፣ በፈላ ውኃ ውስጥ መንከርና እንዲደርቁ ማስጣት፣ በጭቃ የተሰራ ማከማቻ ከሆነ የትኛውም ተባይ ወይም የሻጋታ ዘር በግድግዳ ስንጥቅ ውስጥ ተሸሽጎ ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግ በየዓመቱ ግድግዳው መለቅለቅ አለበት)፣ አንዳንድ ጊዜ እንደ ትልቁ ዘር ቦርቧሪ አይነት ተባይ እንጨት ቦርቡሮ ስለሚሸሸግ ምናልባት ማከማቻው የተሰራበት እንጨት ውስጥ ገብቶ ከተገኘ እንጨቱ መወገድና መቃጠል አለበት]፤  በማከማቻው ውስጥ የተቀመጠውን ምርትም ሆነ ማከማቻውን ለማንኛውም የነፍሳት ተባይ ጥቃት ክስተት ቁጥጥር ያመች ዘንድ ዘወትር መጎብኘት (ለምሳሌ ትናንሽ የመመገቢያ ቀዳዳዎች በተከማቸው ነገር ላይ መታየት፣ አቧራ፣ ተባዮች በአካል መገኘት፣ ያልተለመደ ሽታ የመሳሰሉትን ማየትና ተገቢ እርምጃ መውሰድ) ፤ የደረቀውን የስኳር ድንች ስር የሚያጠቁ ዋና ዋና ተባዮች የካሳቫን ድርቆሽ ከሚያጠቁት ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የብዙዎቹ የጎተራ ተባዮች የጉልምስ የዕድገት ደረጃ ከዚህ ቀጥሎ በስዕል 7.6 ላይ ተመልክቷል፡፡ ስዕል 7.6 ስኳር ድንችን የሚያጠቁ የጎተራ ተባዮች (ከላይ በስተግራ: ታላቁ እህል ቦርቧሪ (ፕሮሰትፐሃኑሰ ትራነካተስ) ፣ ትንሹ እህል ቦርቧሪ (ራይዞተርታ ዶሚኒካ) ፣ ቀዩ የዱቄት ጥንዚዛ (ትሪቦሊየም ካስታነም) ፣ የበቆሎ ነቀዝ (ሲቶፍለስ ዚያማይስ)፣ የትምባሆ ጥንዚዛ (ላሲዮ ደርማ ስሪኮርኔ)፣ የቡና ፍሬ ጥንዚዛ (አዲኖደረስ ሚኑተስ፣ ራሰሩስ ፋሲኩላተስ) የጎተራ ተባዮች ባጠቃላይ ትናንሽ ሲሆኑ መጠናቸውም ከ1ሴሜ ያንሳል፡፡ ጉልምሶቹ አብዛኛውን ጊዜ በእህሉ ላይ ቀዳዳ ፈጥረው ዕንቁላላቸውን ይጥላሉ፡፡ ትሉ እየተመገበ ሲያድግ በእህሉ ላይ የመመገቢያ ቀዳዳ/ዋሻና አቧራ በመፍጠር የጥራትም የመጠንም ቅነሳ/ኪሳራ ያስከትላል፡፡ ትሉ በእህሉ ውስጥ እንዳለ ወደ ዕጭ/ፑፓ ይቀየርና ዕጩ/ፑፓው ደግሞ ጉልምስ ይሆናል፡፡ ጉልምሱ ደርሶ ግንኙነት ይፈጥርና እንቁላል ይጥላል፡፡ በዚህ ሂደት መጪው የህይወት ዑደቱ ይቀጥላል፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 38 በጥምር ሊተገበሩ የሚችሉ የደረቁ የስኳር ድንች ምርቶችን በማከማቻ/ማቆያ ውስጥ የሚያጠቁ የተለያዩ ተባዮች መቆጣጠሪያ ተግባራት፡- በጸሐይ ማድረቅ: በሻጋታ የመበስበስን ክስተት ለመከላከል ምርቱ በተገቢው ሁኔታ መድረቅ አለበት፡፡ የደረቁ ምርቶችን ተባይ ያጠቃ እንደሆነ ምርቱን በስሱ በሰሌን ወይም በላስቲክ አድርጎ በጸሐይ ላይ ለተወሰኑ ሰዓታት ማድረቅ የተባዩ እንቁላሎች፣ ትልና ዕጩ/ ፑፓው እንዲሞቱ ያደርጋል፡፡ በተደጋጋሚ ማድረቁ ምርቱ በሚገባ እንዲደርቅ ስለሚያደርግ አርሶ አደሩ በቀላሉ ማንኛውንም የተባይም ሆነ የበሽታ ጥቃት መከላከል ያስችለዋል፡፡ መቀቀል: አዲስ ተቆፍሮ የወጣውን የስኳር ድንች ስር ልጦና ሰነጣጥቆ ለአምስት ደቂቃ ወይም ከዚያ በላይ ጊዜ በእኩል ደረጃ መቀቀልና በጸሐይ ማድረቅ በደረቀ የስኳር ድንች ድርቆሽ ላይ አዲስ ጥቃት የመከሰት እድልንና የተከሰተውም እድገቱ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ እንደአማራጭ አዲስ ተቆፍሮ የወጣውን ስር ከመላጣችን፣ ከመቆራረጣችንና ከማድረቃችን በፊት ከ30-60 ደቂቃዎች መቀቀል የስኳር ደንች ስሮችን ከማከማቻ ውስጥ ተባይ ጥቃት ለመከላከል ያስችላል፡፡ በጨው ማጀል: በተቆራረጡ የስኳር ድንች ስሮች ላይ ከማድረቃችን በፊት ከ20-30 ግራም ጨው በኪሎግራም ማድረግ በተባዮች እድገትና በሚያደርሱት ጉዳት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡ ማንከባለልና መወዝወዝ: በየወቅቱ ምርቱን የያዘውን ጆንያ ማንከባለል ወይም ማወዛወዝ እየተፈጠረ ያለውን ትል ስለሚገድል ሊፈጠር የሚችለውን የጉልምስ ቁጥርና ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት ይቀንሳል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ድርጊት የተወሰኑ የደረቁ የስኳር ድንች ስሮችን ይሰባብራቸዋል፡፡ ባህላዊ መከላከያዎች፡ አመድና አንዳንድ የዕጽዋት አካላትን ከደረቀ የስኳር ድንች ስር ጋር ቀላቅሎ ማስቀመጥ ተባዮችን በማባረር ጉዳቱ እንዲቀንስ ወይም ተባዩ እንዲሞት ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ የተባይ ጥቃትን ለመከላከል የእንደዚህ ዓይነት ባሕላዊ መቆጣጠሪያዎች በብዛት ይጨመራሉና ለምግብነት ለማዋል ሲፈለግ ከድርቆሹ መለየት አለባቸው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ጉልበት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንድ ዕጽዋት ለሰውም መርዘኛ ሊሆኑ ስለሚችሉ የትኛው ተክል ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ነፍሳት ተባይን የማያስገቡ መያዣዎች: ከማስቀመጫው ጊዜ በፊት እስካልተጠቁ ድረስ የስኳር ድንች ድርቆሽን ነፍሳት ተባዮችን በማያስገቡ እንደ ሸክላ ማሰሮ በመሳሰሉ ዕቃዎች ውስጥ አሽጎ ማስቀመጥ የተባይ ጥቃትን በሚገባ ይከላከላል፡፡ የማስቀመጫ ጊዜ ርዝመት: የማስቀመጫ ጊዜ ርዝመት የተባዮችን የመቆጣጠሪያ ተግባራትን ይወስናል፡፡ አብዛኞቹ ተባዮች ከእንቁላል እስከ ጉልምስ የዕድገት ደረጃ እስኪደርሱ የሚፈጀው ጊዜ ወደ አንድ ወር የሚጠጋ ነው፡፡ ምርቱ ለተወሰነ በጣም አጭር ጊዜያት ብቻ የሚቀመጥ ከሆነና አስቀድሞ በከፋ ሁኔታ በተባይ ካልተጠቃ የመጎዳቱ መጠን በመጀመሪያዎቹ የማስቀመጫ ጊዜያት በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ታላቁ እህል ቦርቧሪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት ስለሚያስከትል እንደታየ ወዲያውኑ የመቆጣጠሪያ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው፡፡ የዝርያ ልዩነት፡ በነፍሳት ተባዮች በቀላሉ በመጠቃትና ባለመጠቃት በስኳር ድንች ዝርያዎች መካከል ልዩነት ይታያል፡፡ አርሶ አደሮቹ አንዳንድ ዝርያዎች በማከማቻ ውስጥ በቀላሉ በተባይ የሚጠቁ መሆናቸውን የተገነዘቡ ከሆነ እነኝህ ዝርያዎች አስቀድመው ጥቅም ላይ ማዋል አለባቸው፡፡ ንጽህና: የአንዳንድ ተባዮች ትል በስኳር ድንች ዱቄት ውስጥ ተደብቆ ሊቆይ ይችላል፡፡ የስኳር ድንች ዱቄት በማከማቻው ዙሪያ ተበትኖ የሚገኝ ስለሆነ ለሚቀጥለው ወቅት እንደ መነሻ ጥቃት ሊያገለግል ይችላል፡፡ ስለዚህ የማከማቻ ቁሳቁሶችን በጥንቃቄ ማጽዳትና የባለፈው ዓመት/ወቅት ቅሪት ካለ አዲሱ ምርት ከመግባቱ በፊት ማስወገድ ተባዮቹ በቀጥታ ወደ አዲሱ ምርት ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱ ለመከላከል ይረዳል፡፡ አዲስ ከማሳ የተሰበሰበ ስኳር ድንች ለብዙ ወራት በጉድጓድ ወይም በመጠፈሪያ ውስጥ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ በማስቀመጫው መግባት የሚገባቸው ስሮች በምርት መሰብሰቢያ ጊዜ ወይም ሲጓጓዙ ያልተጎዱ እና በነፍሳት ተባይ ያልተነኩ ብቻ መሆን አለባቸው፡፡ የተከማቹት የስኳር ድንች ስሮች መበስበሳቸውን፣ በተባይ መበላታቸውን ወይም በዘረ-አይጥ መነካታቸውን ለማረጋገጥ ማስቀመጫው ዘወትር መጎብኘትና መፈተሽ አለበት፡፡ ምንም ዓይነት ምልክት ቢታይ ተጨማሪ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ማስቀመጫውን ባዶ ማድረግ፣ የተበላሹትን ማስወገድ፣ ጤናማ የሆኑትን መጠቀም ወይም መሸጥ ያስፈልጋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ምንም ዓይነት ምልክት ካልታየ ማከማቻውን እንደገና በጥንቃቄ ማሸግና ለጥላ የተሰራውንም ጣሪያ በቦታው መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ስለ አዲስ ከማሳ ተሰብስቦ ለሚቀመጥ የስኳር ድንች ስር ማከማቻ የሚገልጽ ተጨማሪ መረጃ በርዕስ 8 ላይ ተገልጧል፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 39 7.8 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር የሥርዓተ-ጾታና ብዝሀነት ጉዳዮች በዚህ የስልጠና መምሪያ በርዕስ 11 ላይ ስኳር ድንችን በተመለከተ የሥርዓተ-ጾታና ብዝሃነት ጉዳይ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ ቁልፍ ለስኳር ድንች ተባይና በሽታ ቁጥጥር የሚጠቅሙ የሥርዓተ-ጾታና ብዝሃነት ጉዳዮች በአጭሩ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡ የተለያዩ ሰዎች ስለ ነፍሳት ተባዮችና በሽታዎች ቁጥጥር የተለያየ አረዳድ፣ ክህሎትና ልምድ አላቸው፡፡ መረጃ የሚያገኙበትም መንገድ እንዲሁ የተለያየ ነው፡፡ የመረጃ ምንጮቻቸው አያቶችን፣ ወላጆችን፣ ጎረቤቶችን፣ የልማት ሰራተኞችን፣ ነጋዴዎችን እንዲሁም ትምህርት ቤቶችንና ቁሳቁሶችን ያጠቃልላሉ፡፡ የልማት ሠራተኞች ማን በስኳር ድንች ማምረት፣ ማከማቸት/ማስቀመጥና ማቀነባበር ሂደት እንደሚሳተፍ ለይተው ቢረዱ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ ልምዳቸውና እውቀታቸው ላይ ተጽዕኖ ስለሚያደርግና በስልጠናው ማን እንዲሳተፍ መመረጥ እንደሚገባ ውሳኔ ለመስጠት ይረዳቸዋል፡፡ ሴቶች በስኳር ድንች ማሳ ክትትል፣ አረምና ምርት የመሰብሰብ ስራ ላይ የሚሳተፉ ከሆነ የስኳር ድንችን ተባዮች ባሕሪያት በማሳ ላይ የመመልከት ወይም የበሽታዎችን ስርጭት ሂደት የመገንዘብና የተለያዩ የተባይ መቆጣጠሪያ ተግባራትን የመፈተሽ ከፍተኛ የሆነ ልምድ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ወንዶችም የተባይና በሽታ መቆጣጠሪያ ስልጠና ወስደው ከሆነ ተገቢ የሆነ የመቆጣጠሪያ ስልት ዕውቀት ይኖራቸዋል፡፡ ማን የትኛዎቹን ተግባራት እንደሚያከናውን፣ ዓይነተኛ የመረጃ ማግኛ/ማስተላለፊያ መንገዶች የትኞቹ እንደሆኑ፣ ምን ዓይነት የተባይና የበሽታ ግንዛቤ በማህበረሰቡ ውስጥ እንዳለና በአሁኑ ወቅት ያሉትን የመቆጣጠሪያ መንገዶችን ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ መረጃ የስልጠና ፕሮግራም ለማዘጋጀት፣ በሰብል ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር ስርዓት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትንና በማሳ ውስጥ ምን መደረግ እንደሚገባ ውሳኔ በሚሰጡት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ስልጠናውን እንዲሳተፉ ለመምረጥ ይጠቅማል፡፡ አብዛኛዎቹ አርሶ አደሮች ስለ ነፍሳት ተባዮች የህይወት ዑደት ወይም የበሽታዎች ስርጭት ግንዛቤ ስለሌላቸው ይህንን ልምድ በማካፈልና አርሶ አደሮች እንዲበቁ በማድረግ በተለያዩ ተግባራት ላይ የራሳቸውን ሙከራ እንዲሰሩ ማድረግ ይቻላል፡፡ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ሴቶች የመስኖ አገልግሎት አግኝተው ዘር ማቆየትና ማባዛት ስለማይችሉ ዘግይተው ይተክላሉ፣ በበሽታ የተበከሉ ቁርጥራጮችን ይጠቀማሉ፣ አነስተኛ ምርት ያገኛሉ፣ ዘግይተው ምርት ይሰበስባሉ እና ለከፍተኛ የነቀዝ ወረራም ይጋለጣሉ፡፡ እነኝህ ሴቶችና ባሎቻቸው ንጹህ የተከላ ቁርጥራጮችን በመጠቀም ሙከራ እንዲያደርጉ መርዳትና ንጹህ ዘር በመጠቀም ምርታቸውን እንዴት ማሳደግና ጥራት ያለው ምርት ማግኘት እንደሚችሉ በማሳየት በቤተሰብ ደረጃ ሊከሰት የሚችለውን ኪሳራ እንዲቀንስ ማድረግ ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ የሚያጠቡና ነፍሰጡር የሆኑ ሴቶች፣ ህጻናት እና በቤት ውስጥ ምግብ የሚያዘጋጁ ሰዎች ጸረ-ተባይ መድኃኒት መርጨት የለባቸውም፡፡ ጸረ-ተባይ መድሀኒቶች መርዘኛ ስለሆኑ ከህጻናት መራቅ አለባቸው፡፡ ህጻናት ከሌላው ይልቅ በጸረ-ተባይ መድሀኒቶች ለሚከሰቱ የጤንነት ችግሮች ተጋላጮች ናቸው፡፡ ምክንያቱም፡- ውስጣዊ አካላቸው በዕድገት ላይ መገኘቱ፤ ከሰውነታቸው ክብደት አንጻር ከአዋቂዎች ይልቅ ብዙ ስለሚመገቡ፣ ስለሚጠጡና ስለሚተነፍሱ በውሃ፣ በምግብና በአየር አማካይነት ለጸረ-ተባይ መድኃኒቶች ጥቃት የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ ስለሆነ፤ አንዳንድ ባሕሪያት – ለምሳሌ በመሬት ላይ መጫወትና አንዳንድ ነገሮችን አፋቸው ውስጥ መክተት የሚያዘወትሩ በመሆኑ ለጸረ- ተባይ መድኃኒቶች ጥቃት የመጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑ፤ በማህጸን ውስጥ ሳሉ ወይም በሌላ ወሳኝ ወቅት ለጸረ-ተባይ መድኃኒቶች ጥቃት የተጋለጡ ህጻናት እንደ የወሊድ እንከን፣ የነርቭ እድገት ማዝገም፣ የጨቅላነት ጊዜ ጭንቅላት ካንሰር፣ ዘገምተኝነት፣ ትኩረት ያለመስጠት/እረፍት የለሽነት እና የሆርሞን/ዝግ ዕጢዎች መበጥበጥ ያሉ ከፍተኛ የጤና ችግሮች ይደርስባቸዋል፡፡ ጸረ-ተባይ መድኃኒቶች በምግብ ቤትና ከምግብ ጋር የሚቀመጡ ከሆነ ህጻናት ወይም አዋቂዎች በድንገት ሊመገቧቸው ስለሚችሉ መድሃኒቶቹን የያዙ እቃዎችን ስናስቀምጥ በጣም ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 40 7.9 የስኳር ድንች ተባዮችንና በሽታዎችን የመቆጣጠሪያ መንገዶችን እየተገበሩ የመማር ሀሳብ ይህ የ10 ቀን በመስራት-መማር የአሰልጣኞች ስልጠና የታለመው ተሳታፊዎች ስለ ስኳር ድንች ማወቅ የሚገባቸውን ማንኛውንም ነገር በተግባር እንዲገነዘቡ ለማድረግ ነው፡፡ "እጅን-በስራ ላይ" ስልትን በመጠቀም በተግባር በመማር ሰልጣኞቹ ሌሎችንም በተግባር እያሳዩ ያሰለጥናሉ የሚል እምነት አለ፡፡ ሙሉ የአሥር ቀን የአሰልጣኞች ስልጠና ትምህርት መርሀ-ግብር በርዕስ 13 ላይ ተተንትኗል፡፡ የሚከተሉት ተግባራት በስልጠናው አምስተኛ ቀን የሚከናወኑ ሲሆን ለግንዛቤ ያክል ለጊዜው መርሃ-ግብሩ በሚቀጥለው ሰንጠረዥ እንደተመለከተው ይሆናል፡፡ቢሆንም እነኚህ ተግባራት እንደ ብቸኛ የመማማሪያ ተግባራት የሚወሰዱና በሌሎችም የስልጠና ጊዜያት በጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሎ ዕምነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ዕለት ርዕስ ከስልጠናው ሊገኝ የሚችል ውጤት ዝርዝር ተግባራት 5 የስኳር ድንች ተሳታፊዎች: - ተግባር 7.9.1: የስኳር ድንች ተባዮችንና በሽታዎችን ተባዮች፣ በሽታዎች - የስኳር ድንች ቁልፍ ተባዮችና በመስክ ላይ ማደንና እንዴት መቆጣጠር እና የመቆጣጠሪያ በሽታዎችን ናሙና መስክ ላይ እንደሚቻል መማር፤ የተጠቁ ስሮችን፣ የተጎዱና መንገዶች፤ ያገኛሉ፤ የሚያስከትሏቸውን የታመሙ ቅጠሎችን መሰብሰብ፣ በመስክ ላይ ጉዳቶች ይገልጻሉ፤ ያሳያሉ፣ የተባዮችን የተወሰነ እንቅስቃሴ በትኩረት መመልከት፣ እነኝህ ተባዮችና በሽታዎች ከየት - የእነኝህን ቁልፍ ተባዮችንና እንደመጡና እንዴት እንደሚሰራጩ በቡድን በሽታዎችን የመቆጣጠሪያ መወያየትና ሀሳብ ማጋራት (ከተቻለ ነጫጭ የተለያዩ ዘዴዎችን ያውቃሉ፤ ዝንቦችን ጨምሮ)፡፡ በውይይቱ ወቅት የአፈር ማሳቀፍና የስኳር ድንች ቫይረስ በሽታዎችን የመንቀስ ተግባራትን ማካተት (7.9.1ን ተመልከቱ) [85 ደቂቃ]፤ - ገለጻ 7ሀ. ቁልፍ የስኳር ድንች ነፍሳት ተባዮችና በሽታዎች የህይወት ዑደት [30 ደቂቃ]፤ - ተግባር 7.9.2: ድብቅ ጉዳት፤ የተጠቃውን የስኳር ድንች ስር ለሁለት መክፈልና የተለያዩ የስኳር ድንች ነቀዝ የዕድገት ደረጃዎችን ለማየትና ለመለየት መሞከር፣ ምን ያህሉ እንደተጎዳ መቀመር [ማስታወሻ: ከስልጠናው አስቀድሞ አመቻቹ የተወሰኑ የተጠቁ ስሮችን ማዘጋጀት አለበት] (7.9.2ን ይመልከቱ) [1 ሠዓት]፤ - ገለጻ 7ለ. የስኳር ድንች ተባዮችንና በሽታዎችን የመቆጣጠሪያ ተግባራት (ፍልፈልን ጨምሮ) እና ውይይት [45 ደቂቃ]፤ - ተግባር 7.9.3: በስኳር ድንች ቁልፍ ተባዮችና በሽታዎች ላይ ለሌሎች ስልጠና መስጠት፤ በዋና ዋና የስኳር ድንች ተባዮችና በሽታዎች ላይ በቂ ገለጻና ተግባራትን ማዘጋጀት (7.9.3ን ይመልከቱ) [1 ሠዓት ከ 45 ደቂቃ]፤ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 41 7.9.1 የስኳር ድንች ተባዮችንና በሽታዎችን በመስክ ላይ ማደንና እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል መማር ከስልጠናው የሚጠበቅ ውጤት፤ ተሳታፊዎች፡- የመስክ ተምሳሌት የሆኑ ቁልፍ ተባዮችና በሽታዎችን መለየት ይችላሉ፤ ያብራራሉ፤ የሚያስከትሏቸውንም ጉዳቶች ያሳያሉ፤ ጊዜ: 85 ደቂቃ ሲደመር የመጓጓዣ ሰዓት፤ የሚያስፈልጉ ነገሮች/ቁሳቁሶች:  የስኳር ድንች ቫይረስ በሽታ ያለበት አዲስ ማሳ፣ ከዚህ ቀደም ብሎ ስኳር ድንች ተመርቶ የነበረበት ማሳ እና ተሳታፊዎች ዞረው ሊያዩ የሚችሉበት በስኳር ድንች ተባይና በሽታ የተጠቃ የደረሰ ወይም ያረጀ ማሳ፤  20 መቆፈሪያ እንጨቶች፤  የተጠቁ ስሮችን ለመያዝ 8 ባልዲዎች፤  8 ጆንያዎች፣ 20 ክዳን ያላቸውና በየክዳኖቻቸው ላይ ትንንሽ ቀዳዳዎች ያሉባቸው ብርሃን አስተላላፊ ጠርሙሶች/መያዣዎች፤  20 የእጅ የማጉያ ሌንሶች፤  ተሳታፊዎች የማስታወሻ ደብተሮቻቸውንና እርሳሶቻቸውን፣ ተገላላጭ ቻርት/ፍሊፕ ቻርትና መቆሚያ፣ ማርከሮች፣ ማጣበቂያዎች፤ ቅድመ ዝግጅት፡ የስኳር ድንች ቫይረስ በሽታ ያለበት አዲስ ማሳ፣ ከዚህ ቀደም ብሎ ስኳር ድንች ተመርቶ የነበረበት ማሳ እና ተሳታፊዎች ዞረው ሊያዩ የሚችሉበት በስኳር ድንች ተባይና በሽታ የተጠቃ የደረሰ ወይም ያረጀ ማሳ ማግኘት፤ የድርጊት ቅደም ተከተል: 1. ተሳታፊዎችን 6 ሰዎች በሚገኙበት ትናንሽ ቡድኖች መክፈል፣ የተባይና የበሽታ ችግሮችን ለመለየት በአቅራቢያቸው ወደሚገኘው የስኳር ድንች ማሳ እንደሚጓዙ ማብራራት፡፡ እነኝህ ተባዮችና በሽታዎች ስሮችን፣ ሀረጎችንና ቅጠሎችን ወይም በጠቅላላው ተክሉን ሊጎዱ እንደሚችሉ ማብራራት፡፡ በስኳር ድንች ሰብል ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩትን ነፍሳት ተባዮችን ወይም ሌሎች ተባዮችን ማግኘትና ሰብስበው ለማሳየት በብልቃጥ ውስጥ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ [5 ደቂቃ] ፤ 2. ጉዞ ወደ ስኳር ድንች ማሳ፤ 3. የተባይና በሽታ አደን  ለእያንዳንዱ ቡድን ጥንድ መቆፈሪያ እንጨትና ናሙና መሰብሰቢያ ብልቃጦችን፣ ባልዲና ጆንያ/ከረጢት መስጠት፤  እያንዳንዱ ቡድን በተቻለ መጠን ሁሉንም ስፍራ እንዲሸፍን መጠየቅ፤  ነፍሳት ተባዮችንና የተባይና በሽታ ጉዳት ምልክቶችን እንዲያድኑ 20 ደቂቃ መስጠት፤ የሚያድኗቸውን በመስክ ጉብኝት ውይይት ወቅት ለመጠቀም ናሙናዎችን መሰብሰብ እንደሚገባቸው ማሳወቅ፤  በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ ተባዮች ምን እንደሚያደርጉና እንዴት ጉዳት እንደሚያደርሱ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ ተሳታፊዎች ተባዮችን በቅርበት እንዲከታተሉ ማስታወስ፤  ቡድኖቹ እያደኑ እያሉ አመቻቹ እየተዟዟረ በቡድኖቹ መሀል በመገኘት እያንዳንዱ ቡድን የቫይረስ በሽታን፣ የተወሰኑ የክሽክሽና የነጫጭ ዝንቦችን እና ጥቂት በነቀዝ የተጎዱ ስሮችን እያዩ እንደሆነ ማረጋገጥ [20 ደቂቃ]፤ 4. በማሳው አጠገብ ወደሚገኘው የጥላ ዛፍ ስር ለውይይት እንዲሰበሰቡ መጥራት፡፡ እያንዳንዱን ቡድን ያመጧቸውን የተጠቁ ስሮች፣ ቅጠሎች፣ ወዘተ እና የመሰብሰቢያ ብልቃጦችን በየከረጢቶቻቸው እንዲያደርጉ መጠየቅ፣ ሁሉም ተሳታፊ ወደቡድኖቹ በመሄድ ትናንሽ ቡድኖቹ ስላዩትና ስለ ሰበሰቡት ነገሮች ሲናገሩ ማዳመጥ፣ አንዳንዶቹ ቡድኖች የሰበሰቡት ተመሳሳይ ከሆነ ጉብኝቱን ለማፋጠን የሚቀጥለው ቡድን የተለየ ነገር እንዳለው እንዲያብራራ በመጠየቅ እንቅስቃሴውን ማፋጠን [20 ደቂቃ] ፤ 5. ክፍትና ጠቋሚ ጥያቄዎችን በመጠቀም አመቻቹ ተሳታፊዎቹ ያዩትንና የሚያስቡትን እንዲያጋሩ እንደሚከተለው መጠየቅ አለበት:  ተባዩን ሲመለከቱ ምን እያደረገ እንደነበረ?  እንዴት ጉዳት እንደሚያስከትል?  በግምት ከየት እንደመጣ? ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 42  የስኳር ድንች ሰብል ባልነበረበት ወቅት እንዴት በህይወት እንደሚቆይ?  በሽታዎች እንዴት እንደሚሰራጩ? ከተሳታፊዎች አንዱን እንደ አጀንዳ ያዥ እንዲሆን በማድረግ በውይይቱ ወቅት የሚነሱትን አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በፍሊፕ ቻርት ላይ እንዲመዘግብ መጠየቅ፤ ወደ ማሰልጠኛው ክፍል ለመውሰድ የሰብሉን የተለያዩ ክፍሎችንና ነፍሳት ተባዮችን የያዘውን ብልቃጥ ወደ ከረጢቶቹ በመመለስ ማሰናዳት [20 ደቂቃ] ፤ 6. አመቻቹ ቡድኖችን ወደ ማሳው መልሶ በመውሰድ በስኳር ድንች ማሳቸው ላይ የተባይና የበሽታ ጥቃትን እንዴት እንደሚከላከሉ መጠየቅ፣ ጥቃቱ ቢከሰትና ወደ ጤናማው ተሰራጭቶ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከትል ምን እንደሚያደርጉ መጠየቅ፤ የንጹህ ዘር፣ በሽታ የሚቋቋሙ ዝርያዎች፣ ማሳ ጽዳት፣ የዘወትር ማሳ ጉብኝት፣ የተፈጥሮ ጠላቶች፣ አፈር ማስታቀፍ፣ አዘውትሮ መንቀስና በጊዜ ምርት መሰብሰብን ጠቀሜታ ላይ መወያያት፤ እያንዳንዱ ተሳታፊ የተወሰኑ የተጋለጡ ስሮችን አፈር የማሳቀፍና የተወሰኑ በቫይረስ በሽታ የተያዙ ተክሎችን መንቀስን መለማመድ አለበት [20 ደቂቃ] ፤ 7.9.2 ድብቅ ጉዳት: የነፍሳት ተባዮችን የህይወት ዑደት የመረዳት አስፈላጊነት ከስልጠናው የሚጠበቅ ውጤት፤ ተሳታፊዎች፡- የተለያዩ የስኳር ድንች ተባዮችን የዕድገት ደረጃና የትኛው የዕድገት ደረጃ የበለጠ ጉዳት እንደሚያደርስ ይረዳሉ፤ ጊዜ: 1 ሠዓት፤ የሚያስፈልጉ ነገሮች/ቁሳቁሶች:  ወደ 50 የሚጠጉ በስኳር ድንች ነቀዝ የተጠቁ ስሮች፤  20 መክተፊያዎች፤  20 የሰሉ ቢለዋዎች፤  20 የእጅ ማጉሊያ ሌንሶች፤  40 ሰሀኖች ወይም ከፕላስቲክ የተሰሩ ከረጢቶች፤  የተበላሸውን ከጤናማው ለይቶ ለመለካት/ለመመዘን የሚረዳ 1 ጥቅል ሚዛን፤  የተሳታፊዎች ማስታወሻ ደብተርና እርሳስ፤ ቅደመ ዝግጅት:  ከስልጠናው ሁለት ሳምንታት በፊት በስኳር ድንች ነቀዝ የተጠቁ ስሮችን መሰብሰብ፤  ተሳታፊዎች ምናልባት በአደን ወቅት የተወሰኑትን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ምናልባት ካላገኙ ተሳታፊዎች በመሰንጠቅ የዕንቁላሎችን፣ ትሎችንና ዕጮችን/ፑፓዎችን እንዲያውም የመመገቢያ ቀዳዳዎችን እንዲያዩ አመቻቾች የተወሰኑ የተጠቁ ስሮች እንዳሏቸው ማረጋገጥ፤  በስልጠናው ወቅት ከማሳ የሚሰበሰቡት ናሙናዎች/ተምሳሌቶች በቀላሉ የማይገኙ ከሆነ በሰው ሰራሽ መንገድ ተባዮቹን በስኳር ድንች ስሮች ውስጥ በላቦራቶሪ እንዲገቡ ማድረግን ሊጠይቅ ይችላል፤ የድርጊት ቅደም ተከተል: 1. የተጠቃ የስኳር ድንች ስርና ሀረግ ማየታቸውንና መሰብሰባቸውን ለተሳታፊዎች ማስታወስ፤ በጥንድ እንዲሰሩ ማድረግ፣ የሰበሰቡትን ስርና ሀረግ እንዲሰነጥቁና በውስጣቸው ያለውን የተለያዩ ነፍሳት ተባዮች የዕድገት ደረጃዎች እንዲፈልጉ/እንዲመለከቱ ማድረግ [ማስታወሻ: በተለያዩ የስኳር ድንች ተባዮችና በሽታዎች ላይ ትምህርታዊ መግለጫ ይሰጣሉ]፡፡ እያንዳንዱ ጥንድ ቢያንስ በ5 የተጠቁ ስሮች ላይ መስራት አለበት፡፡ ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት ያሉትን ስሮች አንድ በአንድ መመዘንና በማስታወሻ ደብተራቸው መጻፍ ይገባቸዋል፡፡ ከዚያም ስሮቹን በጥንቃቄ መሰንጠቅ፣ የተለያዩ ተባዮች የዕድገት ደረጃዎችን ለመመልከት በማጉያ ሌንሳቸው መፈተሽ አለባቸው፡፡ ያገኙትን የዕድገት ደረጃ በስዕል ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ የተሰነጠቁትን ስሮች በሁለት ወገን ማለትም የተጎዳውን በአንድ ወገን ያልተጎዳውን በሌላ ወገን ማስቀመጥ ይገባቸዋል፡፡ አመቻቹ በመዟዟር ጥንዶችን የስኳር ድንች ነቀዝ የዕንቁላል፣ ትል፣ ዕጭ/ፑፓና ጉልምስ የዕድገት ደረጃዎችን መለየትና የመመገቢያ ዋሻ/ቀዳዳ ማየታቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም የተበላሸውንና (ለምግብነት የማይውለውን) ያልተበላሸውን በመለየቱ ሂደት መርዳት አለበት [30 ደቂቃ]፤ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 43 2. መሰንጠቁ ሲገባደድ የተበላሸውን በሙሉ በአንድ ከረጢት ውስጥ ጨምረው መመዘንና መጠኑን መመዝገብ ይችላሉ፡፡ ላልተበላሸውም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይችላሉ፡፡ ከዚያም በተባይ አማካይነት የተበላሸው ካጠቃላዩ ክብደት በመቶኛ ምን ያክል እንደሆነ መቀመር አለባቸው[5 ደቂቃ]፤ 3. ከሙከራው ምን እንደተማሩ አመቻቹ ተሳታፊዎችን መጠየቅ አለበት፡፡ መጠየቅ የሚገባቸው፡-  የተለያዩ የነፍሳት ተባዮችን የዕድገት ደረጃዎች መረዳት ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ፤ የተለያዩ የዕድገት ደረጃዎች ምን እንደሚመስሉና አርሶ አደሮች ጉዳት የማያስከትል የሚመስለው ጉልምስ በአካባቢው መገኘት በትሉ ከተከሰተው ከፍተኛ ጉዳት ጋር ማያያዝ እንደሚችሉ መረዳታቸውን፤  እንዴት የተባዮችን ስርጭት መቀነስና የሚያስከትሉትም ጉዳት ውስን እንዲሆን ማድረግ እንደሚችሉ?  ምን ያህሉ የስኳር ድንች ምርት በስኳር ደንች ነቀዝ አማካይነት እንደሚጠፋ?  ጥቃቱ በስኳር ድንች ገበያ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንደሚፈጥር?  በነቀዝ የተጠቃውን ስር ከጤናማው ጋር አንድ ላይ ማስቀመጥ ምን እንደሚያስከትል? [20 ደቂቃ]፤ 4. ለስልጠና የተጠቀሙበትን ቁሳቁስና የስልጠና ቦታ ማጸዳዳት [5 ደቂቃ]፤ 7.9.3 በቁልፍ የስኳር ድንች ተባዮችና በሽታዎች ላይ ሌሎችን ማሰልጠን ከስልጠናው የሚጠበቅ ውጤት: ሰልጣኞች የማሳ ምልከታቸውን ተጠቅመው ሌሎችን (የልማት ሰራተኞችንና አርሶ አደሮችን) ስለ ስኳር ደንች ተባዮችና በሽታዎች ለማሰልጠን የስልጠና አቀራረብ እና የስልጠና ቁሳቁሶችን የማዘጋጀት ልምድ ይኖራቸዋል፡፡ ጊዜ: 1 ሠዓት ከ45 ደቂቃ የሚያስፈልጉ ነገሮች/ቁሳቁሶች: በዚያን ዕለት ጧት በተባይ አደን ወቅት የሰበሰቡት የስኳር ድንች ስሮች፣ ተባዮች፣ ተገላላጭ ቻርት/ፍሊፕ ቻርት፣ 40 ማርከር እስክሪብቶዎች፣ ማጣበቂያ ፕላስተሮች፣ ማጉያ ሌንሶች፣ የተሳታፊዎች ማስታወሻ ደብተሮችና እስክሪብቶዎች፤ የድርጊት ቅደም ተከተል: 1. ተሳታፊዎችን በትናንሽ ቡድኖች መከፋፈል (በቡድን 3 ሰው) እና ለእያንዳንዱ ቡድን የስኳር ድንች በሽታዎችንና ተባዮችን መደልደል (ለምሳሌ የስኳር ደንች ነቀዝ፣ የስኳር ድንች ቫይረስ፣ ፍልፈል፣ ሸካራ የስኳር ድንች ነቀዝ፣ ተምች ወዘተ.)፡፡ እያንዳንዱ ቡድን 20 ደቂቃ ወስዶ በስኳር ድንች ተባይ ወይም በሽታና በአርሶ አደሮቹ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በተመለከተ መግለጫ፣ ድራማ፣ ወይም ጭውውት እንደሚያዘጋጅና በ5 ደቂቃ ውስጥ አንደሚያቀርብ ማብራራት፡፡ ይህ የሚያዘጋጁት መግለጫ ለወደፊት ሌሎችን ለማሰልጠን እንደሚገለገሉበት ማስታወስ ያስፈልጋል [25 ደቂቃ]፤ 2. እያንዳንዱ ቡድን ያዘጋጀውን ማብራሪያ/መግለጫ ለሌሎች እንዲያጋራ መጠየቅ፣ እያንዳንዳቸው ቢበዛ አምስት ደቂቃ ብቻ እንዳላቸው ማስታወስ እና አንድ ሰው እንደ ሠዓት ተቆጣጣሪ አደርጎ መመደብ፡፡ ሌሎች ተሳታፊዎች የሚለጠፉ ትንንሽ ወረቀቶችን ይዘው ከማብራሪያው/መግለጫው ምን እንደወሰዱ፣ በአቀራረቡ ላይ ምን እንደጎደለና መሻሻል የሚገባቸውን ነገሮች ቶሎ ቶሎ እንዲጽፉ መጠየቅ (ለአንድ አቅራቢ አንድ የሚጣበቅ ወረቀት)፡፡ መግለጫውን ሲመለከቱ የነበሩ ሁሉ አስተያየታቸውን የያዙ ተጣባቂ ወረቀቶቻቸውን እንዲያኖሩ ለእያንዳንዱ ቡድን አንዳንድ የፍሊፕ ቻርት ገጽ ማዘጋጀት (ይህ ማለት ቡድኖቹ የተለጠፉትን ዞረው በማየት ሌሎቹ ቡድኖች እንዴት በተለየ ሁኔታ እንዳከናወኑ ሀሳብ ያገኛሉ ማለት ነው) [1 ሠዓት]፤ 3. አመቻቹ የቀረቡትን ነገሮች ተሳታፊዎች ምን ያህል እንደተረዱ የመገምገሚያ መንገድ አድርጎ ሊገለገልና ያገኙትን እውቀት ከሌሎች ጋር እንዴት መጋራት እንደሚገባቸው ማሰብ እንዲጀምሩ መርዳት ይችላል፡፡ በአቀራረብ ሂደት ላይ የ10 ደቂቃ ውይይት ከመከፈቱ በፊት አመቻቹ እያንዳንዱ ቡድን ዞሮ በተገላላጭ ቻርት/ፍሊፕ ቻርት ገጾች ላይ የተለጠፉትን እንዲመለከትና የ5 ደቂቃ ጊዜ ሰጥቶ ክለሳና ውይይት እንዲያደርግ መጋበዝ አለበት፡፡ አመቻቹ ሁል ጊዜ ትምህርት ላይ እንዳሉ፣ ሌሎችን ማዳመጥና ግብረ-መልስ መቀበል ስራዎቻቸውን ለማሻሻል አስፈላጊ እንደሆኑ ለተሳታፊዎች ማስገንዘብ አለበት [20 ደቂቃ]፤ ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 44 7.10 ዋቢ ጹሑፎች Andrade, M., Low, J., Naico, A., Ricardo, J., Sandramo e Filipe Zano, A., (undated). Manual Sobre O Cultivo Da Batata – Doce. International Potato Centre, Mozambique. pp79. Environmental Protection Agency, (2012). Pesticides and food: why children may be especially sensitive to pesticides. http://www.epa.gov/pesticides/food/pest.htm Schafer, K.S., Marquez, E.C., (2012). A generation in jeopardy: how pesticides are undermining our children’s health and intelligence. Pesticide Action Network North America. 44pp. Smit, N.E.J.M., (1997). Integrated pest management for sweetpotato in East Africa. PhD Thesis, Wageningen. Stathers, T., Namanda, S., Mwanga, R.O.M., Khisa, G., Kapinga, R., (2005). Manual for sweetpotato integrated production and pest management farmer field school in sub-Saharan Africa. CIP, Uganda. pp168+xxxi Stathers, T.E., Olupot, M., Namanda, S., Mwanga, R.O.M., Khisa, G., Gibson, R.W., Julianus, T., Ndamugoba, D., Kapinga, R., (2006). What is damaging my sweetpotato? A field guide for farmers on pests and diseases of sweetpotato. International Potato Centre, Kampala, Uganda. pp26. ISBN 9970-895-05-2. van de Fliert, E., Braun, A.R., (1999). Farmer field school for integrated crop management of sweetpotato: field guides and technical manual. International Potato Centre, Indonesia. Visser, D., (2004). Chapter 9: Pests. In: Guide to Sweet Potato Production in South Africa. Ed. J.G. Niederwieser. ARC-LNR, Pretoria, South Africa. pp85-94. ርዕስ 7 የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር - 45 ማስታወሻ የስኳር ድንች ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር CIP is a research-for-development organization with a focus on potato, sweetpotato and Andean roots and tubers. It delivers innovative science-based solutions to enhance access to aordable nutritious food, foster inclusive sustainable business and employment growth, and drive the climate resilience of root and tuber agri-food systems. Headquartered in Lima, Peru, CIP has a research presence in more than 20 countries in Africa, Asia and Latin America. www.cipotato.org CIP is a CGIAR research center CGIAR is a global research partnership for a food-secure future. Its science is carried out by 15 research centers in close collaboration with hundreds of partners across the globe. www.cgiar.org For more information, please contact CIP Headquarter. Av. La Molina 1895, La Molina. Apartado 1558, Lima 12, Peru. 5-11-3496017 cip-cpad@cgiar.org www.cipotato.org @cipotato @Cipotato @cip_cipotato